DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
DW Amharic የመጋቢት 22 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 31.03.2026 22:20
የኢራኑ ጦርነት የኢትዮ-ኤርትራን ውጥረት ያባብሰዋል ብለው እንደማያምኑ ተንታኞች ተናገሩ፤ እስካሁን የተቋረጠ የአገር ውስጥም ሆነ ዓለማቀፍ በረራ አለመኖሩንም ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡ የቅድስት ክፍሌ መታሰቢያ የመንገድ ደሕንነት ትምሕርት፤ የነዳጅ ዕጥረት እያስከተለው ያለው ጫና፤ የኢራን ጦርነት በአውሮፓ ሐገራት ያሳደረው ጫና
የመጋቢት 21 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 30.03.2026 19:58
የዜና መጽሔት አራት ርዕሰ ጉዳዮች ይተነተናሉ እነርሱም በኦሮሚያ ክልል የተኩስ ድምጽ እንዲቆም የቀረበው ጥሪ ፣ በደቡብ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የወልቂጤ ቅርንጫፍ FM 89.2 ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ ፣ በትግራይ ክልል ሀገራዊ ኹነቶችን ለማከናወን ያለው ወቅታዊ ኹኔታ እንዲሁም የሁቲዎች ጥቃትና ማስጠንቀቂያ በአፍሪካ ቀንድ ስጋት እንዲጨምር ማድረጉ የሚሉት ናቸው። ማኅደረ ዜና ለዛሬ ትኩረቱን የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በኢትዮጵያ ያስከተለውን ችግር ላይ አድርጓል።
የመጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 27.03.2026 18:30
በዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የውይይት ኮሚሽን የትግራይ ክልልልን አጀንዳ ልየታ በአዲስ አበባ፤ የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ እያስከተለ ያለውን ችግር የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ከ300 በላይ የፖሊስ መኮንኖችን ከስራ ማባረሩን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪቃ የባሪያ ንግድ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ መቀበላቸው የሚቃኙ አራት ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የረቡዕ መጋቢት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 25.03.2026 18:54
የዓለም ዜናን ተከትሎ፤ "ከምርጭ ራሳችንን እስከማግለል ርምጃ ልንወስድ እንችላለን" ሲል የ4 ፓርቲዎች ጥንር የሆነው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ መግለፁን፤ስለምርጫው የታጣቂዎች ማስጠንቀቂያ እና የፓርቲዎች አቋም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዛሬው ዕለት አዲስ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ልዩ መልዕክተኛ መሾሙን እንዲሁም የአሜሪካ እና የኢራን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴን የሚቃኙ አራት ዘገባዎች ይኖሩናል።
የመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት 24.03.2026 18:26
ዜና መጽሔት ጥንቅራችን አራት ዘገባዎች ይኖሩናል። እነሱም፤* በሱዳኗ ኩርሙክ የተከሰተው ግጭት የድንበር ነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ስጋት፤* የሶማሌ ክልል የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ስም በሀሰተኛ መረጃ ለማጠልሸት እየተካሄደ ነው ያለውን ድርጊት መኮነኑ፤* የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዮሐንስ ብርሃነ በአስቸኳይ እንዲፈታ ስለ መጠየቁ እና* በሰሜን ሸዋ ዞን ሰላሌ፤ በጠለፋ ምክንያት ለአስከፊ ጉዳት የተዳረገች የ7ኛ ክፍል ተማሪ ጉዳይ ናቸው።
የመጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 23.03.2026 19:21
-በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ለመሻገር ሙከራ ማድረጋቸው የተገለፀ 48 ኤርትራውያንን ማሰሩን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታውቋል። -ጂግጂጋ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ40 በላይ ሱቆች መቃጠላቸውን የሶማሌ ክልል አስታወቀ እነዚህና -በዋግ ህምራ ዞን በእደ ጥበብ ባለሙያዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲሁም አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ አሰጣጥ ሕግ
የመጋቢት 11 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 20.03.2026 21:14
የዛሬው የዜና መፅሔታችን በዒድ በዓል ላይ ያተኮረ ነው። በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣በድሬዳዋ፣በሐዋሳ እና በደሴ የነበረው የበዓሉ ድባብ ያስቃኘናል።
የሐሙስ መጋቢት 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 19.03.2026 25:15
የዜና መጽሔት -በኢትዮጵያ ወቅታዊ ዲፕሎማሲ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች ፣ -በትግራይ ክልል "አፈና እና የዘፈቀደ እሥራት" መኖሩን አንድ የሲቪክ ድርጅት መግለጹ አማርኛ ለምን ከአፍሪካ ህብረት የሥራ ቋንቋዎች አንዱ ሳይሆን ለምን ቀረ? -የነዳጅ ዋጋ ንረት በአሶሳ ፣ እንዲሁም የተወደደው የዒድ ገበያ በደሴ በተሰኙ ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ተካተዋል። ሳምንታዊው የባህል መድረክ በኢትዮጵያ የብርሌ ታሪክ ላይ ያተኩራል ።
የመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 18.03.2026 18:07
በዜና መጽሔት በአማራ ክልል የነዳጅ ዘይት እጥረት የፈጠረው የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎል፤ ባለፉት ሰባት ዐመታት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እና ተፅዕኖው፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዶ/ር ሲሳይ አውግቸው ተፈቅዶ የነበረውን የዋስትና መብት መሻሩ ፤ እና የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ቢያንስ በአንድ በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን እንቃኛን
የመጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 17.03.2026 18:18
የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የተፈፀሙ በደሎችና የፍትሕ ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማሕበር በካናዳ፣ እና የአፍሪቃ ሐገራት አቋም በመካከለኛዉ ምሥራቅ ጦርነት
የመጋቢት 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 16.03.2026 20:44
በዜና መጽሔት -በኢትዮጵያ የነዳጅ አጠቃቀም በቁጠባ እንዲሆን ማሳሰቢያ መሰጠቱ ፣ - በሰሜን ወሎ ዞን ሙጃ ወረዳ በውጊያ ምክንያት መንገዶች መዘጋታቸው በነዋሪዎች ላይ ያስከተለው ማኅበራዊ ቀውስ - የሆርሙዝን ወሽመጥ ለማስጠበቅ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት የእርዳታ ጥሪና የአውሮጳ ኅብረት እንዲሁም የጀርመን የምርጫ ስርዓትና ጠቃሚ ልምዶች በተሰኙት ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.03.2026 26:48
በዜና መጽኄት የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ፡ በቴክኖሎጂ እድገት እና በዜጎች መብት መካከል ያለው ሚዛን፤ የጦርነት ስጋት ያዣበበባት ትግራይ ክልል እና የህወሓት አስገዳጅ የገንዘብ ማሰባሰብያ ፤ በአዲስ አበባ እና ደሴ መንገድ የአሽከርካሪዎችና ተጓዦች የደኅንነት ሥጋት ማየሉ፤ ነጻ ሚዲያ የሚኖረው ሚና ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቁ፤ እንዲሁም የጀርመን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አተገባበር እና ልዩ መገለጫው ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
የመጋቢት 2 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 11.03.2026 19:24
የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መጽሔት በኢትዮጵያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን አሰመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በጋሞ ዞን በናዳና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 64 መድረሱ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው እና የኑሮው ጫና እንዲሁም በፖላንዱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፕዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቶች ቡድን ያጋጠመው የቪዛ ችግርን ይዳስሳል።
የየካቲት 30 ቀን 2018 ዓም የዜና መጽሔት 09.03.2026 22:32
--በጦርነት ግጭት ዉስጥ የሴቶች ከፍተኛ ተጋላጭነት እልባት ያሻዋል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ)መግለጫ ማዉጣቱ --የአፍሪካ ሕብረት የሴቶችን ውክልና የበለጠ እንዲያሳድግ መጠየቁ --የሲቪል ነዋሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ የጠየቀዉ ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ --በደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን አምራቾች በሰላም እጦት ምክንያት ስጋት ውስጥ ነን ማለታቸዉ እንዲሁም -መዲና በርሊን የሚገኘዉ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ እና የጀርመንን ግንኙነት የተመለከተዉ ስብሰባ
የየካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 06.03.2026 19:22
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ -ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ፣ሴቶችን በጅምላ የመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መክሰሱ ፣ -ነገ ስለሚጀመረው የመራጮች ምዝገባ የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች፣ -በኢትዮጵያ በኬንያና በሶማሊያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለድርቅ መጋለጣቸው -ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" እንደምታዘጋጅ መገለጹ
የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 05.03.2026 27:02
የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን 41 ሐገሮች በኢትዮጵያ ያለውን የመናገር ነጻነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሞሽን በአርሲ ስለተገደሉ ዜጎች ያወጣውን መግለጫ፤ ከራያ አላማጣ፣ ኮረምና ኦፍላ ዛታ የተፈናቀሉ ወገኖች የዕርዳታ ጥሪ፤ በምዕራባዊ የሐገሪቱ ክፍል ከመደበኛ በላይ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው የነዳጅ ዕጥረት እንዲሁም የድሬደዋ ስታድየም - የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጋር የሚያደርገውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲያስተናግድ መወሰኑ" የተሰኙትን ጉዳዮች ያስቃኘናል
የየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 04.03.2026 30:25
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ያገረሸው ጸጥታ ችግር፤ በአማራ ክልል የሚካሄደው ውጊያ ወጣቶች ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ፤ ምርጫ ቦርድ በ5 የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ለቀረበበት ክስ ለፍርድ ቤት ምላሽ ማቅረቡ፤ የሱዳን መከላከያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ክስ አንድምታ
የማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት 03.03.2026 13:09
በዛሬው የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ ለታቀደዉ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማሕበራት ድርጅቶችን ዝግጅቶች የሚቃኙ ሁለት ዘገባዎችን ፣ የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት ዝክር በፓሪስ የሚመለከት ዘገባ የእስራኤልና የአሜሪካ ድብደባና የኢራን አፀፋን የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅም ተካቷል።
የየካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 02.03.2026 20:55
130ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በድሉ መታሰቢያ ማዕከል ተከብሯል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን የጅምላ እልቂት አውግዛለች፣ አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራንን አጸፋንና አውሮጳን እንዲሁም ጦርነቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በቀጥታ ሊጎዳ ይችላሉ መባሉ
የየካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 27.02.2026 25:12
በዛሬው የዜና መጽሔት "በንጹሓን ላይ የሚሰነዘር" ያለው ጥቃት "እያደር ከብዷል" ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መግለጫ ማዉጣቱ፣ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በተለይም በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተከሰተ ግጭት ፣ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በኦሮምያ ክልል ስለመጭዉ ምርጫ ምን አስተያየት አላቸዉ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። አሜሪካ በኢራን ላይ ልትፈጸም የምትችለው ጥቃት የምሽቱ ዜና መጽሔት የያዘዉ ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።
የየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት 26.02.2026 24:41
በዛሬው መጽሔታችን አምስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" መታዘዙ፤ ክራይሲስ ግሩፕ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውዝግብ ያቀረበው ምክረ-ሀሳብ፤ 2025 በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ "ሰፊ እሥራቶች፣ አፈናዎች እና ትንኮሳዎች የተጋረጡበት" ነበር መባሉl ፤ «የምግብ ድጋፍ ተነፈግን» ያሉ ተፈናቃዮች ለከፋ ስቃይ ተዳርገናል ማለታቸው ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።
የየካቲት 18 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 25.02.2026 22:03
-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንት ፍቃዱን የሰረዘበት አዲስ ስታንዳርድ ሥራዉን አለማቋረጡን አስታወቀ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት ባሰራጨዉ ደብዳቤ የአዲስ ስታንዳርድ የምሥክር ወረቀት መሰረዙን አሰታዉቆ ነበር።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ያደረጉት ዓመታዊ የመርሕ ንግግር በአብዛኛዉ ሐሰትን ከዕዉነት የቀየጠ መሆኑን አጥኚዎችና ተንታኞች አስታወቁ።ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ዛቻም ከቴሕራን ጠንካራ አፀፋ ገጥሞታል። --በግሪጎሪያኑ አምና 2025፣ 129 ጋዜጠኞች መገደላቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ CPJ አስታወቁ።አብዛኞቹን ጋዜጠኞች የገደለችዉ እስራኤል ናት።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.