DW
እንወያይ
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ዝግጅት፣ የተቃዋሚዎች ሥጋትና የሰላም ጥያቄ 30.11.2025 45:30
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ባንፃሩ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች በሰጡት መልስና ማብራሪያ «ምርጫ ለማድረግ መንግሥት በቂ አቅም አለዉ፤ምርጫ እንኳን ዘንድሮ ባለፈዉም ምርጫ አድርገናል እየተዋጋን።» ብለዋል።በግጭት፣ ዉጥረት፣ ተቃርኖና ዉዝግ መሐል ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሊደረግ ይችላል? ምርጫ ማድረግ ወይም አለማድረጉስ የኢትዮጵያን ዉስብስብ ችግሮች ለማቃለል ይጠቅማል? እንዴት? በዉይይታችን የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸዉ።
ውጥረት ያነገሰው የሰሞንኛው የህወሓት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና ያስከተለው ስጋት 16.11.2025 46:18
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ ግጭትን የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ ባለፈዉ ጥቅምት 23 ሶስኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ሶስቱ ዓመታቱ ብዙዎች እንደሚሉት ሁለቱ ኃይላት በስምምነታቸው መሰረት ግዴታቸውን ያልተወጡበት ወይም ሊወጡ ያልፈለጉበት ሰላምም ግጭት ያልነበረበት ሆኖ ነው ያለፈው።
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው? 09.11.2025 41:24
የውጭ ምንዛሪ ግብይት በአቅርቦት እና ፍላጎት እንዲወሰን ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ዕድገት ቢያሳይም ብር እየተዳከመ ነው። የወርቅ ኤክስፖርት መሻሻል ብር እንዲረጋጋ ሊያደርግ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተስፋ አድርጓል። የፕራግማ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርዕድ ብሥራት፣ የፋይናንስ ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ የተሳተፉበት ውይይት የምንዛሪ ገበያው ብር ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ይፈትሻል።
እንወያይ፣ ሥር የሰደደዉ የኢትዮጵያዉያን ክፍፍል መፍትሔ አለዉ ይሆን? 05.10.2025 45:28
1983 ወታደራዊ ሥርዓት ተወገደ።ኤርትራ ነፃ ወጣች።በ1960ዎቹ መልስ አላገኘም የተባለዉ የብሔር-ብሔረሰቦች ጥያቄ መልስ አገኘ ተባለ።በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፈ,ደራሊዝም መመሥረቱም ታዋጀ።ጦርነቱ ግን ቀጠለ።ክፍፍሉም ከብሔሮች ወይም ጎሳዎች አልፎ ወደ ንዑስ-ብሔሮች፣ ከዚያም እስከ ጎጥ ቀጥሎ ዛሬ ያንድ ብሔር ወይም ጎሳ አባላት የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች እየተቧደኑ ወይም በተናጥል ይጋጫሉ፣ ይገዳደላሉም።
ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ምን ምን ዐበይት ጉዳዮች ተከሰቱ? 14.09.2025 45:00
አሮጌውን 2017 ዓመት ተሰናብተን አዲሱን ዓመት መቁጠር ከጀመርን እነሆ ሦስተኛ ቀናችን ። በ2017 ኢትዮጵያ ውስጥ በዋናነት ምን ተከሰተ? የዕለቱ እንወያይ መሰናዶ ባሳለፍነው ዓመት የተከሰቱ ዐበይት ጉዳዮችን የምንቃኝበት ነው።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድር 07.09.2025 45:51
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በመጪው ማክሰኞ ይመረቃል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ከምትዋሰንበት ድንበር በ30 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ግድብ የግንባታ ሒደቱ 14 ዓመታት ገደማ የወሰደ ነው። የኃይል ማመንጫው 13 ተርባይኖች ተገጥመውለታል። በግድቡ የተገጠሙ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ በድምሩ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። በግድቡ የተፈጠረው ሰው ሠራሽ ኃይቅ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይይዛል። ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፤ ኢንጂነር አሥራት ብርሀኑ እና ወንድወሰን ሚቻጎን ስለ ታሪካዊው ምዕራፍ አወያይተናል።
እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎች 24.08.2025 45:00
ውይይቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ይረዳል በሚል በመስጠት ላይ ስለሚገኘው የክረምት ልዩ ስልጣና ምንነት እና ስለገጠሙት ፈተናዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሊጀምር የአንድ ወር እድሜ ያህል እንደመቅረቱ ከትምህርት ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል።
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ይደረጋል የተባለ ማሻሻያ ለምን ሥጋት ፈጠረ? 13.07.2025 45:55
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ሊደረጉ የታቀዱ ማሻሻያዎችን የመረመሩ ባለሙያዎች እና አጥኚዎች ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ሳለ ዘርፉን ቀፍድደው የያዙ ገደቦች እና አሠራሮች ተመልሰው ተግባራዊ ሊሆኑ ነው የሚል ብርቱ ሥጋት አላቸው። ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት ማሻሻያዎቹን እና ተጽዕኖዎቻቸውን ይፈትሻል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ፣ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሰብአዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ተማሪ እና ተመራማሪ ሕሊና ብርሀኑ በውይይቱ ተሳትፈዋል።
ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር፣እጥረትና እስከፊ ጫናዉ 06.07.2025 46:40
ለድጎማዉ መነሳት ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን የነጃ ዋጋ አለቅጥ ተንቻርሯል።-ለእጥረቱ ተጠያቂዉ ማንም ሆነ ማን እጥረቱ አለ።የዋጋዉ ንረትና እጥረቱ ወትሮም በየአካባቢዉ በሚደረጉ ግጭቶች ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለ፣ መሥራት ያልቻለዉ ወይም ሰላማዊ ዝዉዉሩ የተገደደበበት ሕዝብ፣ በብር የመግዛት አቅም መዳከምና በዓለም ላይ በሚታየዉ ግሽበት ምክንያት ኑሮ የተወደደበት ሕዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን በየአጋጣሚዉ እየተናገረ ነዉ። በዛሬዉ ዉይይታችን የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናርና እጥረቱ ያስከተለና የሚያስከትለዉን ችግር ባጫጭሩ አንስተን መፍትሔዉን ለመጠቆም እንሞክራለን
እንወያይ፤ «የሕዝብ ለሕዝብ» የተባለለት ግንኙነት ወዴት ያመራል? 29.06.2025 45:40
በሕዝብ ለሕዝብ ስም እንዲህ አይነት ግንኙነቶች መጀመሩን ብዙዎች እየተቹት ይገኛሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ግንኙነቱ መጀመሩን ያለፈ ቁስልን በማሻር ወደፊት የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በር ከፋች እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.