SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የመኪና መንዳት ስልጠና ለለማጆች መጀመር ያለበት ከወላጆች፣ ወዳጆች ወይስ ባለሙያ አስልጣኞች? 05.04.2026 9:10
"አንዱ ዓላማችን ማኅበረሰቡን ማገልገል ነውና በአቅም ውስንነት የመንጃ ፈቃድ ለሌላቸው አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ነፃ የመኪና መንዳት ስልጠና እንሰጣለን" ያሉት አቶ ግዛቸው መኮንን፤ የፍቅር ለማጅ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ ማሰልጠኛቸው የምሥረታ ዓላማና የአገልግሎት ዘርፎች ይናገራሉ።
"ማኅበራዊ አንቂ መሆን አለብን፤ ሀገራችን ውስጥ ብዙ የሚሠሩ ማኅበራዊ ነገሮች አሉ" ሶስና ወጋየሁ 02.04.2026 8:29
ለወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት መሥራችና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዳይሬክተር፤ ላቋቋመችው የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት በሜልበርን- አውስትራሊያ ሚሊኒየም ሃውስ የማኅበረሰብ ማዕከል የተካሔደ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ድጋፍ።
አውስትራሊያ የሃርሙዝ ባሕረ ሰላጤ መተላለፊያን ለመክፈት ዩናይትድ ስቴትስን አግልለው በአስቸኳይ ጉባኤ ላይ ከሚታደሙ 35 ሀገራት ጋር መቀላቀሏን አስታወቀች 02.04.2026 2:39
ፕሬዚደንት ትራምፕ የኢራን ጦርነት ለፍፃሜ መቃረቡን ገለጡ
#107 Protecting Wildlife | Talking About Animals and Nature (Med) - #107 የዱር እንሰሳትን መጠበቅ | ስለ እንሰሳትና ተፈጥሮ መናገር 01.04.2026 9:07
Learn useful English for talking about animals, nature, and protecting wildlife. Practise everyday phrases for discussing threats to animals, expressing concern, and describing the environment. - ስለ እንሰሳት፣ ተፈጥሮና የዱር እንሰሳት ጥበቃ ጠቃሚ እንግሊዝኛን መናገር ይማሩ። እንሰሳት ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን አስመልክቶ መወያየትን፣ ስጋትን ማመላከትና የተፈጥሮ አካባቢን የዕለት ተዕለት አዘቦታዊ አባባሎችን መግለፅን ይለማመዱ።
ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ ዛሬ ከምሽቱ 7:00 pm የመካከለኛ ምሥራቅ ጦርነትን አስመልክተው ለመላ አውስትራሊያውያን በሬዲዮና ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ንግግር ሊያደርጉ ነው 01.04.2026 4:24
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዩናይትድ ስቴትስ፣ እሥራኤል፣ ኢራን ጦርነት ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት ጊዜያት ውስጥ ሊያከትም እንደሚችል አመላከቱ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በረራዎችን በከፊል ማስጀመሩን አስታወቀ 01.04.2026 6:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ እንዳለ ገለጠ
"የዳያስፖራ ባንክ አገልግሎት ክፍል ዓላማ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ፍላጎቶችና የባንኩን አቅርቦቶች በማያያዝ ለማገልገል ነው"አቶ ዘሪሁን ተከተል 31.03.2026 35:57
አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መካከል የተካሔደውን የመግባቢያ ሰነድ ፍረማ ፋይዳዎችን አንስተው ያስረዳሉ።
ኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀችው የሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ፎረም ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር የ13 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች 30.03.2026 12:50
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኅን ባለስልጣን በአንድ ዓመት ውስጥ ከማኅበራዊ ሚዲያዎች በናሙና ከታዩ 32 ሺህ ይዘቶች መካከል ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃዎች መሆናቸውን በጥናት መለየቱን አመለከተ
"የፊልም ኢንዱስትሪያችን ገና ዳዴ ማለት እንኳ አልጀመረም" ሶፎንያስ ታድሰ 29.03.2026 25:16
በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ የዕድገት ደረጃና የአሠራር ሂደቶች ነቅሶ ያመላክታል።
"በሚስጥር ከማኅበረሰቡ ውስጥ ተነቅለው የወጡ እውነቶችን የያዘ ነው፤ በሚስጥር ያደረግነው ነገር በአደባባይ ያስለቅሰናል ነው ፅንሰ ሃሳቡ" ሶፎኒያስ ታደሰ 29.03.2026 19:18
በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ፀሐፊ፣ አዘጋጅ፣ ዳይሬክተርና መምህር ሶፎኒያስ ታደሰ፤ በቅርቡ በአቦል ቴሌቪዥን ለታዳሚዎች ዓይነ ገብ ለመሆን የዕይታ መሰናዶው ስለተጠናቀቀለት ባለ 260 ክፍል ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ጭብጥ ቀንጭቦ ያጋራል።
"ልጄ 'ማሚ እኔ ይኼን ቆዳዬን አልወደምው፤ ቀዪሪልኝ' ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በቃል ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም ነው የከፋኝ።" ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ 26.03.2026 23:14
ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ፤ በሀገር ቤት ጎሠኝነትን፣ በሀገረ አውስትራሊያ ዘረኝነትን እምቢኝ ያሉ፤ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእጅጉ የኩራት ሞገስን የተላበሱ ናቸው። ልጃቸው ዕድሜው አምስት ዓመት ሊሞላ ደርሶ ሳለ የገጠመው የቀለም ልዩነት ያሳደረባቸውን ሥነ ልቦናዊ ሁከት እንደምን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈውስ ሆኗቸው ከእነ ልጃቸው እንደተቋቋሙት ይናገራሉ። ያም አስባብ ሆኗቸው "አድዋና ሜልበርን" ያሏትን የስንኝ ቋጠሮ ያስደምጣሉ።
"ጠብን፣ መቀየምን ትፈራለች፤ ፍቅርን፣ ሰው ማክበርን ትወዳለች። በእምነቷም፣ በልጆቿም በትዳሯም ጠንካራ ነበረች።" የወ/ሮ ወርቅነሽ ባለቤት አቶ አብርሃም ተዘራ ገሠሠ 26.03.2026 17:18
ወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) ለሶስት ዓመታት ከማኅፀን ካንሰር ጋር ያካሔዱት ፍልሚያ አክትሞ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተለይተዋል። ባለቤታቸው አቶ አብርሃም ተዘራ፣ የቤተሰባቸው ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ እና የንስሃ አባታቸው መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ችሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል አስተዳዳሪ፤ የወ/ሮ ወርቅነሽን የሕይወት ዘመን አንስተው፤ ጥልቅ ሐዘናቸውን በመግለፅ ይዘክራሉ። የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ማርች 28 ቀን 2026 / መጋቢት 19 ቀን 2018 በወረቢ ቤተ መቃብር Corner Cemetery Rd & Railway Avenue 10:00 am...
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ‘በጣም ትልቅ ስጦታ ሰጠችኝ‘ አሉ 25.03.2026 6:47
የግሪንስ ፓርቲ አውስትራሊያ ያለ ፓርላማ ይሁንታ ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚደነግግ ሕግ እንዲኖራት ፓርቲያቸው ዳግም መጠየቁን አስታወቁ
ኢትዮጵያ በዓለም 5ኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ተባለች 25.03.2026 8:53
በኢትዮጵያ የዩናይድ ስቴትስ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን የንግድና ጉብኝት ቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የሚደርስ የማስያዣ ገንዘብ እንዲያሲይዙ የሚጠይቀው አሠራር ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ጀምሮ ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ
"ኳታር ውስጥ፤ በኑሮ ውድነት ላይ አንዳችም ጭማሪ የለብንም። የነዳጅ ጭማሪ አልተደረገም። መንግሥት ትልቅ ድጋፍ እያደረገልን ነው" ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ 24.03.2026 16:45
የዶሃ - ኳታር ነዋሪ ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ፤ የእሥራኤል - ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ጦርነት በእሳቸውና በቤተሰባቸው፣ እንዲሁም፤ በኳታር ነዋሪ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደረውና እያሳደረ ስላለው ተፅዕኖ አንስተው ያስረዳሉ።
"የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትንና ኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከልን እንደግፍ" ኧኒ ዴቪ እና ማርታ ቦረና 24.03.2026 16:54
ኧን ዴቪ የFlying Fruit Fly Circus አርቲስቲክ ዳይሬክተርና ማርታ ቦረና የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትና የኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከል ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ቅዳሜ ማርች 28 / መጋቢት 19 ስለሚካሔደው የድጋፍ እራት ፕሮግራምና የእገዛ ፋይዳዎች ይናገራሉ።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰላጤን የባሕር መስመር እንድትከፍት የ48 ሰዓታት ዛቻ አዘል የጊዜ ገደብ ሰጡ 23.03.2026 6:34
አውስትራሊያ ለአንድ ወር ያህል የሚበቃ የነዳጅ፣ ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ ክምችት እንዳላት አስታወቀች።
"የሰርከስ ባለሙያ ሆኜ በእዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኔ ዕድለኛ ነኝ" አርቲስት ሶስና ወጋየሁ 23.03.2026 17:32
ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት መሥራችና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዳይሬክተር፤ ከጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት እስከ እንጦጦ ፓርክ እያስገነባችው ስላለው የሰርከስ ማዕከል ተልዕኮዎችን አንስታ ትናገራለች። የአውስትራሊያ ጉብኝት ዓላማዋንም አስመልክታ ቅዳሜ ማርች 28 / መጋቢት 19 በሚሊኒየም ሃውስ የማኅበረሰብ ማዕከል 296 Nicholson St, Seddon ተገኝታ ታስረዳለች።
በአዲስ አበባ በስድስት ወራት ውስጥ ከ5800 በላይ ፍቺዎች ተመዘገቡ 23.03.2026 11:38
የሕግ ከለላ የላቸውም የተባሉ 8000 ኢትዮጵያውያን እሥራኤልን ለቅቀው ሊወጡ ነው
ስንብት፤ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የባሕል ተፋላሚዋ አክስት ሮዳ ሮበርትስ 22.03.2026 9:07
በ66 ዓመታቸው ከእዚህ ዓለም ለተለዩት የSBS ነባር ዜጎች አረጋዊትና የዊድጃቡል ዋይባል ሴት የሐዘን መግለጫዎች እየደረሱ ነው። ከማኅፀን ካንሰር ጋር ሲያካሂዱት የነበረው አጭር ፍልሚያ ቅዳሜ ማርች 21 / መጋቢት 12 ከቀትር በኋላ በሕልፈተ ሕይወት አክትሟል።
መጽሐፍ ሻጮች ስልጠና ቢሰጣቸው ደስ ይለኛል፤ ለደራሲያን የሚሰጡት ክብር አናሳ ነው። በጣት የሚቆጠሩት ካልሆኑ በስተቀር።" ደራሲና ጋዜጠኛ ሃሊ ሙዘይን 22.03.2026 29:19
ሲስተር ሃሊ ሙዘይን የጤና ባለሙያ፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ አርታኢና የበጎ ፈቃድ አገልጋይ ናቸው። በተሰማሩባቸው መስኮች ትድግናን ስለሚሹ ሀገራዊ ጉዳዮችና የሙያ አስተዋፅዖዎቻቸው ይናገራሉ።
"ለመላው ኢትዮጵያውያንና የዓለም ሙስሊሞች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ ተቻችለን የምንኖር ያድርገን፤ መልካም ኢድ ይሁንልን" ሼህ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር 19.03.2026 6:03
ሼህ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር፤ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መሪ፤ የ2026 የኢድ አል-ፈጥር መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
#106 Mmm or Hmm? Trying new and unusual food - #106 Mmm or Hmm? Trying new and unusual food 18.03.2026 8:32
Learn useful English for talking about unusual or strong flavours. Practise everyday phrases for reacting to new foods, sharing opinions, and encouraging someone to try something new. - ያልተለመደ ወይም ወጣ ያለ ጣዕም ስላላቸው ምግቦች ለመናገር ጠቃሚ እንግሊዝኛን ይማሩ። አዲስ ምግቦችን አስመልክቶ ስሜትዎን ለመግለጥ ወይም አተያዮን ለማጋራትና ሰዎች አዳዲስ ነገርን እንዲሞክሩ አበረታች አዘቦታዊ አባባሎችን ይልመዱ።
" 'በሕይወት ሁሉ ነገር ተሳካልን፤ የእናታችንም ሕልም ተሳክቷል' በምንልበት ሰዓት እናታችንን አጣናት" ሊዲያ ዓለማየሁ 18.03.2026 25:07
በአውስትራሊያ የሜልበርን ነዋሪ ስለ ነበሩትና ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ስለ ተለዩት ወ/ሮ ዕሌኒ ብርሃኑ፣ ልጆቻቸው፣ እህታቸውና ወዳጆቻቸው ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ። መልካም ሰብዕናቸውን አንስተው ይዘክራሉ። ቅዳሜ መጋቢት 12 / ማርች 21 ለወ/ሮ ዕሌኒ ብርሃኑ በደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከ7: 00 am ጀምሮ ፀሎተ ፍትሐት ይደረግላቸዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በMaddingley General Cemetery, 67 Griffith St, Bacchus Marsh ይፈፀማል።
በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሳቢያ የደረሰውን የነዳጅ እጥረትና የዋጋ ንረት አስመልክቶ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ካቢኔ በነገው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው 18.03.2026 7:43
ፕሬዚደንት ትራምፕ አውስትራሊያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአጋርነት ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሀገራት ላይ የሰላ ትችት ሰነዘሩ
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.