Abate Tsegaye
ENAB TECH PODCAST
በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ኢናብ ቴክ - ፈጣኑ ቪፒኤን - ፕሮቶን? 21.03.2024 16:17
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በአንድሮይድ ስልካችን ላይ የሚጫነውን፣ የምንጎበኛቸው ውብሳይቶች እና የኔትወርክ አቅራቢዎቻችን የሚሰበስቡብንን የግል መረጃ ለመቀነስ፣ ለእኛ እንዳይሸጡ አልያም እንዳይታዩ በአቅራቢዎቻቸው የተከለከሉ ይዘቶችን ለመመልከት፣ የግል መረጃችንን ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፎ እንዳይሰጥ የሚከላከል ጠንካራ ህግ እና ባህል ባላት ሀገር ውስጥ ሆኖ የሚሰራውን እና ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚረዳንን ፕሮቶን ቪፒኤን የተባለውን አፕሊኬሽን አጠቃቀም ቱቶሪያል ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ። አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት...
ኢናብ ቴክ - ከፎርማት በኋላ ኮምፒውተርን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተካከል 20.03.2024 29:25
ጤና ይስጥልኝ፤ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ጃውስ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ነገሮች እና ማሻሻያዎች እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የመጨረሻውን ክፍል፣ ከፎርማት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኮምፒውተራችንን እንዴት እናስጀምራለን። የሚለውን በማየት ይህንን ቅንብር እናበቃለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወርድ በሰነዶች ላይ መረጃ ከምናቀርብባቸው አደረጃጀቶች አንዱ ስለሆነው ስለሰንጠረዥ አሰራር እንዳስሳለን። ስለ...
ኢናብ ቴክ - የማይከፍትን ኮምፒውተር ፎርማት ማድረግ 14.03.2024 29:42
ሰላም የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 በሙከራ ደረጃ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ የአይፎን ስልክ አምራች የሆነው አፕል ኩባንያ ስልካችሁን በሩዝ አታድርቁ በማለት ማሳሰቡን እና አውዳሲቲ የተባለው የድምጽ ማቀናበሪያ ነጻ ሶፍትዌር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማካተቱን የሚሉትን ዜናዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የማይከፍት እና አፕሊኬሽን የማይጭን ኮምፒውተር ካለን ከፍላሽ ተነስተን ሙሉ በሙሉ እንዴት ፎርማት እንደምናደርግ እናያለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማ...
ኢናብ ቴክ - አውዳሲቲ የድምጽ መቅረጫው እና ማቀነባበሪያው 08.03.2024 51:26
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ማንኛውንም አይነት ድምጽ ሆነ ንግግር ለመቅረጽ እና ለማቀናበር የሚያገለግለው፣ ያላንዳች የገንዘብ ክፍያ በነጻ መጠቀም የሚያስችለው፣ በሶስት አይነት የኮምፒውተር ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚጫነውን (አውዳሲቲ) የተባለውን አፕሊኬሽን ዐጠቃቀም መግለጫ እና በተግባር ሙከራ ሙሉ ዝግጅት አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ፣ ደውላችሁ የድምጽ መልእክት በማስቀመጥ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ።
ኢናብ ቴክ - የማይከፍትን ኮምፒውተር ለፎርማት ማዘጋጀት 03.03.2024 31:27
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3.3 ስላደረጋቸው አነስተኛ ማሻሻያዎች፣ ኋትስአፕ ለሌሎች አፕሊኬሽኖች መልእክት መላላክ የሚያስችል አገልግሎት ሊጀምር ስለመሆኑ እና ጉግል ከሚገድላቸው አገልግሎቶቹ ውስጥ የካሽድ ሪዘልት የሚለው መጨመሩን የሚሉትን ጉዳዮች በቅድሚያ እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የማይከፍት እና አፕሊኬሽን የማይጭን ኮምፒውተር ካለን ከፍላሽ በመነሳት ፋይሎቻችን እንዴት እንደምናድን እና ድራይቨሮችን ኮፒ እንዴት እንደምናደርግ እንመለ...
ኢናብ ቴክ - በሩፈስ ፍላሾችን ኮምፒውተር ፎርማት ለማድረግ ማዘጋጀት 25.02.2024 33:18
ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ እንደሁልጊዜው፣ በዝግጅታችን መጀመሪያ በሚቀርቡት የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ በለቀቀው አዲስ ቨርዥን ስላደረጋቸው ማሻሻያዎች በዝርዝር እናወራለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የማይከፍት እና አፕሊኬሽን የማይጭን ኮምፒውተር ካለን ከፍላሽ በመነሳት ፎርማት ማድረግ እንድንችል የሚረዳንን ፍላሻችንን ፎርማት ለማድረግ እንድንችል የሚያዘጋጀውን አፕሊኬሽን ሩፈስን እንተዋወቃለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወርድ በጽሁፋችን ው...
ኢናብ ቴክ - ዶት ወከር 15.02.2024 50:26
እንደምን አላችሁ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በስልካችን ኢንተርኔት ሳይኖረንም ቢሆን ሳተላይትን በመጠቀም ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚረዳን እና ያለንበትን ቦታ የሚነግረን የአንድሮይድ አፕሊኬሽን "ዶት ወከር" አጠቃቀም የሚያብራራ ዝግጅት ይኸው ቀርቧል። በሙሉ በአንዴ እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮችን እንድናውቅ ሰርቬይ ልትሞ...
ኢናብ ቴክ - በእርግጥም ኮምፒውተርን ፎርማት ማድረግ 11.02.2024 31:11
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ እንደሁልጊዜው፣ በዝግጅታችን መጀመሪያ በሚቀርቡት የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሜይል ቤዚክ ኤችቲኤምኤል የተባለውን የኢሜይል አገልግሎቱን በቀላሉ ለመጠቀም የሚያስችል ክፍል ማቋረጡን፣ ኦፔራ ጂኤክስ የተባለው ብራውዘር ለተማሪዎች ከወላጆቻቸው እና ለሰራተኞች ከአለቆቻቸው የሚሰሩትን ስራ መደበቅ እንዲችሉ የሚያስችል አገልግሎት ይዞ መምጣቱን ስለማስታወቁ እንዲሁም በአለማችን የኢንተርኔት ዝውውር መጠን በሀያ አምስት በመቶ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ስለመጨመሩ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል...
ኢናብ ቴክ - ሻርፕ ኪስ የኮምፒውተር ቁልፍ ማስተካከያው 05.02.2024 11:05
ሰላም፣ ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በኮምፒውተራችን እየቀሩ ያሉ ቁልፎችን ለማምጣት፣ ያለቦታቸው የተቀመጡትን እኛ ወደምንፈልገው አካባቢ ለመቀየር፣ የተበላሹብንን የኮምፒውተር ቁልፎች እምብዛም በማንጠቀማቸው ቁልፎች በመተካት ከወጪ ለመዳን እና ለመሳሰሉት የኮምፒውተር ቁልፍ ነክ አገልግሎቶች የሚረዳንን ሻርፕ ኪስ የተባለውን የዊንዶውስ አፕሊኬሽን አጠቃቀም አቅርበናል። አድምጡ፣ ተጠቀሙበት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @en...
ኢናብ ቴክ - ከኮምፒውተር ፎርማት በፊት ልናደርጋቸው የሚገቡ ዝግጅቶች እና ጥንቃቄዎች እንዲሁም የኢዚ ቢሲዲ አጫጯን 01.02.2024 32:16
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ቀዳሚ በሆኑት በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር ቶክ ባክ በለቀቀው አነስተኛ ማሻሻያ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ የዊንዶውስ አብሮት የሚመጣው ስክሪን ሪደር "ናሬተር" ዊንዶውስ 11 በሚጫን ጊዜ አልጀምርም ብሎ የማስቸገር ጸባይ ስለማሳየቱ እና ፌስቡክ የጀመረው የማመስጠር ቴክኖሎጂ ለወንጀለኞች ምቹ እንደሆነ በአንጻሩ ለህግ አስከባሪዎች አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ የሚሉትን መረጃዎች እናወጋችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ ፎርማት ከማድረጋችን በፊት ልና...
ኢናብ ቴክ - በአንድሮይድ ስልኮች መጽሀፍትን ማንበብ 12.01.2024 44:38
ጤና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ዲጂታል መጽሀፍትን ለመዝናኛ፣ ለጥናት፣ ለእውቀት እና ለሌሎች ጥቅሞቻቸው ለማንበብ እና ለማድመጥ የሚረዳውን አት ቮይስ አላውድ ሪደር የተባለውን አፕሊኬሽን አጠቃቀም እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮችን እንድናውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልን ትችላላችሁ። በዝ...
ኢናብ ቴክ - ኮምፒውተር ፎርማት ለማድረግ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች 08.01.2024 32:11
በዚህ ክፍል፣ ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በአሉን ለምታከብሩ እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ እያልን፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ ስክሪን ሪደር በለቀቀው ማሻሻ ያይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ጉግል በክሮም ብራውዘሩ ኩኪስ የተባለውን የቴክኖሎጂ አይነት ለማስቀረት የሚያስችለውን ሂደት ሀ ብሎ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል ፎርማት ለማድረግ ከሚጠቅሙ አፕሊኬሽኖች ሁለቱን እናስተዋውቃችኋለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወርድ ጽሁፋችን እንዴት እንመርጣ...
ኢናብ ቴክ - የኮምፒውተር ፎርማት አደራረግ 25.12.2023 31:54
በዚህ ክፍል፣ ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዩቲውብ የማስታወቂያ መከላከያ ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ቪድዮዎችን እያዘገየ ማሳየት መጀመሩን፣ ቲክቶክ በአሜሪካ ሞንታና ግዛት ተጥሎበት የነበረው እገዳ በፍርድ ቤት የተነሳለት መሆኑን፣ ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 10 የደህንነት ማሻሻያዎችን ከ2025 በኋላ በክፍያ ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን ማስታወቁን እና ጉግል ተጠቃሚ የሌላቸው አካውንቶችን መሰረዝ መጀመሩን መግለጹን የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል የመጀመሪያው ክፍል ይቀርብላች...
ኢናብ ቴክ - የጃውስ አጠቃቀም 16.12.2023 56:56
በዚህ ክፍል ጤና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ ከስክሪን ሪደሮች ሁሉ ለረጅም ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኘው፣ ዝነኛው፣ ባለብዙ ተጠቃሚው፣ ለብዙዎች የመጀመሪያ የሆነውን የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር "ጃውስን" አጠቃቀም ይዘንላችሁ መጥተናል። በተለይ፣ ኮምፒውተር ጀማሪ ለሆኑ በእጅጉ ስለሚጠቅም በስጦታም ሆነ በማስታወቅ ይህንን ዝግጅት እንድትጋቡልን። ኮምፒውተር ለለመዳችሁትም አንዳንድ ቁመነገር አታጡበትም አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ...
ኢናብ ቴክ - በፖኬት ካስት ፖድካስቶችን ማድመጥ እና ኤፒሶዶችን ማደራጀት 12.12.2023 33:15
በዚህ ክፍል፣ እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዊንዶውስ 11 በቨርዥን 23H2 ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ነገሮች፣ ፐርግ የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ማይክሮሶፍትን የዊንዶውስ 10ን እድሜ እንዲያራዝም መጠየቁን እና ማይክሮሶፍት ወርድ 40ኛ አመቱን ማክበሩን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን።። በሞባይል ወርልድ፣ ስለፖኬት ካስት የተዘጋጀው ዝግጅት በመጨረሻው ክፍል፣ ሳብስክራይብ ያደረግናቸውን ፖድካስቶች እንዴት እንደምናደምጥ እና የፖድካስት ኤፒሶዶቻችንን እንዴት ማደራጀት እንደምንችል የሚሉትን በተግባር እንሰማለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወድ በጽሁፋችን...
ኢናብ ቴክ - ዊንዶውስ ኤክስፕሎረርን መጠቀም 08.12.2023 30:15
በዚህ ክፍል ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች። በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም፣ መሰረታዊ የሆነው፣ ከፊት ለፊት መጥተው የምናዛቸውን የዊንዶውስ ክፍሎች ከጀርባ ሆኖ የሚያስተዳድረው፣ መሰረታዊ የሆኑ የዊንዶውስ ፋይሎችን የማስተዳደር እንደመሰረዝ፣ መገልበጥ እና ማንቀሳቀስ የመሳሰሉትን የምንከውንበት ዊንዶውስ ኤክስፕሎረር የተባለውን ክፍል አጠቃቀም አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመ...
ኢናብ ቴክ - ፖኬት ካስት አካውንት አፈጣጠር እና የፖድካስት ሰብስክራይብ አደራረግ 04.12.2023 32:15
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር ጃውስ በቨርዥን 2024 ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ለየት ያሉ ነገሮች እና ስላሻሻላቸው ጉዳዮች እንዲሁም ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 11 ቨርዥኖች ውስጥ አንዱን ድጋፍ ያቆመበት መሆኑን ማስታወቁን የሚሉን መረጃዎች እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ፣ ፖኬት ካስትን ማስተዋወቃችንን ቀጥለን፣ በአፑ አካውንት እንዴት ክርኤት እንደምናደርግ እና የምናደምጣቸውን ፖድካስት እንዴት ሰብስክራይብ እንደምናደርግ በተግባር እንሰማለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት በማይክሮሶፍት ወድ ጽሁፍን ስለማስገባት እና ስለመሰረዝ በተግባ...
ኢናብ ቴክ - የዊንዶውስ ምንነት እና መሰረታዊ ክፍሎቹ 27.11.2023 18:26
በዚህ ክፍል ጤና ይስጥልን፣ ኢናባውያን። ከኮምፒውተር ጋር ተያይዞ ሁሌ ስሙ የሚነሳው ዊንዶውስ የተባለው የኮምፒውተር ክፍል ምንነት እና እና ዋና ክፍሎቹን የሚያስተዋውቅ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮችን እንድናውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልን ትችላላችሁ።
ኢናብ ቴክ - ፖድካስት ምንድን ነው? 25.11.2023 33:26
በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር ዔንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3 ይዟቸው ስለመጣቸው እና ስላሻሻላቸው ነገሮች እንዲሁም ለግለሰብ ተጠቃሚዎች ኢንቴል ለገበያ ያቀረበው ፕሮሰሰር ፍጥነት ሪከርድ መስበሩን የሚሉትን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ ፖኬት ካስት ስለተባለው አፕሊኬሽን የመጀመሪያ ክፍል ስለፖድካስት ምንነት እናብራራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት የማይክሮሶፍት ወድ አፕሊኬሽን እንዴት እንከፍታለን የሚለውን እናያለን። በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ ያለስክሪን ሪደር ጭምር ወርድን የምንከፍትበትን ዘዴም እንተዋወቃለን። ፖድካስቱን ለመከታተል፣...
ኢናብ ቴክ - የኮምፒውተር ኪቦርድ አጠቃቀም 15.11.2023 20:13
በዛሬው ክፍል ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ እንደምን አላችሁ! ኮምፒውተርን በተለይ በስክሪን ሪደር ለምንጠቀም ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆነው፣ በየእለቱ ኮምፒውተራችንን ስንጠቀም የግድ የሚያስፈልገን የኮምፒውተራችን ክፍል ኪቦርድ" ምንነት፣ ስለሚያካትታቸው ቁልፎች፣ ስለአጠቃቀማቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች በተለይ ለኮምፒውተር ጀማሪዎች ያዘጋጀሁትን ፕሮግራም አቅርቤላችኋለሁ። የኮምፒውተር ጀማሪም ባትሆኑ አንዳንድ ቁምነገር እንደማታጡበት ተስፋ አለኝ። አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ...
ኢናብ ቴክ - የዩኒግራም መሰረታዊ የአጠቃቀም ዘዴዎች 12.11.2023 32:46
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አዲስ ክፍል ይዘን ቀርበናል። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 14 ለገበያ ስለመቅረቡ እና ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እንዲሁም አፕል ዋነኛ ተፎካካሪው የሆነውን ጉግልን የመጀመሪያ ምርጫ ሰርች ኢንጅን ለምን እንዳደረገው የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ የቴሌግራም ክላያንት የሆነው ዩኒግራምን መሰረታዊ የአጠቃቀም ዘዴ እንዳስሳለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት ደግሞ ስለማይክሮሶፍት ወርድ ምንነት ማብራሪያ አቅርበናል። በተከታታይ ክፍሎችም የማይክሮሶፍት ወርድን መሰረታዊ አጠቃቀም እንቃኛለን። ፖ...
ኢናብ ቴክ - ሶፍትዌር ምንድን ነው? 02.11.2023 24:18
ሰላም ኢናባውያን፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኮምፒውተር ስርአት ውስጥ አንዱ ክፍል ስለሆነው ስለሶፍትዌር ምንነት፣ አይነቶች እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን በሚመለከት ያዘጋጀሁትን ዝግጅት አቅርቤላችኋለሁ። አዲስ ነገር እንደምታገኙበት ተስፋ አለኝ።
ኢናብ ቴክ ወ3ክ4 - የዩኒግራም ጠቃሚ ሴቲንጎች 30.10.2023 33:36
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ እነሆ ኢናብ ቴክ ፖድካስት አዲስ ክፍል ይዘን ቀርበናል። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ለአይፎን ስልኮች ኦፐሬቲንግ ሲስተም የሆነው አይኦኤስ አዲስ ቨርዥን ስለመልቀቁ እና ስላካተታቸው ነገሮች፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚደረሱ መጻህፍት ብዛት የተነሳ የመጻህፍት አከፋፋዩ ድርጅት በቀን መታተም በሚችሉት የመጻህፍት ብዛት ላይ ገደብ ስለማስቀመጡ የሚሉትን መረጃዎች እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዩኒግራምን ስንጠቀም ማስተካከል ስለሚጠቅሙን ሴቲንጎች ምንነት እና እንዴት እንደምናስተካክላቸው እንመለከታለን። ከአድማጭ በቀረበ ጥያቄ፤ "በራዲዮ ሹር አፕሊኬሽን አዳዲስ የተጨመሩ ኤፌም...
ኢናብቴክ - ሃርድዌር ምንድን ነው? 15.10.2023 20:50
ሰላም ኢናባውያን፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኮምፒውተር ስርአት ውስጥ አንዱ ክፍል ስለሆነው ስለሀርድዌር ያዘጋጀሁትን ዝግጅት አቅርቤላችኋለሁ። አዲስ ነገር እንደምታገኙበት ተስፋ አለኝ።
ኢናብ ቴክ - ወ3ክ3 - ዩኒግራም እና ዩኒግራም ፕላስ 06.10.2023 32:24
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ እነሆ ኢናብ ቴክ ፖድካስት ወቅት 3 ክፍል 3 ቀርቦላችኋል፤ ተጋበዙልን። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆኑት ጉግል ቶክ ባክ እና ጂሺዎ አዳዲስ ቨርዥኖችን ስለመልቀቃቸው እና ይዘዋቸው ስለመጧቸው ነገሮች እናወራችኋለን።። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዩኒግራምን ከኤንቭዲኤ ጋር ስንጠቀም ስለምናስተካክላቸው ሴቲንጎች እናብራራለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ጃውስንም ሆነ ኤንንቪዲኤን ስንጠቀም የሚያስፈልጉን መሰረታዊ የሚባሉ የዊንዶውስ ሾርትከቶችን እንገልጻለን። ከአድማጭ በቀረበ ጥያቄ፤ "ቢ ማይ አይ" ስለተባለው አፕሊኬሽን አገልግሎት አጭር ማብራሪያ ተካቷል።። ፖድካስቱን ለመከታ...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.