DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 10.07.2026 28:32
የዓለም ዜናን በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሄት ፣ በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭ፤ በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄ፤ የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን?፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽ፣ በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው መገለጹ እንዲሁም አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። የወጣቶች ዓለም መሰናዶ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፦ የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎች የንባብ ባህልን እያዳከሙ ይሆን? በሚል ርእስ ተቀናብሯል ።
የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 07.07.2026 20:13
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነዉ ሲሉ፣ -የዚያዉ ከትግራይ ክልል ወጣቶች ደግሞ አፈሳና የጦርነት ዝግጅት እንዳሳሰባቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የዳግም ጦርነት ዝግጅት፣ ወቀሳና ሥጋቱን ዜና መጽሔቱ በሁለት ዘገቦች ያስተነትናል።የኢትዮጵያ ምርጫ የጥቃት ኢላማ እንደነበር፣ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ግን ዘንድሮም በ10.2 በመቶ አድጓል መባሉ ከወደ አዲስ አበባ ተሰምቷል።ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕስችን በሱዳንዋ ሥልታዊ ከተማ አል-ዑቤይድ የተፈፀመዉ የመብት ጥሰትና ይደርሳል የተባለዉ ተጨማሪ ጥፋት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ኮሚሽንን እያባተለ መሆኑን ይቃኛል።
DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 06.07.2026 14:21
በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋት፣ የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢ፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታ
የሰኔ 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 03.07.2026 22:11
እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢ ፣ በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ፣በድሬደዋ የተማሪ ህፃናት ምገባን በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ እንዲሁም የቀድሞ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 02.07.2026 26:05
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች 13 ሰዎች መግደላቸዉን የሚቃኝ ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን አስተማሪዎች ተማሪዎችን ላለመፈተን ማደማቸዉን ከዞኑ አስተዳደር መልስ ጋር ያሰባጠረ ዘገባም አለዉ።የአዉሮጳ የሙቀት መጠን ማየልና የፖለቲካዊ መርሕ ለዉጥ ጥያቄ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ 105ኛ ዓመት በአል፣ የዓለም የእግር ኳስ ግጥሚያ የአፍሪቃ ቡድናት ሽንፈት ያልናቸዉንም ርዕሶች ያስተነትናል።
የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.07.2026 18:17
የዜና መጽሔት፤ አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናት፤ በጋምቤላ ክልል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስለሚኖራቸው ሚና፤ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጀመሩ እንዲሁም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እዚያ ስለሚወለዱ ልጆች ዜግነት ያሳለፈው ውሳኔን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 30.06.2026 19:25
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።
DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 29.06.2026 19:59
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ
የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 26.06.2026 25:03
ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።
የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 25.06.2026 24:34
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?
የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 24.06.2026 17:17
በዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤ የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁን ከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።
የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 23.06.2026 24:01
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 22.06.2026 17:33
መጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገ 20.06.2026 3:29
ምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።
DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 19.06.2026 23:21
በሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።
የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 18.06.2026 25:10
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤ መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
የሰኔ 10 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 17.06.2026 21:17
አሳሳቢው የጦርነት ስጋት በሰሜን ኢትዮጵያ ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ «የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ»ን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ፣ ዩናይትድ ስቴትሰና ኢራን ደረሱበት የተባለው ስምምነት አፍሪካን እንዳያዘናጋ ተንታኛች ማሳሰባቸው እንዲሁም ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች ዩክሬንን ለመደገፍ መስማማታቸው የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው
የሰኔ 9ቀን 2018 የዜና መፅሔት 16.06.2026 19:04
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ዉድነት በደሞዝተኞች ላይ ያሳረፈዉን ጫና ችግር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በትግራይ ክልል አዲስ የወጣዉ የወታደራዊ አገልግሎት ሕግ ያስከተለዉ ተቃዉሞና ሥጋት፣ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ መታሰሯና የአፍሪቃ ሕብረት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ በተቀጣጠለዉ የዉጪ ጠል ጥቃትና ዛቻ ላይ ሊነጋገር ማቀዱን ዜና መፅሔቱ በየተራ ይተነትናል።
DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 15.06.2026 16:26
በሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተና፣ የኢራን አሜሪካ ስምምነት እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ተካተዋል።
የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.06.2026 23:43
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጥሪ ነዋሪዎች ከአሸናፊው ፓርቲ ምን ይጠብቃሉ ? ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች፤ 1655 ዜጎች ደግሞ በምህረት እንዲለቀቁ ተደረገ ለአሜሪካዉያን የኤቦላ ማገገምያ ማዕከል ኬንያ ዉስጥ መገንባቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረትና ደቡብ ኮሪያ፤ የሰሜን ኮሪይና ቻይና ጉባኤዎች
የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 11.06.2026 25:31
በዜና መፅሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ መሆኑን መናገሩ፣ ሰቆጣ የተጠለሉ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ መጋለጣቸውን መግለፃቸው ፣ -ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ መቀጠሉ ፣ የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ መጠየቁ ፣ ዛሬ በሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው ። በባህል መድረክ ለህክምና ወደ በጀርመን በመጣበት አጋጣሚ እና የስዕል እግዚቢሽን ያቀረበውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላን እንግዳዉ አድርጓል።
የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዜና መፅሔት 10.06.2026 18:11
ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት፣ ጋምቤላ ክልል ዳግም ያገረሸው የፀጥታ ስጋት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ24 የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ይፋ ማድረግ መጀመሩ፤ ለመጪው ዓመት ከ2,3 ትሪሊየን በላይ ብር የመንግሥት በጀት መታቀዱ እንዲሁም የዲጂታል ገቢ እና አዲሱ ፈተና የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
የዜና መጽሔት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 09.06.2026 19:46
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ፈደ,ራዊ መንግሥትና በህወሓት መካከል የናረዉን ዉጥረት ለማርገብ የአፍሪቃ ሕብረትን ሚና የሚቃኝ ቀለ ምልልስን ያስቀድማል።የትግራይ ወጣቶች በብዛት ከክክልሉ መዉጣታቸዉንና ምክንያቱን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።የትራፊክ አደጋ መደጋገምና መፍትሔዉ ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የኤርትራና የግብፅ ወዳጅነት ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም የሚኖረዉን በጎ መጥፎ ዉጤት በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.