Abate Tsegaye
ENAB TECH PODCAST
በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ኢናብ ቴክ - በቴሌብር ጉዳዮችን መፈጸም 25.08.2024 29:51
በዝግጅቱ ቀዳሚ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ከስክሪናችሁ ኬብል የሚወጣን ጨረር በመመልከት ብቻ ስክሪን ላይ ያለውን ጽሁፍ መለየት ስለመቻሉ፤ እንዲሁም ጉግል ሰርች ህገወጥ ሞኖፖሊ ነው ተብሎ የተፈረደበት ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ መጨረሻ ክፍል፣ በቴሌብር ገንዘብ ማስተላለፍን ጨምሮ አንዳንድ ጉዳዮችን እንዴት እንደምንፈጽም በተግባር እንቃኛለን። ከአድማጮች ጥያቄዎች ውስጥ፥- የኮምፒውተር ቁልፍ አቀማመጡ ከተለመደው ተዘበራርቆ አስቸገረኝ። ምሳሌ፣ ዜድ ወደ ደብልዩ፣ ደብልዩ ወደ ዜድ እየተቀያየሩ፣ እንዴት ባደርገው ይስተካከላል? የምጠቀመው የጥር 20 ጂሺዎ ቨርዥን ነው...
ኢናብ ቴክ - ቴሌብርን ለመጀመሪያ ጊዜ መክፈት 22.08.2024 30:18
ጤና ይስጥልን፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በኤፒሶዱ የመጀመሪያ ክፍል በሆነው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ስካይፕ በተባለው የቪዲዮ መደዋወያ አፕሊኬሽኑ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ሊያቆም ስለመሆኑ እና ጉግል በክሮም ብራውዘሩ ሴቭ የተደረጉ ፓስወርዶችን በአፕዴት ችግር ምክንያት ለ18 ተከታታይ ሰአታት ማሳየት ሳይችል መቅረቱን የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ቀጣይ በሆነ የዝግጅት ክፍል፣ ቴሌብር አፕሊኬሽንን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንደምንከፍት አጠቃቀሙን በተግባር እየሞከርን እናስተዋውቃችኋለን። ቴሌብር በጣም በርካታ ክፍሎች ስላሉት በተለየ እንድናተኩርበት የምትፈልጉት የቴሌብር ክፍል...
ኢናብ ቴክ - ቴሌብርን መተዋወቅ 20.08.2024 29:44
ሰላም፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች፤ በዚህ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ኤንቪዲኤ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 11 ዋን ድራይቭ የተባለው አገልግሎቱን በሙሉ ስክሪን ማስታወቂያ ለተጠቃሚዎቹ በማድረስ ማስቸገሩን የሚሉትን መረጃዎች እናወራችኋለን። ዛሬ በሚጀምረው የሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ሁላችንም በተለያየ አጋጣሚ ስለምንሰማው እና በርካቶቻችን በተለያየ መጠን እየተጠቀምነው እንደሆነ ስለምንገምተው ቴሌብር አገልግሎት እናስተዋውቃችኋለን። በተለየ እንድናተኩርበት የምትፈልጉት የቴሌብር ክፍል ካለ አስተያየት እና ጥቆማዎችን ላኩልን። ከአድማጮች ጥያቄዎች...
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድን ከሩቁ መቆጣጠር እና ሙዚቃውን በስልካችን ላይ መስማት 18.08.2024 29:37
እንዴት ናችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ ዛሬ ደግሞ ይዘነው በመጣነው ኤፒሶድ፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ጉግል ኩኪስ የተባሉት ቴክኖሎጂ ለማስቀረት ያወጣውን እቅድ ስለመቀልበሱ እና ክራውድ ስትራይክ ድርጅት ፋልኮን የተባለው አንቲቫይረሱ አፕዴት ሲያደርግ በአለማቀፍ ደረጃ ያስከተለው ቀውስ እንዳይደገም ስለሚያደርገው ጥረት የሚመለከቱ መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የመጨረሻ ክፍል፣ በስልካችን አፕሊኬሽኑን እንዴት እንደምንቆጣጠር እና ካሻንም በስልካችን ፒሲ ላይ ያለውን ሙዚቃ እንዴት እንደሚያሰማን እንመለከታለን። አድማጮች ከላኳቸው ጥያቄዎች ውስጥ፥-...
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድ ቀሪ ሴቲንጎች እና በመደበኛ ከማጫወት ባሻገር ያሉ አጠቃቀሞች 17.08.2024 29:34
ሰላም ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ስላካተታቸው አዳዲስ ነገሮች እና ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ እያስተዋወቅነው ባለው ዋን ባይ ዋን በተባለው የኦዲዮ ማጫወቻ አፕሊኬሽን ቀሪ ሴቲንጎችን እንዴት እንደምናስተካክል፣ ድምጽን እንዴት አፍጥነን እንደምናጫውት፣ ያለንበትን የትራክ ቦታ እንዴት መዝግበን ማስቀመጥ እንችላለን? "በተለይ ለኦዲዮ መጻህፍት ይሄ ጠቃሚ ነው፤" ያሉንን ትራኮች በቅምሻ እየቆነጠረ እንዲያሰማን እንዴት እናደርጋለን የሚሉትን አጠቃቀሞች እንቃኛለን። ከአድማጮች ለተነሱ...
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድ ስፔሻል እና ዊንዶውስ ሴቲንጎች 25.07.2024 29:42
እንዴት ቆያችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች? በቅድሚያ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የዝግጅቱ ክፍል፣ በክራውድ ስትራይክ የአንቲቫይረስ ድርጅት አፕዴት ያስከተለው ቀውስ በመጠኑም ቢሆን መቀጠሉን፣ ሳምሰንግ በስልኮቹ አንድሮይድ ያጋጠመን የደህንነት ክፍተት ባልተለመደ ፍጥነት ፈፕዴት ሊለቅ ስለመሆኑ እንዲሁም ጉግል ክሮም ፋይል ዳውንሎድ ስታደርጉ ለምንድን ነው የምታወርዱት ብሎ መጠየቅ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የምናሳይበት ቀጣይ ክፍል ከሴቲንጎች ውስት ስለስፔሻል ሴቲንግ እና ስለዊንዶውስ ሴቲንግ የተመለከተ ዝግጅት ይዘናል። በመሰረታዊ የኮምፒ...
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድን ሴቲንጎችን ማስተካከል 24.07.2024 30:06
ጤና እና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች። ኤፒሶዱን በምናስጀምርበት የቴክኖሎጂ መረጃዎች፣ የአንቲቫይረስ አፕዴት በፈጠረው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በመላው አለም የሚገኙ ትላልቅ ኩባንያዎች እና ተቋማት አገልግሎቶቻቸው ተቋርጠው ስለመዋላቸው፣ ዊንዶውስ አዲስ የአፕዴት መንገድ ስለማስጀመሩ እና የአፕል አይኦኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም በቀላሉ ሀክ ማድረግ አለመቻሉን ይህንን የሚሰራ ተቋም ስለማስታወቁ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የምናሳይበት ቀጣይ ክፍል ሴቲንጎችን ስለማስተካከል እንመለከታለን። ከአድማጮች ለተነሳ አስተያየትም ምላሽ አካት...
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድ ላይ ፕለጊኖች መጨመር እና የኦዲዮ ሴቲንጎችን መመልከት 23.07.2024 30:11
ሰላም እንዴት አደራችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች። በዛሬው ኤፒሶድ ቀድሞ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 ይዞት ሊመጣ ነው ስለተባለው ስልካችንን እንደኮምፒውተር መጠቀም የሚያስችለን አገልግሎት እና ማይክሮሶፍት ወደ ፍልስጥኤም የሚደውሉ ደንበኞቹን አካውንት እየሰረዘ መሆኑን ስለመዘገቡ የሚሉ መረጃዎችን እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ማስተዋወቅ በጀመርነው የዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን ፕለጊኖችን እንዴት እንደምናካትትበት እና የኦዲዮ ሴቲንጎችን በከፊል እንፈትሻለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም፣ አበቃለት ብዬው የነበረውን የማይክሮሶፍት ኤክሴል፣ ጠቃሚ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ መጨመር አለባቸው ብዬ...
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድ የኦዲዮ ማጫወቻውን መተዋወቅ 22.07.2024 30:07
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል፣ ብያችሁ እንደነበር ይታወሳል። ለፈጠርኩት የመረጃ ክፍተት ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ፖድካስቱ የሚቀጥል መሆኑን የተነገረኝ ስለሆነ እነሆ ቀጣይ ክፍል ይዤ መጥቻለሁ። ዝርዝሩን ከኤፒሶዱ ታገኙታላችሁ። እንደተለመደው፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ክፍል፣ ጃውስ ባደረገው ማሻሻያ ስለጨመራቸው ነገሮች እና ጃፓን ፍሎፒ የተባለው እጅግ የቆየ ቴክኖሎጂ ከመንግስት አገልግሎቶች ማስወገድ ስለመቻሏ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዋን ባይ ዋን ስለሚባል የኦዲዮ ምቹ ማጫወቻ አስተዋውቃችኋለሁ። ከ...
ኢናብ ቴክ - ከስልክ በተግባር ፕሪንት ማድረግ 26.06.2024 34:22
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል። በዚ በመጨረሻ ክፍል ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2024.2 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና አፖል ኩባንያ በአይኦኤስ የወደፊት ኦፐርቲንግ ሲስተሙ ቨርዥን 18 ከተደራሽነት ጋር ስላካተታቸው ነገሮች መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የመጨረሻ ክፍል ከስልካችን በቀትታ ፕሪንት እያደረግን በተግባር እንሞክራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ክፍል ስለፎርሙላዎች እና ስለፋንክሽንስ እንዴት እንደምንጠቀም እናያለን። ከ...
ኢናብ ቴክ - በስልካችን ላይ ሞቢሊቲ ፕሪንትን ማስተካከል 25.06.2024 30:00
ሰላም፣ ጤና ይስጥልን፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዩቲውብ በስልካቸውም ሆነ በኮምፒውተራቸው ላይ አድ ብሎከሮችን ጭነው ዩቲውብን ለመጠቀም የሚሞክሩ ተጠቃሚዎቹን ቪዲዮዎችን መመልከት እንዳይችሉ አልያም የሚመለከቱትን ነገር እንዳይመች የማድረግ ሙከራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል የሚለውን መረጃ እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል ሞቢሊቲ ፕሪንትን በስልካችን ላይ እንዴት እንደምናስተካክለው በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ፣ የከፈትነውን ባዶ የስፕሬድ...
ኢናብ ቴክ - ፖድካስት እና ፖኬት ካስት 24.06.2024 25:13
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ይህ እኔ የማቀርበው ዝግጅትም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ፖድካስት እየተባለ ሲጠራ ሰምታችኋል። በዚህ ዝግጅት ስለ ፖድካስት ምንነት እና ፖድካስትን ለመከታተል እና ለማድመጥ ከሚረዱን የስልክ አፕሊኬሽኖች አንዱ ስለሆነው ፖኬት ካስት የሚስተካከልበትን መንገድ እና አጠቃቀም እናብራራለን። ሙሉ ዝግጅቱን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማድመጫ አፕሊኬሽኖች https://pnc.st/s/enab-tech-podcast የሚለውን ሰብስክራይብ በማድረግ አድምጡ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ...
ኢናብ ቴክ - ሞቢሊቲ ፕሪንትን ኮምፒውተር ላይ መጫን እና ማስተካከል 23.06.2024 29:15
ሰላም የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ከዚህ በፊት በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ዘገባዬ የነገርኳችሁ አንድሮይድ 15 ቤታ ወይም የሙከራ ቨርዥን አካል ሆኖ ይለቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ቶክ ባክ 15.0 ስላካተታቸው ነገሮች መረጃ ይዘናል። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል በሁሉም አይነት ፕሪንተሮች ከስልካችን ፕሪንት ለማድረግ ስለሚያስችለን ሞቢሊቲ ፕሪንት አጫጫን እና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሰራ ሴቲንጎቹን እንዴት እንደምናስተካክል የሚያሳይ ዝግጅት አቅርበንላችኋል። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ፣ በማይክሮሶፍት...
ኢናብ ቴክ - ሞቢሊቲ ፕሪንትን ማስተዋወቅ 17.06.2024 30:13
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አፕል ኩባንያ በኮምፒውተር እና በስልክ መካከል ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይፓድ የተባሉትን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ያካተቱ ታብሌቶቹን ለገበያ ማቅረቡን፣ ማይክሮሶፍት ወርድ ከተለያዩ ቦታዎች በኮፒ ፔስት ጽሁፍ ስታደራጁ ያጋጥም የነበረውን የቅርጽ መዘበራረቅ የሚያስቀር አፕዴት ስለመልቀቁ እንዲሁም ኦፕን ኤአይ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰሪ ድርጅት ቻት ጂፒቲ በተባለው አገልግሎቱ ከሰው ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ የሆነ አዲስ ማሻሻያ ለህዝብ በይፋ ስለማቅረቡ የሚሉትን መረጃዎች በዝርዝር እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረ...
ኢናብ ቴክ - ስለሞባይል ፕሪንት ማስተዋወቅ 15.06.2024 29:23
ሰላም ጤና ይስጥልን፣ እንደምን አላችሁ፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 በ2ኛ ሙከራ ቨርዥኑ አዲስ ስላካተታቸው ነገሮች እንዲሁም ታዋቂው እና ተወዳጁ የሞባይል ቪዲዮ ማጋሪያ እና መመልከቻ ቲክቶክ አፕሊኬሽን በአሜሪካ ሀገር ስላጋጠመው ተግዳሮት ዝርዝር እናወራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልኮቻችን ፕሪንት ስለማድረግ ማብራሪያ እናቀርባለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ በማይክሮሶፍት ኤክሴል ዶኪውመንት ውስጥ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚረዱ ተጨማሪ መንገዶችን እንቃኛለን። ከአድማጭ ለተነሱ ጥያቄ እና አስተያየቶች ማብ...
ኢናብ ቴክ - ፕሪንት አደራረግ 22.05.2024 30:30
ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ዋነኛ ስክሪን ሪደር የሆነው ጃውስ ፎር ዊንዶውስ በሜይ 2024 አፕዴት በሚል አዲስ በለቀቀው ማሻሻያ ስላደረጋቸው ለውጦች እና ማስተካከያዎች እንዲሁም ሳም ኦልትማን የተባለው የቴክኖሎጂ ባለሀብት የድሆችን የግል መረጃ ለመግዛት ሀምሳ ዶላር እየከፈለ ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት የመጨረሻ ክፍል፣ በማይክሮሶፍት ወርድ እንዴት በተግባር ፕሪንት እንደምናደርግ እየሞከርን እንተዋወቃለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው...
ኢናብ ቴክ - ማይክሮሶፍት ወርድ 20.05.2024 1:41:51
ሰላም? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ኮምፒውተርን ስንጠቀም ለትምህርትም ሆነ ለስራ መሰረታዊ ከሆኑ አፕሊኬሽኖች ውስጥ ዋነኛው የማይክሮሶፍት ኦፊስ ጥቅል ነው። ከዚህ ጥቅል ውስጥ ደግሞ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ አንደኛ ሊባል የሚችለው ማይክሮሶፍት ወርድ ነው። ለኮምፒውተርም ሆነ ለማይክሮሶፍት ወርድ በስክሪን ሪደር ለመጠቀም መጀመሪያቸው ለሆኑ መሰረታዊ የሆኑ አጠቃቀሞችን ያሳያል ብለን ያሰብነውን ሙሉ ቱቶሪያል አቅርበናል። ሙሉውን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማድመጫ አፕሊኬሽኖች https://pnc.st/s/enab-tech-podcast የ...
ኢናብ ቴክ - ፕሪንተርን ከኮምፒውተር ጋር ማስተዋወቅ 18.05.2024 29:38
እንደምን አላችሁ ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች ዝርዝሩን እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ፕሪንተራችንን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ስለሚደረገው ፕሪንተርን ከኮምፒውተር ጋር የማስተዋወቅ ሂደትን በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። ለአድማጮች ጥያቄ፣ የማይክሮሶፍት ኤክሴል የሚከፈትበትን ተጨማሪ መንገድ ከአድማጭ በተገኘ ግሩም ጥቆማ አማካይነት የምናብራራ ሲሆን ሌሎችንም ማብራሪያዎች ይዘናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me...
ኢናብ ቴክ - የፕሪንተር አካላዊ መግለጫ 16.05.2024 29:43
ሰላም ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት በስቶር ውስጥ የሚገኙ አፖችን በሌላ አማራጭ የሚጫኑበትን መንገድ ስለማመቻቸቱ፣ በአሜሪካ የሚገኙ የፖሊስ ተቋማት የጂፒኤስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌቦችን በመኪና ማሯሯጥ ማቆማቸው ስለመዘገቡ እንዲሁም አፕል በአይፎን ስልኮቹ እና በሌሎቹ መሳሪያዎቹ ጋር በመያያዝ ሲጠፉ ለማግኘት የሚረዳ አገልግሎቱ የንጹሀን ግለሰቦች ቤት በፖሊስ ተሰብሮ እንዲገባ እና ንብረታቸው እንዲበለሻሽ ምክንያት መሆኑን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ አንድ ፕሪንተር ያሉትን ክፍ...
ኢናብ ቴክ - የፕሪንተር አይነቶች 02.05.2024 31:01
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ኤንቪዲኤ በአዲስ ቨርዥኑ ይዟቸው ከመጣቸው ነገሮች ውስጥ በተለይ በዋና ዋና ጉዳዮች ዘርዘር ያለ ማብራሪያ አቅርበናል። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ስለፕሪንተር አይነቶች ምንነት እናቀርባለን። ከአድማጮች ከተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፣ ስለኮምፒውተር ፎርማት አደራረግ ዙሪያ፣ ስለኢትዮቴሌኮም ቴሌብር ኢንጌጅ እና ስለማይክሮሶፍት ኦፊስ 2010 አክቲቬተር ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች አቅርበናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpo...
ኢናብ ቴክ - ዩኒግራም ተደራሹ የዊንዶውስ ቴሌግራም ክለያንት (ማጠቃለያ) 23.04.2024 57:50
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ዩኒግራም የተባለው የዊንዶውስ ቴሌግራም አፕሊኬሽን ክለያንት ምንነት፣ ከየት ልናገኘው እንደምንችል እና አጫጫኑን በማስተዋወቅ ጀምረን ከጫንነው በኋላ ስለሚመጣው ምርጫዎች ወደ ቴሌግራም አካውንታችን በዩኒግራም አማካይነት ስለምንገባባቸው መንገዶች እንቃኛለን። ከዚያ በማስቀጠል ዩኒግራምን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት በኤንቪዲኤ ዩኒግራም ለመጠቀም የሚረዱ ሴቲንጎችን የትኞቹ እንደሆኑ በተለይ የዩኒግራም አድኦን ክፍሉን ከተመለከትን በኋላ በዩኒግራም ውስጥ ብናስተካክላቸው ይጠቅማሉ ያልናቸውን ሴቲንጎች እናስተዋውቃችኋለን። በመጨረሻም፣ መሰረታዊ የሆነውን የዩኒግራም አጠቃቀም በተግባር እየሞከርን እ...
ኢናብ ቴክ - ፕሪንተርን መተዋወቅ 21.04.2024 30:23
ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ሌላኛው አማራጭ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ዊንዶውስ 32 ቢት ቨርዥን ኦፐሬቲንግ ሲስተም በ2038 ስለሚገጥሙት ችግሮች የሚሉትን መረጃዎች እናካፍላችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ዘመናዊውን የሶት ኮፒ ዘመን ከቀድሞው ሃርድ ኮፒ ዘመን የሚያገናኘውን "ፕሪንተር" የተባለውን መሳሪያ መተዋወቅ እንጀምራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል አጠቃቀም የኤክሴል መክፈቻ መንገቾችን በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። ከአድማጮች፣ ስለቮልት፣ ስለጉግል ሜሴጅ እና ስለዩኒግራም ለ...
ኢናብ ቴክ - በኢትዮቴሌኮም የኤምኤምኤስ መልእክትን መላክ እና መቀበል 02.04.2024 29:41
ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃ፣ የአንድሮይድ መደበኛ ስክሪን ሪደር የሆነው ጉግል ቶክ ባክ በአዲሱ ቨርዥኑ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ውስጥ የኤምኤምኤስ መልእክት እንዴት እንደምንልክ እና እንዴት እንደምንቀበል በተግባር እየሞከርን እናሳያችኋለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል አጠቃቀም ቀጣይ ክፍል ስለኤክሴል የት ሊገኝ እንደሚችል እና እንዴት እንደምንከፍተው እናብራራለን። ከአድማጮች ስለኮምፒውተር ፎርማቲንግ እና ስለኢትዮቴሌኮም አገልግሎቶች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ቀር...
ኢናብ ቴክ - ኢትዮቴሌኮም RCS እና MMS አገልግሎቶች 25.03.2024 30:20
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ቨርዥን 2024 ሊለቀቅ ስለመሆኑ እና የአይፎን አምራች የሆነው ኩባንያ አፕል በአይፎን ስልኮቹ ላይ የሶስተኛ ወገን አፕሊኬሽኖች እንዲጫኑ እንዲፈቅድ ስለመገደዱ የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ውስጥ RCS እና MMS የተባሉትን ለመጠቀም የምናስተካክላቸውን ሴቲንጎች እንጎበኛለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል አጠቃቀም የመጀመሪያ ክፍል ስለኤክሴል ምንነት በማስተዋወቅ እንጀምራለን። ከአድማጮች ስለኮምፒውተር ፎርማቲንግ እና ስለኢት...
ኢናብ ቴክ - የኢትዮቴሌኮም ተጨማሪ አገልግሎቶችን መተዋወቅ 23.03.2024 29:49
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ኤንቪዲኤ በለቀቀው አነስተኛ ማሻሻያ ስላደረጋቸው ለውጦች፣ በዊንዶውስ 11 አንድሮይድ አፕሊኬሽኖችን የሚያስጠቅመው አገልግሎት ሊቋረጥ መሆኑን እና ቲክቶክ በአሜሪካ ሀገር እንዳይሰራ ሊደረግ መሆኑን የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ስላስጀመራቸው ተጨማሪ አገልግሎቶች ምንነት እና አጠቃቀም የሚያብራራ ዝግጅት ይዘናል። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወርድ ስለሰንጠረዥ ሁለተኛው መፍጠሪያ መንገድ እና በሰንጠረዥ ውስጥ ከአንዱ ክፍል ወደ ሌላው እንዴት እንቀሳቀሳለን የሚ...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.