DW

እንወያይ

News AM ↓ 100 episodes

በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 5, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

አንድ - ለአንድ፦ ከአቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ጋር 29.11.2024
የኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ ማብቂያ ያገኝ ይሆን ? ተፋላሚዎች ተስፋ ይሰጡት ይሆን ? 24.11.2024
የእንወያይ ፕሮግራም ማስተዋወቂያ 20.11.2024

በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።

Diskussion-Addis Abeba Corridor Development necessary or urgent? 15.11.2024 - MP3-Stereo 15.11.2024

የአዲስ አበባ ችግሮች መፍትሔ እንደሚሹ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትም ይሁኑ ዋና ከተማዋን በጥልቀት ያጠኑ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በከፍተኛ ወጪ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በዚህ ወቅት አስፈላጊ ነው ወይስ አንገብጋቢ? ፒያሳ እና ካዛንቺስን ለመሳሰሉ ነባር ሠፈሮች ነዋሪዎችስ ምን ይዞ መጣ? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ፣ በበርሚንግሐም ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ ልማት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር ኤዛና ሐዲስ እና በፊንላንድ ራምቦል በተባለ ተቋም የከተማ መሠረተ-ልማት የንድፍ (Design) ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ዱጋሳ ተሳትፈዋል።

ዉይይት፣ የትራምፕ ድል፣ መርሐቸዉ፣ የዓለም ሥጋትና ተስፋ 10.11.2024

ኮሚንስታዊ ሥርዓት በአብዛኛዉ ዓለም ከፈራረሰ (እጎአ) ከ1991 ወዲሕ በጦር ኃይል፣በሐብት፣ በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስና ርዳታ ከዓለም ቀዳሚዉን ሥፍራ የምትይዘዉ ዩናይትድ ስቴትስ፣ለአራት ዓመት የምትመራዉ በትራምፕ ይሁንታና ፍቃድ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም ዩናይትድ ስቴትስ ጠላትም ሆነ ወዳጅ የትራምፕን መርሕና ርምጃ ማማተር ግድ አለበት።

በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ለውጥ ወይንስ የፖሊሲ ማሻሻያ? 27.10.2024
የአፍሪቃው ቀንድ ውጥረት 20.10.2024
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአማራ ክልል ይካሄዳል ያሉት «የዘፈቀደ የጅምላ እሥር» 13.10.2024
ለመንግስት ሰራተኞች የታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ምን ያህል ይደጉማል ? 29.09.2024
ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን? 22.09.2024
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያና የግብፅ መዛዛት እንደቀጠለ ነዉ።ከእንግዲሕስ? 15.09.2024
የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል? 08.09.2024

በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት? በውይይቱ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ተሳትፈዋል።

የሰሞኑ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል 01.09.2024
ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው? 17.08.2024
«የኤኮኖሚ ማሻሻያው» የብር አቅም መዳከም ለብዙኀኑ ሕዝብ ምን ማለት ይሆን? 11.08.2024
የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ምን ፋይዳ ይኖረዉ ይሆን? 04.08.2024
ውይይት፦ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል? 28.07.2024

የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ የሚያደርገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር አካል የሆኑ የተለያዩ አዋጆች ባለፉት ወራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቀዋል። ለመሆኑ የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ጫንቃ ላይ ይወድቃል? በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሚና ምንድነው? በዚህ ውይይት የገንዘብ አስተተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ፣ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ እና በዩናይትድ ኪንግደም ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኘው ፔሪቮሊ አፍሪካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪው ዶክተር ኢዮብ ባልቻ ተሳትፈዋል።

እንወያይ፤ የሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ 14.07.2024
የሰላም ዋጋው ስንት ነው? 07.07.2024
እንወያይ፣ የኢትዮጵያዉን ተፈናቃዮች ፈተና፣ የለጋሾች ዳተኝነት 01.07.2024
እንወያይ፤ አሳሳቢዉ በሴቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ 23.06.2024
የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው 14.06.2024
ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ 09.06.2024
ውይይት፦ የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው? 02.06.2024

የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት አስር ዓመታት ገደማ ከሁለት ወደ አርባ ሰባት አድጓል። ባለሙያዎች በተማሪዎች ቁጥር እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ ዕድገት ቢኖርም ውጤቱ ለመንግሥትም ሆነ ለዜጎች አመርቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅትመት ዳይሬክተር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ ተሳትፈዋል።

ከ33 ዓመታት በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ሚና በኢትዮጵያ ፖለቲካ 26.05.2024

Listen to the እንወያይ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.