SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ኢትዮጵያ የትራንስፖርቱን ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክና የተፈጥሮ ጋዝ የማሸጋገርና የነዳጅ ቁጠባ ሀገራዊ ጥሪ አቀረበች 18.03.2026 8:01
የኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይት ከ18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ መሻገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
የአውስትራሊያ ማዕከላዊ ባንክ የ4 ነጥብ 1 ፐርሰንት ወለድ ጭማሪ አደረገ 17.03.2026 4:32
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኩባን በበላይነት ለመቆጣጠር እንደሚሹ ገለጡ
አውስራሊያ በቂ የነዳጅ ክምችት ስላላት ዜጎቿ እንዲረጋጉ አሳሰበች 16.03.2026 3:51
እሥራኤል ትልሟ ግቡን እስኪመታ የሊባኖስና ኢራን ጥቃቷን እንደምትቀጥል አስታወቀች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣሪያ የፓርቲ አባል የሆኑ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ማሰናበቱናን በአንድ ሳምንት ውስጥ 9.36 ሚሊዮን መራጮች መመዝገባቸውን አስታወቀ 16.03.2026 10:49
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 31 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ በአየር መንገዶች የማስፈፀም አቅም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ
ስንብት - ሩፋኤል ተሰማ 13.03.2026 19:51
ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ከእዚህ ዓለም በሞት ስለ ተለዩት የሁለት መንታ ሴት ልጆች አባት አቶ ሩፋኤል ተሰማ፤ መልካም ሰብዕና እና ትውስታዎችን ነቅሰው የቅርብ ወዳጆችና የትግል አጋሮች በስንብት ቃሎቻቸው ይዘክራሉ።
"የቤት ግዢ ብድርን ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከፍሎ መጨረስ ይቻላል" አቶ በፈቃዱ ወለሎ 12.03.2026 15:53
አቶ በፈቃዱ ወለሎ፤የ Bef Homes Australia መሥራችና ባለቤት፤ ድርጅታቸው በምዕራብ አውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ስለሚሰጣቸው አግልግሎቶች ይናገራሉ። የመኖሪያና ሙዋዕለ ንዋይ ቤት ግዢና ሽያጭ መንገዶችን ያመላክታሉ።
ሴናተር ማት ካናቫን የናሽናልስ ፓርቲ መሪ ሆነው ተመረጡ 11.03.2026 4:13
አውስትራሊያ ለመቅረት ጥገኝነት ከጠየቁት ሁለት ተጨማሪ የኢራን የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ውስጥ አንደኛይቱ ሃሳቧን ቀይራ ወደ ኢራን ልትመለስ ነው።
አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛ የሰው ሠራሽ መረጃ ፍለጋ አገልግሎት ውስጥ ተካተቱ 11.03.2026 8:09
እያደገ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ራሱን በቻለ ተቋም ለማስተዳደር መታቀዱ ተገለጠ
አውስትራሊያ ወደ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የቅኝት አውሮፕላን፣ ሚሳየሎችንና ወታደሮቿን በዛሬው ዕለት ልትልክ ነው 10.03.2026 4:40
ዴቪድ ሊትልፕራውድ ከናሽናልስ ፓርቲ መሪነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ
'ሕወሓት ለክልሉ ልማት የተመደበውን በጀት ለታጣቂዎች ቀለብና ለጦርነት ዝግጅት እያዋለ ነው' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጡ 09.03.2026 13:44
41 ሀገራት የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች የተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጡ
"በጄሲ ጃክሰን የምርጫ ዘመቻ ወቅት ትልቅ አስተዋፅዖ አደረግኩ የምለው፤ዜግነት የሌላቸውም አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ያቀረብኩት ሃሳብ ውጤታማ መሆኑ ነው"የሐረርወርቅ ጋሻው 05.03.2026 26:09
የፖለቲካ አንቂ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ቀስቃሽ፣ የቀድሞው የዲሞክራት ፓርቲ የሁለት ዙር ዕጩ ፕሬዚደንት ጄሲ ጃክሰን የወጣቶች ኮሚቴ ሰብሳቢና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ የሐረወርቅ ጋሻው፤ ፌብሪዋሪ 17 ቀን 2026 ከእዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ጄሲ ጃክሰን ፕሬዚደንታዊ የምርጫ ዘመቻ ወቅት ስላበረከቷቸው አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ። የጃክሰንን ሰብዓዊ ገፅታም ይዘክራሉ።
#105 Celebrating small wins at work - #105 Celebrating small wins at work 04.03.2026 7:23
Learn useful English for talking about small wins at work. Practise phrases for celebrating achievements, staying motivated, and making progress step by step. - በሥራ ቦታ ስለ አነስተኛ የአሸናፊነት ውጤት ለመናገር ጠቃሚ እንግሊዝኛን ይማሩ። ስኬቶችን የማክበር፣ በከፍተኛ ተነሳሽነት መዝለቅንና ደረጃ በደረጃ ዕድገት የማስየትን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱ።
በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የነበሩ አውስትራሊያውያን ወደ ሲድኒ እያቀኑ ነው 04.03.2026 3:40
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኢራን ጦርነት ከሳምንታት ዐልፎ ለተራዘመ ጊዜያት ሊዘልቅ እንደሚችል አመላከቱ
በኢትዮጵያ ለመሬት መንቀጥቀጥ ራሱን የቻለ ተቋም እንዲኖር ጥያቄ ቀረበ 03.03.2026 9:48
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ዓለም ያሉ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትን ለማገልገል የሚያስችሉትን አዳዲስ አሠራሮች ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታወቀ
"ፖፕ ፍራንሲስ 'ተስፋ ፅዮን የራሳቸውን ዕውቀት ያካፈሉ የእምነት አባቶች ውስጥ ሊጠቀስ የሚገባው ነው' ብለው ነበር" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 03.03.2026 15:03
ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ በተባባሪ ደራሲነት ለሕትመት ስላበቁት "The Many Lives of Tesfa Seyon: An Ethiopian Intellectual in Early Modern Rome" መፅሐፋቸው አንኳር ይዘቶች ያስረዳሉ።
የእኛ ሰው በሮማ - የኢትዮጵያዊው ፈላሲ ልሂቅ ተስፋ ፅዮን በቫቲካን የመንፈሳዊ ዓለም ተፅዕኖ ፈጠራ 03.03.2026 29:43
ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ በተባባሪ ደራሲነት ለሕትመት ስላበቁት "The Many Lives of Tesfa Seyon: An Ethiopian Intellectual in Early Modern Rome" መፅሐፋቸው አንኳር ይዘቶች ያስረዳሉ።
"የአድዋ ድል በሁሉም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፤ በመላው ጥቁር ሕዝብ ሊከበር የሚገባው ነው" አቶ ንብረት ዓለሙ 03.03.2026 16:45
የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አዘጋጅነት ሜልበርን ከተማ ውስጥ ተከብሮ ስለዋለው የ130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ትሩፋቶች አንስተው ይናገራሉ።
130ኛውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የጥቁር ሕዝብን ክብር፣ ባሕልና ቅርስ ለማስጠበቅ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፕሬዚደንት ታየ አፅቀ ሥላሴ አሳሰቡ 02.03.2026 10:57
ኢትዮጵያ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ትምህርትን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለመስጠት ወጠነች
"ማሚ ቆዳዬን አልወደውም፤ ቀዪሪልኝ" እናት "እምቢኝ!" በአድዋ አንደበት 27.02.2026 15:19
ሥነ ግጥም በጃዝ አዳዲስ ገጣሚያንን አካትቶ በሜልበርን - አውስትራሊያ አሰልሶ ተካሔደ።
"ነፃነትን የሚወድ ማንም ሰው አድዋን ማክበር አለበት" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 26.02.2026 30:55
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንትና ተዋናይ ጌታሁን ይርጉ፤ ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 28 / የካቲት 21 በሜልበርን ከተማ - አውስትራሊያ 21 Yardley St, Maidstone ከ4:00 pm - 6:00 pm ስለሚከበረው 130ኛው የአድዋ ክብረ በዓል መሰናዶና ዝግጅቶች ይናገራሉ። ማኅበረሰባዊ ጥሪም ያቀርባሉ።
"የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ፣ የማይደበዝዝ፣ የብሔራዊ ክብር፣ የነፃነትና የሉዓላዊነት ምልክት ነው።" አምባሳደር አንዋር ሙክታር 24.02.2026 5:51
በአውስትራሊያ፣ በኒውዚላንድ፣ በፊጂ፣ በፓፕዋ ኒው ጊኒ እና በሰሎሞን ደሴቶች የኢፌዴሪ ጥብቅ አምባሳደር አንዋር ሙክታር፤ 130ኛውን የአድዋ ድል አስመልክተው የክብረ በዓሉን ታላቅነትና ልዩ ብሔራዊ መገለጫነት ያመላክታሉ። የሀገራዊ አንድነትና ትብብር ጥሪም ያቀርባሉ።
የፌዴሬሽን ም/ቤት በአማራና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄዎች የተነሱባቸው አካባቢዎች ችግሮች እስኪፈቱ ድረስ ከትግራይ ውጪ የቀጥታ ምርጫ እንዲደረግባቸው ውሳኔ አሳለፈ 24.02.2026 10:08
ኢትዮጵያ ኃይሏን የምትገነባው በቀጠናው ሽብር እንዳይፈጠር ለመከላከል እንደሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመላከቱ
አድዋ - አሉላ አባ ነጋ 24.02.2026 7:25
ግጥም - ጌትነት እንየው *** ድምፅ - ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
"የአድዋ ትልቁ ፋይዳ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተባብረው በአፄ ምኒሊክ አመራር ያንን የመሰለ አንፀባራቂ ድል መቀዳጀት ነው" ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ 24.02.2026 19:35
የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፤ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ውልደትና ዕድገት እስከ አድዋ ድልና ሕልፈተ ሕይወት አንስተው ይናገራሉ።
በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶች ይፋ ሆነ 23.02.2026 12:13
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ ለስምንት ወራት የሥራ ማራዘሚያ ጊዜያት ተሰጠው
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.