Abate Tsegaye

ENAB TECH PODCAST

News AM ↓ 100 episodes

በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።

Author

Abate Tsegaye

Category

News

Podcast website

www.ethionab.org

Latest episode

Aug 25, 2024

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ኢናብ ቴክ - ወ3 ክ2 - በዩኒግራም ቴሌግራምን የመክፈቻ መንገዶች 30.09.2023

በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት 3ኛ ወቅት 2ኛ ክፍልን ይዘን መጥተናል። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አፕል ኩባንያ ለገበያ ስላቀረባቸው የአይፎን 15 ስልኮች፣ የዊንዶውስ አፕዴት ጉግል ክሮም ላይ ችግር እያስከተለ ስለመሆኑ እና የቀድሞ ትዊተር ተጠቃሚዎቹን በሙሉ ወርሀዊ ክፍያ ለማስከፈል ማሰቡን ስለመናገሩ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር አፕሊኬሽኖች ማስተዋወቂያ ዝግጅት በዩኒግራም አፕሊኬሽን ወደቴሌግራም አካውንታችን የምንገባባቸውን 3 መንገዶች እና ዩኒግራምን መጀመሪያ ጊዜ ስለመክፈል እናያለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ የጃውስ አጠቃቀም ቀጣይ ክፍልን አቀርባለሁ። ከአድማጭ ለ...

ኢናብ ቴክ - የኮምፒውተር ምንነት እና ታሪካዊ አመጣጥ 28.09.2023

በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በኢናብ ቴክ ፖድካስት በተለያዩ ክፍሎች ሲተላለፉ ከነበሩ ዝግጅቶች ውስጥ፣ በመሰረታዊ ዝግጅት የኮምፒውተር ምንነት እና አመጣጥ የተመለከተው ዝግጅት በአንድ ክፍል ተሰናድቶ ቀርቦላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮቼን እንዳውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልኝ ትችላላችሁ።

ኢናብ ቴክ - ወ3 ክ1 - ዩኒግራም፣ ተደራሹ የቴሌግራም መጠቀሚያ 26.09.2023

በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጭ እና ተከታታዮች፤ እንደምን ከርማችኋል? የፖድካስቱን 3ኛ ወቅት ዝግጅት እነሆ ጀምረናል። በመጀመሪያው ክፍል፥- በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ 2023.2 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ጂሺዎም አዲስ ስላሻሻላቸው ነገሮች እንሰማለን። በኮምፒውተር አፕሊኬሽኖች ማስተዋወቂያ ዝግጅት ስለዩኒግራም አፕሊኬሽን እንመለከታለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ በጃውስ የኮምፒውተራችንን ኪቦርድ እንዴት እንደምንቆልፍ እና አንዳንድ ሌሎች ጠቃሚ ገጽታዎች አቀርባለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577...

ኢናብ ቴክ ክፍል 46 - ፕሮቶን ቪፒኤን 30.06.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ በሰኔ 2023 ቨርዥን ስለጨመራቸው ነገሮች እና ኢንቴል ከ15 አመት በኋላ የፕሮሰሰሮቹ ስም ላይ ለውጥ ሊያደርግ መሆኑን የሚሉትን መረጃዎች እንሰማለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት ስለፕሮቶን ቪፒኤን አጠቃቀም እንመለከታለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለጃውስ ልዩ ልዩ ሴቲንጎች እና አንዳንድ ኪቦርድ ሾርትከቶች ከነአጠቃቀማቸው አቀርባለሁ። የአድማጮች አስተያየትም ተካቷል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 45 - ቪፒኤን ምንድን ነው? 24.06.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በአዲሱ ቨርዥን ስላሻሻላቸው ነገሮች እና ጉግል ድራይቭ በቀድሞ ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ላይ መስራት ስለማቆሙ የሚሉትን እናነሳሳለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት ስለቪፒኤን ምንነትና ከቪፒኤን አፕሊኬሽኖች ስለአንዱ አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለጃውስ ከርሰሮች ቀሪ አጠቃቀም እንመለከታለን። በአድማጮች አስተያየት፣ ስለማይክሮሶፍት ወርድ፣ ስለኤምፒ3 ዳይሬክት ከት እና ሌሎችም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 44 - በአውዳሲቲ የማጀቢያ ሙዚቃን ማስተካከል 05.06.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ቲክቶክ የአሜሪካዋን ሞንታና ግዛት ስለመክሰሱ፣ ኒቫ የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ አገልግሎቱን ማቋረጡን ስለማስታወቁ እና ሞዚላ ፋየርፎክስ ዊንዶውስ 7 እና 8ን እስከወዲያኛው ስለመሰናበቱ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ በአውዳሲቲ ማሳያ የመጨረሻው ክፍል ከስር የሚሰማ ሙዚቃን በአውዳሲቲ ከፍ እና ዝቅ እንዲልልን እንዴት እንደምናደርግ በተግባር እንሞክራለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ የጃውስ ልዩ ልዩ ከርሰሮችን እንዴት እንደምናበራ የምንዳስስ ይሆናል። በአድማጮች አስተያየትም በማይክሮሶፍት ወርድ ጽሁፍ ከጻፍኩ በኋላ ፎንቱ ልክ አይደለም እየተባልኩ ነው፣ ቶ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 43 - በአውዳሲቲ ድምጽን ማስተካከል እና ማሳመሪያዎችን መጨመር 31.05.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ሜታ የተባለው የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ኩባንያ ትልቅ የተባለውን የ1.5 ቢሊየን ዶላር ቅጣት የተወሰነበት ስለመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሶስተኛውን የቴሌኮም ኩባንያ ወደገበያ ሊያስገባ መሆኑን ስለማስታወቁ፣ ኢንቴል 32 ቢት ፕሮሰሰሮችን ሊያስቀር ማሰቡን እና የታላላቅ ኮምፒውተሮች ዝርዝር ስለመውጣቱ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስንቀርጸው ድምጹ ያነሰብንን ክፍል እንዴት ለብቻው ድምጽ መጨመር እንደምንችል እና የገደል ማሚቶ ማሳመሪያን ወደቀረጽነው ድምጽ አጨማመር በአውዳሲቲ በተግባር እናያለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ መሰረታዊ መረጃዎችን እንደሰአት፣ እ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 42 - በአውዳሲቲ ኤክስፖርት ማድረግ እና የድምጽ አቀራረጽ 28.05.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ስላሻሻላቸው ነገሮች እንዲሁም ጉግል አካውንታችሁን ለሁለት አመት ካልተጠቀማችሁበት እሰርዘዋለሁ ማለቱን ከነምክንያቱ እነግራችኋለሁ። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ በአውዳሲቲ አጠቃቀም ያስተካከልነውን ድምጽ እንዴት ኤክስፖርት አድርገን ለራሳችንም ሆነ ለሌላ ሰው እንዲያዳምጠው ማድረግ እንደምንችል እና በኤላላ በኩል ደግሞ ድምጽ እንዴት እንደምንቀርጽ እንመለከታለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ የጃውስን አጠቃቀም በሚያብራራው ዝግጅቴ ጃውስን እንዳይለፈልፍብን እንዴት ዝም እንደምናስብል እና የንባቡን ፍጥነት እንዴት ከፍ እና ዝግ እንደምናደርግ እና ሌሎችንም እንመለከታ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 41 - በአውዳሲቲ ድምጽ ማስገባት፣ ማርተእ እና ማስቀመጥ 22.05.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዊንዶውስ በሚያዚያ ወር የለቀቀው አፕዴት የጉግል ክሮም አንድ አገልግሎት እንዳይሰራ ያደረገው ስለመሆኑ እና ሞንታና የተባለችው የአሜሪካ ግዛት ቲክቶክን ለብቻዋ ብሎክ እንዲደረግ ስለማገዷ የሚሉትን እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ በአውዳሲቲ አጠቃቀም ድምጽን እንዴት እንደምናስገባ፣ ኤዲት እንደምናደርግ እና ሴቭ አደራረግ በሚሉት ላይ በዛሬው ክፍል እናተኩራለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለስክሪን ሪደርስ የጃውስን አጠቃቀም በሚያብራራው ዝግጅቴ ጽሁፍን እንዴት እንደምናነብ የምንመለከት ይሆናል። በአድማጮች አስተያየትም ስለቲክቶክ፣ ስለቪዲዮ ኤዲተር፣ ስለጂሺዎ፣ ስለጉግል ክሮም፣...

ኢናብ ቴክ ክፍል 40 - አውዳሲቲ የድምጽ መቅረጫ እና ማርተኢያውን መተዋወቅ 18.05.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2023-05-06 ስላሻሻላቸው ነገሮች፣ ፋየርፎክስ ዊንዶውስ ሰባትን አልተውም ስለማለቱ፣ በተጠቃሚዎች ብዛት ደረጃዎችን ስለያዙት የዊንዶውስ ቨርዥን እና ብራውዘሮች እንዲሁም ዊንዶውስ 10 ያበቃለት መሆኑን ማይክሮሶፍት አስታወቀ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ አውዳሲቲ የሚባለውን አፕ ማስተዋወቅ ጀምሬ ስለምንነቱ እና ስለአጫጫኑ በዛሬው ክፍል እነግራችኋለሁ። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለስክሪን ሪደርስ የጃውስን አጠቃቀም ቀጣይ ክፍል ይዤ ቀርቤ ስለአከፋፈቱ እና ስለአዘጋጉ እንመለከታለን። በአድማጮች አስተያየትም ጂሺዎ በስልካችሁ በድንገት ጸጥ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 39 - በዶትወከር ወደምንፈልገው ቦታ በተግባር መድረስ 09.05.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ በቨርዥን 2023 ኤፕሪል አፕዴት ስላሻሻላቸው ነገሮች፣ የማይክሮሶፍት ቴክኒሻን ለማይክሮሶፍት ደንበኛ ዊንዶውስን ክራክ ሲያደርግ ስለመገኘቱ እና ቲክቶክ በተጨማሪ ሀገሮች ብሎክ እየተደረገ ስለመሆኑ የሚሉ መረጃዎችን አጋራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ፣ በዶት ወከር እስካሁን ስንሰበስባቸው የነበሩ የቦታ መረጃዎችን በእንቅስቃሴ ላይ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው እንመለከታለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለስክሪን ሪደርስ የጃውስን አጠቃቀም የመጀመሪያ ክፍል ይዤ ቀርቤያለሁ። በአድማጮች አስተያየትም ስለኮምፒውተር ቫይረሶች ጥንቃቄ የተወሰነ ምላሽ ተካቷል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https:...

ኢናብ ቴክ ክፍል 38 - ከኦፕን ስትሪት ማፕ ቦታዎችን ወደ ዶት ወከር ማስገባት እና ራሳችን ቦታዎችን ስለመመዝገብ 22.04.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2023-04-04 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ ሜታ የተባለው የፌስቡክ ባለቤት ኩባንያ ትዊተርን የሚፎካከር አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን ስለማስታወቁ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የምናውቃቸውን ሰዎች ድምጽ በማስመሰል የሚፈጸሙ የማታለል ወንጀሎች እየጨመሩ ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ ዶት ወከር በመጀመሪያ ይዞት ስለመጣው በበጎ ፈቃደኞች ስለሚመዘገበው ኦፕን ስትሪት ማፕ ከሚባለው አገልግሎት የቦታ መረጃ እንዴት እንደምናወርድ እንዲሁም በራሳችን ቦታዎችን እንዴት እንደምንመዘግብ አብራራለሁ። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለዊንዶውስ ኤክስፕሎረር...

ኢናብ ቴክ ክፍል 37 - ለዶት ወከር ከጉግል ፕሌስስ እና ከፎር ስኴር መረጃ ማስገባት 06.04.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2023.1 ይዟቸው ስለመጣቸው፣ ስላሻሻላቸው ነገሮች እና አንድ በምእራባውያን ባልተለመዱ ቋንቋዎችን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት ኤንቪዲኤ ስርአተ-ነጥቦችን በአማርኛ በአግባቡ ማንበብ ያልቻለበትን እና ሁለት አማራጭ መፍትሄዎቹን እነግራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ፣ ዶት ወከር ስለተባለው አፕሊኬሽን ማስተዋወቄን ቀጥዬ ከጉግል ፕሌስስ እና ከፎርስኴር የሚገኙ መረጃዎችን በመጠቀም ዶትወከርን እንዴት እንደምትገለገሉ አብራራለሁ።። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለዊንዶውስ ኤክስፕሎረር በሚያብራራው ዝግጅቴ ክፍል ስለፋይሎች አመራረጥ፣ ስለመሰረዝ፣ ስለስም አቀያየር እና ስለኮፒ አደራረግ አብራራለ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 36 - ከሰው የተላከልንን የቦታ መረጃ ዶትወከር ውስጥ ማስገባት 25.03.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጉግል በቶክ ባክ ስክሪን ሪደር ቨርዥን 13.1.0.5033 ስላሻሻላቸው ነገሮች አወራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ፣ ዶት ወከር ስለተባለው አፕሊኬሽን ማስተዋወቄን ቀጥዬ ከሰው የተላከላችሁን ዳታ በመጠቀም ዶትወከርን እንዴት እንደምትገለገሉ አብራራለሁ።። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለዊንዶውስ ኤክስፕሎረር በሚያብራራው ዝግጅቴ ክፍል ሁለት ስለትሪ ቪው፣ ስለፎልደር ቪው እና አጠቃቀማቸው አብራራለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 35 - ዶት ዎከር 11.03.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2023-03-03 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ ዊንዶውስ 11 ሞመንት 2 የተሰኘ አዲስ አፕዴት ስለመልቀቁ፣ የካናዳ መንግስት ሰራተኞቹ ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ ስለመከልከሉ እና ቀጣዩ ዊንዶውስ ቨርዥን ስለመታወቁ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ ዶት ወከር ስለተባለው አፕሊኬሽን አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለዊንዶውስ ኤክስፕሎረር የሚያብራራ ዝግጅት ይዤ ቀርቤያለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት...

ኢናብ ቴክ ክፍል 34 - ሻርፕ ኪስ የኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፍ ማስተካከያ 25.02.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 14 የሙከራ ቨርዥን መለቀቁ፣ በአንድሮይድ 14 ጉግል የሶስተኛ ወገን አፕ ስቶሮችን ሊፈቅድ ስለመሆኑ፣ ማይክሮሶፍት አምርሮ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረርን ከሁሉም ተጠቃሚዎቹ ኮምፒውተር ላይ ሊሰርዝ መሆኑን እና ኢትዮቴሌኮም ለግል ባለሀብቶ ድርሻው የሚሸጥበት ሂደት በድጋሚ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕ ስ ኤንድ ትሪክስ፣ የኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎችን ከአንዱ ወደ ሌላው መቀያየር ስለሚያስችለን ሶፍትዌር አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና፣ በዊንዶውስ ፊት ለፊት ከሚመጡ ክፍሎች ውስጥ ስለታስክ ባር እና ስለሲስተም ትሬይ አስተዋውቃችኋለሁ። ፖድካ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 33 - በአትቮይስ ጽሁፎችን ማድመጥ 19.02.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ ፎር ዊንዶውስ ለቨርዥን 2023 የየካቲት 2023 አፕዴት መልቀቁን እና ስላካተታቸው ነገሮች፣ ጉግል ክሮምም ቨርዥን 110ን ስለመልቀቁ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅቴ፣ ስለአት ቮይስ አላውድ ሪደር የመጨረሻውን ክፍል፣ ጽሁፎችን በአትቮይስ እንዴት ማድመጥ እንችላለን? ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ አቀርባለሁ። በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና፣ ስለዊንዶውስ ሲስተም ማስተዋወቅ እጀምራለሁ። ከአድማጭ አስተያየት አካትቼ አቅርቤያለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 097303457...

ኢናብ ቴክ ክፍል 32 - የአት ቮይስ ቀሪ ሴቲንጎች ማብራሪያ 10.02.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ቻት ጂፒቲ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት አፕሊኬሽን ደንበኞችን በማፍራት ሪከርድ መስበሩን፣ ሳምሰንግ አዲስ ስለለቀቃቸው ስልኮች እና በዊንዶውስ ሰንጠረዥ ዊንዶውስ 10 መምራት መቀጠሉን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅቴ፣ በአት ቮይስ አፕሊኬሽን ቀሪዎችን የሴቲንግ ክፍሎች አብራራለሁ። ከአድማጭ ጥያቄዎች ባላቦልካ ከማይክሮሶፍት የሆኑትን እነአመሀ በድጋሚ እየሰራ ስለመሆኑ እና ሌሎች ምላሾችን አካትቼ አቅርቤያለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣...

ኢናብ ቴክ ክፍል 31 - የአትቮይስ አላውድ ሪደር ሴቲንጎችን ስለማስተካከል 29.01.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 10 ለመደበኛ ተጠቃሚዎች መሸጥ ማቆሙን ማስታወቁን፣ የሁሉም ኦስትሪያ ዜጎች የግል መረጃ ለገበያ ስለመቅረቡ፣ በአሜሪካ የበረራ ተቆጣጥራኢ ተቋም የአንድ ፋይል መሰረዝ የመላው ሀገሪቱን በረራ ለሰአታት ማስቆሙን እና ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 11 21ኤች1 ን በግድ ወደ 21ኤች2 አፕዴት ማድረግ መጀመሩን የሚሉትን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅቴ፣ በአት ቮይስ አፕሊኬሽን የሪዲንግ፣ የስክሪን እና የስሊፕ ታይመር ሴቲንጎችን አብራራለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎች አጠቃቀም በመጨረሻው ክፍል በኮምፒውተር ኪቦርድ በተሻለ ፍጥነት ለመጻፍ የሚያስች...

ኢናብ ቴክ ክፍል 30 - የአትቮይስ የመጀመሪያ ስክሪን እና ሴቲንጎቹ 22.01.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2023-01-17 ይዞት ስለመጣው ጉዳይ፣ ዊንዶውስ ዲፌንደር አንቲቫይረስ ባለፈው ሳምንት የለቀቀው አፕዴት ስለሚሰርዛቸው ፋይሎች እና ችግሩ ከገጠማችሁ ልታደርጉት ስለምትችሉት ነገር መረጃ አጋራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ፣ አት ቮይስ አፕሊኬሽን ያሉትን ክፍሎች አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎች አጠቃቀም በክፍል ሶስት ሲክስ ፓክ ስለተባሉት ቁልፎች ማብራሪያ አቀርባለሁ። ከአድማጭ ጥያቄም ሂድን የሆነን ፎልደር እንዴት መመለስ እንደሚቻል፣ ጂሺዎን እንዴት ማስጀመር እንዳለብን እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ አካትቼ አቅርቤያለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣...

ኢናብ ቴክ ክፍል 29 - አት ቮይስ የአንድሮይድ ጽሁፍ ማድመጫው 15.01.2023

በዚህ ክፍል፣e በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ቶክባክ በቨርዥን 13.1 ስለጨመራቸው፣ ዊንዶውስ 8.1 እና 7 የመጨረሻ ድጋፋቸውን በዚህ ሳምንት ስለማግኘታቸው እና ኢንቴል 6 ግጋ ሀርዝ ፕሮሰሰር ለገበያ ስለማቅረቡ የሚሉ መረጃዎችን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ አት ቮይስ ስለተባለው የአንድሮይድ የጽሁፍ ማድመጫ አፕሊኬሽን አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎች አጠቃቀም የማብራራበትን ክፍል ሁለት አቀርባለሁ። ከአድማጭ ጥያቄም በባላቦልካ እነአመሃን እንዴት መቅረጽ እንደሚቻል እና ስለዊንዶውስ 11 በአሮጌ ኮምፒተር ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabte...

ኢናብ ቴክ ክፍል 28 - ስሪ ዲ ዩቲውብ ዳውንሎደር በራሱ ዳውንሎድ ማድረግ 10.01.2023

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2022.4፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2023-01-04 እና ቡክወርም የተባለው መጽሀፍ ማንበቢያ በቨርዥን 2022.1 ቤታ 3 በለቀቋቸው ማሻሻያዎቻቸው ስለጨመሯቸው ነገሮች እንዲሁም ትዊተር የተባለው ማህበራዊ ድህረገጽ የ400 ሚሊዮን ደንበኞቹ መረጃ ተሰርቆ ለገበያ ስለመውጣቱ የሚልትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስሪ ዲ ዩቲውብ ዳውንሎደር የተባለውን ሶፍትዌር አጠቃቀም መንገድ ቀሪዎቹን እና የመጨረሻዎቹን ሁለቱን አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎች አጠቃቀም ማብራራት እጀምራለሁ። ለአድማጭ ጥያቄም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 27 - ስሪዲ ዩቲውብ ዳውንሎደርን ከብራውዘር ሊንኮችን በማምጣት ስለመጠቀም 31.12.2022

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በቨርዥን 2022.12.30 ስለጨመራቸው ጉዳዮች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስሪ ዲ ዩቲውብ ዳውንሎደር የተባለውን ሶፍትዌር አጠቃቀም መንገድ ሁለቱን አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ዋና ዋና ስለሚባሉት ስክሪን ሪደር አይነቶች እነግራችኋለሁ። በአድማጭ ጥያቄም ስለጂሺዎ፣ ስለኖኪያ ኢ5 እና ስለጃቫ ፕሮግራሚንግ ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ...

ኢናብ ቴክ ክፍል 26 - ከስሪ ዲ ዩቲውብ ዳውንሎደር ባች ጋር መተዋወቅ 26.12.2022

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ በቨርዥን 2023.2212.23 እና ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3.3 ስላደረጓቸው ማሻሻያዎች የምንመለከት ሲሆን ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር እስከወዲያኛው ከኮምፒውተሮች ላይ ሊወገድ ስለመሆኑ እዘግብላችኋለሁ። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስሪ ዲ ዩቲውብ ዳውንሎደር ስለተባለው ሶፍትዌር አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ ማቅረቤን ቀጥዬ አፕሊኬሽን ከተባለው የሶፍትዌር አይነት ውስጥ ለእኛ በቀጥታ በየቀኑ ስለሚያገለግለን ስክሪን ሪደር ምንነት አስረዳለሁ። ለአድማጭ ጥያቄም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/en...

ኢናብ ቴክ ክፍል 25 - የዋይ ሚውዚክ አጠቃቀም 19.12.2022

በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አፕል ኩባንያ አዲስ ስለለቀቃቸው ሶፍትዌሮች፣ ዊንዶውስ 7 እና 8 ይፋዊ ድጋፋቸው የሚቋረጥበት ቀን ስለመገለጹ፣ ፋየርፎክስ ብራውዘር ቨርዥን 108 ስለመልቀቁ እና ቦነስ! ስለኢትዮቴሌኮም እንዲሁም ሳፋሪኮም ስለጨውመሯቸው አገልግሎቶች አወራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ ዝግጅቴ፣ ዋይ ሚውዚክ የተባለውን የዩቲውብ ማዳመጫ አፕ አጠቃቀም አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ ማቅረቤን ቀጥዬ አፕሊኬሽን ስለተባለው የሶፍትዌር አይነት አስረዳለሁ። ለአድማጭ ጥያቄም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ...

Listen to the ENAB TECH PODCAST podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.