DW

የዓለም ዜና

News AM ↓ Odcinki: 213

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

Koniecznie odwiedź stronę podcastu i wesprzyj twórcę: www.dw.com

Autor

DW

Kategoria

News

Strona podcastu

www.dw.com

Ostatni odcinek

30 paź 2026

Gdzie słuchać?

Podcasty w aplikacji Replaio Radio Już wkrótce

Podcasty trafią do aplikacji już wkrótce. Zainstaluj teraz i jako pierwszy zobacz nowe podejście do podcastów

Pobierz z Google Play Zainstaluj za darmo Android prawie 10 mln pobrań · ocena 4,8 iOS niedługo

Odcinki

የአርሲ-ሺርካ ዋሪዎቹ እና የጥቃቱ ሰለባዎቹ ዘመዶች ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት የአካባቢው ባለስልጣናት የተጎጂዎችን ዘመዶች "ምንም ምክንያት ሳይኖር" በማሰራቸው በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ እየተሰማ ነው። 30.10.2026

አርዕስተ ዜና -በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ዛሬ ተፈጽሟል በተባለ የድሮን ጥቃት11 ሰዎች መገደላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ AFP ዘገበ። - አርሲ-ሺርካ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ ከተፈጸመ ወዲህ፣ ነዋሪዎች በአስተዳዳሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ - ደቡብ ወሎ ዞን፣ የቱርክ ካምፕ መጠለያ ላይ በደረሰ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ከፍ አለ።

የጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 29.10.2026

በደቡብ ወሎ ዞን፣ ተወለደሬ ወረዳ በሚገኘው የቱርክ ካምፕ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ ላይ በደረሰ የድሮን እና የመድፍ ጥቃት 14 ሰላማዊ ሰዎች ሞተው 22 መቁሰላቸውን የመጠለያው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ሳውዲ ዓረቢያ በየመን ታይዝ በተባለች መንደር በፈጸመችው ጥቃት 12 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የየመን ሑቲ አማፅያን አስታወቁ።

የጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 28.10.2026

የጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የአርሲው ተደጋጋሚ ግድያ እንዲቆም ተጠየቀ ። ከሞያሌ ወደ ኬንያ የሸሹት ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ የየመን ሁቲዎች የአደን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ዛሬ ጥቃት መፈጸማቸውን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና የሰጠው የመን መንግስት ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 27.10.2026

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 60 የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ምዕመናን መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዛሬ ዘገበ።-በእስራኤል እየተካሄደ ባለዉ አጠቃላይ ምርጫ ዜጎች ድምፅ እየሰጡ ነው።-ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሚካሄድባት ደቡባዊ ዩክሬን ኦሌሽኪ ከተማ የተኩስ አቁም ስምምነት መጀመራቸዉ ተሰማ።

Nachrichten 261026 - MP3-Stereo 26.10.2026

አርሲ-ሺርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ ባለፈው ቅዳሜ በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። በሞያሌ ከተማ ዛሬ ተኩሱ ረገብ ማለቱን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። የግብፅ ፓርላማ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ሳዑዲ አረቢያ ከሁቲ አማፂያን ጥቃት ራሷን እንድትከላከል ወታደራዊ ድጋፍ እንዲሰጡ አጸደቀ ።

የጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 25.10.2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ “በሰሜን ወሎ ማጥቃት የጀመረው” እና እርሳቸው “ሕገ-ወጥ” ያሉት “የህወሓት ቡድን በአሥር ቀናት ውስጥ በሚገባው ልክ ተመትቶ ኤርትራ መንደፈራ ገብቷል” ሲሉ ተናገሩ። በፈረንሳይ በተካሄዱ ነውጥ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፉች በድምሩ ከ 1,300 በላይ ሰልፈኞች ታሰሩ

የጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 24.10.2026

የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ የህልውናና የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ አስታወቁ። የትግራይ የሰላም ኃይል ቃል አቀባይ የህወሓት ካድሬዎች በየአካባቢያቸው ወደሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረቡ። የፈረንሳይ ፖሊስ 135 ሰልፈኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተነገረ ።

የጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም የዓለም ዜና 23.10.2026

የጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም የዓለም ዜና

የጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 22.10.2026

የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም በዓለም አቀፍ ሸምጋዮችና በተመድ እንደ አዲስ ጄኔቭ ላይ የተካሄደው ውይይት ያለውጤት ተጠናቀቀ። አፍሪካ CDC ኮንጎ ውስጥ የተከሰተው የኤቦላ ተሀዋሲ ወደሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመዛመቱ አስቸኳይ ጉባኤ ጠራ። ግብጽ ሳውድ አረቢያ እና የየመን ሁቲ አማጽያን ለውዝግባቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበች።

የጥቅምት 11 ቀን 2019 የዓለም ዜና 21.10.2026

-የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪዎች ድንበር አቋርጠዉ ኤርትራ ገብተዋል የሚለዉን መግለጫ የኤርትራና የህወሓት ባለሥልጣናት አስተባበሉ።ከኢትዮጵያ የፌደራል ጦር ጋር አብሮ ህወሓትን የሚወጋዉ የትግራይ ኃይል አዛዥ የህወሓት መሪዎች ኤርትራ ገብተዋል ብለዉ ነበር።የአስመራና የህወሓት ባለሥልጣናት ግን መግለጫዉን «አሌ» ብለዉታል።

የጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 20.10.2026

ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ ኤርትራ ለአማፅያን የምትሰጠውን ድጋፍ ከቀጠለች «ከባድ መዘዝ» ይጠብቃታል ሲሉ አስጠነቀቁ። ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ይፈጸማሉ ያላቸው ግድያዎችን፣ አፈናዎችና የግዳጅ ማፈናቀሎችን አወገዘ። ደቡብ ሱዳን ውስጥ በድሮን ጥቃት የተገደሉት ቁጥር 153 ደረሰ።

DW Amharic የጥቅምት 09 ቀን 2019 የዓለም ዜና 19.10.2026

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት “ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ” ጥቃቶችን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “ሽብርተኝነት” ብለው መፈረጃቸውን ትብብር ለሕልውና ተቃወመ። በሱዳን በገበያ አጠገብ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 80 ሰዎች ተገደሉ። የርዋንዳ መንግሥት ተቺ በተሰደደበት ዩጋንዳ አንገቱ ተቀልቶ አስከሬኑ ቁጥቋጦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።

የጥቅምት 08 ቀን 2019 የዓለም ዜና 18.10.2026

በዛሬው የዓለም ዜና፤ የኤርትራ ወታደሮች አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለቀው ቢወጡም አሁንም በድንበር አካባቢ መኖራቸውን፤ በፈረንሳይ በተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በተፈጸሙ ዘረፋዎችና የእሳት ቃጠሎዎች 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤።በጀርመን የላይፕዚግ አየር ማረፊያ አጥር በመደርመሱ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አካቷል።

የጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 17.10.2026

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ አስጠነቀቀ። የትግራይ የሰላም ኃይል ከፌደራል መከላከያ ሰራዊ ጋር በመሆን «ፅንፈኛ» ባለው የህወሓት ሰራዊ ላይ ባካሄደው የጸረ ማጥቃት እርምጃ የኃይል ሚዛኑን «ሙሉ በሙሉ መዛባቱን» የሰላም ኃይሉ ቃል አቀባይ ገለጹ።

የጥቅምት 6 ቀን 2019 የዓለም ዜና 16.10.2026

-የኢትዮጵያና ኤርትራ ሙሉ ጦርነት እንዳይገጥሙ ማሕበራትና መንግሥታት የሚያደርጉት ግፊትና ጥሪ እንደቀጠለ ነዉ።-የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልልን በጊዚያዊነት የሚያስተዳድር የባለአደራ አስተዳደር መሠረተ።--በየመን ሶስተኛ ትልቅ ከተማ ታዝ የመሸገዉ የሐገሪቱ መንግሥት ጦር ኃይል ባልደረቦች እጃቸዉን እንዲሰጡ አንሳር አላሕ አሳሰበ።

DW Amharic የጥቅምት 05 ቀን 2019 የዓለም ዜና 15.10.2026

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች በድንበር ላይ በምትገኘው የዛላአምበሳ ከተማ አካባቢ ተፋጠው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ። ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው የበረታውን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚገባ አሳስባለች። በጋምቤላ በተፈጸመ ጥቃት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ከከተማው የሸሹ ነዋሪዎች እንዲመለሱ አስተዳደሩ ጥሪ አቀረበ።

የጥቅምት 4 ቀን 2019 የዓለም ዜና 14.10.2026

-የኢትዮጵያ የፌደራል ጦርና የትግራይ የሰላም ኃይል ታጣቂዎች ኤርትራን ሳላምበሳ ጥግ መድረሳቸዉን ነዋሪዎችና ተዋጊዎች አስታወቁ።--አማራ ክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያም እንደቀጠለ ነዉ።-የየመን አንሳርአላሕ የሳዑዲ አረቢያን የነዳጅ ተቋማትና አዉሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደባቸዉን እንደሚቀጥሉ አሰታወቁ።

የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ማክሰኞ 13.10.2026

በአማራ ክልል ዉስጥ በደቡብ ወሎ ና በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ዉግያ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።-ሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣዉ ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ በፊት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፤ ግፊት እንዲያደርግ ኦነግ አሳሰበ፡፡

የጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 12.10.2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎችና ተባባሪዎቻቸው አደዋ ከተማ መግባታቸውን ነዋሪዎች አመለከቱ። ከጅቡቲ ወደ የመን ለመጓዝ አልማ አደጋ ባጋጠማት ጀልባ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን IOM አመለከተ። በሱዳን ግብፅ ድንበር በአየር ጥቃት 72 ሰዎች መገደላቸው ተገነገረ። የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የበጀት እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ።

የጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 11.10.2026

የዛሬው የዓለም ዜና በትግራይ ለምርጫ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር ክልሉ በቀጥታ በፌደራል መንግስቱ ስር ሊተዳደር ይችላል መባሉን፣በጂቡቲ በጀልባ አደጋ ከ100 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን፣ሁቲዎች መንገደኞች የሪያድ አየር ማረፊያዎችን እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቃቸውንና ሩሲያ እና ዩክሬን በሀይል መሰረተ ልማት ላይ ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን አካቷል።

የመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 10.10.2026

ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ዐስታወቀች ። ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች።

የዓለም ዜና፤ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ 09.10.2026

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንዱ አንዱን ፣ "የጥቃት ጦርነት" ጀምሮብኛል ሲሉ መወነጃጀል ጀመሩ።

የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 08.10.2026

የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና

የመስከረም 27 ቀን 2019 የዓለም ዜና 07.10.2026

-የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ከአዲግራት ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ የኤርትራ ጦር ቅፍለትን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱ ተነገረ።-የየመን አንሳር አላሕ ቡድን የአደንና የሪያድ አዉሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደቡ ተዘገበ።---እስራኤል በሐማስ የተጠቃችበት ሶስተኛ ዓመት ዛሬ በሐዘን፣በፀሎት፣በስብሰባና በአደባባይ ሰልፍ ተዘክሮ ዋለ።

የመስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 06.10.2026

የተመድ ሱዳን ውስጥ ሲቪሎች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን አወገዘ። የመን ውስጥ በሁቲ አማጽያንና በመንግሥት መካከል በሚደረገው ውጊያ ከ184 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። ሳውድ አረቢያ ሁለት የአውሮፕላን ማረፊያዎቿ መመታታቸውን አስታወቀች። በጀርመን ዛክሰን አንሀልት ፌደራል ግዛት የአማራጭ ለጀርመን ለም/ቤት አፈ ጉባኤነት ተመረጠ።

Słuchaj podcastu የዓለም ዜና w Replaio

Radio i podcasty w jednej aplikacji - za darmo, bez zakładania konta. Zainstaluj już dziś i nie przegap premiery

Pobierz z Google Play

Replaio nie jest wydawcą podcastów; nazwy audycji, okładki i audio należą do ich autorów i są rozpowszechniane przez publiczne kanały RSS