SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
"ሥነ ፅሑፍ ቁራኛ ነው፤ ከፀሐፊው ጋር በፍቅርም በትንቅንቅም ተያይዘው ይዘልቃሉ፤ አይላቀቁም" ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ 04.05.2024 18:33
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉና የሥነ ግጥም በረከቶቹ ይናገራል።
"ጋዜጠኛ በንፁህ ኅሊናው ሚዛናዊ የጋዜጠኛነት ሥራን መሥራት እንጂ፤ ሙያውን የሚያራክስ ነገር መሥራት የለበትም። አሁን እንደወረርሽኝ የወረረን እሱ ነው" አበራ ለማ 04.05.2024 14:17
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ የአገረ ኢትዮጵያን የራዲዮ ስርጭት፣ የጋዜጣ ሕትመት ውጤቶችንና የባለ ሙያዎቹን የሥነ ምግባር ደረጃ መዝኖ ግለ አተያዩን ያጋራል።
አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት 03.05.2024 12:23
ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።
Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት 02.05.2024 7:28
The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለሚከናወነው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አስታወቀች 30.04.2024 9:00
ከአፍሪካ ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ መመዝገቡ ተገለጠ
“ ግላኮማን አንዴ ከተከሰተ ባለበት ማቆም እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማዳን አይቻልም ” - ዶ /ር ለምለም ታምራት 30.04.2024 16:47
ዶ /ር ለምለም ታምራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የዓይን ሐኪምና የግላኮማ ስፔሽያሊስት (ልዩ ሐኪም ) የዓይን ውስጥ ዕብጠት ግላኮማ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ዕይታችንን ሊጋርድ የሚችል በሽታ መሆኑን ያስረዳሉ።
ሰሙነ ህማማት እና ትርጓሜው - በመጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ 30.04.2024 16:48
መጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማንያን ዘንድ በተለየ ሁኔታ የሚታሰቡትን የሰሙነ ህማማት ቀናት ትርጓሜ አስረድተዋል ።
"ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓለ ትንሣኤን እንመኛለን" በሜልበርን-አውስትራሊያ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን 30.04.2024 11:27
በአገረ አውስትራሊያ-ሜልበርን ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤልና የመካነ ሰላም ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት መዘመራን፤ ቤተልሔም ትዕግስቱ፣ ፅዮን ብሩክ፣ ኤማንዳ ወንድወሰንና ኤፍራታ ሚሊዮን ሰሙነ ሕማማትን ምክን ያት በማድረግ "በጌቴ ሰማኔ" መንፋሳዊ መዝሙርን ያሰማሉ።
ዜና - በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የአውስትራሊያ ፓርላማ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረገ 29.04.2024 6:18
በአብላጫው በሴቶች ለሚሰሩ ስራዎች የ9 በመቶ የክፍያ ጭማሪ እንዲደረግ የሰራተኞች ማህበር ጠየቀ
በአዲስ አበባ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ ከ77 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚኖሩና 92 በመቶው ኤርትራውያን መሆናቸው ተገለጠ 28.04.2024 8:31
የ2016 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተወሰኑ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
የአንዛክ ቀን በመላው አውስትራሊያና በባሕር ማዶ ተከበረ 25.04.2024 4:54
የአውስትራሊያ ፌዴራል ፖሊስ ከእምነት መሪዎች ጋር መክረናል ሲል፤ በሲድኒ የእስልምና እምነት መሪዎች አሰሳውን አስመልክቶ "እንድናውቀው" እንጂ "እንድንመክርበት" አልተደረገም ይላሉ
#60 Talking about commemorating | Anzac Day (Med) 24.04.2024 16:31
Learn how to talk about commemorating Anzac Day, plus find out why it's important for all Australians.
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመግታት የድርጊት እርምጃ ጥሪ ቀረበ 24.04.2024 6:40
ሕወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ነው የሚለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው አለ
በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተገለጠ 23.04.2024 6:28
ከየመን የባሕር ዳርቻ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ በነበረች አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ተሳፋሪ ከነበሩት 77 ኢትዮጵያውያን ውስጥ 5 ሕፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ የ16 ዜጎች ሕይወት አለፈ
Tackling misinformation: How to identify and combat false news - ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል 23.04.2024 12:55
In an era where information travels at the speed of light, it has become increasingly difficult to distinguish between true and false. Whether deemed false news, misinformation, or disinformation, the consequences are the same - a distortion of reality that can affect people's opinions, beliefs, and even important decisions. - መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች...
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትጥቅ ታጋዮች በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ፤ ጥበቃም እንደሚደረግላቸው ገለጠ 23.04.2024 3:24
የራያና አላማጣ ተፈናቃዮች ቁጥር እንደሚጨምር ተመለከተ
በጅሮንድ ቻልመርስ የአውስትራሊያ የወደፊት የምጣኔ ሃብት ዕድገት ትንበያን አለዝበው ገለጡ 22.04.2024 8:44
በሲድኒ ቦንዳይ ጃንክሽን የገበያ ማዕከል በስለት ተወግታ የነበረችው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን አገግማ ከሆስፒታል ወጣች
"የጋምቤላ ችግር መታየት ያለበት የኑዌሮችና አኟኮች ተደርጎ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ሊያዋጋ የሚችል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ነው" ዶ/ር ኦፒዎ ቻም 22.04.2024 15:20
ዶ/ር ኦፒው ኦሙት ቻም፤ የቀድሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ተከስተው ስላሉት ዋነኛ ችግሮች፣ መንስዔዎችና ምክረ ሃሳቦችን አንስተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በአገራዊ ምክክር ሂደቱና በኮሚሽኑ ዕቅዶች ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ገለጠ 21.04.2024 6:49
ኢትዮጵያ የጠየቀችውን አዲስ ብድር አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር ያላት ልዩነት አልተፈታም
"በሐረሪ ሕብረተሰብ ውስጥ 40 ያህል የአለላ ስፌት ዓይነቶች መኖራቸውን ጥናቶች ያመለከታሉ" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም 20.04.2024 16:04
ወ/ሮ ዉዳድ ሳሊም፤ የጤና ባለሙያና አንቂ፤ ስለ ሐረሪ ማኅበረሰብ የአለላ ስፌት ባሕላዊ ቅርስነትና የማንነት መገለጫነት አስመልክተው ይናገራሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በረሃብና ተላላፊ በሽታ እየተፈነች እንደሆነና ከፍ ያለ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻት አሳሰበ 18.04.2024 5:09
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት 'ሕወሓት ወረራ ፈፅሞብኛል' ሲል ለፀጥታ አካላት፣ ለነዋሪዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አስታወቀ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ግጭት ውስጥ አይደለሁም አለ
የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ 18.04.2024 9:51
በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ 16.04.2024 6:35
ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች? 16.04.2024 20:21
የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
"የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የማነአብ 16.04.2024 18:52
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.