DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: www.dw.com
¿Dónde escuchar?
Podcasts en la app Replaio Radio Muy prontoLos podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts
Episodios
የመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 23.09.2026 23:02
የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይላት እና የትግራይ አማጽያን ውጊያ፤ የትግራይ ክልል አለመረጋጋት፤ የአየር በረራው መቋረጥ፤ አፋር ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት ኃይላት እና በሕወሓት መካከል ውጊያው ቀጥሏል መባሉ፤ ቃለ መጠይቅ፤ በርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪ ላይ ደረሰ የተባለ የድሮን ጥቃት እንዲመረመር መጠየቁ
የዜና መፅሔት፤ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 22.09.2026 18:55
ትብብር ለህልውና የተባለው የታጣቂዎች ቡድን ምስረታ ላይ አስተያየቶች ፤ ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በርካታ ተጎጂዎች ጋምቤላ ውስጥ ወደሚገኘው የህክምና መስጫ መምጣታቸውን መግለፁ፤ በሶማሊያ የአፍሪካ ኀብረት ተልዕኮ የሚደረገው ድጋፍ በአንድ አመት መራዘም መጠነኛ እፎይታ እንደሚሰጥ መነገሩ
የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 21.09.2026 19:25
በዜና መጽሔት አስተያየት ሰባት ታጣቂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የፈጠሩት ትብብር በራያ አካባቢ የወታደራዊ ውጥረቱ ማይልና ተፈናቃዮች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዎች የጥቃት እና እገታ ሥጋት እና በበርሊን እና በሜክለንቡርግ ፎርፖመርን ግዛቶች የተካሄደዉ ምርጫ ዉጤትና የመራኄ መንግስቱ እጣ ፈንታን ያስቃኛል።
የመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት 18.09.2026 25:08
በኢትዮጵያ ከተካሄደ 20 ዓመታትን የደፈነው የህዝብና ቤት ቆጠራ -በአማራ ክልል ዘንድሮ 4.9 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበዋል መባሉ -የኢትዮጵያዉያንና የኤርትራዉያን ስደተኞች ችግር በዩጋንዳ የናይል እና ቀይባህር ስልታዊ መድረክ ምስረታ- በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኀብረት የሁቲ አማጺያን የፈፀሙትን ጥቃት ማዉገዙ፤
የመስከረም 6 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 16.09.2026 21:05
የዜና መጽሔት እስረኞችን በምህረትና በይቅርታ የመልቀቅ ሕጋዊ ማዕቀፍን የሚያስቃኘው ዘገባ ይቀድማል ። ድርቅ በአማራ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች ያስከተለውን ጉዳት፣ኤልኒኖ ሌላው የግብርና ምርት ተግዳሮት፣ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የጉዞ አቅም ከዓለም የመጨረሻዎቹ ተርታ መመደቡ ላያ ያተኮሩ ዘገባዎችም ተሰናድተዋል
የመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት 15.09.2026 16:35
ትግራይ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ሌላ አካባቢ እንዲመደቡ መወሰኑና የክልሉ ተቃዉሞ። የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚኒስቴር የ2019 የትምህርት ዘመን የሬሜዲያል መርሐ ግብር።
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 14.09.2026 32:59
በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ አዲስ ከሚመሰረተዉ መንግሥት ምን ይጠበቃል? በኮንሶ ምንድን ነው የሆነው ?በዋግህምራ በግጭትና ድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተሰደዱ ነውä፣በህንድ የተካሄደው የብሪክስ ጉባኤና የኒውዴልሂዉ መግለጫን አካቷል።
የአዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት 11.09.2026 32:25
እንቁጣጣሽ፣ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ አሮጌውን 2018 ዓ.ም.ሸኝታ አዲsune 2019 ዓ.ም ተቀበለች። በ2018 ግጭት፣ አለመረጋጋትና የኑሮ ውድነት የተፈታተናቸው ኢትዮጵያውያን በአዲሱ ዓመት ለውጥ ይናፍቃሉ። የተሻለ ሕይወት ይመኛሉ። የዶቸ ቬለ ዘጋቢዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የላኳቸው ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 10.09.2026 24:30
በአዲስ ዓመት ዋዜማ ዘና መጽሔት ዘገባችን፦ -ፖለቲከኛ ክርስቲያን ታደለን እና በርካታ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በዛሬው እለት ከእስር መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐሳውቋል። ይህና -ግጭት ያጠላበት የአዲስ አመት አከባበር በአማራ ክልልና ሌሎችም ዘገባዎች አካትተናል ።
የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 09.09.2026 22:35
በትግራይ ክልል በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መኖሩን ህወሓት መግለፁ፤ በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት የጸጥታ ችግር ያስከተለው ስጋት፤ በአላማጣ ከተማ ይፈጸማል የተባለው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ፤ የመስቃን እና ማረቆን ሰላም ለመመለስ የተደረገውን ጥረት እንዲሁም የአሜሪካ እና ኢትዮጵያን የኤኮኖሚ ጉድኝት የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል።
የጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 07.09.2026 19:32
የትግራይ ክልል በኦባሳንጆ የአሸማጋይነት ሚና ላይ የገለልተኝነት ጥያቄን ማንሳቱ፣ ቻይና በአባይ እና ቀይባህር ላይ የግብጽን አቋም መያዟ ለኢትዮጵያ ስጋት ነውን?የኤልኒኞ ክስተት ተፅዕኖ በሶማሌ ክልል ያሳደረዉ ስጋት፤ ፖሊስ የዋስትና መብት በተፈቀደላቸው የኢሕአፓ አመራሮች ላይ ይግባኝ ጠየቀ
የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 04.09.2026 22:33
በራያ እና በአላማጣ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ፣ ድርቅ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተዳርገናል ሲሉ አማረሩ። ደብዛው የጠፋው የፎቶግራፍ ባለሙያ ፊልሞን ገብረሕይወት የት እንዳለ ይፋ እንዲደረግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ ። በእሥር ላይ ለሚገኙት የኢሕአፓ አመራሮች የዋስትና መብት መፈቀዱ፣
የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 03.09.2026 27:34
በዛሬው መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪቃ ህብረት የምታበረክተውን የገንዘብ አስተዋጽዖ በእጥፍ ለማሳደግ መፈለጓ ፣ ህወሃት በፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው ማለቱ፣ በኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ ላይ የአብን መግለጫ እና አንድምታው፣ የተሰኙ ዘገባዎች በትንታኔ ይደመጣሉ።
የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 02.09.2026 19:53
የዜና መጽሔት የምስራቅ ወለጋ ዞን አንጌር ጉቴ አከባቢ ግጭትና ግጭቱ ያፈናቀላቸው ሰዎች ብሶት በጃናሞራ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ መዳረጋቸው መነገሩ፣ በጋምቤላ የምርት መቀነስን ለማካካስ መስኖ እንደማራጭ መያዙ፣ጀርመን በሀገርዋ የሚገኙ የተለያዩ የሩስያ ተቋማት እንዲዘጉ መወሰኗ ላይ ያተኮሩ ቅንብሮች ይቀርባሉ።
የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.09.2026 19:29
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤን ከነሒደቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉድቅ ማድረጋቸዉ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሠላም እንዲሰፍን በተደጋጋሚ የሚደረገዉ ጥሪና ዉጤቱ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የመሬት መንሸራተት ያደረሰዉ ጉዳትና አልርጀንቲናዊዉ የእግር ኳስ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጡረታ መዉጣቱን ያስቃኘናል።
DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 31.08.2026 18:45
በባቲ ወረዳ «የኦነግ ሸኔ» ጥቃት፣ እገታና መፈናቀል ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ምሬት መዳረጉ፤ ግጭት ማስወገድ የተሳናቸው የአፍሪካ ኀብረት መዋቅሮችና የማሻሻል ሂደቶች፤ በአሜሪካ እና ካናዳ መካከል ያገረሸው የንግድ ጦርነትና የዲፕሎማሲ ውጥረት፤ አይስላንድ ለግዜው ወደ አውሮጳ ህብረት ላለመግባት ወሰነች
የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዜና መፅሄት 28.08.2026 23:39
የዛሬው የዜና መፅሄት-ዛሬ ችሎት የነበሩት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ለመጪው ሐሙስ መቀጠራቸዉ ፤, በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች የቀጠለዉ ጥቃት፤ በአፋር ክልል የክረምት ዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ የአርብቶ አደሩን ህይወት መፈተኑ፤ በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ለማኅበረሰባቸው በጎ የሰሩ ግለሰቦች ተሸለሙ የተሰኙ አምስት ርዕሶችን አካቷል።
የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና የዜና መፅሄት 26.08.2026 18:42
ከዓለም ዜና በኋላ በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የመቀሌ ጉብኝት ያመጣው አዲስ ምክረሃሳብ የለም ማለታቸው፤በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የኦባሳንጆን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው መግለፁን፣ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ሰዎች ገድለው፤ ንብረት ስለማውደማቸው እንዲሁም በአላማጣ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ከባድ የእህል እና የገንዘብ መዋጮ በግዴታ እየተጠየቅን ነው ማለታቸውን የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።
የነሐሴ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መፅሔት 25.08.2026 18:47
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የዛሬዉ የመዉሊድ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት መሪዎችን እንደገና ለመሸምገል የጀመሩትን ዲፕሎሲ የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ሥለ ዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት የተጠናቀረዉ ያሰልሳል።ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በተከፈቱ ጥቃቶችና ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛትና ጥያቄን የሚዳስስ ዘገባም አለን።
የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም መጽሔተ ዜና 21.08.2026 25:50
ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፤ ሰሜን ወሎ በፀረ ተሽከርካሪ ቦምብ ፍንዳታ አራት ሰዎች መገደላቸው፤ የመቀሌው የአየር ጥቃት ሰላባዎችና ነዋሪዎች አስተያየት በምክክሩ የጎላ መነጋገሪያ ሆኖ የቀጠለው የአዲስ አበባ ጉዳይ ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው ከፍተኛ የዶላር ጨረታ እንዲሁም በአውሮጳ አትሌቲክስ ውድድር ለጀርመን ወርቅ ያስገኘው ትውልደ ኤርትራዊው ጀርመናዊ አማናል ጴጥሮስን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤ የዕለተ ዓርብ ሳምንታዊ መሰናዶ ከወጣቶች ዓለም፤ እንዲሁም የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ እንወያይ የቅምሻ ጥንቅርም ይኖረናል።
የነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.08.2026 25:01
በዜና መጽሔት ፤ ስለአገራዊው ምክክር የነዋሪዎች አስተያየት ፣ በትግራይ ክልል እየተፈፀሙ ያሉ የድሮን ጥቃቶች ፣ የምስራቅ ወለጋው የጊዳ አያና ጥቃትና የነዋሪዎች ተቃውሞ ፣ በደቡብ ወሎ 3,500 ያህል ከአረብ ሀገራት ተመላሾች በሀገራቸው የስራ እድል ማግኘታቸውን ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አርማውን ያለ አግባብ የሚጠቀሙ እንዳሉ መግለጹን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።
የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 19.08.2026 18:04
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ የመጨረሻ ሰነድ ነገ ለተመካካሪዎች ይቀርባል ሥለመባሉ የተጠናቀረ ዘገባን ያስቀድማል።የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት አሜሪካ ዉስጥ በጊዚያዊነት እንዲኖሩ የተፈቀደላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ፍቃድን ማቋረጡን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳን ድርቅና ወረርሺኝ የሰዉና የእንስሳት ሕይወት ማጥፋታቸዉን የሚያወሳዉ ያሰልሳል።ዜና መፅሔቱ የኑሮ ዉድነት በቡሔ በዓል ላይ ያደረሰዉን ጫና የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
Podcasts similares
Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos