DW
እንወያይ
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ከ1997 ምርጫ ወዲህ ከወዴት አለ? 18.05.2025 44:00
በ1997 ምርጫ ኢሕአዴግን የተገዳደሩት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፉት 20 ዓመታት ተዳክመዋል። ኢሕአዴግን በብልጽግና ፓርቲ የተካው ለውጥ ያነቃቃቸውም በውስጣቸው ተከፋፍለዋል። የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ሞተ ወይስ እያጣጣረ ነው? ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር አዲሱ ላሽተው የተሳተፉበት የእንወያይ መሰናዶ የኢትዮጵያን የፓርቲ ፖለቲካ ህልውና ከ1997 ወዲህ እና በሚቀጥለው ዓመት ሊካሔድ ከታቀደው ምርጫ አኳያ ይዳስሳል።
የኢትዮጵያ ባንኮች ውህደት፦ በግዳጅ ወይስ በገበያው ፍላጎት? 16.03.2025 46:49
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ሲጸድቅ አንድ ባንክ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ቅርንጫፍ ከፍቶ ለመሥራት የሚያስችለውን ፈቃድ ለማግኘት 66 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ሐብት ሊኖረው ይገባል። ረቂቅ መመሪያ ውህደትን የሚገፋፋ እንደሆነ በባለሙያዎች ዘንድ ግንዛቤ አለ። ይህ ውይይት የባንኮች ውህደትን ፋይዳ እና ተግዳሮት ይፈትሻል። በውይይቱ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት አቶ ባህሩ ያሲን፣ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ የባንክ ባለሙያነት ያገለገሉት የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ለማ እና የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ ተሳትፈዋል።
የእርዳታ መታገድ አሉታዊ እና አዎንታዊ ፋይዳ 16.02.2025 40:19
አሜሪካ ለውጭ የምትሰጠውን እርዳታ ማቆሟ በተለይ በአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛ ግርታና ድንጋጤ ፈጥሯል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ የሥልጣን መንበር የመጡት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ እርዳታ ለዘጠና ቀናት እንዲቆም ወስነዋል። ትራምፕ እርዳታ አፍሪቃውያንን አሳንፏቸዋል ነው የሚሉት።
እንወያይ፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ-ብዙ ቀዉስ፣ ምክንያቱና መፍትሔዉ 07.02.2025 48:20
የአማራና የኦሮሚያ ክልሎችን የሚያብጠዉ የመንግሥትና የአማፂያን ግጭቶች፣ በየአካባቢዉ የተንሠራፋዉ ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታ፣ ዘረፋ፣ መፈናቃል፣ የኑሮ ዉድነት ብዙዎች እንደሚሉት ሕዝቡን ለመከራ፣ ሐገሪቱን ደግሞ ለሕልዉና አደጋ ዳርጓቸዋል
እንወያይ፦ የአራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ዕግድ ስለ ኢትዮጵያ የሲቪክ ምኅዳር ምን ይናገራል? 12.01.2025 46:07
የብሔራዊ ምክክር ሒደት የጀመረችው፤ ለሽግግር ፍትሕ የምትዘጋጀው እና በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የምታካሒደው የኢትዮጵያ መንግሥት አራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችን አግዷል። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል የተላለፈው ዕግድ ሕጋዊ ነው? ዕግዱ ስለ ሲቪክ ምኅዳሩ ይዞታ ምን ይናገራል? በውይይቱ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፣ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሰብአዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበራ ኃይለማርያም ተሳትፈዋል።
ውይይት፤ የአማራ ክልል ምስቅልቅል እና የክልሉ ነዋሪ ሰቆቃ እንዴት ያብቃ? 01.12.2024 41:43
በአማራ ክልል በመካለከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የክልሉን ነዋሪ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጓል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰላማዊ ሰዎችም በግጭቱ የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የመብት ተሟጋቾች የሚያወጧቸው መረጃዎች ያሳያሉ።ያም ሆኖ ይህንን ሰቆቃ ለማስቆም በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የንግግር ፍንጭ አልታየም።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.