DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: www.dw.com
¿Dónde escuchar?
Podcasts en la app Replaio Radio Muy prontoLos podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts
Episodios
የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 27.10.2026 19:32
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የተፈጸመው ግድያ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ጉዳዩ የሰጡትን አስተያየት፤ በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዕገታዎች የገጠማቸውን ሥጋት የተመለከቱ ዘገባዎች ዜና መጽሔት የያዛቸዉ ናቸዉ።
News magazine 261026 - MP3-Stereo 26.10.2026 21:23
በዜና መጽሔት፤ የቀጠለው የአርሲ- ሺርካው የጅምላ ግድያ፣የሞያሌ ግጭትና ሰብዓዊ ቀውሱ፣ የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ በሞያሌ ግጭት የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቁ ፣ በአፋርና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ሰዎች ተገደሉ፣ እንዲሁም - ስለ ትግራይ ክልል ኹኔታ መንግሥትና ሌሎች የሚሰጡት መረጃዎች የተሰኙ ዘገቦች ይደመጡበታል
የስራ ዘመኑን ያጠናቀቀው አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና ውጤቱ 24.10.2026 4:09
ከአራት አመት በላይ በስራ ላይ የቆየው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ በህግ የተሰጠውን የስራ ዘመኑን አጠናቋል፡፡የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 8 ዋና ዋና አገራዊ አጀንዳዎች እና የውሳኔ ምክረ ሐሳቦችንም አስቀድሞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት አስረክቧል፡፡ ለመሆኑ የኮሚሽኑ ስራና ውጤቱ እንዴት ይገመገማል?
የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች 24.10.2026 4:14
የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአፍሪካ የደህንነት ጉባኤ የኾነው ጣና ፎረም ባዘጋጀው መድረክ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ኢትዮጵያ የደህንነት ሰጋቶችን የማስወገድና የንግድ መርከቦቿን የመጠበቅ አስፈላጊ ኃላፊነት አለባት ብለዋል።
የጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 22.10.2026 31:33
በአፍሪካ ቀንድ "እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋት መነሻ ኢትዮጵያን ናት"ስትል - ኤርትራ መክሰስዋ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ቀዉስና ሰብዓዊ አቅርቦቱ በአማራና በትግራይ ክልሎች ያለዉ ወቅታዊ ሁኔታ፤ ሞያሌ ከተማ በሰንደቅ ዓላማ ውዝግብ ሕይወት መጥፋቱ፤ በጋምቤላ ግጭት በመሳተፍ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ፤ የአሜሪካ አጋማሽ ምርጫና አንደምታዉ
የጥቅምት 11 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 21.10.2026 19:56
የዜና መጽሔት፤ በኦሮሚያ አርሲ ዞን ሲቪሎች ላይ ጥቃት እና ግድያ መቀጠሉ ፤ በትግራይ ለተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የተመድ መግለፁ፤ የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታ በፓለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዕይታና በቀይ ባሕር ያለው የፀጥታ ችግር መቀጠል የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት የመነሳት እድል ይቀንሳል? ሲል የሚጠይቅ ዘገባዎችን አካቷል።
የጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.10.2026 19:27
የዜና መፅሔት ጥንቅር፤የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ኤርትራን መዉቀስና ማስጠንቀቃቸዉን የሚዳስሰዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፤ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ተሥፋና ሥጋት፣ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ፊንጫኣ ሥኳር ፋብሪካ ላይ የከፈቱት ጥቃትና ያደረሱት ጥፋት፣የኢቦላ ተሕዋሲ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የሚደረገዉ ጥንቃቄን አካቷል
DW Amharic የጥቅምት 09 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 19.10.2026 15:54
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስተያየትና ትብብር ለሕልውና የሰጠው ምላሽ፤ ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ የፀጥታ ኹኔታ የፓርቲዎች እና የሲቪክ ድርጅት አስተያየት፤ የህብረት ለምርጫ የ7ኛው ምርጫ ትዝብት እና ዘገባ
የጥቅምት 6 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 16.10.2026 31:30
-በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር መቋቋሙእና የህዝቡ አስተያት-ቆቦ የሚገኙ የራያ አካባቢ ተፈናቃዮች ተሳታፊነታቸውን ያገለለ የምርጫ ሂደት እንዲቆም መጠየቃቸዉ -በኦሮሚያ ክልል የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና የፀጥታው ችግር-የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" አሳሳቢ ጉዳዮች ተለይተዋል ያለዉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
DW Amharic የጥቅምት 05 ቀን 2019 ዜና መፅሔት 15.10.2026 25:50
በዶቸ ቬለ የዜና መጽሔት አሜሪካን ጨምሮ ብዙዎች እንዲናገሩ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት፤ በትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም መጠየቁ፤በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት፤ በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ፤ በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ የሚል ርዕስ የተሰጣቸው ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የጥቅምት 4 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 14.10.2026 25:57
የዕለቱ ዜና መጽሔታችን አምስት ጉዳዮችን ያስደምጣል። የቀጠለው የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ውጊያ ፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ መድረሳቸው ፣ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ማለቱ፣
የዜና፤ መጽሔት፤ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ማክሰኞ 13.10.2026 21:35
በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለው ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊ እና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ አስቀድሞ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ አገራት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አሳሰበ፡፡
የጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.10.2026 19:07
የዜና መጽሔት፤ በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት እና የኑሮ ዉድነት በትግራይ ክልል የፌዴራል አመራሮች አቀባበል እና አሁንም ያሉ ስጋቶች ስለ ትግራይ ክልል ቀጣይ ኹኔታ በባለሥልጣናት የተሰጡ አስተያየቶችን የሚያስደምጡ ዘገባዎችን አካቷል
የዜና መጽሔት፤ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ 09.10.2026 41:52
በዜና መጽሔት፤ የትግራይ ክልል ከተሞች ፀጥታ፤ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች ፤ሰሜን ወሎ በአፋር አማራ ድንበር ግጭት ተፈናቃዮች መጎዳታቸው፤ ያገረሸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መወነጃጀልንም የሚቃኝ የባልደረቦች ቃለምልልስ ይኖራል
የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት 08.10.2026 37:35
የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት
የመስከረም 27 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 07.10.2026 31:55
በነገሌ ቦረና በተከሰተው ተኩስ የሰው ሕይወት ማለፉ፤በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት የምግብ ድጋፍ አልተደረገልንም ማለታቸውን፤ እንዲሁም የየመን ጦርነት የሚሉ ርዕሶችን ያስተነትናል።
የመስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 06.10.2026 33:04
የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ለምክር ቤቶች ያደረጉት የመርሕ ንግግር፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት፣ የሐገሪቱ የሰላም እጦትና የመሪዎችዋን ቃል በተመለከተ የሕዝብ አስተያዮቶች፤ መካነ-ሰላም ደቡብ ወሎ ዞን በመንግስት ጦርና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ዉጊያ መደረጉ፤ ስለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተመድ፣ አሜሪካና የአዉሮጳ ሕብረት መልዕክቶች
የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 05.10.2026 20:26
የዜና መፅሄት ዝግጅታችን፤የቀጠለው የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እና አዲስ የመንግስት ምስረታን፣ የፌደራል መንግስት ሀይሎች የተቆጣጠሩት የመቀሌ ከተማ የአመራር ለውጡን እንዴት እያስተናገደች ነው?፣በአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ የነበሩ የጻግብጅ እና አበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ መባሉን እንዲሁም የኤርትራ የሚሉ ዘገባዎች ተካቷል።
የመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄት 02.10.2026 42:32
በዛሬው የዜና መፅሄት አብዛኛ ጊዜን የሚሸፍነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራና ግብፅ ጋር በገጠመችዉ ጠብ፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የማቋረጥና ዲፕሎማቶችን የማባረርና አፀፋዉን የሚቃኙ ዘገባዎች ናቸዉ።አዲስ አበባ ፍንዳታ ከተሰማ ወዲሕ የሚደረገዉ የፀጥታ ቁጥጥርና የኢሬቻ በአል ዝግጅትን የሚቃኝ ዘገባና ቃለ ምልልስም ተካቷል።
የመስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.10.2026 42:45
ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ በሦስት ቦታዎች ፍንዳታዎች እንደነበሩ መነገሩ፤ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ ወደ አዲስ አበባ ቀረበ ወይ የሚል ሥጋት አጭሯል፤እስራኤል ውጊያ እየተካሔደ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች ዜጎቿን ማስወጣቷ ተሰምቷል፤ በጋዞ ዞን ዘጠኝ የፖሊስ አባላት ስለተገደሉበት ጥቃት የተዘጋጀ ዘገባም አለ።
የመስከረም 20 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 30.09.2026 21:50
የዜና መጽሔት፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአካባቢውን ሃገራት እንዳያዳርስ ማስጋቱን፤ የኤርትራ ሠራዊት አፋር ውስጥ ገብቷል ስለሚለው የተደረገ ቃለ ምልልስ፣ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላገረሸው ጦርነት ምን ያህል መረጃ እየሰጡ ነው? ላሊበላ ያገረሸው ጦርነት ያስከተለባትን ስጋት የሚመለከቱ ዘገባዎችንም አካቷል፤
የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ዜና መጽሔት 29.09.2026 19:38
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በተፈናቃዮችና በየአካባቢዉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ያደረሰዉን ጉዳትና መከራን በሁለት ዘገቦች ይቃኛል። የኦሮሚያ ክልል 21 የአስተዳደር ዞኖችን ወደ 6 ዞኖች ማጠፉን የሚቃኘዉ ዘገባ አሠልሶ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 81ኛ ጉባኤና የድርጅቱ ፋይዳ ቢሲስነት በሚተነትነዉ ያሳርጋል።
የመስከረም 18 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄት 28.09.2026 19:55
በዛሬው የዜና መፅሄት በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በተቀሰቀሰው ውጊያ ላይ የጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። የኦሮሚያ ምክር ቤት ዛሬ አዲስ ክልላዊ መንግሥት መሥርቷል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሬዝደንትነት ሲቀጥሉ ስድስት ምክትሎች ተሾመውላቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቅ የተመለከቱዘገባዎችም ተካተዋል
News Magazine 250926 - MP3-Stereo 25.09.2026 36:33
ዜና መጽሔት ከሚያስቃኘን መካከል - የባልስልጣናት እስርና ዕገዳ በትግራይ - በትግራይ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቋረጡ - ጦርነት ኤርትራንና ሱዳንን ያሳትፍ ይሆን? - ጦርነቱ የሚያስከትለዉ ሰብዓዊ ቀዉስ ምን ሊሆን ይችላል? - ኤርትራዊ ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሀቅ 25 ዓመታት በኤርትራ እስር ቤት የሚሉት ይገኙበታል።
የመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 24.09.2026 28:05
የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላይ የሚያተኩሩ ዘገባዎች ተካተዋል። -የአፋር ክልል «አሸባሪ» ባለው የህወሓት ጦር ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ማለቱ - የፀጥታው መናጋት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች -ጦርነቱ ሺዎችን ማፈናቀሉ እና የቀረበው የምግብ ድጋፍ ጥያቄ -የአውሮጳ ህብረትና ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ጥሪን ይመለከታል
Podcasts similares
Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos