SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

" 'የመኢሶን ሰማዕታት' መጽሐፍ ፋይዳ አንድ ተጨባጭ የሆነ የታሪክ ሰነድ ማቆየት ነው" ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ 16.04.2024

"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የድርጅታቸው የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት የመዘከሪያ መጽሐፍን መሰናዶና ትሩፋቶቹን አስመልክተው ያስረዳሉ።

የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ የገበያ ማዕከል በስለት የተገደሉ ስድስት ሰዎችን በክብርና በሐዘን ለመዘከር በግማሽ ዝቅ ብሏል 15.04.2024

አውስትራሊያ ኢራን በእሥራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አወገዘች

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተካተተች 14.04.2024

ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች ከሥራና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች እንዲገለሉ የሚያደርግ ምዝገባ ልትጀምር ነው

ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ባቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ ገለልተኛና ሙሉዕ ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ 11.04.2024

ዩናይትድ ስቴትስ የዊኪሊክስ መሥራቹን ጁሊያን አሳንጅ ክስ ልታነሳ እንደምትችል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አመላከቱ

#59 Talking about cooking (Med) 11.04.2024

Learn how to talk about cooking and sharing recipes.

ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ይጓዙ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ 10.04.2024

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ አውስትራሊያ ለፍልስጤም አገራዊ ዕውቅና ለመስጠት ዕሳቤ እንዳላት አመላከቱ

"ኢድ አልፈጥር! አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን፤ ደም ማፍሰሱን አላህ በኃይሉ ያስተካክልልን" ሼክ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር 10.04.2024

ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የዘንድሮውን ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የፆምና ፀሎት መንፈሳዊ ፋይዳዎችንና የሰላም ምኞታቸውን አሰናስለው ይገልጣሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ ከ2035 አንስቶ በነዳጅና በናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዳይውሉ ጥሪ ቀረበ 09.04.2024

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት አዲስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሾመ

ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድርድር ሊቀጥል ነው 09.04.2024

በነዳጅ የሚሠሩና ሙሉ በሙሉ በውጭ አገር ተገጣጥመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ ተጣለ

በአዲሱ የምግብና ግሮሰሪ ሥነ ምግባር ደንብ ሱፐርማርኬቶች እስከ 10 ሚሊየን ዶላርስ የሚደርስ መቀጮ ሊያገኛቸው ነው 08.04.2024

የቀድሞው የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አዛዥ በእሥራኤል የአየር ጥቃት ለተገደለችው አውስትራሊያዊት የእርዳታ ሠራተኛ ምርመራ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሰየሙ

"ኤልያስ ካለ ጎል አለ፤ አብዛኛዎቹ የመብራት ኃይል ቡድን ዋንጫዎች የኤልያስ ጁሐር ዋንጫዎች ናቸው" የፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 08.04.2024

"የኤልያስ ዋንጫ" አዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ በዘጋቢ ፊልም ቀርፀው ለሕዝብ ዕይታ ለማቅረብ ስለምን እንደወደዱና የፊልሙን ጭብጥ አሰናስለው ይናገራሉ። "የኤልያስ ዋንጫ" በሳምንቱ መጨረሻ በሜልበርን - አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ በነፃ ይቀርባል።

" የደብረ ዘይት በዓልን ስናከብር የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እያሰብን ነው ። ” መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ 07.04.2024

መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ በአውስትራሊያ የልደታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በትናንትናው እለት የተከበረውን የደብረ ዘይት በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ አደራ ብለዋል ።

በነባር ዜጎች መካከል ያለ ባሕላዊ ዝንቅነትን የመረዳት ጠቀሜታ 07.04.2024

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ከሆኑት የአቦሪጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ተሳትፎ በማድረግ ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመገንባት ካሹ በመካከላቸው ያሉ ባሕላዊ ዝንቅነቶችን መረዳት ግድ ይላል።

#58 How to say 'no' at work (Adv) 07.04.2024

Learn how to professionally and politely decline additional workload.

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ የአውስትራሊያዊቷን እርዳታ ሠራተኛ ሞት ተከትሎ የእሥራኤል መንግሥት ኃላፊነት እንዲወስድ ጠየቁ 03.04.2024

*** ሰማንታ ሞስቲን በአውስትራሊያ የንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ እንደራሴ ሆነው ተሾሙ

" የ29ኛው ኩዊል የጋዜጠኛነት ልህቀት ሽልማት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውያንም ጭምር ነው ። "- የኩዊል ሽልማት አሸናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ 02.04.2024

“ ይህ ታሪክ እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አይደለም ፤ ሲያነቡትም ሆነ ሲጽፉት ስሜትን የሚፈታተን ስለሆነ አጠናቅቆ ለማውጣት ስድስት ወራትን ፈጅቷል ። ” ሩቺካ ታልወር

“ ጋዜጠኝነት ለእኔ ሕዝብን እና አገርን በቀናነት ማገልገል ነው ። ” የኩዊል ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ 02.04.2024

“ በሽልማቱ ላይ ከተገኙት ሰዎች መካከል የኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ዝርያ ካላቸው የተገኘሁት እኔ ብቻ ነበርኩ ።ይህ የታሪክ አጋጣሚም የሽልማቱን ዋጋ በተለየ ሁኔታ ላቅ ብሎ እንዲታይ አድርጎታል ። ” ለሜልበርን ፕሬስ ክለብ በመድብለባሕል ጉዳዮችና ሚዲያ ዘርፍ በአውስትራሊያ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ሙያ የላቀ ደረጃ ያለውን 29ኛውን የኩዊል የጋዜጠኛንት ልህቀት ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ “ SBS ታሪኬን ሲያወጣ ከስደተኝነት ባሻገር ለአውስትራሊያ ማኅበረሰብ የማበረክተው እንዳለ እድርጎ አጉልቶ በማሳየቱ በበርካቶች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል ። ” ቤተልሔም ጥበቡ

የረመዳን ጾም እና የሴቶች ድርሻ 02.04.2024

ወይዘሮ ነጁም አብደላ የረመዳን ጾም ወቅት በመስጠት በረከትን የምንቀበልበት ቅዱስ ወር ነው ይላሉ። ወ/ሮ ነጁም የሜልበርን ነዋሪ እና የአራት ልጆች እናት ናቸው ፤ ምንም እንኳን ልጆቻቸውን ለብቻቸው ቢያሳድጉም ውጤታም ልጆችን ለማውጣት እና እርሳቸውም ያለሙትን የከፍተኛ ትምህርት ግብ ለማጠናቀቅ ብቸኝነታቸው እንዳላገዳቸው ነግረውናል ።

በአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውኃ እየተሟጠጠ ነው ተባለ 01.04.2024

*** በቀይ ባህር በተፈጠረው የጸጥታ ሁከት ሳቢያ የገቢ እና ወጪ ንግድ ላይ ችግር መፈጠሩ ተገለጠ

በኩዊንስላንድ የዝናቡ መጠን እንደቀነሰ ቢነገርም ፤ ውኃው እስኪደርቅ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገለጸ 01.04.2024

*** የአርስናል የሴቶች ቡድን ቼልሲን አንድ ለባዶ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆነ

በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ምዕመናን መገደላቸው ተመለከተ 28.03.2024

የአውስትራሊያ ጦር አዛዥ ይቅርታ ጠየቁ

#57 Talking about ageing (Med) 27.03.2024

Learn fun phrases you can use to describe the process of growing older.

Australian Easter: Exploring social and cultural traditions beyond religion - በዓለ ትንሣኤ በአውስትራሊያ፤ ከሃይማኖት ባሻገር የማኅበራዊና ባሕላዊ ልማዶች ዳሰሳ 27.03.2024

Easter holds great significance for Christians. Yet, for those of different faiths or non-religious backgrounds, it presents a chance to relish a four-day weekend, partake in family and social gatherings, engage in outdoor activities, and attend events where children take centre stage. Here's your essential guide to celebrating Easter in Australia. - በዓለ ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ትልቅ ፋይዳ አለው። ይሁንና ለሌላ እምነት ተከ...

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር 'የኢትዮጵያ ውስብስብ ፖለቲካዊና የደህንነት ቀውሶች በውይይት መላ ሊበጅላቸው ያሻል' አሉ 26.03.2024

አውስትራሊያን ለቅቀው እንዲወጡ ሲጠየቁ 'እምቢኝ' የሚሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ፍልሰተኞች እስከ አምስት ዓመታት ለእሥር የሚዳርጋቸው ሕግ ሊፀድቅ ነው።

ስንብት፤ ዶ/ር አንድዓለም ሙላው 1944-2024 26.03.2024

"አውስትራሊያ ውስጥ ደስታ ካልሆነ በስተቀር ምንም የገጠመን እንከን የለም" የሚሉት አቶ በሪሁን ካሠኝ፤ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ስለተለዩት የቀድሞ የትግል አጋራቸው ዶ/ር አንድዓለም ሙላው፤ የከፋኝ ኢትዮጵያ ጀግኖች ግንባር መሪ የግልና ሰብዓዊ አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.