SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

"የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያው የሚያስከትለው የዋጋ ግሽበት ሀብትን ከፍተኛ ገቢ ላላቸው በተለይም ለነጋዴዎች ያሸጋግራል፤ ይህም በቅርብ ጊዜ የሚታይ ውጤት ነው" ዶ/ር ወርቁ አበራ 19.08.2024

ዶ/ር ወርቁ አበራ፤ በዶውሰን ኮሌጅ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰርና የምጣኔ ሃብት ዲፓርትመንት ሊቀመንበር በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግሥት ግብር ላይ የዋለው "ውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ" ፖሊስን አስመልክተው አተያይቸውን ያጋራሉ።

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሀገራዊ ምክክር ተወካዮች ሰንደቅ ዓላማን አካትቶ እስከ መገንጠል የሚፈቅደው የፌዴራል ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ምክረ ሃሳብ አቀረቡ 18.08.2024

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረመድኅን የተመራው የሕወሓት ጉባኤ የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የማዕከላዊ አባላትን ማግለልና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ሰብሳቢነት እየተካሔደ ያለው ሌላኛው "ሕወሓትን መታደግ" ጉባኤ በሕወሓት መካከል ተከስቶ ያለውን ልዩነት አስፍቶ ቀጥሏል።

#68 Discussing the news (Med) 14.08.2024

Learn how to talk about news that makes us feel scared or hopeful.

የሕወሓት ጉባኤ አወዛጋቢነቱ ቀጥሏል 14.08.2024

የኢትዮጵያና ሶማሊያ ውይይይት በአንካራ ተካሔደ

የአውስትራሊያ ኦሎምፒክ ቡድን ሲድኒ ላይ የሞቀ አቀባበል ተደረገለት 14.08.2024

የዝንጀሮ ፈንጣጣ አፍሪካን አስግቷል

"ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን 13.08.2024

እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።

"የዳያስፖራ ሰዎች ብዙ ማድረግ ስንችል ያለንን አጋጣሚና ሁኔታ መጠቀም ባለመቻላችን እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ ውስን ናቸው" ደራሲ አዳሙ ተፈራ 13.08.2024

ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ ሰሞኑን ለሕትመት ስለበቃው "ዳያስፖራው" መፅሐፋቸው አንኳር ጭብጦችና ፋይዳዎች ይናገራሉ።

"እሥራኤል ቃሎችን አትሰማም" የአውስትራሊያ ፌዴራል ሚኒስትር እሥራኤል ላይ ጠንካራ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳሰቡ 12.08.2024

የፓሪስ ኦሎምፒክ ተፈፀመ፤ ሎስ አንጀለስ የ2028 ኦሎምፒክ ተራን ተረከበች

"የዳያስፖራው መፅሐፍ ተልዕኮ በተለያዩ ምክንያቶች ለሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በሚሔዱባቸው ሀገራት ስለሚገጥማቸው ሁኔታ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው"ደራሲ አዳሙ ተፈራ 12.08.2024

ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ ሰሞኑን ለሕትመት ስለበቃው "ዳያስፖራው" መፅሐፋቸው አንኳር ጭብጦችና ፋይዳዎች ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ አቡ ሴራ በዓመት ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ ሊገነባ ነው 11.08.2024

ሕወሓት በምርጫ ቦርድ በልዩ ሁኔታ የተሰጠውን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እንደማይቀበል አስታወቀ፤ በሌላም በኩል ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት የሰጠው የምዝገባ ማረጋገጫ በተጭበረበረ ማስረጃ የተመሠረተ በመሆኑ ምርመራ እንዲካሔድበት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንትና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ

"እመቤቴ ማርያም" የንስሐ ዝማሬ በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዘማሪያን 08.08.2024

ዘማሪያን፤ ቤተልሔም ዘገየ ተፈራ፣ ሲካር ያሬድ፣ ደሊና ካሳሁን ላይችሉህ፣ አፎምያ ብስራት ታዬ፣ ቤቴል ጌታቸው ለገሰ፣ ኑኅሚን ወንድወሰን ክብረት፣ በጸሎት አስማረ ይታይህ፣ ማርያማዊት ጌታቸው ለገሰ፣ ማርያማዊት ገብረሕይወት ተፈሪ፣ ኤድና ብስራት ታዬ እና አርሴማ ተስፋዬ።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ ቲም ዎልዝን በዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት መረጡ 07.08.2024

የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ በመካከለኛ ምሥራቅ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲከናወን ዳግም ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብይታቸው በዶላር ለሚካሔድ ዓለም አቀፍ በረራዎች የተለየ ለውጥ አለማድረጉን አስታወቀ 06.08.2024

ኢትዮጵያ ለ2017 ከተመደበው 971.2 ቢሊየን ብር በጀት ላይ ተጨማሪ ከ500 ቢሊየን ብር በላይ አክላ ልታፀድቅ ዝግጅት መደረጉ ተገለጠ

What is genocide? - SBS Examines: ዘር ማጥፋት ምንድነው? 06.08.2024

'Genocide' is a powerful term — it's been called the "crime of crimes". When does large-scale violence become genocide, and why is it so difficult to prove and punish? - 'ዘር ማጥፋት' እጀግ ብርቱ ቃል ነው፤ "የወንጀሎች ወንጀል" ተብሏልም። የመጠነ ሰፊ አመፅ ክስተት የዘር ማጥፋት ድርጊት ሆኖ ሲገኝ እውን መሆኑን ለማረጋገጥና ቅጣትን ለመጣል በእጅጉ አዋኪ የሚሆነው ስለምን ነው?

የአውስትራሊያ የሽብር ስጋት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ወደ 'ሊከሰት ይችላል' ከፍ አለ 05.08.2024

ከ40 ፐርሰንት በላይ ወጣት አውስትራሊያውያንና ከአራት አንድ ጎልማሶች ለብቸኝነት የተዳረጉ መሆኑ ተመለከተ

የአምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሥነ ሕዝብና ጤና ቆጠራ መጀመሩ ተገለጠ 04.08.2024

በአንድ ቀን ውስጥ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 542 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ

"ብር እየወደቀና የዋጋ ንረት እየበዛ የሚያስቸግር ከሆነ፤ዋጋውን ለመቆጣጠር ያለችን ትንሽ ቁልፍ የወለድ መጠን መጨመር ነው፤ያ ደግሞ ምርታማነትን ይጎዳል" ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024

ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግብር ላይ መዋሉን ስላስታወቀው "የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ" ፖሊሲ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች፣ የሚያስከትላቸውን መዘዞችና ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊቀሰሙ የሚገቡ ልምዶችን ነቅሰው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።

"የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ ትልቁ ችግር ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችንም ማናጋት መቻሉ ነው፤በጀትን ጨምሮ ከታክስ፣ እስከ ወለድ መጠን ድረስ"ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024

"ሚዲያ/ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መንግሥት ገንዘቡን ጣለ የሚለው ትክክል አይደለም። መንግሥት ገንዘቡን አይደለም የጣለው፤ ይደግፈው የነበረውን ብር ነው መደገፍ የተወው። በነፃ ገበያ እንዲወሰን ነው ያደረገው፤ ይህ ፖሊሲ ነው ብር እንዲወድቅ ያደረገው፤ ሁለቱን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል" የሚሉት ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ፖሊሲ ያስረዳሉ።

"በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማን ሐዘን ጥልቅ ነው፤የእርዳታ ፕሮግራም አዘጋጅተናል"አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ 02.08.2024

በምዕራብ አውስትራሊያ የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት ተጎጂዎች ጊዜያዊ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፤ አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ፤ በፐርዝ ከተማ ለእሑድ ሐምሌ 28 ስለተዘጋጀው ልዩ የእርዳታ ፕሮግራም ያስረዳሉ።

"ከ2011 ጀምሮ ኢትዮጵያ በአማካይ ከባሕር ማዶ ኢትዮጵያውያን ታገኝ የነበረው 4 ቢሊየን ዶላር በእዚህ የበጀት ዓመት 6.5 ቢሊየን ደርሷል" አቶ በላይነህ አቅናው 02.08.2024

አቶ በላይነህ አቅናው፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ አገልግሎቱ ለባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለሚያበረክታቸው አስተዋፅዖዎች ያስረዳሉ።

#67 Complaining about kids (Med) 31.07.2024

Learn how to talk about your kids when they are a bit challenging.

የሃማስ ፖለቲካ መሪ ኢራን ውስጥ ተገደሉ 31.07.2024

በሬክስ አየር መንገድ ከበረራ መገታትና ለኪሳራ መዳረግ ሳቢያ 850 ያህል ሠራተኞች ሥራቸውን እንደሚያጡ ተመለከተ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የፓሪስ ኦሎምፒክ ሃይማኖት ነክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ትዕይንት አወገዘች 30.07.2024

87 በመቶ የሚሆኑ የግል ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸው ተገለጠ

"በግሌ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተነሳ ይህችን የምንወዳትን ሀገር የሚረከብልን ወጣት አናገኝ ይሆናል የሚል ስጋት ውስጥ ነው ያለሁት" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ 30.07.2024

ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ የይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ የአዕምሮ ሕመምና አደንዛዥ ዕፅ ሱስ ምን ያህል ስር እንደሰደደ፣ የመንግሥት፣ የሕዝብ፣ የሃይማኖት መሪዎችና የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን የትድግና ድርሻ ያነሳሉ። ለእገዛቸውም ጥሪና ምስጋና ያቀርባሉ።

በባሕር ዳር ከተማ ሰዓት ዕላፊ ተጣለ 29.07.2024

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.