DW
የዓለም ዜና
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: www.dw.com
¿Dónde escuchar?
Podcasts en la app Replaio Radio Muy prontoLos podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts
Episodios
የኅዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 12.11.2026 11:32
የቡድን 7 የው/ጉ/ሚኒስትሮች በኢትዮ-ኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እንዳሳሰባቸዉ አመለከቱ። ከሞያሌ ተፈናቅለው ወደ ኬንያ የተሰደዱ እናቶች ከጥቃት ቢሸሹም ለልጆቻቸው ምግብና መጠለያ ለማግኘት ተቸግረዋል። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የአውሮፓ ሃገራት ዩክሬን ውስጥ ሰላም ወይም ጦርነት ይፈልጉ እንደሁ እንዲወስኑ ጠየቁ።
የሕዳር 2 ቀን 2019 የዓለም ዜና 11.11.2026 10:45
-በአማራ ክልል ዋግሕምራ ዞን ሰሐላ ወረዳን የመታዉ ድርቅ ከወባ ወረርሺኝ ጋር ተዳምሮ ሰዎች መሞት፣ መራባቸዉን ነዋሪዎች አስታወቁ።-የዓየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትለዉን ጉዳት ለመቀነስ የበለፀጉት ሐገራት ሁነኛ ርምጃ እንዲወስዱ የሚደረገዉ ጥሪና ጥያቄ እንደቀጠለ ነዉ።
የዓለም ዜና፤ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓም ማክሰኞ 10.11.2026 12:38
የሩስያን እና የዩክሬይንን ጦርነት ለማስቆም ፤ አቡ ዳቢ ላይ ዛሬ በሩሲያ፣ በዩክሬን እና በአሜሪካ መካከል የሰላም ድርድር እየተካሄደ ነዉ።-የቀድሞዉ የፎክስ ኒዉስ አቅራቢ የዛሬዉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር፤ በኢራን ላይ ጦርነት እንዲጀመር ግፊት በማድረግ ጨምሮ ብዙ ክስ ቀረበባቸዉ።
በርሊን ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነር የመጀመሪያዋ ሴት የጀርመን እጩ ፕሬዝዳንት ሆነው በሜርስ ተመረጡ 09.11.2026 11:32
ሮቤ-ዲዳዓ ወረዳ እንደቶ ከተማ በታጣቂዎች የተገደሉትች ቁጥር ወደ 40 ከፍ አለ። ባለፈው ቅዳሜ በግሪክዋ ደሴት ክሬታ ደቡባዊ ክፍል፣ ስደተኞችን ጭነው የነበሩ 4 ጀልባዎች ባጋጠማቸው አደጋ ቢያንስ 20 ስደተኞች ሞቱ። የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየርን ለመተካት፣ ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነርን በእጩነት ቀረቡ።
DW Amharic የጥቅምት 29 ቀን 2019 የዓለም ዜና 08.11.2026 7:02
በሴኔጋል አንዲት ትንሽ ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ የሶማሊያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዲሱ ዋና ዳኛ ኢብራሒም ሱሌይማን ቃለ-መሐላ ፈጸሙ። የፖላንድ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በካራኮቫ ስድስት ሰዎች የተገደሉበትን የጅምላ ተኩስ የሽብር ጥቃት በማለት በየነ። የእስራኤል ፕሬዝደንት ጋዲ አይዘንኮት መንግሥት እንዲመሰርቱ ኃላፊነት ሰጡ።
የጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 07.11.2026 11:06
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤በትግራይ ከተሞች እየተስተዋለ ያለውን የፀጥታ ችግር፤ በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ አካባቢ በምትገኝ መንደር በተፈጸመ የአየር ጥቃት 25 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን
የጥቅምት 27 ቀን 2019 የዓለም ዜና 06.11.2026 10:47
-የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ የሠላም ኃይላት ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ ከህወሓት ጋር በገጠሙት ጦርነት የማረኳቸዉ ጦር መሳሪያዎች ዛሬ ለዉጪ ዲፕሎማቶች ለዕይታ ቀረቡ።-ኬንያ ዉስጥ የምፅዓት ቀን ኑፋቄ ሰባኪ የተባለ ፓስተር ሰዎችን እያስራቡ በመግደል ወንጀል 200 ዓመታት እስራት ተፈረደበት።
የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ሐሙስ 05.11.2026 9:55
የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት የገጠሙት መወቃቀስና መወጋገዝ ወደ ፍጥጫና ዲፕሎማሲያዊ መበቃቃር እየናረ ነዉ። ሁለቱ ሃገራት አንዱ በሌላዉ ላይ ቆንስላ ዘግተዋል።-ኦሮሚያ ክልል ኪረሙ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የሰዉ ህይወት ጠፋ፤ንብረትም ወደመ።--በአፍሪቃ ቀንድ የናረው ውጥረት «በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይረግባል» የሚል ተስፋ እንዳላች ቻይና አስታወቀች።
የዓለም ዜና፦ የዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2019 ዓ.ም 04.11.2026 10:04
ኮንሶ፥ ታጣቂዎች አራት አርሶ አደሮችን በአሰቃቂ ኹኔታ ገደሉ አንድ አገሩ፤ ዩኒሴፍ፤ ዴሞክራቶች ታሪካዊ በኾነ ድል ሁለቱንም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ተቆጣጠሩ፤ ቴሕራን፥ የፕሬዚደንት ትራምፕ እና ፓርቲኢቸው ሽንፈት ኢራኖችን በደስታ አደባባይ አትምሟል፤ ዓለም፥ ስለአሜሪካ ምርጫ ውጤት ዓለም አቀፍ አስተያየቶች
የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 03.11.2026 13:00
-በኦሮሚያ ክልል አርሲ ከ60 በላይ የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን ኢሰመኮ አስታወቀ።-በሰሜን ኢትዮጵያ ልጆችን እና የተወለደ ሕፃን የገደሉ ጥቃቶች የክልሉን ደካማ የጤና ስርዓት ወደ ውድቀት እያቀረቡት ነዉ ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አመለከተ።-በዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ለ435ቱ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ድምፅ እየሰጡ ነዉ።
የጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 02.11.2026 10:23
በዛሬው የዓለም ዜና፤ሪፖርተር ጋዜጣ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን፣በአርሲው ግድያ የተጠረጠሩ 73 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፣የንጽሃን ግድያ እንዲቆም ጎጎት ለጉራጌ ፍትህ እና አንድነት ፓርቲ መጠየቁን፣በሱዳን የሀይልማመንጫዎች ለደረሰው ጥቃት ኢትዮጵያ መወንጄሏን፣ ዩጋንዳ በሶማሊያ ያስማራችውን ጦር ማስወጣቷን እና ሌሎችን አካቷል።
የጥቅምት 22 ቀን 2019 የዓለም ዜና 01.11.2026 6:49
የኢትዮጵያ መንግሥት በአርሲ ዞን የተፈጸመውን ግድያ በመመርመር ተጠያቂዎቹን ለሕግ እንዲያቀርብ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች። የጀርመን ፖለቲከኞች በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የኑሮ ውድነትን ለመቃወም በወጣቶች የተደረጉ ሰልፎች ወደ ኹከት እና ዘረፋ መቀየራቸውን አወገዙ።
የቅዳሜ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 31.10.2026 10:51
የዛሬው የዓለም ዜና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን፣በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ፖለቲካዊ ተልዕኮ ዛሬ ማብቃቱን፤በአፍሪካ ኢኮኖሚ እያደገ ቢሆንም የፖለቲካ ነፃነት መቀነሱን፣ኢራን ለአዳዲስ ጥቃቶች መልከዓምድራዊ ገደብ የሌለው ወታደራዊ ምላሽ እሰጣለሁ ማለቷን እና ሌሎችን አካቷል።
የአርሲ-ሺርካ ዋሪዎቹ እና የጥቃቱ ሰለባዎቹ ዘመዶች ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የአካባቢው ባለስልጣናት የተጎጂዎችን ዘመዶች "ምንም ምክንያት ሳይኖር" በማሰራቸው በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ እየተሰማ ነው። 30.10.2026 12:25
አርዕስተ ዜና -በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ዛሬ ተፈጽሟል በተባለ የድሮን ጥቃት11 ሰዎች መገደላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ AFP ዘገበ። - አርሲ-ሺርካ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ ከተፈጸመ ወዲህ፣ ነዋሪዎች በአስተዳዳሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ - ደቡብ ወሎ ዞን፣ የቱርክ ካምፕ መጠለያ ላይ በደረሰ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ከፍ አለ።
የጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 29.10.2026 10:54
በደቡብ ወሎ ዞን፣ ተወለደሬ ወረዳ በሚገኘው የቱርክ ካምፕ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ላይ በደረሰ የድሮን እና የመድፍ ጥቃት 14 ሰላማዊ ሰዎች ሞተው 22 መቁሰላቸውን የመጠለያው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ሳውዲ ዓረቢያ በየመን ታይዝ በተባለች መንደር በፈጸመችው ጥቃት 12 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የየመን ሑቲ አማፅያን አስታወቁ።
የጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 28.10.2026 10:46
የጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የአርሲው ተደጋጋሚ ግድያ እንዲቆም ተጠየቀ ። ከሞያሌ ወደ ኬንያ የሸሹት ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ የየመን ሁቲዎች የአደን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ዛሬ ጥቃት መፈጸማቸውን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና የሰጠው የመን መንግስት ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 27.10.2026 12:33
በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 60 የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ምዕመናን መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዛሬ ዘገበ።-በእስራኤል እየተካሄደ ባለዉ አጠቃላይ ምርጫ ዜጎች ድምፅ እየሰጡ ነው።-ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሚካሄድባት ደቡባዊ ዩክሬን ኦሌሽኪ ከተማ የተኩስ አቁም ስምምነት መጀመራቸዉ ተሰማ።
Nachrichten 261026 - MP3-Stereo 26.10.2026 11:25
አርሲ-ሺርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ ባለፈው ቅዳሜ በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። በሞያሌ ከተማ ዛሬ ተኩሱ ረገብ ማለቱን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። የግብፅ ፓርላማ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ሳዑዲ አረቢያ ከሁቲ አማፂያን ጥቃት ራሷን እንድትከላከል ወታደራዊ ድጋፍ እንዲሰጡ አጸደቀ ።
የጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 25.10.2026 8:11
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ “በሰሜን ወሎ ማጥቃት የጀመረው” እና እርሳቸው “ሕገ-ወጥ” ያሉት “የህወሓት ቡድን በአሥር ቀናት ውስጥ በሚገባው ልክ ተመትቶ ኤርትራ መንደፈራ ገብቷል” ሲሉ ተናገሩ። በፈረንሳይ በተካሄዱ ነውጥ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፉች በድምሩ ከ 1,300 በላይ ሰልፈኞች ታሰሩ
የጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 24.10.2026 10:46
የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ የህልውናና የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ አስታወቁ። የትግራይ የሰላም ኃይል ቃል አቀባይ የህወሓት ካድሬዎች በየአካባቢያቸው ወደሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረቡ። የፈረንሳይ ፖሊስ 135 ሰልፈኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተነገረ ።
የጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም የዓለም ዜና 23.10.2026 11:01
የጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም የዓለም ዜና
የጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 22.10.2026 10:55
የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም በዓለም አቀፍ ሸምጋዮችና በተመድ እንደ አዲስ ጄኔቭ ላይ የተካሄደው ውይይት ያለውጤት ተጠናቀቀ። አፍሪካ CDC ኮንጎ ውስጥ የተከሰተው የኤቦላ ተሀዋሲ ወደሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመዛመቱ አስቸኳይ ጉባኤ ጠራ። ግብጽ ሳውድ አረቢያ እና የየመን ሁቲ አማጽያን ለውዝግባቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበች።
የጥቅምት 11 ቀን 2019 የዓለም ዜና 21.10.2026 11:15
-የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪዎች ድንበር አቋርጠዉ ኤርትራ ገብተዋል የሚለዉን መግለጫ የኤርትራና የህወሓት ባለሥልጣናት አስተባበሉ።ከኢትዮጵያ የፌደራል ጦር ጋር አብሮ ህወሓትን የሚወጋዉ የትግራይ ኃይል አዛዥ የህወሓት መሪዎች ኤርትራ ገብተዋል ብለዉ ነበር።የአስመራና የህወሓት ባለሥልጣናት ግን መግለጫዉን «አሌ» ብለዉታል።
የጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 20.10.2026 10:54
ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ ኤርትራ ለአማፅያን የምትሰጠውን ድጋፍ ከቀጠለች «ከባድ መዘዝ» ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ። ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ይፈጸማሉ ያላቸው ግድያዎችን፣ አፈናዎችና የግዳጅ ማፈናቀሎችን አወገዘ። ደቡብ ሱዳን ውስጥ በድሮን ጥቃት የተገደሉት ቁጥር 153 ደረሰ።
DW Amharic የጥቅምት 09 ቀን 2019 የዓለም ዜና 19.10.2026 11:44
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት “ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ” ጥቃቶችን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “ሽብርተኝነት” ብለው መፈረጃቸውን ትብብር ለሕልውና ተቃወመ። በሱዳን በገበያ አጠገብ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 80 ሰዎች ተገደሉ። የርዋንዳ መንግሥት ተቺ በተሰደደበት ዩጋንዳ አንገቱ ተቀልቶ አስከሬኑ ቁጥቋጦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።
Podcasts similares
Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos