SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር በሕወሓት መካከል የተፈጠረው ልዩነት በንግግር እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ 15.09.2024 9:29
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የወደብ ስምምነት ከተገበረች ሶማሊያ ኢትዮጵያውያን አማፅያንን ልደግፍ እችላለሁ አለች
"ጥላቻውና መገፋፋቱ ተወግዶ፣ በመላ ሀገራችን ሰላም ሰፍኖ ሕዝባችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የሚሸጋገርበት ዘመን ይሁንልን፤ እንኳን አደረሳችሁ" አምባሳደር ሀደራ አበራ አድማሱ 11.09.2024 8:43
ሀደራ አበራ አድማሱ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን፤ የ2017 አዲስ ዓመትን አስመልክተው ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ፤ መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።
"የአባቶቻችን መታወቂያ ሰውን ማክበር፣ሰላምን ማረጋገጥ ነውና እኛ ኢትዮጵያውያን የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማስመስከር አለብን" መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ 11.09.2024 6:13
መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የ2017 አዲስ ዓመት መልዕክት።
"2017 የለውጥ፣ የመጎብኘትና የመዳሰስ ዘመን ይሁንላችሁ" ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ 10.09.2024 7:07
የወንጌላዊ የምሩ ታደሰ - በሜልበርን የዘጸዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አገልጋይ የ2017 አዲስ ዓመት መልዕክት።
"ቀጣዩ ዓመት ሁላችንም ሰላም የምንሆንበት፤ በዘር የማንለያይበት፣ ይቅር ተባብለን አንድ የምንሆንበት ዓመት ያድርግልን፤ መልካም አዲስ ዓመት" ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ 10.09.2024 11:37
ድምፃዊት ቬሮኔካ አዳነ፤ ስለ ነጠላ ዘፈኖቿና የመድረክ ትውስታዎቿ አንስታ ታወጋለች።
"መጠሪያዬ - ፍቅር፣ ተስፋ፣ አንድነና የሀገር ፍቅር ላይ የሚያጠነጥን፤ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን የተመኘሁበት አልበም ነው" ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ 10.09.2024 20:31
ድምፃዊት ቬሮኔካ አዳነ፤ ከፍተኛ ሬኮርድ አስመዝግቦ የ17 ሚሊየን ብር ሽያጭ ስላስመዘገበው "መጠሪያዬ" የሙዚቃ አልበሟና የዘፈኖቿ ይዘቶች ትናገራለች።
"እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደርሳችሁ" የማኅበረሰብ መሪዎች - ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና ዶ/ር ለገሰ ጋረደው 09.09.2024 3:25
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅብረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንትና ዶ/ር ለገሰ ጋረደው በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የ2017 ዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ።
"መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 09.09.2024 16:56
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።
ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም 08.09.2024 25:35
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል።
የቀድሞው የሌበር ፓርቲ መሪ ቢል ሾርተን በአዲሱ ዓመት ከፖለቲካ ዓለም እንደሚሰናበቱ አስታወቁ 05.09.2024 3:36
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አንድ የ14 ዓመት ተማሪ ሁለት ተማሪዎችንና ሁለት መምህራንን ገደለ
የአውስትራሊያ ምጣኔ ሃብት በአዝጋሚ ሁኔታ በ 1 ፐርሰንት ዕድገት ማሳየቱ ተመለከተ 04.09.2024 7:28
ኩዊንስላንድ በታዳሽ ኃይል ትግበራና ዒላማዎች ከአውስትራሊያ የመሪነት ሥፍራን መያዟ ተገለጠ
"ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 03.09.2024 12:54
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።
Is the cost of living affecting social cohesion? - SBS Examines: የኑሮ ውድነት ማኅበራዊ ትስስር ላይ ተፅዕኖን ያሳድራል? 02.09.2024 3:59
According to recent research, the biggest concern facing Australians today is the economy, and it’s causing ruptures within our society. - በቅርቡ በተካሄደ ምርምር መሠረት፤ በአሁኑ ወቅት አውስትራሊያን ገጥሟት ያለው ትልቁ ስጋት ምጣኔ ሃብት ነው። ሕብረተሰባችን ውስጥም ብርቱ ውጥረትን ፈጥሮ አለ።
ጂቡቲ በአፍሪካ ቀንድ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በቀጥታ እንድታስተዳድር አማራጭ ሃሳብ ማቅረቧን አስታወቀች 01.09.2024 11:45
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ደህንነት ስጋትን የሚፈጥሩ ደንበኞች በዓለም አቀፍ አቪየሽን ሕግ እንደሚጠየቁ አስገነዘበ
"የአባቶች ቀን ለመላ አባቶች የልጆቻንን ሰብዕና በመልካም ጎኑ ለመቅረፅ ኃላፊነታችንን ለመወጣት አስበን የምንውልበት ቀን እንዲሆንልን እመኛለሁ" አቶ በፈቃዱ ወለሎ 31.08.2024 8:56
በየዓመቱ ወርኃ ሴፕቴምበር በገባ በመጀመሪያው እሑድ ከፀደይ የዳግም ውልደትና ሕይወተ ተሃድሶ ባሕላዊ ታሪክ ጋር ተያይዞ በመላው አውስትራሊያ የአባቶች ቀን ይከበራል። አባቶችንና የአባት ተምሳሌዎችን ቤተሰብዓዊና ሀገራዊ አስተዋፅዖዎች አጣቅሶ ክብር ለመቸርና ሞገስ ለማላበስ። አቶ በፈቃዱ ወለሎም ግላዊና ቤተሰባዊ ትውስታዎቻቸውን አጣቅሰው ስለ አባቶች ቀን ፋይዳዎች ይናገራሉ።
#69 Getting a haircut (Med) 28.08.2024 17:04
Learn how to talk to your hairdresser about getting your hair cut.
“ሁለት ፍቅረኛሞች ለዕጮኛነት ወይም ለጋብቻ ከመድረሳቸው በፊት ከአንድ እስከ ሶስት ዓመታት አብረው ቢያሳልፉ ጥሩ ነው” - ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ 28.08.2024 32:57
ዳግም የቀረበ፤ ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ - የናታን የጋብቻና ቤተሰብ ምክር አገልግሎት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ፣ ደራሲ፣ የጋብቻና ቤተሰብ ምክር አገልግሎት ባለ ሙያ ስለ ቅድመ ጋብቻ የፍቅር ግንኙነቶች ይናገራሉ።
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት በአፀደ ሕፃናት ዳግም ሊጀመር ነው 27.08.2024 7:00
ኢሰመጉ የአስገድዶ መድፈር ሕግ እንዲሻሻል ጠየቀ
Embracing the wisdom of traditional Indigenous medicine - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ጥበብ ሞገስ ማላበስ 27.08.2024 8:31
Understanding and respecting Indigenous knowledge of medicine may be the key to providing more holistic and culturally sensitive care in today's healthcare setting. - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ዕውቀት መረዳትና ከበሬታንም መቸር፤ ጥንቃቄ የተመላበት ክብካቤን ለሚሻው ሁሉን አቀፍ የዘመናዊው ጤና ክብካቤ አወቃቀር ቁልፍ ሊሆን ይችላል።
"በ'ውጫሌ ውል' ተውኔት መክፈቻና መዝጊያ ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ፈንቅሎ የወጣ የጋለ ሀገራዊ ስሜት ነበር" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 27.08.2024 16:48
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ውልደትና ዕድገቱን፣ የቀለም ትምህርትና የትወና ጅማሮውን ነቅሶ ግለ ታሪኩን በከፊል አውግቷል። ወደ ቀጣዩ ግለታሪክ ትረካው ያመራው እንደምን ከአንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር ለመድረክ እንደበቃ በማንሳት ነው።
የአውስትራሊያ ሠራተኞች ከመደበኛ ሥራ ሰዓት ውጪ የስልክ ጥሪዎችንና ኢሚሎችን ያለመመለስ መብት ግብር ላይ ዋለ 26.08.2024 14:40
የአውስትራሊያ የአውሮፕላን ተጓዦች ተጨማሪ መብቶችን ሊያገኙ ነው
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይፋ ተደረገ 26.08.2024 14:40
የቻይናው አሊባባ በይነ መረብ የሸቀጦች ጅምላ መገበያያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የንግድ ሥራውን ለመጀመር ስንዱ መሆኑን አስታወቀ
ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና፤ ከወላይታ እስከ አውስትራሊያ 22.08.2024 15:36
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና ከስመ ገነን የተውኔት ተጠባቢዎች አንዱና ተጠቃሽ ነው። በሀገረ አውስትራሊያ ከቤተሰቡ፤ በሀገረ ኢትዮጵያ ከትወና ጋር ተዋድዶና ተዛንቆ አለ።
Why is sex and sexuality education taught in Australian schools? - SBS Examines: አውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የወሲብና ወሲባዊነት ትምህርት የሚሰጠው ስለምን ነው? 22.08.2024 5:11
Sex ed in schools is controversial, but experts say it's vital for young people to learn about their bodies, identities, and healthy relationships. Why are some parents concerned? - የትምህርት ቤቶች ወሲባዊ ትምህርት አወዛጋቢ ነው፤ ይሁንና ጠበብት የወጣቶች ስለ አካሎቻቸው፣ ማንነቶቻቸውና ጤናማ ግንኙነት መማር ወሳኝ እንደሁ ይናገራሉ። የተወሰኑ ወላጆች ስጋት ያደረባቸው ስለምን ነው?
በኢትዮጵያ ከ120 ሺህ በላይ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሚገኙና 1400ዎቹ ሕፃናት መሆናቸው ተመለከተ 21.08.2024 7:42
በሀገር ውስጥ ከተለያዩ ተቋማት ከሚመረቁ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች 42 ፐርሰንቱ ሥራ እንደማያገኙ ተገለጠ
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.