Abate Tsegaye
ENAB TECH PODCAST
በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ኢናብ ቴክ ክፍል 24 - ዋይ ሚውዚክ የይቲውብ ማዳመጫው 13.12.2022 34:16
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ሜታ የተባለው የፌስቡክ ባለቤት ኩባንያ ሶስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ስለተቀጣበት ጉዳይ፣ በአንድሮይድ ቶክ ባክ ስለተጨመረው አዲስ ነገር እና ማይክሮሶፍት ኤጅም በዊንዶውስ 7 እና 8 ላይ መስራት ሊያቆም ስለመሆኑ ይቀርባል። በሞባይል ወርልድ ዝግጅቴ፣ ዋይ ሚውዚክ ስለተባለው የይቲውብ መጠቀሚያ አንድሮይድ አፕሊኬሽን አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ ማቅረቤን ቀጥዬ ስለሶፍትዌር ምንነት አስረዳለሁ። በርከት ላሉ የአድማጮች ጥያቄም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን...
ኢናብ ቴክ ክፍል 23 - የራዲዮ ሹር አጠቃቀም እና የሲፒዩ ምንነት 04.12.2022 29:15
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አዲስ ስለተለቀቀው የኮመንተሪ ስክሪን ሪደር ቨርዥን፣ ስለአዲስ ቨርዥኑ ጉግል ክሮም 108፣ ማይክሮሶፍት ኤጅ ስለጀመረው የስእመግለጫ አገልግሎት እና በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ባለብዙ ተጠቃሚ ስለሆነው ብራውዘር አወራችኋለሁ። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ካለፈው ክፍል የቀጠለ ሬዲዮ ሹር የተባለውን በኮምፒውተር ሬዲዮ ማዳመጫ አፕሊኬሽን አጠቃቀም አሳያችኋለሁ። በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ ማቅረቤን ቀጥዬ ስለሲፒዩ ምንነት አስረዳለሁ። ለአድማጮች ጥያቄም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 22 - ሬዲዮ ሹር በኢንተርኔት ሬዲዮ ማዳመጫውን ስለማስተካከል 26.11.2022 28:49
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዊንዶውስ 10 22ኤች 2 በጠቅላላ በሰፊው መለቀቁን እና ሊፕ ሰከንድ ስለተባለችው የጊዜ አቆጣጠር ማስተካከያ ስለመደረጉ የሚሉ መረጃዎችን አጋራችኋለሁ። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ሬዲዮ ሹር ስለተባለ በኮምፒውተር ሬዲዮ ማዳመጫ አፕሊኬሽን አስተዋውቃችኋለሁ። ዛሬ በሚጀምረው በመሰረታዊ ዝግጅቴ፣ ስለኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ አቀርባለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod ወይም...
ኢናብ ቴክ ክፍል 21 - ሳፋሪኮም አገልግሎት ተደራሽነት 19.11.2022 33:17
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን ቴሌኮም ወደ ገበያ ልታስገባ ስለመሆኑ፣ ጉግል ክሮም በዊንዶውስ 7 ላይ መስራት ሊያቆም ነው ስለመባሉ፣ ዊንዶውስ ዲፌንደር ያኒንተርኔት ቫይረስ የመለየት ችሎታው ደካማ ነው እና ኢንቴል የፕሮሰሰር ፍጥነት ሪከርድ ስለመስበሩ የሚሉ መረጃዎችን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ስለሆነው ሳፋሪኮም የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽነት አንዳንድ ምልከታዎቼን አቀርብላችኋለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 20 - የፉባር ኮምፖነንቶች 12.11.2022 31:58
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ በኮምፒውተር ላይ ኤንቪዲኤ፣ በስልክ ላይ ጂሺዎ አዲስ ቨርዥን ስለመልቀቃቸው እና ስላካተቷቸው ነገሮች፣ በአውሮፓ የዩኤስቢ ቻርጀር አስገዳጅ የተደረገ ስለመሆኑ፣ በብራዚል ደግሞ አፕል በቻርጀር ምክንያት ለሶስተኛ ጊዜ በፍርድ ቤት በገንዘብ ስለመቀጣቱ እንነግራችኋለን። ስለኮምፒውተር ሶፍትዌር በማስተዋውቅበት የዝግጅቴ ክፍል፣ ፉባር 2000 ማስተዋወቄን ቀጥዬ በዛሬው ዝግጅት በፉባር 2000 ጠቃሚ ሆነው ስላገኘኋቸው ኮምፖነንቶች አስተዋውቃችኋለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 19 - የፉባር ሁለት ሺን ዋና ዋና ሴቲንጎችን ማስተካከል 05.11.2022 34:33
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ በጉግል ላይ የሚያተኩሩ ሆነው፣ ጉግል ስላስተዋወቃቸው ፒክስል ወች፣ ፒክስል 7 እና ፒክስል 7 ፕሮ ስለተሰኙት የእጅ ሰአት እና ስልኮች እንዲሁም ነቫ የተሰኘው የጉግል ሰርች ተፎካካሪ አወራችኋለሁ። ስለኮምፒውተር ሶፍትዌር በማስተዋውቅበት የዝግጅቴ ክፍል፣ ፉባር 2000 ማስተዋወቄን ቀጥዬ በዛሬው ዝግጅት ፉባርን ለመጠቀም ያግዛሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና ሴቲንጎችን እንዴት እንደምናስተካክል እንመለከታለን። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በሆነ ጉዳይ ማብራሪያ ወይም ቱቶሪያል ፈልጌ አጣሁ የምትሉት ካለ ጥያቄውን ላኩት፣ እኔ አዘጋጅቼ አ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 18 - ፉባር ሁለት ሺህ፣ ምቹውን ኦዲዮ ፕሌየር ማስተዋወቅ 29.10.2022 34:36
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አዲስ ስለተለቀቁት ጃውስ 2023 እና ዊንዶውስ 11 22H2 ሞመንት ዋን ስለተባለው እንዲሁም ዊንዶውስ 10 22H2 ይዘዋቸው ስለመጡት ነገሮች ይብራራል። ስለኮምፒውተር ሶፍትዌር በማስተዋውቅበት የዝግጅቴ ክፍል፣ ፉባር ሁለት ሺህ ስለተሰኘው ቀልጣፋ እና ምቹ የኦዲዮ ፕለየር አስተዋውቃችኋለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በሆነ ጉዳይ ማብራሪያ ወይም ቱቶሪያል ፈልጌ አጣሁ የምትሉት ካለ ጥያቄውን ላኩት፣ እኔ አዘጋጅቼ አቀርብላችኋለሁ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልት...
ኢናብ ቴክ ክፍል 17 - በሚክስፕሎረር ፋይሎችክ ከስልክ ወደ ስልክ፣ ከስልክ ወደ ፒሲ እና ክላውድ ሰርቪሶችን አጠቃቀም 22.10.2022
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አዲስ ስለተለቀቁት ኤንቪዲኤ 2022.3.1 እና ጂሺዎ 2022-10-15 ይዘዋቸው ስለመጡት ነገሮች ይብራራል። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በሚክስፕሎረር ክፍል ሁለት ፋይሎችን ከስልክ ወደስልክ፣ ከስልክ ወደ ፒሲ፣ ከፒሲ ወደ ስልክ እንዲሁም የስልካችንን ስቶሬጅ በነጻ በክላውድ አማካይነት እንዴት ማሳደግ እንደምንችል እና የክላውድ ሰርቪሶችን እንዴት እንደምንጠቀም በተግባር አቀርባለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በሆነ ጉዳይ ማብራሪያ ወይም ቱቶሪያል ፈልጌ አጣሁ የምትሉት ካለ ጥያቄውን ላኩት፣ እኔ አዘጋጅቼ አቀርብላችኋለሁ። ጥያቄ፣ አ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 16 - ሚክስፕሎረር፣ የአንድሮይድ ፋይል ማደራጃው 15.10.2022 32:53
ፖድካስቱ የሚያተኩርባቸው፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የጃውስ ቨርዥን 2023 ፐብሊክ ቤታ 2 ስለመለቀቁ፣ ጂሺዎ ቨርዥን 2022-10-01 ይዟቸው ስለመጣው ነገሮች፣ በምስል የሚታዩትን ቁጥር ጻፉ ለሚለው የተደራሽነት ችግር መፍትሄ ይዞ ስለመጣ አንድ ድርጅት እና ቴሌግራ የፕሪሚየም አገልግሎቱን በህንድ አገር ቅናሽ ስለማድረጉ ይተነተናሉ። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ ሚክስፕሎረር ስለተባለው በአንድሮይድ ስልክ ላይ ፋይሎችን እንደልባችን እንድናበጃጅ ስለሚያስችለው አፕሊኬሽን አስተዋውቃችኋለሁ። ከአድማጭ ለተነሳ ጥያቄ ምላሽ የሰጠሁበት ዝግጅትም ተካቷል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 15 - ኤንቪዲኤ ፕሮፋይልስ 08.10.2022 29:00
በፖድካስቱ የሚተነተኑ ጉዳዮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ ቨርዥን 2022.3 ስለመለቀቁ እና ስላካተታቸው ነገሮች፣ አፕል አይፎን 14 እና ሌሎች መሳሪያዎች ለገበያ ስለማቅረቡ፣ ጉግል አንድሮይድ 13ን ስለመልቀቁ እና ለአንድሮይድ 13ስለሚያስፈልገው አነስተኛ ይዘት ምን እንደሆኑ፣ ዲሞክራሲያዊ ነው የሚባለው የህንድ መንግስት ቪኤልሲ ሚዲያ ፕሌየር የተባለውን አፕሊኬሽን ዜጎቹ እንዳያወርዱ ብሎክ ስለማድረጉ እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለኤንቪዲኤ ፕሮፋይልስ አስተዋውቃችኋለሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ኤንቪዲኤን ከዚህ፣ ያውርዱ። This podcast is powered by Pinecast .
ኢናብ ቴክ ክፍል 14 - የጂሺዎ መጨረሻ ክፍል፣ አድቫንስድ ሴቲንግስ እና ጂሺዎ ፈንክሽን ሜኑ 01.10.2022 33:46
በፖድካስቱ የሚዳሰሱ፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ ቨርዥን 2022.2.4 ስለመለቀቁ፣ አንድ የብራዚል ዳኛ አፕል ከአይፎን ስልክ ጋር የቻርጀር ገመድ ባለማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲከፍል ስለማዘዙ፣ ጉግል በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የስልክ ጥሪ መቅረጫ አፕሊኬሽኖች እንዳይጫኑ ክልከላ ስለማድረጉ፣ የሚሉት ጉዳዮች ይቀርባሉ። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ የጂሺዎ መጨረሻ ክፍል፤ በአድቫንስድ ሴቲንግስ ስር የሚገኙ ዝርዝሮችን የምንመለከት ሲሆን ከነሱም ውስጥ፦ ጂሺዎ ባትሪ እንዳይጨርስ እንዴት ማድረግ እንደምንችል፣ የጂሺዎን ሜኑ እንዴት እንደምናስተካክል፣ የጂሺዎን ሴቲንጎች እንዴት ሴቭ እንደምናደርግ እና ሌሎችን፣ በፈንክሽን ሜኑ ስ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 13 - የጂሺዎ ኦፐሬሽን ልዩ ልዩ፣ የሪዲንግ፣ የኖቲፊኬሽን እና የድምጽ ረዳት ቅብሮች 24.09.2022 35:30
በፖድካስቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎቼ፣ የዊንዶውስ 11 ማሻሻያ ቨርዥን 22H2 ማይክሮሶፍት ስለመልቀቁ፣ ስለኤንቪዲኤ አነስተኛ ማሻሻያ ቨርዥን 22.2.3 እና ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ከዚች አለም ድካም ስለማረፉ እነግራችኋለሁ።። ሞባይል ወርልድ! በተሰኘው የዝግጅቴ ክፍል፣ በጂሺዎ ስልካችንን በመነቅነቅ ብቻ የፈለግነውን ነገር ማዘዝ እንዴት እንደምንችል፣ ስለኦፐሬሽን ልዩ ልዩ ቅንብሮች፣ ስለሪዲንግ፣ ስለኖቲፊኬሽን ቅንብሮች እና በጂሺዎ አማካይነት የማናውቀው ቋንቋ ጽሁፍ ሲያጋጥመን እንዴት ወደምናውቀው ቋንቋ አስተርጉመን መጠቀም እንደምንችል አብራራለሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ኤንቪዲኤን ከዚህ፣ ጂሺዎን ከዚህ ያውር...
ኢናብ ቴክ ክፍል 12 - የጂሺዎ ናቪጌሽን፣ ኤጅ ጀስቸር፣ ሾርት ከት እና ሆት ኪ ስኪም ሴቲንግስ 17.09.2022 32:33
ፖድካስቱ የሚመለከተው፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ 2022.3 እና ጃውስ 2023 ሊለቀቁ ስለመቃረቡ እንዲሁም ስለቴሌግራም ፕሪሚየም አንዳንድ ነገሮችን አነሳለሁ። በስማርት ፎን ስልኮች ላይ በሚያተኩረው ዝግጅቴ ስለጂሺዎ የማቀርበው ማብራሪያ ክፍል ውስጥ፣ ስለ ናቪጌሽን፣ ስለኤጅ ጀስቸር፣ ስለሾርት ከት ሴቲንግስ እና ስለሆትኪ ስኪም ሴቲንግስ መግለጫ አቀርባለሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ኤንቪዲኤን ከዚህ፣ ጂሺዎን ከዚህ ያውርዱ። This podcast is powered by Pinecast .
ኢናብ ቴክ ክፍል 11 - ጂሺዎን በኤንቪዲኤ ድምጽ ስለማናገር፣ ቀሪ ቲቲኤስ ሴቲንጎች፣ ፊድባክ እና የኦፐሬሽን ሴቲንጎች 10.09.2022 31:35
በፖድካስት ክፍሉ የቀረቡ በቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎች ኤንቪዲኤ ለደህንነት ማሻሻያ ስለለቀቃቸው አነስተኛ ክለሳዎች፣ በዊንዶውስ 11 ፕሮ ጭምር የማይክሮሶፍት አካውንት አስገዳጅ ስለመደረጉ፣ የአንድሮይድ አፕሊኬሽንን በዊንዶውስ 11 ላይ ለመጫን ስለሚያስፈልጉ ነገሮች እና ስለየመጨረሻው የአይኦኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እነግራችኋለሁ። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት ስለጂሺዎ በቀጠለው ማብራሪያ የጂሺዎን ኢስፒክ ድምጽ እንዴት እንደምናስተካክል፣ ስለቀሪ የቲቲኤስ ሴቲንጎች፣ ስለፊድባክ እና ስለኦፐሬሽን ሴቲግ ማብራሪያ ይዤ ቀርቤያለሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ኤንቪዲኤን ከዚህ፣ ጂሺዎን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ክፍል 10 - ጂሺዎ ጀነራል ሴቲንግስ፣ ጄስቸርስ እና ቲቲኤስ 03.09.2022 33:54
በፖድካስት ክፍሉ የማተኩርባቸው በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎቼ ጃውስ 2022 በሚያዚያ፣ ሰኔ እና ሀምሌ ማሻሻያዎቹ ስለጨመራቸው ነገሮች፤ ፌስቡክ በ18 አመት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላጋጠመው ችግር እነግራችኋለሁ። የዛሬ ዋናው ዝግጅት ሞባይል ወርልድ ሲሆን በስሩም ካለፈው የቀጠለው ጂሺዎ የተባለውን ስክሪን ሪደርን ማስተዋወቄን ቀጥዬ ሴቲንግስ ውስጥ እንዴት እንደሚገባ፣ ስለጀነራል ሴቲንግስ፣ ስለጂሺዎ ጀስቸርስ እና ቲቲኤስ እንዴት እንደምናስተካክል አብራራለሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ጃውስን ከዚህ፣ ጂሺዎን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ፖድካስት መጀመሩን ለማስታወቅ 27.08.2022 3:01
Episode Notes ኢናብ ቴክ ፖድካስት እንደገና መጀመሩን የሚያበስር ቀረጻ ነው።
ኢናብ ቴክ ክፍል 9 - ጂሺዎን ማስተዋወቅ 27.08.2022 29:11
ክፍል ዘጠኝ _ ጂሺዎ አዲሱ እና ፈጣኑ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር በቴክኖሎጂ ዜናዎቻችን፣ በኤንቪዲኤ 2022.1 እና በ2022.2 ስለተጨመሩ አዳዲስ ነገሮች፣ ማይክሮሶፍት ኤጅ ሰዎች ጉግል ክሮምን እንዳያወርዱ መለመን ስለመጀመሩ፣ ዊንዶውስ ዲፌንደር የአመቱ ምርጥ አንቲ ቫይረስ ስለመባሉ እና ሌሎችም ቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎች እንነግራችኋለን። የሞባይል አፕሊኬሽን በምናስተዋውቅበት የዝግጅት ክፍላችን ጂሺዎ ስለተባለው እና በቅርቡ መጥቶ ከነባሩ ቶክባክ የተሻለ አገልግሎት ስለሚሰጠው የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የማስተዋወቂያ ክፍል እናቀርባለን። በፖድካስቱ የተጠቀሰውን ጂሺዎን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ክፍል 8 - ቡክወርም 09.04.2022 29:25
ክፍል ስምንት _ በቡክወርም መጽሀፍትን ማንበብ፣ ተደራሽ ያልሆኑ የአማርኛ ጽሁፎችን ጨምሮ በቴክኖሎጂ ዜናዎቻችን፣ ቲክቶክ የተሰኘው የሞባይል ቪዲዮ መመልከቻ አፕሊኬሽን ከነጉግል ስለመብለጡ፣ አፕል ኩባንያ ወደ ገበያ ስላወጣው አዲስ ስልክ፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዚደንት ስላስጀመሩት አዲስ የማህበራዊ መገናኛ እና ሌሎችም ቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ቡክወርም ስለተሰኘ የዲጂታል መጽሀፍትን በስክሪን ሪደር አማካይነት ለማንበብ የሚያስችል እና ሂደቱን የሚያቀል ሶፍትዌር የተወሰነ ማብራሪያ እናቀርባለን። በተለይ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች አማርኛ ጽሑፍን ከስካንድ ዶኪውመንትስ ለማንበብ ማስቻሉ ለ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 7 - በሪፐር ኦዲዮን ማርተእ፣ መቅረጽ እና ድምጽ መለወጫዎችን መጨመር 02.04.2022 29:43
ክፍል ሰባት _ በሪፐር ድምጽን ማርተእ፣ መቅረጽ እና ድምጽ መለወጫዎችን መጨመር በቴክኖሎጂ ዜናዎች፣ ኔትፍሊክስ የተሰኘው በኦንላይን አዳዲስ ፊልሞችን በማሳየት የሚታወቀው ኩባንያ በደቡብ ኮርያ ያሰራጨው ፊልም የአንዲት ግለሰብን ስልክ ቁጥር በማካተቱ በግለሰቧ ላይ ስለተፈጠረው ችግር፣ የኢትዮጵያ ኮሚውኒኬሽን ባለስልጣን ለ3ኛው የቴሌኮም ኩባንያ ፈቃድ ጨረታ ሊያወጣ ስለመሆኑ እና ሌሎች ዜናዎችን አካተን አቅርበናል። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ስለሪፐር አጠቃቀም የመጨረሻ ክፍል ድምጽን እንዴት መሰረዝ እና ማስተካከል እንደሚቻል፣ ድምጽን እንዴት እንደምንቀርጽ እንዲሁም የጨረስነውን ስራ እንዴት ወደተለመዱት የሙዚቃ ፋይሎች እ...
ኢናብ ቴክ ክፍል 6 - የሪፐር መሰረታዊ ሴቲንጎች ማስተካከል እና ድምጽን ማስገባት 26.03.2022 30:48
ክፍል ስድስት _ የሪፐር መሰረታዊ ሴቲንጎች ማስተካከል እና ድምጽን ማስገባት በዜና ጊዜ፣ በኤንቪዲኤ 2021.3 ስለተጨመሩ አዳዲስ ነገሮች፣ በደቡብ ኮርያ ለህጻናት ተከልክሎ የነበረው የኦንላይን ጨዋታዎች ገደብ መነሳቱ እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ወሬዎችን አወራችኋለሁ። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ከቀድሞው ኤፒሶድ የቀጠለ የሪፐርን መሰረታዊ ሴቲንጎች እንዴት እንደምናስተካክል እና ድምጽ ወደ ሪፐር እንዴት እንደምናስገባ እንመለከታለን። በፖድካስቱ ከተጠቀሱት ሪፐር ቨርዥን 6.52ን ከዚህ ያውርዱ። ኤንቪዲኤ ቨርዥን 2021.3.5ን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ክፍል 5 - ሪፐርን ማስተዋወቅ እና አጫጫኑ 19.03.2022 30:22
ክፍል አምስት፣ ሪፐርን ማስታወቅና አጫጫኑ በዜና ጊዜ፣ ቴሌግራም በአንድ ቀን ብዙ ተጠቃሚዎችን በመመዝገብ ሪከርድ መስበሩን እና በጃውስ 2022 ስለተጨመሩ አዳዲስ ነገሮች እናወራችኋለን። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ሪፐር ስለተባለው አፕሊኬሽን ማስተዋወቂያ እና ስለአጫጫኑ መግለጫ ይቀርባል። በፖድካስቱ ከተጠቀሱት ሪፐር ቨርዥን 6.11ን ከዚህ ያውርዱ። ሪፐር ቨርዥን 6.51ን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ክፍል 4 - ኤምፒ3 ዳይሬክትን በመጠቀም ከብዙ ትራኮች ማስታወቂያ በአንድ ጊዜ ቆርጦ ማውጣት 19.10.2021 29:28
ክፍል አራት፣ በኤምፒ3 ዳይሬክት ከት ከብዙ ትራኮች በአንድ ጊዜ ማስታወቂያዎችን መቁረጥ በዜና ጊዜ፣ ቢንግ በተሰኘው ሰርች ኢንጅን ጉግል አንደኛ ደረጃ ተፈላጊ ቃል ስለመሆኑ፣ በአውሮፓ ዩኤስቢ ሲ የተባለው ቻርጀር አስገዳጅ ይደረጋል መባሉ፣ በአመቱ መጀመሪያ አፕል ወደ ገበያ ስላወጣቸው አራቱ የአይፎን አይነቶች፣ ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2021 የሚባል ቨርዥን ስለመልቀቁ እና ሌሎች ቴክኖሎጂ ነክ ወሬዎችን እናወራችኋለን። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ኤምፒ3 ዳይሬክት ከት የተባለውን ሶፍትዌር በመጠቀም ከብዙ ትራኮች በአንድ ጊዜ ማስታወቂያዎችን ቆርጠን እንደምናስወግድ እና ለግላችን ለስልክ ጥሪም ሆነ ለሌላ ምክንያት የምንፈልገው...
ኢናብ ቴክ ክፍል 3 - በአንድ ፋይል ከሆነ አልበም ውስጥ ትራኮችን ማውጣት 18.10.2021 30:04
በኤምፒ3 ዳይሬክት ከት ትራኮችን ከአልበም ማውጣት በዚህ ክፍል፣ በዜና ጊዜ፣ ዊንዶውስ 11 ክልከላ ላደረገባቸው ኮምፒውተሮች አፕዴት እየለቀቀ ስለመሆኑ፤ ቲክቶክ የተባለው የቪዲዮ መመልከቻ አፕ ታዋቂውን ዩቱብን እየበለጠው ስለመሆኑ እናወራችኋለን። በኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍል ደግሞ ኤምፒ3 ዳይሬክት ከት የተባለውን ሶፍትዌር በመጠቀም እንዴት አድርገን አንድ ፋይል ከሆነ አልበም ትራኮችን ነጣጥለን እንደምናወጣ በተግባር እናሳያለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ከአባከስ ቀጥሎ ስለመጡት የኮምፒውተር ቀዳሚዎች እንተርካለን። በፖድካስቱ ከተጠቀሱት ኤምፒ3 ዳይሬክት ከትን ከዚህ ያውርዱ። የኤንቪዲኤ ኤምፒ3 ዳይሬክት አድ ኦንን ከዚህ ያውርዱ።
ኢናብ ቴክ ክፍል 2 - የጃውስ አጫጫን እና ክራክ አደራረግ 09.10.2021 30:55
በክፍል 2 ኢናብ ቴክ ፖድካስት፣ በዜና ጊዜ በጃውስ 2021 የተጨመሩ አዳዲስ ነገሮችን እንነግራችኋለን። አዲስ ስለተለቀቀው ዊንዶውስ 11 የተባሉ ነገሮችን አካተናል። በኮምፒውተር ክፍል ደግሞ ስለጃውስ አጫጫን እና ክራክ አደራረግ አጠር መጠን ያለች ማሳያ አቅርበናል። በመጨረሻም፣ የኮምፒውተርን አመጣጥ ታሪክ መተረክ ጀምረናል። ጃውስን ለመጫን የሚያስፈልጉ ፋይሎችን ከሚከተሉት ሊንኮች ያውርዱ። ጃውስ 32 ቢት ኢንስቶለር ጃውስ 32 ቢት ክራክ ጃውስ 64 ቢት ኢንስቶለር ጃውስ 64 ቢት ክራክ
ኢናብ ቴክ ክፍል 1 - ኤንቪዲኤን መጫን እና ሴቲንጎቹን ማስተካከል 01.10.2021 29:44
በኢናብ ቴክ ፖድካስት ክፍል አንድ፣ በኤንቪዲኤ ክለሳ ወይም ቨርዥን 2021.1 እና ቨርዥን 2021.2 የተጨመሩ ነገሮችን እንዲሁም በ17 ደቂቃ ውስጥ 100% ቻርጅ ስለሚያደርገው ስልክ ዜናዎች የተነገሩ ሲሆን የኤንቪዲኤ አጫጫን እና ወሳኝ የሆኑ ሴቲንጎችን እንዴት እንደምናስተካክል በተግባር የምናሰማበት ክፍል አለው። በመጨረሻም በሞባይላችን ከሙዚቃ ውስጥ የማንፈልገውን ክፍል እንዴት አድርገን ቆርጠን እንደምናወጣ እና የምንፈልገው አጭር ክፍል ለምሳሌ ለስልክ ጥሪ፣ እንዴት አድርገን ቆርጠን እንደምናዘጋጅ የሚያሳይ ዝግጅትም አለበት። በዝግጅቱ የተጠቀሱትን ማለትም ኤንቪዲኤን ከዚህ ያውርዱ። የaudio vidio manager የተባለው...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.