DW

በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle

News AM ↓ 50 episodes

ሳይንሳዊ እና ስነ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እና ለህብረተሰቡ ያላቸቸውን ጠቀሜታ ይመለከታል።

Author

DW

Category

News

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በህግ እንዲመራ ጥሪ ቀረበ 08.07.2026

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውሰራሽ አስተውሎት AI አስተዳደርን የሚመለከት ዓለም አቀፍ ውይይት በዚህ ሳምንት አካሂዷል።በዚህ ውይይት ፤የሰውሰራሽ አስተውሎት በተለይም በልጆ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለማስቀረት በህግ መመራት እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል። ቴክኖሎጂውን ለጦርነት መጠቀም አሳሳቢ ነው ተብሏል።

የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በህግ እንዲመራ ጥሪ ቀረበ 08.07.2026
እንደ ቲክቶክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ለስዓትት እዚያው እንድንቆይ ለምን ያደርጋሉ? 01.07.2026

ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ የቲክቶክ ያሉ የአጫጭር ቪዲዮ መድረኮች የተነደፉት ሱስ እንዲያስይዙ ሆነው ነው በሚል የሚቀርብባቸውን ክስ ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት እንዳረጋጠው ግን የአጫጭር የቪዲዮመድረኮች የተነደፉት ተጠቃሚዎችን የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ በሚያደርጉ የሰዎች የሥነ-ልቦና እና የነርቭ ስርዓቶች ላይ ተመስርቶ ነው።

እንደ ቲክቶክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ለረዥም ስዓት እንድንመለከታቸው ለምን ያደርጋሉ? 01.07.2026
ስልክ እና አድራሻን በቀላሉ ለማግኘት የሚያግዘው ዲጅታል መድረክ 24.06.2026

ኢትዮጵያ ውስጥ ስልክ እና አድራሻ ማግኘት ተቸግረዋል? ብሩክ ጌታቸው እና ብሩክ እንድሪያስ በተባሉ ሁለት ወጣቶች የተሰራው ዲጅታል መድረክ ችግሩን የሚፈታ ይመስላል። ዲጅታል መድረኩ በኢትዮጵያ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣የአደጋ ጊዜ ቁጥሮችን እና አድራሻዎችን በቀላሉ ተደራሽ የሚያደርግ መሆኑተገልጿል።

ክፉ መካሪው ቻት ጂፒቲ 17.06.2026

እንደ ቻት ጂፒቲ ያሉ ዲጂታል መድረኮች ከቀላል እስከ ውስብስብ ሀሳቦች ድረስ መረጃ በመስጠት ነባሩን የጉግል ፍለጋ በመተካት ላይ ይገኛሉ።ያም ሆኖ ቻት ጂፒቲን የመሳሰሉ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተመሰረቱ ዲጅታል መድረኮች ልጆችን ለአደጋ በማጋለጥ ፣ሱስ በማስያዝ፣ እና ተጠቃሚዎቹ ራሳቸውን እንዲያጠፉ በመገፋፋት በተደጋጋሚ ይከሰሳሉ።

ቲክ ቶክ፣ ፌስቡክ እና ዩቱዩብ ሱስ የሚሆኑት ለምንድነው? 10.06.2026
ድምፅ እና ምስል የሚቀርፁት የዓይን መነፅሮች 27.05.2026

እነዚህ የስማርት መነፅሮች ካሜራ፣ ማይክሮፎን፣ ድምጽ ማጉያዎች፣ ዳሳሾች/ሴንሰሮች/ እና እንደ ኮምፒውተር ቺፕስ ያሉ ትናንሽ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ያሏቸው ሲሆን፤ ከኢንተርኔት ጋር በብሉቱዝ ወይም በዋይፋይ ይገናኛሉ።በዚህም ያለ እጅ ንክኪ በድምፅ ትዕዛዝ ብቻ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ የስልክ ጥሪ መቀበል፣ ቢዲዮ መቅረፅ እና ፎቶ ማንስሳትም ይችላሉ።

ድምፅ እና ምስል የሚቀርፁት የዓይን መነፅሮች 27.05.2026
ምርጫ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ 20.05.2026

ዲጅታል ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት በእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን ያህል፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶችን ለመገንባት በሚካሄዱ ምርጫዎች ውስጥም አንድ አካል እየሆነ መጥቷል። ከመራጮች ምዝገባ እስከ የድምጽ ቆጠራ እና የውጤት ማሳወቂያ ድረስ ቴክኖሎጂ ምርጫዎች የሚካሄዱበትን መንገድ እየቀረጸ ይገኛል።

ምርጫ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ 20.05.2026
የ115 ሀገራት ባለሙያዎች በተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ወጣት 13.05.2026

ናትናኤል ጌጤነው የተባለ 24 ዓመት ወጣት ሰሞኑን አማዞን ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ወጣቱ አሸናፊ የሆነው አይቪ የተባለ ለትምህርት አጋዥ የሆነና ያለኢንተርኔት የሚሰራ የሰውሰራሽ አስተውሎት ዲጅታል መድረክ በመፍጠር ነው። ወጣቱ ለወደፊቱም ኢትዮጵያን የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ህልም አለው።

የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት በወጣት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ላይ 06.05.2026

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሰዎች ተሰጦዎቻቸውን እንዲያወጡ፣ ሀሳቦችን እንዲያካፍሉ እና መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያግዛሉ። በዚያው ልክ፤መድረኮችቹ የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት የሚስፋፋባቸው ቦታዎች እየሆኑ ነው። በተለይ ወጣት ሴቶች ለዚህ ጥቃት የበለጠ ተጋላጭ ሲሆኑ፤ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ሥነልቡናዊ ጫና እንደሚፈጥርም ጥናቶች ያሳያሉ።

የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት በወጣት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ላይ 06.05.2026
የናሳ አዳዲስ ፕላኔቶች ፍለጋ 29.04.2026

ናሳ ያለፈው ማክሰኞ፣ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 22 ቀን ፣ ከስርዓተ ፀሐይ/ Solar System/ ውጭ ያሉ ፕላኔቶችን ለመፈለግ እና ያልታወቀ ቁስ ሀይልን ሚስጥሮችን ለመመርመር አዲስ ቴሌስኮፕ ይፋ አድርጓል። በመጭው መስከረም ተልዕኮውን ለመጀመር ወደ አፅናፈ ዓለም ወይም ዩንቨርስ የምትጓዘው ይህቺ ቴሌስኮፕ ሮማን የሚል ስም ተሰጥቷታል።

የናሳ አዳዲስ ፕላኔቶች ፍለጋ 29.04.2026
የሮቦት አትሌቶች በማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆኑ 22.04.2026

ሰሞኑን በቻይና ቤጂንግ በተካሄደ ግማሽ ማራቶንን ውድድር ሮቦቶች ከሰዎች ጋር የሩጫ ውድድር አድርገዋል።በውድድሩ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ብራዚልን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከ100 በላይ ሮቦቶች ተሳትፈዋል።አሸናፊው፣ ላይትኒግ የተባለ የቻይና ሮቦት ሲሆን፤ የ21 ኪሎ ሜትር ውድድሩን በ50 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ውስጥ አጠናቋል።

የሮቦት አትሌቶች በማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆኑ 22.04.2026
የነዳጅ እጥረት ያስከተለው ጫና 01.04.2026
ቲክ ቶክ፣ ፌስቡክ እና ዩቱዩብ ሱስ የሚሆኑት ለምንድነው? 01.04.2026

እንደ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቲኮክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ለተግባቦት ብቻ የሚያገለግሉ ዲጅታል መድረኮች ብቻ አይደሉም። ባለሙያዎች እንደሚሉት እነዚህ ዲጅታል መድረኮች ትኩረታችንን ለመሳብ እና ይዞ ለማቆየት ጭምር በጥንቃቄ የተነደፉ ናቸው።ለተጠቃሚዎቹ መረጃ የሚጠቁሙበት እና ለፍላጎት የሚስማሙ ይዘቶችን የሚያቀርቡበት መንገድም በዚህ የተቃኘ ነው።

ጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃን ያስፋፉት በኤአይ የሚሰሩ ይዘቶች 25.03.2026

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ማሽን ሰወችን ተክቶ እንዲሰራ በማድረግ ጊዜን ፣ገንዘብን እና የሰው ሀይልን ይቆጥባል።ጥራትን እና ምርታማነትን በመጨመር ረገድም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ያም ሆኖ ቴክኖሎጂው ሀሰተኛ ድምፅን፣ ምስልን እና ቪዲዮዎችን አስመስሎ በመስራት ሀሰተኛ ወይም የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ረገድም አሉታዊ ጎን አለው።

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ፣በትምህርት እና ጤና 18.03.2026

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ፣በዓለም ላይ ከዐይን ጥቅሻ በፈጠነ ሁኔታ እያደገ ይገኛል። ይህንን በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ በጤና እና ትምህርት ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል እና የስልጠና ድጋፍ መሆኑን ፒፕል ቱ ቲፕል የተባለው ተቋም ገልጿል።ተቋሙ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመ ነው።

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ፣በትምህርት እና ጤና 18.03.2026

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ፣በዓለም ላይ ከዐይን ጥቅሻ በፈጠነ ሁኔታ እያደገ ይገኛል። ይህንን በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ በጤና እና ትምህርት ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል እና የስልጠና ድጋፍ መሆኑን ፒፕል ቱ ቲፕል የተባለው ተቋም ገልጿል።ተቋሙ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመ ነው።

በታዋቂ ሴቶች ላይ የበረታው ዲጅታል ጥቃት በኢትዮጵያ 11.03.2026

አዲስ ፓወር ሃውስ የተባለ ሀገር በቀል ተቋም በቅርቡ ባወጣው ጥናት፤ በኢትዮጵያ ታዋቂ ሴቶችን ኢላማ ያደረገ ዲጅታል ጥቃት ጨምሯል።ጥናቱ በቲክቶክ፣በፌስቡክ፣በቴሌግራም፣በዩቱብ እና በሊንክዴን ላይ በተለጠፉ1307 ይዘቶች ላይ ትንተና ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በታዋቂ ሴቶች ላይ ጥቃቱ የበረታ መሆኑን የተቋሙ ዳይሬክተር ሀና ለማ ገልፃለች።

በታዋቂ ሴቶች ላይ የበረታው ዲጅታል ጥቃት በኢትዮጵያ 11.03.2026

Listen to the በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.