DW
እንወያይ | Deutsche Welle
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Koniecznie odwiedź stronę podcastu i wesprzyj twórcę: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Autor
DW
Kategoria
Strona podcastu
www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_diskussionsforum-8741-xml-mrss
Ostatni odcinek
5 lip 2026
Gdzie słuchać?
Podcasty w aplikacji Replaio Radio Już wkrótcePodcasty trafią do aplikacji już wkrótce. Zainstaluj teraz i jako pierwszy zobacz nowe podejście do podcastów
Odcinki
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ? 05.07.2026 43:25
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።
የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤትና ፋይዳው እንዲሁም ተግዳሮቶቹና ተስፋው 28.06.2026 40:34
ምርጫው ከመካሄዱ አስቀድሞም በስፋት እንደተጠበቀው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሲያሸንፍ ከቀደሙት ምርጫዎች በተለየ በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ትኩረት ስቧል።
በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ፥ እንዴትስ ይቆማል? 21.06.2026 43:35
ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይሰነዘራሉ ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የመገደል የመፈናቀላቸው፣ የቤት ንብረታቸው መዘረፍና መውደም ሰበቡ ምን ይኾን፥ እንዴትስ ይቁም? ሙሉ ውይይቱን በማገኛው በኩል ማድመጥ ይቻላል ።
ውይይት፤በምርጫው ከሚያሸንፈው መንግስት በመጭው አምስት የስልጣን ዓመታት ምን ይጠበቃል? 14.06.2026 45:21
በኢትዮጵያ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡበት ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል።ያም ሆኖ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተካሄደው የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት እና የኢኮኖሚ ችግር ባየለበት እና በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት፣መፈናቀል እና ሞት በሚሰማበት ነው። ለመሆኑ ከመንግስት በመጭዎቹ 5 ዓመታት ምን ይጠበቃል?ቅድሚያ የሚሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይስ የቱነው?
ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ 07.06.2026 42:54
ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ምርጫ ፤ዋዜማው፣ የምርጫው ዕለት እና ድህረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ ምን ይመስላል።?7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ፤ ከዘገቡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች መካከል አራቱን አነጋግረናል።
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የሐገሪቱን ችግሮች ለማቃለል ይፈይድ ይሆን? 24.05.2026 41:22
ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዳዶቹ የፓርቲነት ፍቃድ ላለማጣት ሲሉ ብቻ የሚወዳደ,ሩ እንዳሉ አስታዉቀዋል።የኢትዮጵያን ምርጫ ሒደትና ሁኔታን የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የዘንድሮዉን ምርጫ «ለገዢዉ ፓርቲ ሕጋዊ ዕዉቅና ለመስጠት ያለመ የታይታ» ምርጫ ይሉታል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የምርጫዉ የእስካሁን ሒደት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና የሕዝብ ተሳትፎን ያሰፋ በማለት ያወድሱታል
እንወያይ፤ የመናገር ነጻነት እና የጋዜጠኝነት ፈተናዎች በኢትዮጵያ 17.05.2026 46:24
ኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት በቅርቡ ይፋ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት "የፖለቲካ እና የግጭት ኹኔታዎች ጋዜጠኞች ላይ "ብሔራዊ ጥቅም" በሚል ሽፋን በጋዜጠኞች ላይ የደኅንነት አደጋዎችን ለመፍጠር በመደበኛነት ሥራ ላይ መዋላቸውን ጠቅሷል። የጥናት ግኝቱ ጋዜጠኞች " ዛቻ፣ እሥር፣ አፈና፣ የግዳጅ መሰወር እና ዝርፊያ" እንደተፈፀመባቸው አትቷል።
የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅትና ተግዳሮቶቹ 03.05.2026 45:48
ከ20 በላይ ሀገራዊ እና ከ40 በላይ ክልላዊ ፓርቲዎች ይሳተፉበታል የተባለው ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአንድ ወር ጊዜ ነው የቀረው። ቦርዱ በስድስት ክልሎች «የፀጥታ እና አስቻይ የፖለቲካ ምህዳር»ን እንዲገመግም ያደራጀውን ቡድን ማሰማራቱን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።
የእሥራኤል-ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ጦርነት ዳፋ ለኢትዮጵያ፦ እንወያይ 26.04.2026 43:43
የእሥራኤል-ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ጦርነት የተኩስ አቁሙ ቢራዘምምም በሆርሙዝ ሰርጥ ኢራን ቁጥጥሯን በማጥበቋ እና ዩናይትድ ስቴትስም በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችው ገደብ ባለመነሳቱ ውጥረቱ አይሎ ቀጥሏል ። ለመሆኑ ይህ የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት መቀጠሉ ኢትዮጵያ ላይ ያሳደረው ጫና እንዴት ይቃኛል? ሙሉውን ውይይት ያድምጡ ።
የጄነራል ታደሰ ወረደ ሹመት መራዘም ለክልሉ መፍትሔ ወይስ ሌላ ቀውስ ? 19.04.2026 47:29
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሣምንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዳራዘሙ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በገታው ግጭት የማቆም ሥምምነት ለተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ሉቴናንት ጄኔራል ታደሰ ሁለተኛ ፕሬዝደንት ናቸው።
ውይይት፤የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 8 የስልጣን አመታት ሲቃኙ 12.04.2026 54:26
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዶክተር ዓብይ አህመድ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ወደ መንበረ ስልጣን መጥተዋል። የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት የኢህአዴግን አመራር ይወቅሱ በነበሩ በብዙዎች ዘንድ የለውጥ ተስፋ አሳድሯል።ያም ሆኖ፣ መንግስታቸው እንዳጀማመሩ አለመቀጠሉ፤ የነበረው የለውጥ ተስፋ መደብዘዙ ይነገራል።
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ 05.04.2026 47:17
ጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።
በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች 29.03.2026 46:28
በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህርና የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተመራማሪ ፍቅር ጌታቸው በውይይቱ ተሳትፈዋል።
ውይይት፤ ኢትዮጵያ ብርቱ ፈተና የደቀነውን የነዳጅ እጥረት እንዴት ትወጣ? 22.03.2026 46:26
የኢራን ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የፈጠረው መስተጓጎል ለመቋቋም ሕዝቡ እና ተቋማት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነዳጅ እንዲጠቀሙ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስጠንቅቋል። የነዳጅ ግብይትም መንግስት ባስቀመጠው ታሪፍ መሰረት እንዲከናወን አሳስቧል። ያም ሆኖ ችግሩ ከዓቅም በላይ መሆኑን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው።
Podobne podcasty
Replaio nie jest wydawcą podcastów; nazwy audycji, okładki i audio należą do ich autorów i są rozpowszechniane przez publiczne kanały RSS