DW
እንወያይ
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።
Où écouter ?
Les podcasts dans l'appli Replaio Radio Bientôt disponibleLes podcasts arrivent très bientôt dans l'appli. Installe-la dès maintenant et découvre en avant-première une toute nouvelle façon de vivre les podcasts
Épisodes
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የሐገሪቱን ችግሮች ለማቃለል ይፈይድ ይሆን? 24.05.2026 41:22
ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዳዶቹ የፓርቲነት ፍቃድ ላለማጣት ሲሉ ብቻ የሚወዳደ,ሩ እንዳሉ አስታዉቀዋል።የኢትዮጵያን ምርጫ ሒደትና ሁኔታን የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የዘንድሮዉን ምርጫ «ለገዢዉ ፓርቲ ሕጋዊ ዕዉቅና ለመስጠት ያለመ የታይታ» ምርጫ ይሉታል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የምርጫዉ የእስካሁን ሒደት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና የሕዝብ ተሳትፎን ያሰፋ በማለት ያወድሱታል
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ 05.04.2026 47:17
ጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።
በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች 29.03.2026 46:28
በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህርና የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተመራማሪ ፍቅር ጌታቸው በውይይቱ ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ 01.03.2026 46:50
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት ልጃለም፤ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ዳምጠው ተሰማን በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዷል።
እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው? 22.02.2026 45:00
ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ሆነዋል።
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ? 25.01.2026 40:17
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነት 18.01.2026 45:30
የትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።
Podcasts similaires
Replaio n'est pas éditeur de podcasts ; les noms des émissions, les visuels et l'audio appartiennent à leurs auteurs et sont diffusés via des flux RSS publics