SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
"ጥምቀት ከፍተኛ የሆነ ምስጢር ያለው፣ የስላሴ ሶስትነት፣ አንድነት የተገለፀበት፤ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የተወለደበት ሙሉ የሆነበት ነው" ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሉ 22.01.2026 20:14
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊው በዓለ ጥምቀት በሀገረ አውስትራሊያ - ብሪስበን ከተማ በ Oxley Creek Common ከጃኑዋሪ 24 - 25 / ጥር 16 - 17 ተከብሮ ይውላል። ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ እንዲሁም አቶ ወርቅነህ ባየህ፤ በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስለ በዓሉ መሰናዶ፣ መርሃግብርና የበዓለ ጥምቀትን ተምሳሌነትና ፋይዳዎች ያስረዳሉ።
የፀረ ጥላቻ ንግግርና የጠብመንጃ ባለቤትነት ሕጎች በፓርላማ ይሁንታ ተቸራቸው 21.01.2026 5:29
ኩዊንስላንድ ውስጥ ሕይወቷ አልፎ የተገኘችው ካናዳዊት ቱሪስት ምናልባትም በዲንጎ ተጠቅታ ይሆናል የሚል ስጋት አሳድሯል
ግብፅ ኢትዮጵያ ካሣ ትክፈለኝ አለች 21.01.2026 8:51
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ገንዘብ ሚኒስቴር 'ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አራተኛውን ዙር የኢትዮጵያ የብድር ግምገማ ሰሞኑን ማፅደቁ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ቀደም ሲል ከተጠበቀው በላይ ጠንካራ መሆኑን ያረጋግጣል' አሉ
"ግጥምን በጃዝ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ዒላማ 'ለሰዎች የመዝናኛ መድረክ መክፈት፤ ባሕልን፣ የሀገር ፍቅርንና ዕሴትን ማስተዋወቅ ነው" ተዋናይ ጌታሁን ሰለሞን 20.01.2026 20:14
መታሰቢያነቱ ለሰዓሊ ታምራት ገብረማሪያም የተቸረውና ለሁለተኛ ጊዜ የተከወነው 'ግጥምን በጃዝ' የአንድ ሰው ተውኔትን አጣምሮ በዕለተ እሑድ ጃኑዋሪ 18 / ጥር 10 ለሕዝብ ቀርቧል። የመድረክ መሪዎች፣ ገጣሚዎችና የሙዚቃ መሳሪያ ባለሙያዎች አተያያቸውን አጋርተዋል። ለቀጣዩ ዝግጅት ኢትዮጵያውያን በነቂስ እንታደሙ የግብዣ ጥሪያቸውን በጥበብ አንደበት አቅርበዋል።
"የጥምቀትን የተለያዩ የሃይማኖት ሥርዓቶችንና የሕዝቡን ደስታ ስመለከት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያለሁ ነው የመሰለኝ" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ 20.01.2026 25:41
የከተራና ጥምቀት በዓል በሀገረ አውስትራሊያ የሜልበርንና ፐርዝ ከተሞች ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ደምቆና ገንኖ ተከብሮ ውሏል። በዓለ ጥምቀቱን በጋራ የአንድነት መንፈስ ያከበሩት ቤተክርስቲያናት፣ ምዕመናንና ምዕመናት የእምነትና ሀገራዊ አንድነትን አንፀባርቀዋል። የሃይማኖት አባቶችና ታዳሚዎች አተያያቸውን አጋርተውናል።
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የፍልሰት ቪዛ ከማያገኙት 75 ሀገራት መካከል አንዷ ሆነች 19.01.2026 10:31
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ጉባኤ ላይ ከአራት ሺህ በላይ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተባለ
"በጥራት ስለምንጨርስ ከደንበኞች ጋር ጥሩ ወዳጅነት አለን፤ እምነት ይጥሉብናል" ዳይሬክተር ጀማል አይዲን 15.01.2026 12:56
አቶ ጀማል አይዲን፤ የGo Cabinets & Home Renovation ዳይሬክተር፤ እንደምን ወደ ግንባታና ዕድሳት ሙያ እንደተሠማሩና ለሜልበርን የምሥራቅ አፍሪካና የሕንድ ማኅበረሰብ አባላት ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር እየሰጡ ስላሉት ሙያዊ አገልግሎታቸው ይናገራሉ።
ጀማል አይዲን፤ የቤት ግንባታና የቤት ውስጥ ዕድሳት 15.01.2026 13:08
አቶ ጀማል አይዲን፤ የGo Cabinets & Home Renovation ዳይሬክተር፤ እንደምን ወደ ግንባታና ዕድሳት ሙያ እንደተሠማሩና ለሜልበርን የምሥራቅ አፍሪካና የሕንድ ማኅበረሰብ አባላት ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር እየሰጡ ስላሉት ሙያዊ አገልግሎታቸው ይናገራሉ።
ኢራን በአንድ ተቃዋሚ ሠልፈኛ ላይ ይሙት በቃ ፈረደች 14.01.2026 2:41
በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረሱ ዛቻዎች በ63 ፐርሰንት ማሻቀቡ ተመለከተ
በአዲስ አበባ ቅሬታ ካሰሙ ግብር ከፋዮች መካከል የ58 በመቶዎቹ ቅሬታ ትክክል ሆኖ እንዳገኘው የከተማይቱ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ 14.01.2026 8:21
'በአማራ ክልል አዲሱ የገጠር መሬትና አስተዳደር አጠቃቀም አዋጅ በተበታተነ መንገድ የሚኖሩ የክልሉን አርሶ አደሮች በፈቃደኝነት በአንድ አካባቢ ለማስፈር ያለመ ነው' ሲል የክልሉ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ገለጠ
"የSBS አማርኛ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሆኜ መሥራቴ በጣም ነው የሚያስደስተኝ" ፎቶ አንሺ ስንታየሁ በቀለ 13.01.2026 16:06
የፎቶግራፍ ባለሙያ ስንታየሁ በቀለ፤ ስለ ፕሮፌሽናል የፎቶ ባለሙያነትና ከሞባይል ይልቅ የግል የፎቶ ካሜራን የመጠቀምን ተመራጭነት አንስቶ ምክረ ሃሳቡን ይቸራል።
"በሕይወት ያሉትንና የሌሉትን አስታዋሽና ጊዜን ገላጭ ሆኖ የሚቀረው ፎቶግራፍ ነው" ፎቶ አንሺ ስንታየሁ በቀለ 13.01.2026 16:47
የፎቶግራፍ ባለሙያ ስንታየሁ በቀለ፤ እንደምን ከግራፊክ ዲዛይን ወደ ፎቶ ማንሳት እንደተሸጋገረ ይናገራል።
"ምግብ አቅርቤ ባዶ ሳህን ሲመለስልኝ ደስ ይለኛል" ወ/ሮ ገነት ሐብተወልድ 12.01.2026 25:42
የሐረር መሶብ ምግብ ቤት ባለቤቶች፤ ወ/ሮ ገነት ሐብተወልድና አቶ አንተነህ ሐረገወይን፤ ስለ ምግብ ቤታቸው ከፈታና የደንበኞች መስተንግዶ አንስተው ይናገራሉ።
የቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል መያዝ ከሚችለው የተጠርጣሪዎች ቁጥር በላይ እየያዘ በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ መፈጠሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አመለከተ 12.01.2026 11:51
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧ ተነገረ
በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችና መራጮች በስድስት ቋንቋዎች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ ድረገፅ ይፋ ሆነ 07.01.2026 9:10
ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልታቋቁም ነው
#101 Having a laugh (Med) - #101 መሳሳቅ 07.01.2026 10:06
Learn how to talk about things that make you laugh. Practise phrases that help you share stories, react to jokes, and enjoy conversations more. - ስለ ሚያስቅዎት ነገሮች በእንግሊዝኛ እንደምን መናገር እንዳለብዎት ይወቁ። ወጎችን ለማጋራት፣ ለቀልዶች ምላሾችን ለመስጠትና በሃሳብ ልውውጦች ይበልጥ ተደሳች ለመሆን እንዲያግዝዎ ቃለ ሐረጎችን ይካኑ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች መያዝ የሚገባቸውን ወርሃዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ ምጣኔ በሁለት መደበ 04.01.2026 7:55
በሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ብዙኅን መገናኛና ጋዜጠኞች በአግባቡ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ተባለ
"እንኳን ለዘላለማዊ ተስፋ ላገኘንበት ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ" መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ 04.01.2026 12:49
መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አሕጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓለ ልደት አከባበርን አስመልክተው ያስረዳሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።
"የልደት በዓል ታሪክ አይደለም፤ እውነት ነው። እግዚአብሔር መልካም በዓል ይስጣችሁ" ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 04.01.2026 15:15
ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ፤ በዘጸዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር የ2006 በዓለ ልደት መልዕክታቸውን ለእምነቱ ተከታዮች ያስተላልፋሉ፤መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።
የሁለት ክፍለ ሀገራት የማኅበረሰብ አባላትን ለፍቅር አብቅቶ ወደ አንድ ጣራ ስር ኑሮ የመራው ዓመታዊው የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ 29.12.2025 11:18
ሰቲት ሁመራ ከግዕዝ ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጎ በ5 ለ 4 የፍፁም ቅጣት ምት ውጤት ለሁለተኛ ጊዜ የድል ዋንጫ ባለቤት ሆነ
በኢትዮጵያ ከ35 ሚዮን በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከቀላል እስከ ከባድ የአዕምሮ ሕመም እንዳለበት የባለ ሙያዎች ጥናት አመለከተ 28.12.2025 9:37
በወርኅ ጥቅምት በቀን 1456 ያህል ሰዎች ድንበር እንዳቋረጡ ተገለጠ
"የዓመታዊ ስፖርቱ መንፈስ በየሳምንቱ እንዲሆን የምንመኘው ዓይነት ኢትዮጵያዊነትን ያንፀባረቀ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 26.12.2025 11:53
ረቡዕ ዲሴምበር 24 / ታህሳስ 15 የተጀመረው ዓመታዊው 29ኛው የኢትዮጵያውያን የእግርኳስ ውድድር ዓርብ ታህሳስ 27 ሶስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። የሶስቱ ቀናት የግጥሚያ ውጤቶችና ሌሎች ክንውኖች ተጠናቅረው ተካትተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የሚውል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ልታደርግ ነው 24.12.2025 7:20
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር ፈቀደ
"የኢትዮጵያ ቀን ትልቁ የቶርናመንቱ ቀን ነው። ከኢትዮጵያ ብንወጣም፤ ኢትዮጵያ ከውስጣችን አልወጣችም። እየሠራን ያለነው ትንሽቷን ኢትዮጵያ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 22.12.2025 18:12
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ዲሴምበር 27 / ታህሳስ 18 በሜልበር ከተማ በልዩ ድምቀት ስለሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ትሩፋቶች ያስረዳሉ። ዓመታዊው በዓል ተከብሮ የሚውለው Arndell Parke Reserve, 49 Federation Blvd, Truganina ነው።
"ይህ ቶርናመንት በዋነኛነት የሚያደርገው፣ ኢትዮጵያዊነታችንን ማጉላት፤ ልጆቻችን ደህና ቦታ እንዲውሉና የተጠፋፉ ሰዎች እንዲገናኙ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 22.12.2025 20:23
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ከዲሴምበር 24 - 28 / ታህሳስ 15 - 19 በሜልበር ከተማ ስለሚከበረው ዓመታዊው 29ኛ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ሂደትና ተልዕኮ ይናገራሉ። አ ምስት ቀናት የሚፈጀው ዓመታዊው የስፖርት በዓል የሚከናወነው Arndell Parke Reserve, 49 Federation Blvd, Truganina ነው።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.