DW
የዓለም ዜና
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: www.dw.com
¿Dónde escuchar?
Podcasts en la app Replaio Radio Muy prontoLos podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts
Episodios
የጥቅምት 08 ቀን 2019 የዓለም ዜና 18.10.2026 6:41
በዛሬው የዓለም ዜና፤ የኤርትራ ወታደሮች አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለቀው ቢወጡም አሁንም በድንበር አካባቢ መኖራቸውን፤ በፈረንሳይ በተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በተፈጸሙ ዘረፋዎችና የእሳት ቃጠሎዎች 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤።በጀርመን የላይፕዚግ አየር ማረፊያ አጥር በመደርመሱ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አካቷል።
የጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 17.10.2026 12:05
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ አስጠነቀቀ። የትግራይ የሰላም ኃይል ከፌደራል መከላከያ ሰራዊ ጋር በመሆን «ፅንፈኛ» ባለው የህወሓት ሰራዊ ላይ ባካሄደው የጸረ ማጥቃት እርምጃ የኃይል ሚዛኑን «ሙሉ በሙሉ መዛባቱን» የሰላም ኃይሉ ቃል አቀባይ ገለጹ።
የጥቅምት 6 ቀን 2019 የዓለም ዜና 16.10.2026 10:50
-የኢትዮጵያና ኤርትራ ሙሉ ጦርነት እንዳይገጥሙ ማሕበራትና መንግሥታት የሚያደርጉት ግፊትና ጥሪ እንደቀጠለ ነዉ።-የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልልን በጊዚያዊነት የሚያስተዳድር የባለአደራ አስተዳደር መሠረተ።--በየመን ሶስተኛ ትልቅ ከተማ ታዝ የመሸገዉ የሐገሪቱ መንግሥት ጦር ኃይል ባልደረቦች እጃቸዉን እንዲሰጡ አንሳር አላሕ አሳሰበ።
DW Amharic የጥቅምት 05 ቀን 2019 የዓለም ዜና 15.10.2026 10:38
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች በድንበር ላይ በምትገኘው የዛላአምበሳ ከተማ አካባቢ ተፋጠው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ። ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው የበረታውን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚገባ አሳስባለች። በጋምቤላ በተፈጸመ ጥቃት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ከከተማው የሸሹ ነዋሪዎች እንዲመለሱ አስተዳደሩ ጥሪ አቀረበ።
የጥቅምት 4 ቀን 2019 የዓለም ዜና 14.10.2026 11:50
-የኢትዮጵያ የፌደራል ጦርና የትግራይ የሰላም ኃይል ታጣቂዎች ኤርትራን ሳላምበሳ ጥግ መድረሳቸዉን ነዋሪዎችና ተዋጊዎች አስታወቁ።--አማራ ክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያም እንደቀጠለ ነዉ።-የየመን አንሳርአላሕ የሳዑዲ አረቢያን የነዳጅ ተቋማትና አዉሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደባቸዉን እንደሚቀጥሉ አሰታወቁ።
የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ማክሰኞ 13.10.2026 11:56
በአማራ ክልል ዉስጥ በደቡብ ወሎ ና በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ዉግያ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።-ሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣዉ ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ በፊት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፤ ግፊት እንዲያደርግ ኦነግ አሳሰበ፡፡
የጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 12.10.2026 10:08
የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎችና ተባባሪዎቻቸው አደዋ ከተማ መግባታቸውን ነዋሪዎች አመለከቱ። ከጅቡቲ ወደ የመን ለመጓዝ አልማ አደጋ ባጋጠማት ጀልባ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን IOM አመለከተ። በሱዳን ግብፅ ድንበር በአየር ጥቃት 72 ሰዎች መገደላቸው ተገነገረ። የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የበጀት እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ።
የጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 11.10.2026 9:30
የዛሬው የዓለም ዜና በትግራይ ለምርጫ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር ክልሉ በቀጥታ በፌደራል መንግስቱ ስር ሊተዳደር ይችላል መባሉን፣በጂቡቲ በጀልባ አደጋ ከ100 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን፣ሁቲዎች መንገደኞች የሪያድ አየር ማረፊያዎችን እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቃቸውንና ሩሲያ እና ዩክሬን በሀይል መሰረተ ልማት ላይ ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን አካቷል።
የመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 10.10.2026 11:53
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ዐስታወቀች ። ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች።
የዓለም ዜና፤ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ 09.10.2026 11:58
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንዱ አንዱን ፣ "የጥቃት ጦርነት" ጀምሮብኛል ሲሉ መወነጃጀል ጀመሩ።
የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 08.10.2026 11:46
የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
የመስከረም 27 ቀን 2019 የዓለም ዜና 07.10.2026 11:59
-የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ከአዲግራት ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ የኤርትራ ጦር ቅፍለትን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱ ተነገረ።-የየመን አንሳር አላሕ ቡድን የአደንና የሪያድ አዉሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደቡ ተዘገበ።---እስራኤል በሐማስ የተጠቃችበት ሶስተኛ ዓመት ዛሬ በሐዘን፣በፀሎት፣በስብሰባና በአደባባይ ሰልፍ ተዘክሮ ዋለ።
የመስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 06.10.2026 10:01
የተመድ ሱዳን ውስጥ ሲቪሎች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን አወገዘ። የመን ውስጥ በሁቲ አማጽያንና በመንግሥት መካከል በሚደረገው ውጊያ ከ184 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። ሳውድ አረቢያ ሁለት የአውሮፕላን ማረፊያዎቿ መመታታቸውን አስታወቀች። በጀርመን ዛክሰን አንሀልት ፌደራል ግዛት የአማራጭ ለጀርመን ለም/ቤት አፈ ጉባኤነት ተመረጠ።
የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 05.10.2026 10:04
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግስት ምስረታ ጉባኤውን በማካሄድ ዶክተር አብይ አሕመድን በጠቅላይ ሚኒስት አድርጎ ሰይሟል።ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና በቀይ ባሕር ያላትን ታሪካዊና መልከዐምድራዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየር አይችልም ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የመስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 04.10.2026 7:54
የመቐለ ከተማን ለቆ የወጣው ህወሓት መራሹ «የትግራይ ክልል መንግስት» በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ አስታወቀ። የህወሓት ባለስልጣናት የመቐለ ከተማን ለቀው ሲወጡ ቆስለው በህክምና ላይ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ይዘው መውጣታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።
የመስከረም 23፣ 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 03.10.2026 9:55
• የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ኃይሎች የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ተቆጣጠሩ። • የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዛሬ ጠዋት ወደ ግብጽ ካይሮ ተጓዙ ። • የ2019 የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ዛሬ በድምቀት ተከበረ።
የመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 02.10.2026 10:57
የትግራይ ሰላም ሀይል ከመቀለ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለች ከተማን ተቆጣጠርኩ ማለቱን፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞት፣ መፈናቀልና ሰብአዊ ቀውስማድረሱን፣ግብፅ የኢትዮጵያን ዲፕሎማት ከሀገሯ ማስወጣቷን፣የአፍሪቃ ሕብረት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅ መካከል ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ ማቅረቡን እና ሌሎችን አካቷል።
የመስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.10.2026 11:26
ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ፍንዳታ መሰማቱን ሮይተርስን ጨምሮ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘገቡ። ኢትዮጵያ አስመራ ያለውን ኤምባሲ ለመዝጋት ወሰነች። በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ስጋቱ የሰብአዊ አቅርቦትን ማስታጎሉን የተmm,ድ ገለጸ። እስራኤል በፍላይ ዱባይ አውሮፕላን ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት ከመሠረቱ እንደምታጣራ ዛተች።
የመስከረም 20 ቀን 2019 የዓለም ዜና 30.09.2026 11:42
-የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት የድርድርን መንገድ እንዲመርጡ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተማፀኑ።ዉጊያ እንደቀጠለ ነዉ።-- አዲስ አበባና አካባቢዋ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን እንዳይበር ታገደ።-ኢትዮጵያን ጨምሮ ለምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል የተባለ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ላሙ-ኬንያ ዉስጥ ተጀመረ።
የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 29.09.2026 8:36
ዋሽንግተን፥ ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን ውጥረት ለማርገብ አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ፣ አ.አ፥ በሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ፣ ወሎ፥ በተቀሰቀሰው ጦርነት የተፈናቃዮችን መከራ ማባሱ ተገለጠ፣ ካይሮ፥ የአፍሪቃ አገራት ለንድግ ግብጽ ውስጥ ይሰበሰባሉ፣ ፑንትላንድ፥ አንዲት ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከባሕር ላይ ዘራፊዎች ነጻ ወጣች
የዓለም ዜና 28.09.2026 11:58
በዛሬው የዓለም ዜና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተለያዩ ከተሞች የበርክታ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፤የትግራይ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድሮን ተመታ ባሉን፣ ቀይመስቀል 161 ሰዎችን ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች ዛሬ ማስወጣቱን፣በሽብርተኝነት ተከሰው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የነበሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አስጊ ወደተባሉ እስር ቤቶች ተዛወሩ መባሉን አካቷል።
የመስረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 27.09.2026 8:19
በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦና አላማጣ አካባቢዎች ከባድ ውግያ ሲካሄዱ እንደዋሉ መረጃዎች አመላከቱ። አላማጣ፣ ጥሙጓና ሰሌን ውሃ በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ታውቋል። በመቐለ ከተማ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
DW Amharic የመስከረም 16 ቀን 2019 የዓለም ዜና 26.09.2026 10:56
ሩሲያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ያሳስበናል አሉ። መከላከያ ሠራዊት በትግራይ አምስት ትምህርት ቤቶች እና በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ ላይ በፈጸማቸው ድብደባዎች ሰዎች መገደላቸውን የተመ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። በመቐለ መከላከያ ሠራዊት የፈጸመው ጥቃት እንደ “የጦር ወንጀል ሊመረመር እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።
የመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. የዶቼቬለ የዓለም ዜና 25.09.2026 11:46
አርዕስተ ዜና -የኢትዮጵያ ጦርና የትግራይ ኃይሎች ዛሬ በተለያዩ ግንባሮች ከባድ ውጊያ መካሄዳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ -በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መታጎሉን ተጠቃሚዎች አስታወቁ ። -በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ።
የመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 24.09.2026 10:41
የትግራይ ኃይሎች ከፌድራል መንግሥት ጋር “ሙሉ ጦርነት” መግጠማቸውን ገለፁ። የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት “በአፋጣኝ ማርገብ” እንደሚያስፈልግ አሳሰበ። ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኝ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘጋ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ፑቲንን ለቡድን 20 ጉባኤ ጋበዘቻቸው
Podcasts similares
Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos