DW

ዜና መጽሔት

News AM ↓ 100 episodes

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 10, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 05.05.2026

ዛሬ ታስቦ የዋለዉን 85ኛ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል መታስብያን በማስታከክ ፤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም ሲል የሚያጠይቅ ዘገባን ይዘናል። ለ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ እና የሚያሳድረዉ ጫናን የሚዳስስ ዘገቦችም በተከታታይ ይቀርባሉ። የአሜሪካዉ ትራምፕ በጀርመን ከሰፈሩ የአሜሪካን ወታደሮች መካከል ወደ 5,000 የሚሆኑትን ለማስወጣት እቅድ መያዛቸዉ እና የተሰጡ ግብረ መልሶችን የሚዳስስ ዘገባንም ይዘናል።

የዜና መጽሔት፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 04.05.2026
የሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.05.2026

የደቡብ አፍሪቃው መጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያንን ብርቱ ስጋት ላይ ጥሏል አውሮፓ ሕብረት የፕሪቶሪያን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥሉ 'ርምጃዎች እንዲረግቡ ጠየቀ “አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ሲታወስ ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት የቤት አቅርቦት ቀውስ ፈጥሯል-ተመድ

የዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 30.04.2026
የሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 29.04.2026

ለኦሮሚያ ክልል ዘላቂ ሰላም መፍትሄ የሚሻው የወጣቶች ምክክር ፣ በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት ያስከተለው የኑሮ ምስቅልቅል ፣ ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር የጀመረው የብትን ጭነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ዕድል ፣ «በኢትዮጵያ አካታች ዕርቅ ይምጣ» የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኅበራት ጉባዔ በአሜሪካ፣ እንዲሁም አፍሪቃ ወደ ኋላ የቀረችበት የተመድ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች የትኞቹ ናቸው

የሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 28.04.2026

በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ።የኢትዮጵዊያን ግድያ በጆሃንስበርግ ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ምርጫ ፤ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የተረቀቀው የሳይበር ደህንነት አዋጅ ምን ይዟል? እንዲሁም የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ወቅታዊ መግለጫ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።

የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት 27.04.2026

በዜና መጽሔት፤ የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ መብት እንዳይገድብ መጠየቁ ፤ ምርጫ ቦርድ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚያጣራ ቡድን ማሰማራቱ፤ ከፀሐይ ኃይል የሚያመነጭ ቴክኒዎሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍሪካ የፖሊሲ አውጭዎች ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ትኩረት እንዲሰጡ የዘርፉ ባለሙያ ማሳሰባቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።

የሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት 24.04.2026

በዜና መጽሔት፤ በአርሲ ዞን ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ ንጹሐን ላይ የተፈጸመው ጥቃት፤የአፍሪካ ሃገራት በሰብዓዊ መብት ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንደማይተገብሩ ተገለፀ በ614 ምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንደሚያካሂድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ፤ ተዛብተው ተጽፈዋል የተባሉ ታሪኮች እንዲታረሙ ያሳሰበው የኦሮሞ ምርምር ማሕበር ጉባኤ ፤እንዲሁም እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት መራዘሙን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።

የሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 23.04.2026

የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው እና አወዛጋቢ በሆኑት የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የመብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ወች መግለፁን ኢትዮጵያ ከነዳጅ ወደ ኤለክትሪክ መኪኖች ሽግግር እያደረገች መሆኑን፤ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኤለክትሪክ መኪና አጠቃቀም፣ እና መቋጫ ባጣው የአሜሪካ እና የኢራን ውዝግብ እንዲሁም የተዘጋው ሆርሙዝ ወሽመጥ

የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ዜና መፅሄት 22.04.2026

የዜና መጽሔታችን በአበርገሌ ወረዳ ስለተከሰተው ግጭት፤ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳይቀበለው መቅረቱ፤ የአውሮፓ ኮሚሽን ለአፍሪካ አገራት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት የሚውል ዕርዳታ መስጠቱ፤ እንዲሁም የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያስተላለፉት ውሳኔና አንደምታ በተመለከተ ከብራስልሱ ወኪላችን ያደረግነው አጭር ቆይታ ይዳሰሳሉ።

የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት 21.04.2026

b,ዛሬ የዜና መጽሔታችን ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሰፊ ሥልጣን የሰጠው "የአቪዬሽን ደኅንነት" ማሻሻያ አዋጅ መፅደቅ፣ የነዳጅ እጥረት እና የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር በአሶሳ ፣’"ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተጣለብን ነው" ሲሉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች መግለፃቸው ፣እንዲሁም ቀነ ገደቡ እየተጠናቀቀ ያለው የተኩስ አቁም እና ተጠባቂው የኢስላማባድ ድርድር በተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል። በቅደም ተከተል ይተነተናሉ።

DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 20.04.2026

ህወሓት ከ2013 ዓ.ም በፊት የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወሰነ፣ ሕገወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው? ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» - አዲስ ስታንዳርድ

የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 17.04.2026

በዓለም ዜና የሚጀምረዉ የአንድ ሰዓቱ ስርጭታችን፤ በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ 1, የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና መልስ የማግኛዉ መንገድ 2, በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችን እንመለስ ጥሪ 3, ሕገ ወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው? 4, በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ የተካሄደ ጉባኤ እንዲሁም 5, ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነት የሚወዳደር የጋራ ዕጩ ያላፀደቀችዉ አፍሪቃ የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።

የዜና መጽሔት፤ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ሐሙስ 16.04.2026

በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ወረዳ በጸበል ቦታ በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከ30 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ማኔጂንግ ኤዲተር ትላንት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ገበታው ከተወሰደ በኋላ ዛሬም የደረሰበት አልታወቀም። ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች እና አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታጣቂዎች ተገድለዋል። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።

የሚያዝያ 7 ቀን 2018 የዜና ፅሔት 15.04.2026

በዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ኢሕአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚመለከት ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀ፤ ደቡብ ወሎ ዞን ፓስፖርት ለማውጣት 161 ሐሰተኛ ሰነዶች፤ የኢራኑ ጦርነት፣ ለሱዳኑ ግጭት የሚሰጠው ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለፀ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የመርከቦች እገዳ በፍኖተ ሆርሙዝ ለኢራን ምን አመጣ? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ፣

የሚያዚያ 6 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት 14.04.2026

ዜናውን ተከትሎ በሚቀርበው የዛሬ የዜና መፅሔታችን ፤መራጮች ምን ይላሉ?፣በነጻ የንግድ ቀጠና ባለሃብቶችን ከገቢ ግብር ነጻ የሚያደርገው መመሪያ፣በአማራ ክል ተፈናቃዮች የምግብ ዕርዳታ ከተሰጠን 2 ወራት አለፉ ማለታቸውን ፣እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስሱ ጥንቅሮች አካቷል። ሳምንታዊዎቹ ጤና እና አካባቢ እና አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅቶችም ተካተዋል።

የመጋቢት 5 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 13.04.2026

ዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና፤2, በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ነዋሪዎችን እየፈተነ ያለዉ የኤሌክትሪክ መቋረጥ፤ በተለያዩ የዓማር ክልል ከተሞች የንግድ ማህበረሰቡን የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ባለፈዉ ሰሞን በባሌ ሮቤ መናኸሪያ ላይ በወጣት ወንጀለኞች ተደበደቡት አባት የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።

DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 10.04.2026

የነዳጅ እጥረት፣ የመጓጓዣ ዋጋ እና የጤፍ አቅርቦት፤ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር፤ ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ሕብረት የሠላምና ፀጥታ ምክር ቤት የአንድ ወር ሊቀመንበር ሆነች፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ተኩስ አቁም ያሳደረዉ ተስፋ በኢትዮጵያ፤ የአሜሪካና ኢራን ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት

የሚያዝያ 1 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 09.04.2026
የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ ም ዜና መጽሔት 08.04.2026

የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣የትግራይ ክልል ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የጄኔራል ታደሰ ወረደ ዘመነ-ሥልጣን ለተጨማሪ አንድ ዓመት መራዘሙንና ያስከተለዉን ቅሬታ የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞንን የመታዉ ድርቅ ከሁለት ወረዳ ብቻ ከ4000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተሰምቷል።የአፍሪቃ ሕብረትና የኢትዮጵያ መሪዎች በአንጋፋዋ ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ሞት የተሰማቸዉን ሐዘን እየገለፁ ነዉ። ዜና መፅሔቱ ዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤልና ኢራን ለሁለት ሳምንት ተኩስ ማቆማቸዉን፣ ምክንያቱንና የወደፊቱን ሁኔታ በተመለከተ ከባልደረቦቻችን ጋር የቀጥታ ዉይይት ይሰማበታልም።

የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 07.04.2026

በዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል?፤ በነዳጅ እጥረቱ የተስተጓጎለው ትራንስፖርትና መጪው የበዓል ሸመታ፤ የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል የፍትህ ስርዓት ላይ እንቅፋት እየሆነ ነው መባሉ ይሰኛሉ ። እንዲሁም የዪናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የሰጡት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ጫፍ መድረሱ እና ያጠላው ሥጋት የሚዳስስ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል

የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 06.04.2026

በዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ማራዘሙ በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ የፈጥረው ተፅዕኖ የለም መባሉ በአረብ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እሳት እየለበለባቸው የሚያገኙትን ገንዘብ እንዲያጠራቅሙላቸው ወደ አገር ቤት ሲልኩ መከዳታቸው የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር በር ለመክፈት ስምምነት ላይ እንድትደርስ የሰጡት ቀነ ገደብ ነገ ያልቃል በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አጭር ቆይታ ይኖረናል።

የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዜና መፅሄት 03.04.2026

በዛሬው የዜና መፅሔታችን በጅቡቲ መኪኖቻቸው ያለስራ የቆሙባቸው የነዳጅ ጫኝ ቦቴ አሽከርካሪዎች ምሬት፤የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ፤ኢትዮጵያ አሳካሁ ያለችው የ13 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት አንድምታ፤እንዲሁም አዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።

የመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 02.04.2026

የስደተኞች ሰቆቃ በየመን እና በሳውዲ አረቢያ ድንበር ላይ በትግራይ ክልል እና ውዝግብ ባለባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ ምን ይመስላል? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን መምራት የጀመሩበት ስምንተኛ ዓመት የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ ማዳከም ጀምሯል ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኢራን ጦርነት ለህዝባቸው ያስተላለፉት መልዕክት

የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.04.2026

በዜና መጽሔት ዝግጅታችን አዲስ አበባ ውስጥ የተሰየመው የትግራይ ምክክር እና አንድምታው፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዲሱ “የህገወጥ ቤቶች ግንባታ” ደንብ እና ያስተናገደው አስተያየት ፤ገቢና ወጪ ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሥራቸው በምን ኹኔታ ላይ ይገኛል? የሚለውን ጨምሮ ፤ በነዳጅ እጥረት ቀውስ በሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖን የተመለከቱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው ።

Listen to the ዜና መጽሔት podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.