SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

"ኢትዮጵያውያንም ማንኛውም ጥቁር የሚደርስበት ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ጥቁር አይደለሁም የሚል አስተሳሰብ ካለ ይህ የንቃት ጉድለት ነው፤ ያሳስባል" ዶ/ር ተበጀ ሞላ 19.11.2025

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አክሎ በፍልሰተኞች ዘንድ ያሉ የማንነት አተያዮችን ያጋራሉ።

"ዘረኝነት ቴክኖሎጂ እያገዘው እየሰፋ የሔደበት ጊዜ ላይ ስለምንገኝ በተለይ ኢትዮጵያውያንን ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው" ዶ/ር ይርጋ ገላው 19.11.2025

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ አውስትራሊያ ውስጥ በተለይም ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ከማንነት ጉዳዮችን ጋር ተያይዘው ገጥመዋቸው ስላሉ ማኅበራዊ እንከኖች አንስተው ያስረዳሉ።

የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ከሕግ ውጪ የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ ምጣኔ ሃብታዊ ውድቀትና የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ በአስቸኳይ እንዲገታ ጥሪ አቀረበ 19.11.2025

የተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊ ድጋፋቸውን ለነፈጓቸው የምክር ቤት አባል ምፀታዊ ውዳሴ አቀረቡ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በቦታው ሆኖ መመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪ ወደ አካባቢው መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ 19.11.2025

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 'የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሙስሊሙ መሪ ተቋም ጋር ሳይወያይ የሙስሊም ተማሪዎች በግዳጅ የግዕዝ ቋንቋ እንዲማሩ ውሳኔ ማሳለፉ ተቀባይነት የለውም' አለ

ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁሶች ከአውስትራሊያ ወደ ድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል እያመሩ ነው 18.11.2025

በሜልበርን አውስትራሊያ የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጃማ ፋራህ፤ የድሬዳዋን መርጃና መደጎሚያ ማኅበር በአውስትራሊያ ተጠሪዎች፤ አቶ ሳምሶን ከበደና አቶ ዳዊት ከበደ ስለምን ለድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁሶችን ለመላክ እንደተነሳሱ ይናገራሉ።

የጤና ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ ከተማ ተከሰተ የተባለው አዲሱ በሽታ ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ማርበርግ ቫይረስ እንደሆነ አስታወቀ 17.11.2025

'ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግሥት በሉዓሏዊነቷና የግዛት አንድነቷ ላይ በሚፈፅማቸው ጥሰቶች ላይ ስትከተል የቆየችው እርምጃ ከመውሰድ የመታቀብ አካሔድ ሁሌም የሚቀጥልና ገደብ የለሽ ተደርጎ መወሰድ የለበትም' አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ

#99 Saying ‘No’ to alcohol - #99 አልኮልን ‘እምቢኝ’ ማለት 13.11.2025

Learn polite ways to refuse a drink in English. Discover useful expressions for taking it slow, sitting one out or explaining you're on a permanent dry spell. - ትህትና በተመላው መልኩ በእንግሊዝኛ መጠጥን እምቢ ማለትን ይማሩ። እያዘገምኩ፣ እቆያለሁ ወይም አልኮል ዳር ሳልደርስ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል ዓይነት ጠቃሚ አባባሎችን ይግለጡ።

በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ፍጆታዎች ዋጋ መናሩን ነዋሪዎች ተናገሩ 12.11.2025

ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ በ2027 አዲስ አበባ ላይ ለማስተናገድ ይሁንታን አገኘች

ተስፋ የራዲዮ ድራማ፤ ሕይወትና ሞት - ነፃነትና ፅልመት 11.11.2025

ተስፋ የራዲዮ ድራማ፤ ድርሰት በሱራፌል ወንድሙ - ተዋናዮች ተስፋዬ ገብረሃና፣ ጌታሁን ሰለሞን እና ዐቢይ አየለ - ድምፅ ቀረፃና ቅንብር SBS

ቲክቶክ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ 2017 ከ2.1 ሚሊዮን በላይ በኢትዮጵያውያን የተለቀቁ ቪዲዮዎችን 'በአደገኛነት' ፈርጆ ለዕይታ እንዳይበቁ ማድረጉን አስታወቀ 09.11.2025

የአፍሪካ ሕብረት፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ 'የናይጄሪያ መንግሥት በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ግድያ እጁ አለበት' በማለት በሀገሪቱ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ መዛታቸው ያሳሰበው መሆኑን አስታወቀ።

የቀድሞው የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሣና ቤተሰቦቻቸው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ 04.11.2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሩብ ዓመት ክንውኑ በትግራይና አማራ ክልሎች ከ20 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማስቻሉን አስታወቀ

"ትልቁ ነገር ባለ ትልቅ ቤት መሆኑ ሳይሆን፤ ከልጆቻችን ጋር ያለን ትልቅ ግንኙነት ነው፤ በተለይ አባቶች። ለእናቶች ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ" ዶ/ር ብርሃን አሕመድ 04.11.2025

ዶ/ር ብርሃን አሕመድ፤ የAfricause ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ አፍሪካውያን አውስትራሊያውያን ልጆቻቸውን ለመታደግና እየናረ ላለው ፍቺ ብልሃት ለማበጀት ማለፊያ ቤተሰባዊ ትስስሮሽ ስለሚኖረው ሚና ይናገራሉ።

"እኛ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ሶማሌ እንላለን፤ ልጆቻችን የሚኖሩት እንደ አፍሪካዊ ነው። በእነሱ ጭንቅላት ማሰብ ግድ ይሆናል" ዶ/ር ብርሃን አሕመድ 04.11.2025

ዶ/ር ብርሃን አሕመድ፤ የAfriCause ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ የድርጅታቸውን ተልዕኮና ሚና፣ አፍሪካውያን - አውስትራሊያውን አውስትራሊያ ውስጥ ገጥሟቸው ስላሉ አንኳር ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን ነቅሰው ያመላክታሉ።

ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ የሚሰጥበት ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ጥሪ ቀረበ 02.11.2025

በሶማሌ ክልል ማረሚያ ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች፤ በታሳሪዎችና ተጠርጣሪዎች ላይ ይፈፀሙ የነበሩ ድብደባዎችና የማሰቃየት ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እንዳስየ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጠ

"ይቅርታ ይደረግልኝና የኢትዮጵያ ፊልም ከአዳራሽና ሬስቶራንት በባሕል ማዕከል ወይም ሲኒማ ቤት ቢታይ ሲኒማችን ክብር ይኖረዋል" ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ 30.10.2025

ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ፤ ለ10ኛ ዓመት የበቃው የHabeshaview ተባባሪ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ስለ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ዕድገትና ሂደት አተያያቸውን ያጋራሉ።

"ከኔትፊሊክስ ጋር ያለን ችግር 'የኢትዮጵያን ፊልም ከፍሎ የሚያየው ማነው?'ነው፤ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ፊልም አክብረን፤እየከፈልን ማየት ይኖርብናል"ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ 30.10.2025

ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ፤ ለ10ኛ ዓመት የበቃው የHabeshaview ተባባሪ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ድርጅታቸው እያበረከተ ያለውን ሚናና ዋነኛ ተልዕኮውን ነቅሰው ያስረዳሉ።

#98 Splitting the bill (Med) - #98 Splitting the bill (Med) 29.10.2025

Learn how to split the bill in English. Discover useful expressions for sharing costs, shouting rounds, and transferring your share easily. - Learn how to split the bill in English. Discover useful expressions for sharing costs, shouting rounds, and transferring your share easily.

"ግጥም በጃዝን በየሶስት ወራቱ ወደ ተለያዩ የአውስትራሊያ ዋና ዋና ከተሞች እየተዘዋወርን እናሳያለን" ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን 29.10.2025

ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን፣ እሑድ ጥቅምት 30 / ኖቬምበር 9 በKindred Studio, 3 Harris St, Yarraville በሜልበርን ለተመልካቾች ስለሚቀርበው "ግጥም በጃዝ" ልዩ ዝግጅት ፕሮግራም ይገልጣል።

ግጥም በጃዝ በሜልበርን አውስትራሊያ ዳግም መድረክ ላይ ሊያዋዛ ነው 28.10.2025

ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን፣ ጥቅምት 30 / ኖቬምበር 9 ተቋርጦ ከርሞ ዳግም በሜልበርን ከተማ ለመድረክ ስለሚበቃው "ግጥምን በጃዝ" ልዩ ዝግጅት አስመልክቶ ይናገራል።

"ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ድርሰትን ለድርሰት ብለው ነው የጀመሩት፤ የኢትዮጵያ ደራሲያን ግን ድርሰትን ለሀገር የችግር መፍቻ ብለው ስለሆነ ልዩ ያደርጋቸዋል"ደራሲ ጌታቸው በለጠ 28.10.2025

ምልሰታዊ ምልከታ፤ ደራሲ ጌታቸው በለጠ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር (ኢደማ) ፕሬዚደንት፤ ስለ ኢደማ ምሥረታ፣ ተልዕኮና ሚና ይናገራሉ።

ምልሰታዊ ምልከታ "የወታደር ክፉ የለውም፤ የመሪ ክፉ ነው ያለው" ሻለቃ ቦጋለ ንጋቱ 27.10.2025

ደራሲ ሻለቃ ቦጋለ ንጋቱ፤ ስለ "ትውልድ ያናወጠ ጦርነት" መፅሐፋቸው ተልዕኮና ታሪካዊ ፋይዳ አንስተው ይናገራሉ።

አውስትራሊያና ጃፓን ነፃ የኢንዶ - ፓስፊክ ቀጣና ስትራቴጂያዊ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ 27.10.2025

በእሥራኤል እገዛ የሐማስ አሳሽ ቡድን የታጋች አስከሬኖች ፍለጋውን አስፍቶ ቀጥሏል

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያውን ፕሬዚደንት ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት በሁለት የሩስያ ነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣሉ 23.10.2025

በመጪው ዓመት 2026 በይፋ የሚመረቀው አዲሱ የምዕራብ ሲድኒ አውሮፕላን ማረፊያ በዛሬው ዕለት የቅድመ ምረቃ በረራዎችን አካሔደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠልም፤ መጠቅለልም አይሠራም። ኢትዮጵያ ትውልድ ተቀባብሎ የሚያፀናት ሀገር ትሆናለች" አሉ 22.10.2025

በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ፍልሰት መጨመሩ ተነገረ

"ጠለፋና ደፈራን ለመከላከል በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ በየደረጃው የሥነ ፆታ ትምህርት ቢሰጥ ጥሩ ነው እላለሁ" ደራሲና የፊልም አዘጋጅ ሔለን እሸቱ 21.10.2025

የ 'ምሰሶዋ' መፅሐፍ ደራሲና 'ጀቢና' ፊልም አዘጋጅ ሔለን እሸቱ፤ በልጅነት ጋብቻ፣ የቤት ውስጥ ጥቃትና የሴት ልጅ ደፈራ ተኮርና የእራሷ እውነተኛ የሕይወት ታሪክ ምንጭ ስለሆነው ፊልሟ ታስረዳለች።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.