SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

"በአፍሪካውያን ሴቶች ዘንድ የቅድመ እርግዝና እንክብካቤ አገልግሎቶች አጠቃቀም ዝቅተኛ ነው" በየነ መረሳ 27.11.2024

በየነ መረሳ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የነርስነትና አዋላጅነት ትምህርት ቤት ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ፤ በቪክቶሪያ ነዋሪ በሆኑ አፍሪካውያን ሴቶች ላይ በማካሔድ ላይ ስላሉት የቅድመ እርግዝና ክብካቤ ጥናታዊ ምርምር ፕሮጄክት ያስረዳሉ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕ/ት ጌታቸው ረዳ "ወደ ስልጣን ሽኩቻ እንድንገባ ተገደናል፤ እንደ ሕወሓት መዳን ከፈለግን በእራሳችን እንጂ በውጭ ኃይሎች መሆን የለበትም" አሉ 26.11.2024

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ የተቸረውን 582 ቢሊየን ብር አክሎ የኢትዮጵያ 2017 በጀት ከ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ ደረሰ፤ የመጪው ዓመት በጀት ከአሁኑ እንደሚበልጥ ተመለከተ።

SBS Examines: In Conversation with the Governor-General - SBS Examines: ወግ ከጠቅላይ እንደራሴዋ ጋር 26.11.2024

Australia's Governor-General is hopeful about Australia's future, despite conflict and difficulty dominating headlines. - ምንም እንኳ ርዕሰ ዜናዎች በግጭትና ሁከት ቢሞሉም፤ የአውስትራሊያ ጠቅላይ እንደራሴዋ የአውስትራሊያ መጪ ዕድል ላይ ተስፈኛ ናቸው።

በትግራይ ክልል ለሠራዊት ብተናና መልሶ ማቋቋም ሥራ የሚውል ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት 60 ሚሊዮን ዶላር፤ ከፌዴራል መንግሥቱ አንድ ቢሊየን ብር መመደቡ ተገለጠ 24.11.2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካይሮ - ግብፅ በተካሔደው 56ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር አጠቃላይ ስብሰባ ላይ በዓለም አቀፍ አገልግሎት ዘርፍ "የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ" ሆኖ ለስምንተኛ ጊዜያት ሽልማት ተቀዳጀ

"በደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ ባካሔድነው ጥናት የዕንቅልፍ ማጣት ችግር 40 ፐርሰንት ነው" ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ 24.11.2024

ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፤ በፍሊንደርስ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና መካነ ተቋም ገዲብ ተመራማሪ፤ በተለይ በአደላይድ - ደቡብ አውስትራሊያ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎችን በተመለከተ በቡድን ስላካሔዱት የዕንቅልፍና አመጋገብ ጥናታዊ ምርምር ዓላማና ግኝቶችን ነቅሰው ያስረዳሉ። በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ጋር በመተባበር ሂደትና ውጤቱንም ቅዳሜ ኖቬምበር 30 / ሕዳር 21 ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደምን ለውይይት እንደሚበቃ ይገልጣሉ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ጌታቸው ረዳ ከኤርትራ ጋር ሥራን መፍጠር እንደሚፈልጉና ዳግም ጦርነት ማካሔድ እንደማያሻ አመላከቱ 21.11.2024

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት መሆኑ እስከሚያበቃ ድረስ ኢትዮጵያ አልሻባብን ከማዳከም ተግባር እንደማትገታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

"መንገደኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የሚያገኙት መስተንግዶ ብቻ አይደለም፤ ባሕልም ነው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ 20.11.2024

ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የአየር መንገዱን ሁነኛ ትልሞችና ትግበራዎች ያመላክታሉ።

"ርዕይ 2035 ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢያንስ ወደ ሶስት የአውስትራሊያ ከተሞች ለመብረር ወስኗል" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ 20.11.2024

ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ አውስትራሊያ የሥራ ጉብኝታቸው ተልዕኮና የአየር መንገዱን ውጥኖች አንስተው ያስረዳሉ።

"የተቃውሞ ሰልፍ ያካሔዱ ወገኖች በአማራ ክልል ተንቃሳቃሽ የሆኑ ኃይሎች ወጥ አመራር ፈጥረው ለውይይትና ድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ ተፅዕኖ መፍጠር አለባቸው" አምባሳደር ሃደራ 18.11.2024

በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሃደራ አበራ አድማሱ፤ በዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልና በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪነት በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ያካሔዱትን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የተነሱ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክተው የኢፌዴሪ መንግሥትን አተያይ ያንፀባርቃሉ።

በናሙናነት ወደ ውጪ ሀገራት የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ውስጥ እንደማይመለሱ በሕዝብ ምክር ቤት ተነገረ 18.11.2024

የአፋር ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከትጥቅ ትግል ወጥቻለሁ አለ

"በአማራ ክልል የድሮን ጥቃትና ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የአውስትራሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርግ እንጠይቃለን" አቶ ግርማ አካሉ 18.11.2024

አቶ ግርማ አካሉ፤ የዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልን በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪ፣ ወ/ሮ ትዕግሥት አበረ፤ የተቃውሞ ሰልፍ ተሳታፊና አቶ ዳዊት ይኩኑ፤ በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ስለ አካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ ዓላማ ያስረዳሉ።

"በዘር መተዋወቅ ጥላቻን ነው ያመጣው፤ ወገን እንጂ ዘር አያስመካም፤ ከየትኛውም ዘር ሁኑ አንድ ወገን ነን" መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ 13.11.2024

መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ፤ በሜልበርን ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ለሕትመት አብቅተው እሑድ ሕዳር 8 / ኖቬምበር 17 ለምርቃት ስላሰናዱት "እኔ ማነኝ?" መፅሐፋቸው ዋነኛ ጭብጦች ይናገራሉ።

"ማንነታችንን አለማወቅ፤ ከማንነታችን በታች እንድንሆን ያደርገናል" መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ 13.11.2024

መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ፤ በሜልበርን ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ለሕትመት አብቅተው እሑድ ሕዳር 8 / ኖቬምበር 17 ለምርቃት ስላሰናዱት "እኔ ማነኝ?" መፅሐፋቸው ዋነኛ ጭብጦች ይናገራሉ።

አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገለጠች 12.11.2024

የአፍሪካ ኅብረት በአዲሱ የሰላም አስከባሪ ኃይል የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚያከብሩ አገራት ብቻ ይሳተፋሉ አለ

The impacts of First Nations tourism - የነባር ዜጎች ቱሪዝም ተፅዕኖዎች 12.11.2024

Are you seeking a truly impactful Australian travel experience? Whether you’re seeking wilderness, food, art or luxury, there are plenty of First Nations tourism adventure that you can explore, led by someone with 65,000 years of connection to this land. Not only will you deepen your experience, but you’ll help drive cultural and economic opportunities for First Nations communities. - እውነተኛ የሆነ አይ...

“ኢትዮጵያን የሁሉም ነገዶች ቤት ሆና ኖራለች፤ ትኖራለች፤ ክልላዊነትን ዝቅ ማድረግ ያስፈልጋል” ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 12.11.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ ለሕትመት ስላበቁት “ሰሎሞናውያን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ (1262 - 1521) ጭብጦች ይናገራሉ።

ሰሎሞናውያን ከሮሃ ይልቅ አክሱምን፤ ከአምሐራ፣ ሐበሻ (ት) ይልቅ ብሔረ- ኢትዮጵያን ለምን መረጡ? 12.11.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ ለሕትመት ስላበቁት “ሰሎሞናውያን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ (1262 - 1521) ጭብጦች ይናገራሉ።

“አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥታዊ፣ ሃይማኖታዊና ወታደራዊ ሥርዓቶች የቆሙት በመካከለኛው ዘመን ነው” ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 12.11.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ ለሕትመት ስላበቁት “ሰሎሞናውያን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ (1262 - 1521) ጭብጦች ይናገራሉ (ዳግም የቀረበ)።

ዝክረ መታሰቢያ፤ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ገጣሚ ዜናነህ መኮንን 11.11.2024

"የኩላሊት ሕመም እንደያዘኝ ከማወቄ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ የራሴ ስቱዲዮ እንዲኖረኝ ሃሳብ ነበረኝ" ያለን ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ገጣሚ ዜናነህ መኮንን በገጠመው የኩላሊት ሕመም ሳቢያ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተሰናብቷል። በሕይወት ሳለ ከ SBS አማርኛ ጋር ኢትዮጵያውያን ወገኖች ለሕመሙ መፈወሻ የችሮታ ጥሪ ያቀረበበትንና ስለ ሙያ ሕይወቱ በአንደበቱ የገለጠበትን ቃለ ምልልስ ዳግም አቅርበናል።

"በምንሔድበት ሁሉ ኢትዮጵያዊነታችንን አጉልተን የምንገልጥበት፤የይድነቃቸው ተሰማን ስም የምናስተዋውቅበት ተሞክሮዎች እንዲኖሩን ጥረቶችን እያደረግን ነው" አቶ ኢዮብ እሱባለው 11.11.2024

አቶ ኢዮብ እሱባለው፤ የይድነቃቸው ተሰማ ማኅበራዊ እግር ኳስ ክለብ የስልጠና ክፍል ኃላፊ፤ ከኦክቶበር 25-27 የይድነቃቸው ተሰማን ቡድን አካትቶ 313 ቡድኖችና ከ4000 በላይ ታዳጊ ወጣቶች ተሳትፈው የእግር ኳስ ግጥሚያ ስለተካሔድበት የሸፐርተን ዋንጫ 2024 ሂደትና ውጤት ይናገራሉ።

ኢትዮጵያ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ከሆኑባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል በሁለተኛነት ተጠቀሰች 10.11.2024

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ አርጌ በተባለች አነስተኛ ከተማ ሰሞኑን በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከ60 በላይ እንደቆሰሉ ተመለከተ

"ኢትዮጵያ ውስጥ የፅንስ ማቋረጥ/ማስወረድ ሕግ አንዳለ የሚያውቁ ዜጎች 55 ፐርሰንት ያህል ብቻ ናቸው፤ የግንዛቤ ክፍተት አለ" ዶ/ር ግዛቸው ተሰማ 10.11.2024

ዶ/ር ግዛቸው ተሰማ፤ በከርቲን ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ፅንስን የማቋረጥ / የማስወረድ አፋላሚ አስባብ ከሆኑት ከሕግ፣ ሃይማኖት፣ ሕክምና፣ ፖለቲካና ሥነ ምግባር አኳያ ነቅሰው ያስረዳሉ።

"ኢትዮጵያዊነት የደም፣ የባሕልና የቋንቋ ልውውጥ ውጤት ነው" ዶ/ር አውግቸው አማረ 07.11.2024

ዶ/ር አውግቸው አማረ አጎናፍር፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ናቸው። በ Journal of Afroasiatic Languages, History and Culture (JAAL) ላይ "በኢትዮጵያ የሕዝብና ባሕል ትስስር የጦር ሠራዊቱን ሚና የሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች (ከ14ኛው እስከ 16ኛው መካከለኛ ክፍለ ዘመን)" በሚል ርዕስ መጣጥፋቸውን ለሕትመት አብቅተዋል። በዘመኑ 'የጨዋ ሠራዊት' ተብሎ ይጠራ ስለነበረው የጦር አደረጃጀት ታሪክና የብሔራዊ ማንነት ግንባታ አስተዋፆ ታሪካዊ ዋቤ ነቅሰው ያመላክታሉ።

"የጨዋ ሠራዊት በተሠማራበት ሁሉ ቀልጦ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በማስጠበቅ ቀጣይ አድርጓል" ዶ/ር አውግቸው አማረ 06.11.2024

ዶ/ር አውግቸው አማረ አጎናፍር፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ናቸው። በ Journal of Afroasiatic Languages, History and Culture (JAAL) ላይ "በኢትዮጵያ የሕዝብና ባሕል ትስስር የጦር ሠራዊቱን ሚና የሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች (ከ14ኛው እስከ 16ኛው መካከለኛ ክፍለ ዘመን)" በሚል ርዕስ መጣጥፋቸውን ለሕትመት አብቅተዋል። በዘመኑ 'የጨዋ ሠራዊት' ተብሎ ይጠራ ስለነበረው የጦር አደረጃጀት ታሪክና የብሔራዊ ማንነት ግንባታ አስተዋፆ ታሪካዊ ዋቤ ነቅሰው ያመላክታሉ።

#74 Talking about your pet peeves (Med) 06.11.2024

Learn how to talk about things that annoy you.

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.