SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ምክር ቤት የትሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቀናት በፊት ያነሳውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ልዩ ከለላ ተቃወመ 22.12.2025 14:16
ኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት የሚከናወን 'ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030'ን በይፋ አስጀመረች
Understand Aboriginal land rights in Australia - የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን የመሬት መብቶች መገንዘብ 18.12.2025 7:47
You may hear the protest chant, “what do we want? Land rights!” —but what does it really mean? Land is at the heart of Aboriginal and Torres Strait Islander identity, culture, and wellbeing. Known as “Country,” it includes land, waterways, skies, and all living things. In this episode of Australia Explained, we explore Indigenous land rights—what they involve, which land is covered, who can make c...
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ በጠብመንጃ ሕግ ማሻሻያ ሳቢያ የፀረ አይሁድ አሳሳቢነት ቸል እንደማይባል አስገነዘቡ 17.12.2025 8:26
የ5 ነጥብ 4 ቢሊየን በጀት ማሻሻያ በዘንድሮው የፋይናንስ ዓመት ውስጥ መካተቱን በጅሮንድ ቻልመርስ አመላከቱ
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያውያን ሰጥታ የነበረውን ጊዜያዊ ከለላ አነሳች፤ በውሳኔው ከ5000 በላይ ኢትዮጵያውያን ተጎጂ ይሆናሉ 17.12.2025 7:46
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን ጎበኙ
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ለቦንዳይ የሽብር ጥቃት ሐዘናቸውን እየገለጡ ነው 15.12.2025 11:32
የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ዕቅድ ልዑክ የሩስያና ዩክሬይን የሰላም ስምምነት እውን ሊሆን እንደተቃረበ አመለከቱ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሩብ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን የአልጀርስ የድንበር ስምምነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቀረቡ 14.12.2025 11:32
ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባልነቷ በድጋሚ መውጣቷን አስታወቀች
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ ታዳጊ ወጣት አውስትራሊያውያን በጋውን ያለ ማኅበራዊ ሚዲያ በደስታ እንዲያሳልፉ አሳሰቡ 10.12.2025 7:22
ፕሬዚደንት ዜለንስኪ የዩክሬይንን ድንበር ለመለወጥ ሕጋዊም ሆነ የሞራል መብት እንደሌላቸው ገለጡ
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 እንዲሆን ቀን ተቆረጠ 10.12.2025 8:34
የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚያችል ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያና በሲዳማ ክልል በተመረጡ አካባቢዎች ለፈቃደኛ ግለሰቦች መሰጠት ተጀመረ
"ሼክስፒር እኔ ኮርዴሊያን ሆኜ ስጫወት ቢያየኝ፤ እርግጠኛ ነኝ፤ ጥቁር ሴት በመሆኔ ይደነግጣል። በእሱ ጊዜ ዘረኛነት በጣም ነበር።" ተዋናይት አሁንም አበበ 09.12.2025 23:30
ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ሲድኒ በትወና ላይ ያለውና ጃኑዋሪ 4 የሚያከትመው የሼክስፒር King Lear ተውኔት ኮርዴሊያን ብቻ አይደለችም። ከተውኔት ባሻገር ስላላት የማኅበራዊ ፍትሕና የተፈጥሮ ክብካቤ አንቂነት ሕይወቷ፣ የሼክስፒር ተውኔቶች ዘመን ተሻጋሪነትና አሁንም ድረስ ገነን ሆኖ የቆየበትን አስባብ አንስታ አተያይዋን ታጋራለች።
"ወጣት ሴቶች ውስጣቸው ጥንካሬና ችሎታ እንዲኖራቸው ነው የምፈልገው፤ ለውጥ ቢኖርም አሁንም ወንዶችና ሴቶች ገና እኩል አይደሉም" ተዋናይት አሁንም አበበ 09.12.2025 23:22
ተዋናይት አሁንም አበበ ከኖቬምበር 15 አንስቶ ጃኑዋሪ 4 ለማብቃት መድረክ ላይ ለቲአትር አፍቃሪዎች እየተተወነ ባለው የሼክስፒር King Lear ተውኔት የኮርዴሊያን ገፀባሕሪ ተላብሳ በመተወን ላይ ናት። ከስሟ ስያሜ እስከ ተውኔት ሕይወቷ ታወጋለች። አውስትራሊያ ተወልዳ ብታድግም፤ አማርኛዋ የጠራ ነው።
የቀድሞው የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የዋን ኔሽን ፓርቲን ተቀላቀሉ 08.12.2025 5:45
በኒው ሳውዝ ዌይልስ የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ የአንድ እሳት አደጋ ተከላካይ ሕይወት አለፈ
ኢትዮጵያ በእዚህ ሳምንት የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው 08.12.2025 11:02
የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ለመሳተፍ የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚደነግገው አዋጅ ታገደ
የቪክቶሪያ መንግሥት ከአንድ ሺህ በላይ የመንግስት ሠራተኞችን ሊቀንስ ነው 04.12.2025 2:57
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ በ2025 ያደመጧቸውን ዋነኛ ዘፋኞችና ባንድ ይፋ አደረጉ
ዶናል ትራምፕ የሩስያና ዩክሬይን ጦርነትን ለማክሰም ተቃርቤያለሁ ሲሉ፤ በጦርነት ላይ ያሉት ሃገራት እርግጠኞች አይደሉም 03.12.2025 5:54
ዩቱዩብ - አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የጣለችውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዕቀባ ግብር ላይ አውላለሁ አለ
በአዲስ አበባ የHIV / AIDS ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ይገኛል ተባለ 03.12.2025 9:02
በኢትዮጵያ ያሉ ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ የመሠረተ ልማት ክፍተት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
"ዕድሜ ልክ እየለመን መኖር የለብንም። የእኛ ሕዝብ አስተዋፅዖ ማድረግ አለበት፤ እንደ ሕዝብ ክብራችንም ይጨምራል" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 02.12.2025 46:02
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራትን አስፈላጊ ሁነኛ ሚናዎች ነቅሰው ያመላክታሉ።
"በኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዘንድ ትልቁ ተግዳሮት አዳዲስ አመራሮችን ለመምረጥ ተተኪዎችን አለማግኘት ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ 02.12.2025 26:16
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራት ግንኙነቶችን አስመልክተው ይናገራሉ።
ከሶስት ሀገራት ጋር ፍርደኞችን ለማስተላለፍና አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችሉ ስምምነቶች ይሁንታ እንዲያገኙ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ 01.12.2025 13:43
ድንቅነሽ (ሉሲ) በኖረችበት ዘመን እንደኖረ የተገመተ የ3.4 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ ተገኘ
"ዓይኔ - እግዚአብሔር የሰጠኝ ትልቁ ስጦታዬ አንቺ ነሽ እላት ነበር" የወ/ሮ ዓይንዋጋ አስናቀ ባለቤት ዶ/ር ተክቶ ካሣው 27.11.2025 38:08
በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩትን የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ ዓይንዋጋ አስናቀ ትኩ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ ባለቤታቸው ዶ/ር ተክቶ ካሣው፣ እህት ድርብ ካሳው ገብረመድኅን፣ የቅርብ የቤተሰብ ወዳጆች ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፣ ዶ/ር ማማሩ አየነውና ዶ/ር አዳነ ዳምጠው ዓይንዋጋን በክብር ይዘክራሉ፤ ትውስታዎቻቸውን ያጋራሉ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ቅዳሜ ኅዳር 20 / ኖቬምበር 29 ከቀኑ 7 ሰዓት (1:00 pm) Springvale Botanical Cemetery ይፈፀማል።
#100 More or less? Talking about quantities - #100 ይነስ ወይም ይብዛ? ስለ መጠን መናገር 27.11.2025 7:33
Learn how to talk about amounts and quantities in everyday English. - ስለ ብዛትና ስፍር አዘቦታዊ የእንግሊዝኛ አነጋገርን ይማሩ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ማካሔጃ 10 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታወቀ 26.11.2025 8:49
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ 'ስምንት ስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ይዞታ ለማዞር ያደረግኩት ጥረት ባለ ሃብቶች ፍላጎት ባለማሳየታቸው አልተሳካም' አለ
"የኢትዮጵያ አየር መንገድን 'ከአፍሪካ የወጣ አፍሪካዊ አየር መንገድ' ነበር የምንለው፤ አሁን 'ከአፍሪካ የወጣ የዓለም አየር መንገድ' ነው የምንለው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ 25.11.2025 30:50
"አውስትራሊያ ጥሩ ሀገር ናት፣ ብንመጣም የምናተርፍባት እንጂ የምታከስረን ሀገር አይደለችም፤ ሕዝቧም ተቀባይ የሆነ ሀገር ስለሆነች ወደ አውስትራሊያ መብረር የማይፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የለም። እርግጠኛ ነኝ፤ አውሮፕላን እንደተገኘ የድርጅቴ ቀዳሚ ጉዳይ የሚሆነው ወደ አውስትራሊያ መብረር ነው" ያሉት ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ፤ ተሰናባች የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላናድ ቀጣና ሥራ አስኪያጅ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የቀጣና ተግዳሮቶችንና ስኬታማ ክንውኖችን አንስተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበራትን በባሕር ማዶ የማቋቋም ፋይዳ፣ ሳቢና ገፊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? 25.11.2025 15:56
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የማኅበረሰብ ማኅበራትን የአገልግሎት ፋይዳዎች ያስረዳሉ።
በአዲስ አበባ በፆታዊ ጥቃት የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሔዱት መካከል ከ70-80 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች መሆናቸው ተገለጠ 25.11.2025 13:01
ከ44 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የላቸውም ተባለ
ለሥራ አጥነትና የወጣት ጥፋተኞች እሥራት ቁጥር መናር አስባቦች ምንድን ናቸው? 19.11.2025 30:04
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ስለ ወጣት አፍሪካውያን ሥራ አጥነት ቁጥርና ማኅበራዊ ተግዳሮት አስባቦች ይናገራሉ።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.