SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የአያሌ ኢትዮጵያውንን ዕንባ ያስፈሰሰው የጎፋ ዞን የሕይወት ጥፋት ከዓለም መሪዎች የጥልቅ ሐዘን መግለጫዎች እየጎረፉለት ነው 28.07.2024

የዋቻሞ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

"ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ 28.07.2024

ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።

"በጎፋ ዞን ከደረሰው ችግር ስፋትና ብዛት አንፃር ያሉ ድጋፎች በቂ ስላልሆኑ በሁሉም በኩል ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንጠይቃለን" አቶ ካሳሁን አባይነህ 27.07.2024

አቶ ካሳሁን አባይነህ ሓጎስ፤ የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ፤ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የደረሱትን የሕይወት ጥፋቶች፣ የአስከሬን ፍለጋ ሂደቶች፣ የሚያሹ አስቸኳይና ዘላቂ ልገሳዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራ በረራዎቹን እንዲያቋርጥ ከኤርትራ ሲቪል አቬይሽን እንደተነገረው አስታወቀ 25.07.2024

የአውስትራሊያ የወሊድ ቁጥር ከ2006 ወዲህ ከፍተኛ በተባለ ሬኮርድ መጠን ቀነሰ

በመሬት ናዳ ሕይወታቸው ያለፈ የደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን ነዋሪዎች ቁጥር ከ229 በላይ መድረሱ ተገለጠ 24.07.2024

የኒውዚላንድ ኦሎምፒክ ቡድን ካናዳ የድሮን ስለላ አካሂዳብኛለች ሲል ክስ አቀረበ

በደቡብ ኢትዮጵያ በደረሰ የመሬት ናዳ ሳቢያ ከ100 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ 23.07.2024

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ፤ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለ2024 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን የዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት መጠነ ሰፊ ድጋፍ እንዳገኙ ተመለከተ

"በዓለም አቀፍ ተቋም ግፊት የኢትዮጵያን የጥሬ ብር ምንዛሪ ግብይት አቅም መቀነስ አንገትን የመታነቅ ያህል ነው" ኢንጂነር አያሌው አስፋው 23.07.2024

ኢንጂነር አያሌው አስፋው፤ ሉላዊ የገንዘብ ዝውውርን፣ ከአሜሪካን ዶላር ውጭ ዓለም አቀፍ ግብይት የማድረግ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።

"የሳይበር ጥቃትን ዜሮ ማድረግ አይቻልም፤ ያንንም ማድረግ የቻለ ሀገር የለም" ኢንጂነር አያሌው አስፋው 23.07.2024

ኢንጂነር አያሌው አስፋው፤ የሳይበር ጥቃቶች በግለሰቦች፣ ተቋማትና መንግሥታት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖዎች፤ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርን አንስተው ያመላክታሉ።

በአዲስ አበባ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ8 ሺህ በላይ ጥንዶች ፍቺ መፈፀማቸው ተገለጠ 22.07.2024

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኑ ተመለከተ

ጆ ባይደን ከዕጩ ፕሬዚደንትነታትቸው ለቀቁ፤ በፕሬዚደንታዊ ስልጣናቸው ፀንተው እንደሚቆዩ አስታወቁ 21.07.2024

የሪፑብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ካማላ ሃሪስ ዕጩ ፕሬዚደንት ሆነው ከቀረቡ በቀላሉ ድል እንደሚነሷቸው ገለጡ

Is immigration worsening the housing crisis? - SBS Examines: ኢሚግሬሽን የቤት ቀውስን ያባብሳል? 21.07.2024

Australia's facing a worsening housing crisis. At the same time, the number of overseas migrant arrivals is at its highest ever since records began. Is increased migration driving up housing and rental prices? - አውስትራሊያ የቤት እጥረት ቀውስ ተጋርጦባት አለ። በሌላም በኩል የባሕር ማዶ ፍልሰተኞች ቁጥር ሬኮርድ መመዝገብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቶውንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። የፍልሰተኞች ቁጥር መናር የቤት ግዢ / ግንባታና የኪራይ ዋጋዎች እንዲያሻቅቡ ያደርጋል?

"የግብፁ መንፈሳዊ ጉዞ የሚካሔደው ከጥቅምት 28 ቀን 2017 እስከ ኅዳር 10 ቀን 2017 ነው" ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ 18.07.2024

ዶ/ር ተፈሪ በላይነ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ወደ ግብፅ ስለሚደረገው የመንፈሳዊ ጉዞ ፕሮግራም ሂደት ይናገራሉ።

"ወደ ገዳማትና አድባራት መሔድ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ በረከቶችን ማግኘት፣ ተቀድሶ መምጣት፣ ያላሰበውን ፀጋም ማግኘት ነው" ሊቀ ትጉሃን ገብረመድኅን መሰሉ 18.07.2024

ሊቀ ትጉሃን ገብረመድኅን መሰሉ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የፍኖተ ሕይወት ዘማኅበረ ካህናት የመንፈሳዊ ጉዞ አስተባባሪ፤ የግብፅ ጉዞ መሰናዶንና የመንፈሳዊ ጉዞ ትሩፋቶችን አንስተው ያስረዳሉ።

"የመንፈሳዊው ጉዞ ዓላማ ምዕመናን የቅዱሳን፣ የፃድቃንንና ሰማዕታት ሥፍራዎች ላይ በመሳተፍ፤ ለክብርና ንስሃ እንዲበቁ ነው" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና 18.07.2024

መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሰሜን አፍሪካ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ በፍኖተ ሕይወት ዘማኅበረ ካህናት የመንፈሳዊ ጉዞ አስተባባሪነት ስለተዘጋጀው የ10 ቀናት የግብፅ ጉዞ መንፈሳዊ ተልዕኮ ይናገራሉ።

#66 What to ask when looking to rent (Med) 18.07.2024

Learn how to ask questions when looking for a home to rent.

በእሥራኤል የቦምብ ጥቃት ተጨማሪ 57 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተመለከተ 17.07.2024

የMH17 ሰለባዎች 10ኛ ዓመት ዝክረ መታሰቢያ ተካሔደ

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት የሁለትዮሽ ስምምነት አደረጉ 16.07.2024

ለውጭ ሀገር ዜጎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሆቴሎች ሁሉንም የአገልግሎት ክፍያዎች በዶላር ብቻ እንዲቀበሉ ብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈ

How to lodge your tax return in Australia - አውስትራሊያ ውስጥ የግብር ተመላሽዎን እንደምን ማቅረብ እንደሚችሉ 16.07.2024

In Australia, 30 June marks the end of the financial year and the start of tax time. Knowing your obligations and rebates you qualify for, helps avoid financial penalties and mistakes. Learn what to do if you received family support payments, worked from home, are lodging a tax return for the first time, or need free independent advice. - አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 30 የፋይናንስ ዓመት ማክተሚያና የግብር ጊዜ መጀመሪያ ነው። ግዴታዎች...

ሰናይት መብራህቱ፤ የእናት ሚና "ምርጥ አጭር ፊልም" ዳይሬክተርና "ምርጥ ተዋናይት" 16.07.2024

"Mother's Role" - "የእናት ሚና" ፊልም ፀሐፊ፣ ተዋናይትና ዳይሬክተር ሰናይት መብራህቱ፤ እንደምን ፊልሟ "ምርጥ አጭር ፊልም" ተብሎ እንደተሸለመና እሷም "ምርጥ ተዋናይት" ሆና ለመሸለም እንደበቃች ትናገራለች።

ጄዲ ቫንስ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው በዶናልድ ትራምፕ ተሰየሙ 16.07.2024

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) በአቶ በቀለ ገርባ ምትክ አቶ ሙላቱ ገመቹን የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት አድርጎ መረጠ

#65 Talking about the Olympics (Med) 15.07.2024

Learn how to talk about the success of athletes during a big sporting event like the Olympic Games.

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንና የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የብሔራዊ አንድነት ጥሪ አቀረቡ 15.07.2024

ከደርዘን በላይ ፍልስጤማውያን በእሥራኤል የአየር ጥቃት ተገደሉ

ቅዱስ ሲኖዶስ ከሐምሌ 22 እስከ 28 በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ፀሎት እንዲፈፀም አወጀ 14.07.2024

በአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት በ17 ከተሞች ተለቀቀ

"ነቢይ ሀገር ነው፤ ረቂቅ፣ ሩቅና እንደ ተፈጥሮ ጥልቅ ሰው ነው" አቶ አያሌው ሁንዴሳ 12.07.2024

አቶ አያሌው ሁንዴሳ፤ በቅርቡ ከእዚህ ዓለም በሞት የተለየውን የገጣሚ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔትና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንንን የጥበብ ውርሰ አሻራዎች ዋቤ ነቅሰው ይገልጣሉ። ሰማያዊ ሕይወቱም ሰላምን የተላበሰ እንዲሆንና ለቤተሰቡ አባላትም ልባዊ መፅናናትን ይመኛሉ።

"ነቢይን ያጡት ቤተሰቦቹ ብቻ አይደሉም፤ ሀገሪቱም ትልቅ ፈላስፋ፣ ደራሲ፣ ዐዋቂና ዳግም የማይፈጠር ሰው አጥታለች" አቶ ፍቅሬ "ራያ" ረታ 12.07.2024

"ነቢይ መኮንን፤ የያኔውን የጨለማ ጊዜና እሥር ቤት ወደ ብርሃን የለወጠልን ነው" የሚሉት አቶ ፍቅሬ "ራያ" ረታ፤ ሰሞኑን ላይመለስ ዓለምን ስለተሰናበተው ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን የእሥር ቤት ሕይወትና የጥበብ ክህሎቶቹን አንሰተው ከትውስታዎቻቸው ያጋራሉ። ያፅናናሉ።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.