DW

እንወያይ

News AM ↓ 100 episodes

በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 5, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026
በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ? 22.06.2026
ውይይት፤በምርጫው ከሚያሸንፈው መንግስት በመጭው አምስት የስልጣን ዓመታት ምን ይጠበቃል? 12.06.2026
ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ 07.06.2026
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የሐገሪቱን ችግሮች ለማቃለል ይፈይድ ይሆን? 24.05.2026

ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዳዶቹ የፓርቲነት ፍቃድ ላለማጣት ሲሉ ብቻ የሚወዳደ,ሩ እንዳሉ አስታዉቀዋል።የኢትዮጵያን ምርጫ ሒደትና ሁኔታን የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የዘንድሮዉን ምርጫ «ለገዢዉ ፓርቲ ሕጋዊ ዕዉቅና ለመስጠት ያለመ የታይታ» ምርጫ ይሉታል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የምርጫዉ የእስካሁን ሒደት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና የሕዝብ ተሳትፎን ያሰፋ በማለት ያወድሱታል

እንወያይ፤ በኢትዮጵያ የመናገር ነጻነት እና የጋዜጠኝነት ፈተናዎች 17.05.2026
በቋፍ ያለው የሀገር ውስጥና የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ ፖለቲካዊና የፀጥታ ሁኔታ 10.05.2026
የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅትና ተግዳሮቶቹ 03.05.2026
የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ኢትዮጵያ ላይ ያሳደረው ጫና እንዴት ይቃኛል? 26.04.2026
ውይይት፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 8 የስልጣን አመታት ሲቃኙ 12.04.2026
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ 05.04.2026

ጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።

በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች 29.03.2026

በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህርና የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተመራማሪ ፍቅር ጌታቸው በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ውይይት፤ ኢትዮጵያ ብርቱ ፈተና የደቀነውን የነዳጅ እጥረት እንዴት ትወጣ? 22.03.2026
የኢራን ጦርነት ለዓለምና ለቀጠናችን ያለው አንድምታ 15.03.2026
እንወያይ፤ የነጻ ፕሬስ እና የጋዜጠኞች ፈቃድ መሰረዝ ተጽኖ በኢትዮጵያ 08.03.2026
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ 01.03.2026

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት ልጃለም፤ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ዳምጠው ተሰማን በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዷል።

እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው? 22.02.2026

ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ሆነዋል።

እንወያይ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን? 15.02.2026
የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔ 08.02.2026
ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር? 01.02.2026
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ? 25.01.2026

የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?

ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነት 18.01.2026

የትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።

ዓለም በጎርጎሪዮሱ 2025፥ ዐበይት ኩነቶች 04.01.2026
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ስደተኞች በአሜሪካና በአውሮፓ የገጠማቸው ፈተና 28.12.2025
የመገናኛ ብዙኀን ሁኔታና መጪው ምርጫ በኢትዮጵያ 21.12.2025

Listen to the እንወያይ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.