SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

"ሥነ ጥበብ የቡድን ሥራ ሲሆን፤ ፖለቲካውንና የሕብረተሰብን አስተሳሰብ መምራት ይችላል" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ 21.06.2024

ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ወደ ሀገረ አውስትራሊያ ስለመጡበት መንፈሳዊ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ይናገራሉ። ምዕመናንም ሜልበርንና ሲድኒ በሚካሔዱት መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

"የትዳር አጋሬ ባትረዳኝ ኖሮ የጥበብ ሥራዬ አይቃናም ነበር" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ 21.06.2024

ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ለምዕመናን ስላበረከቷቸው መዝሙሮች፣ ለሕትመት ያበቋቸውን መፃሕፍትና ለዕይታ ያቀረቧቸውን የቅብ ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን አንስተው ይናገራሉ። ለጥበባዊ ሕይወት ስኬታቸው የቤተሰባቸውን ሚና አንስተው ምስጋና ያቀርባሉ።

"እንደ ሀገር የተቋም ግንባታ ችግር አለብን፤ አዲስ አበባ ውስጥ ቢያንስ ተጨማሪ አራት ቲአትር ቤቶች ያስፈልጉናል" አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት 20.06.2024

አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት፤ የኢትዮጵያን ዐበይት የቲአትር ችግሮችና ዕምቅ የኪን ጥበብ ክህሎቶችን አንስተው ይናገራሉ።

ኪነ ጥበብና ዲፕሎማሲ፤ የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ 120ኛው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጥበባዊ ተሃስቦ 20.06.2024

በ1903 በዳግማዊ ምኒልክ ፊርማ መሠረቱ የፀናው የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከኮሪያ እስከ ቀዝቃዛው ጦርነት፤ ከምጣኔ ሃብትና ረድዔት ድጋፍ እስከ ሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ ርዕዮተ ዓለሞች ተፈትኖ 120ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ኪነ ጥበባዊ ትሩፋቶቹም እንደምን በመድረክ ተነስተው በኢትዮጵያውያን የጥበብ ባለሙያዎች አንደበት እንደተዘከሩ አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት ነቅሰው ይናገራሉ።

የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን አውስትራሊያ ውስጥ የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎች የሚተከሉባቸውን ሰባት ሥፍራዎች ይፋ አደረጉ 19.06.2024

የመሣሪያ ዕገዳ መነሳትን አስመልክቶ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተፃራሪ መግለጫዎችን ሰጡ

Facing religious discrimination at work? These are your options - በመሥሪያ ቤትዎ የሃይማይኖት መድልዖ ገጥሞዎታል? አማራጭዎችዎን እነሆ 19.06.2024

Australia is a party to the International Covenant on Civil and Political Rights, which provides extensive protections to religious freedom. However, specific legislated protections vary across jurisdictions. If you have experienced religious discrimination at work, it is important to know your options, whether you are considering submitting a complaint or pursuing the matter in court. - አውስትራሊያ ለ...

73 መሥሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከደንብና መመሪያ ውጪ የ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግዢ መፈፀማቸው ተመለከተ 18.06.2024

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በግለሰቦች ስም የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ከ17 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡና ከእዚያም ውስጥ 9 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ለትርፍ ሰዓት ክፍያና የበዓል ስጦታ መዋሉ ተገለጠ

ፍቅርና አመፅ፤ 'ለምን ለቅቃ አትወጣም?' 'ለምን ኃላፊነትን አይወስድም? 18.06.2024

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅ አማራጭ መፍትሔዎች ምንድን ናቸው? 18.06.2024

ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንትና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

የኢድ አል አድሃ በዓል በመላው ዓለም ተከበረ 17.06.2024

አውስትራሊያና ቻይና ልዩነቶቻቸው ላይ እየተነጋገሩ የጋራ ጥቅሞቻቸውን በትብብር እንደሚገነቡ ተመለከተ

በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊየን 336 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ መረጋገጡ ተገለጠ 17.06.2024

የኢትዮ - ቴሌኮምን ድርሻ ለውጭ ኩባንያዎች የመሸጥ ሂደት በጊዜያዊነት ተገታ

እናቶቻቸው ላይ ጥቃት ሲፈፀም የማወዱ ኢትዮጵያውያን ወንዶች፤ ፍቅረኞቻቸውና ሚስቶቻቸው ላይ ጥቃቶችን አድራሽ የሚሆኑት ስለምን ነው? 16.06.2024

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚረዱት እንደምን ነው? 15.06.2024

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ፋርማሲ - የቤት ሽያጭና ግዢ 14.06.2024

በፍሬድ ማየር ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያዋ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከመሀል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ ያለፉበትን የሕይወት ጉዞ አንስተው አውግተዋል። በውይይታችን መቋጫ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን በሲያትል ከተማ ተሰማርተው ስላሉበት የቤት ግዢና ሽያጭ (Real Estate) የንግድ መስክ ይናገራሉ።

"ሀገር ቤት ፋርማሲ ውስጥ በዝቶ የገጠመኝ የፋርማሲ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው" ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ 13.06.2024

በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ እንደምን ወደ ፋርማሲ ሙያ እንደዘለቁና በሙያው መስክ እንደተሠማሩ ያወጋሉ። የኢትዮጵያንና የአሜሪካ ፋርማሲዎች አሠራርን ነቅሰው ያስረዳሉ።

የአላማጣ የሰላም ጥሪ ችላ ሊባል እንደማይገባ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ አሳሰቡ 12.06.2024

ዩናይትድ ስቴትስ የእሥራኤል - ጋዛ ጦርነትን አስመልክቶ የሃማስን ተኩስ አቁምና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ምላሽ እያጤነች መሆኗን ገለጠች

ኢትዮጵያ የብር መግዛት አቅምን ካዳከመች የዋጋ ንረቱ እንደሚባባስ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አሳሰበ 11.06.2024

የኢትዮጵያ ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር 129.7 ሚሊየን መድረሱና በ28 ዓመታት ውስጥም በእጥፍ እንደሚያድግ ተገለጠ

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ከመሃል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ 11.06.2024

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው። ከመሀል ሜዳ ተነስተው ሀገረ አሜሪካ የዘለቁት የከፍተኛ ትምህርት ጥማታቸው ለማርካትና በላቀ ክህሎት ተጠብበው ሙያዊ አስተዋፅዖ ለማበርከት ተልመው ነው።

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከእሥር ተለቀቁ 11.06.2024

ኮልስ በቪክቶሪያ የኤቪያን ኢንፍሉዌንዛ መከሰትን ተከትሎ ከምዕራብ አውስትራሊያ በስተቀር የዕንቁላል ሽያጭ ገደብ ጣለ

"በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቻለሁ፤በሕይወት እያለሁ ይህን ክብር በማየቴ አመሰግናለሁ"ለማ ክብረት "በዝግጅቱ ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ"የሺሐረግ ግርማ 11.06.2024

ከአምስት ዓለም አቀፍ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የግብ ጠባቂ ሬኮርድ ያስመዘገበውና በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ሞሪሽየስን ለማሸነፍ እንድትበቃ ላስቻለው አንጋፋና ዝነኛው ለማ ክብረት ቅዳሜ ሰኔ 1 ቀን 2016 በሜልበርን - አውስትራሊያ የተካሔደው የዕውቅናና ምስጋና ምሽት ዝግጅት ተጠናቅቋል። ስኬቱም በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ የ"ይበልና ይቀጥል" ስሜትን አሳድሯል።

13 ሚሊየን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የግብርና ግብዓት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ 09.06.2024

ኢትዮጵያ ውስጥ በ10 ወራት ውስጥ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል፤ 16 በመቶ የሚሆነው ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተገኘ መሆኑ ተገለጠ

Australia’s coffee culture explained - የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ሲገለጥ 07.06.2024

Australians are coffee-obsessed, so much so that Melbourne is often referred to as the coffee capital of the world. Getting your coffee order right is serious business, so let’s get you ordering coffee like a connoisseur. - አውስትራሊያውያን አቅላቸው ለቡና የማለለ ነው፤ ተዘውትሮም ሜልበርን የዓለም የቡና መዲና በሚል ተቀጥላ ትጠቀሳለች። ቡናዎን በውል ማዘዝም ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ልክ ቡናን በማጣጣም ክህሎት እንደተላበሰ ባለሙያ ቡናዎን እንዘዝልዎት።

ኢሰመኮ የአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማክተምን ተከትሎ ከአዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ያሉ እሥረኞች እንዲለቀቁ ጠየቀ 06.06.2024

የጁባላንድና ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ አስተዳደር ግዛቶች የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ሶማሊያን ለቅቆ እንዲወጣ የሚሹ አለመሆናቸውን ገለጡ

#63 Taking a dog to the park (Med) 05.06.2024

Learn how to talk about your dog at a dog park.

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ታሰሩ 05.06.2024

የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ድንጋጌ አሳለፈ

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.