DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የሰኞ ሰኔ አንድ ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 08.06.2026 21:26
በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ስጋት በትግራይ የየደረሰዉ የድሮን ጥቃት እና አካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ያልሰጡ በሰሜንና ደቡብ ወሎ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ነገ ሰኔ 2 ቀን የምርቻ ድምፅ ሊሰጡ መሆኑ ፤ እንዲሁም ኢሰመኮ - አርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ምዕመናን እና ቤተክርስትያን ላይ የተፈፀመ ጥቃትን በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለፁ በሚሉ ርዕሶች የተቀናበሩት በስፋት ይተነተናሉ።
የግንቦት 27 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት 04.06.2026 27:07
በዜና መጽሔት በአርሲ ዞን የተገደሉ ወገኖችን በሚመለከት የመንግሥት እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ምላሽ፤በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሔራዊ አስተዳደር የጻግብጂ ወረዳ በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል መባሉ፤ግንቦት 24 ቀን ስለተካሄደው ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት፤ ድኅረ ምርጫ በደቡብ ሕዝቦች ክልል ፤ በሰባተኛው ምርጫ የተሳተፈው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ድሬደዋ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ችግር ደርሶብኛል ማለቱ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMF ለኢትዮጵያ 468 ሚሊየን ዶላር ለመልቀቅ መስማማቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።
የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 03.06.2026 33:10
ከምርጫ ማግሥት ማን ምን አለ? የተሰጡ አስተያየቶች፤ በአርሲ የተፈጸመው ግድያ እና የቀረበው አቤቱታ፤ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የኢጋድና የኅብረት-ለምርጫ የመጀሪያ ጊዜ ዘገባ፣ የአማራ ክልል ወጣቶች ጥሪ ከምርጫው ማግስት በኋላ፤ ብርን ያዳከመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሰኞው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ድህረ ምርጫ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ቃለ መጠይቅ
ልዩ ዝግጅት፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ 02.06.2026 46:52
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ዛሬ በየአካባቢው የወጡ ጊዜያዊ ውጤቶችን እንዲሁም የምርጫውን ሂደት፣ የፀጥታ ችግሮችና እና ተያያዥ ክስተቶችን የሚቃኙ ዘገባዎችን ያካተተ ልዩ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትናንት የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችንም ማጽደቁን መነሻ ያደረገ ዘገባም አለን።
በምርጫ ከሚያሸንፈው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል? 02.06.2026 4:41
ትናንት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በመጭው አመስት አመታት የሚያስተዳድራቸውን ለመምረጥ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል። ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊው አካል በቀጣይ አምስት አመታት ሀገሪቱን የማስተዳደር ሀላፊነት ይጣልበታል።ለመሆኑ ከመጭው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?
የግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.06.2026 12:29
አርዕስተ ዜና ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ዛሬ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ለሚወዳደሩ እጩዎች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በበሻሻ ከተማ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ታዬ ዐፅቀ ሥላሴ ደግሞ በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት ድምጽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በጸጥታ ምክንያት ወደ 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ” አለመከፈታቸውን ዛሬ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ ችግር መቋረጡን ተናግረዋል።
የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 29.05.2026 30:23
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጎሀፅዮን አካባቢ፤ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የጓሚዙ 12 መንገደኞች መገደላቸውን መጭው ምርጫ ከተሳታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከታዛቢዎች እና ከመራጮች አንፃር በአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በክልሉ ባለው ግጭት ሳቢያ ግድያ እና ዝርፊያ እየደረሰብን ነው ማለታቸው በደቡብ አፍሪቃ የሚታየውን የመጤ ጠል ጥቃት የሚያስቃኙ አራት ዘገባዎችን አካቷል።
DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 28.05.2026 29:09
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ማስጠንቀቂያና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምላሽ፣ የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ድባብ በአዲስ አበባ፣ ''ምርጫው፣ አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው።''የጋራ-መድረክ፣ ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣
የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 27.05.2026 33:32
የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱንን የኢድ አል አድሀን በዓል የተመለከቱ ዘገባዎች ያስቀድማል፤ የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ እና የፓርቲዎች አስተያየት፤ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል። በትግራይ ክልል “የወጣቶች የግዳጅ ምልመላ” እየተደረገ መሆኑ መገለጹ፤ በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ከህወሃት ቃል አቀባይ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል።
የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 26.05.2026 32:43
በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በአማራ 8፣ በትግራይ 38 ምርጫ ክልሎች ላይ ግንቦት 24 ምርጫ አይደረግም መባሉ፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በአማራ ክልል፤ የምርጫ ቅስቀሳቃ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫ ዘመቻ እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት ባልተጠናቀቁ የቤት ስራዎቹ ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለፀ በሚሉ ርዕሶች ስር ተጠናቅረዋል።
የግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 25.05.2026 18:01
በፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ክፋይ ምርጫ ቦርድ "የዜጎችን መሠረታዊ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊነጥቅ አይገባም" ሲል ማሳሰቡን፤ የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ " ስልታዊ የሆኑ የምርጫ ሕግ ጥሰቶች ካልታረሙ ከምርጫው እራሱን ለማግለል እንደሚገደድ ማሳወቁን፤ በትግራይ ስላለው የጦርነት ድባብ የባለሙያ አስተያየት
የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም 22.05.2026 24:47
የዜና መጽሔት-1-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅት- 2-ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉ የድሪዳዋ ከተማ እጩ ተወዳዳሪና ሐረሪ ክልል የሚንቀሳሱ ሌላ እጩ ተወዳዳሪ ስለ ምርጫው ሂደት የሰጡት አስተያየት 3 -የንግድ ሱቆቻቸው የፈረሱባቸው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ-4-ወደ ውጭ የሚላክ የኢትዮጵያ ቡና ላይ የተጋረጠው ፈተና - 5 ቻይና በዓለም ኃያላን ተፈላጊ የሆነችበት ምክንያት በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርቡበታል ሳምንታዊው ከወጣቶች ዓለም ከምርጫ 2018፤ ወጣቱ በርግጥ ምን ይፈልጋል?- በሚል ርዕስ ጋር ከተቀናበረ ዝግጅት ጋር ይጠብቀናል ።
የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 21.05.2026 26:46
የዜና መጽሔት፤ ምርጫ ቦርድ ያሰማራው የፀጥታ ኹኔታን የቃኘው ቡድን ያቀረበው ውጤትና የፓርቲዎች አስተያየትን ያስቀድማል፤ በምርጫ 2018 እና የተቀዛቀዘው የኦፌኮ ተሳትፎ፤ የደቡብ ወሎ የምርጫ ካርድ ውዝግብ ታግተው የነበሩ ከመቶ በላይ የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ጊዜያዊ ሠራተኞች መለቀቀቅ፤ የብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እና የኑሮ ውድነት ስጋት እንዲሁም አፍሪካ ሲዲሲ ኢቦላ አስቸኳይ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው ማለቱን የሚስቃኙ ስድስት አካቷል።
የግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.05.2026 16:48
በዜና መጽሔት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎች ለቀጣዩ ምርጫ «እንኳን ሌላ ፓርቲ ብልጽግናም ራሱ አይቀሰቅስም» ማለታቸው፤ ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሥራና ሠራተኛ ባሰሙት ንግግር የሰዎች አስተያየት፤ የሁለት ዓመት አስገዳጁ የቤት ኪራይ ውል አዋጅ ሊያበቃ መቃረቡ፤ እንዲሁም የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) በምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መመሠረቱ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 15.05.2026 28:01
ዜና መጽሔት -ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለው ጥቃት -ስለምርጫ ዝግጅት ከአዲስ አበባ እና ከደሴ የተሰባሰበ የሕዝብ አስተያየት -ፈረንሳይ በአፍሪካ አዲስ አጋሮችን እየፈለገች ነው -የአሜሪካ ፕሬዝደንት የቻይና ጉብኝት እና የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት እና አዲስ የኤች አይ ቪ መድኃኒት ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ መታቀዱን ያስቃኘናል።
የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 13.05.2026 18:44
መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ከ30 በላይ መንገደኞች በታጣቂዎች መገደላቸዉን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል።የህወሓት አባላት ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች ከራያ አለማጣ ከተማ 50 የቤተ-ክሕነት ተማሪዎች ማገታቸዉ ከደሴ ሲዘገብ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ሕብረት አንዳድ አካባቢ በመራጮች ምዝገባ ሒደት ሕግ መጣሱን አስታዉቋል።ዜና መፅሔቱ የትግራይ ጋዜጠኞች ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ ለመሔድ መገደዳቸዉን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
የግንቦት 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 12.05.2026 21:04
የዓለም ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፣-በዋግ ኸምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች አቤቱታ፤ ዓለም አቀፉ የፍልሰኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች በአደገኛው መስመር መጓዛቸውን አላቆሙም ማለቱ፤ የኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት፤ አብላጫ ድምጽ ወይስ ተመጣጣኝ? ፤ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የስብሰባ ትኩረት እንዲሁም ከመሬት ለአራሹ ትግል እስከ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዘለቁትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቶ ዘገየ አስፋውንም የሚያስታውስ ጥንቅር አካቷል።
የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 11.05.2026 19:26
በዜና መፅሄት ጥንቅራችን -ለሰባተኛው ዙር ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በገንዘብ ድልድል ላይ ያቀረቡት ቅሬታ -የኢኮኖሚ ዕድገት መመዘኛ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታም ከግምት ማስገባት አለበት መባሉን -የአየር ንብረትን መቋቋም የሚያስችል የግብርና ቴክኖሎጂን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን -የኢራን የሰላም ዕቅድ በአሜሪካ ውድቅ መሆኑን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።
የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 08.05.2026 27:09
ቀዳሚውን የዓለም ዜና በሚከተለው የዜና መጽሔት -የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)የቅድመ ምርጫ ሂደቶች ላይ ጥሰቶች እንደነበሩ መግለጹ ፣በአማራ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስሞታ፣ ስለ መገናኛ ብዙኃን ምኅዳር የመንግሥት፣ የባለሙያዎች እና አጥኚዎች ዕዉነት፣ -የነዋሪዎችን ህይወት ያቃወሰው የትራንስፖርት እጥረት በኢትዮጵያ፣ -የሞት ፍርድን የሚጠባበቁትን ጨምሮ ሰነድ አልባዎቹ ኢትዮጵያዉያን በሳዉዲ፣ የዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ተኩስ አቁም ወዴት ያመራ ይኾን? በተሰኙ ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ ሳምንታዊ የወጣቶች ዓለምም በሰዓቱ ይቀርባል።
የሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 07.05.2026 25:38
በዜና መጽሔት የደቡብ አፍሪቃው ዘመቻ ዱዱላ’ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን እያደነ ነው፤ የወለንጪቲ የልማት ተነሺ ገበሬዎች ካሳ አልተከፈለንም ሲሉ ማማረራቸውን፤ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮች የገበያ ተግዳሮት ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ርዳታ እንዳይቋረጥ መጠየቁ እንዲሆም ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች 10 ቢልዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዷ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 06.05.2026 22:13
አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀብ ለማንሳት ማጤኗ ለኢትዮጵያ በረከት ወይስ መዘዝ? ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ የጥቃት ኢላማ መሆናቸው የአላማጣና አካባቢው ወጣቶች የጦርነት ሥጋትና ስደት የሱዳን ክስና እና የኢትዮጵያ ምላሽ ህወሓት ትናንት የወሰደው 'ርምጃ እና የሚኖረው ውጤት
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.