SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ሶርያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ የተርኪዬ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠየቁ 23.12.2024

በቪክቶሪያ ለተከሰተው የሰደድ እሳት በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ በሚታየው የአየር ለውጥ ሳቢያ ሊባባስ እንደሚችል ተነገረ

"የኢትዮጵያ ቀን ግብዣችን ለሁሉም ነው፤ እኛ ኢትዮጵያዊነትን አንሰጥም፤ አንነፍግም" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 23.12.2024

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ዲሴምበር 28 / ጥር 20 በሜልበርን - አውስትራሊያ ተከብሮ ስለሚውለው የኢትዮጵያ ቀን ፋይዳዎች ይናገራሉ። ግብዣቸውንም በማኅበሩ ስም ያቀርባሉ።

"በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም እንኳ ኢትዮጵያ ስትጠራቸው እጅግ የሚያኮራ ድጋፍ ማድረጋቸውን እናደንቃለን" ሚ/ር ጫልቱ ሳኒ 20.12.2024

ጫልቱ ሳኒ፤ የኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው፣ የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘርፈ ብዙ የሀገር ግንባታ ሁነኛ ሚናዎችና ተጠቃሚነትን ይገልጣሉ።

"የአውስትራሊያ ከተሞችን በመጎብኘት ለከተሞቻችን የበለጠ ዕድገት፣ ውበትና ምቹነት የሚያግዙ መሠረታዊ ነገሮችን ለመቅሰም ዕድል አግኝቻለሁ" ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ 20.12.2024

ጫልቱ ሳኒ፤ የኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ ሰሞኑን አውስትራሊያ ተገኝተው ስላካሔዱት ይፋ የሥራ ጉብኝት ዓላማና ፋይዳዎች ይናገራሉ።

"ፍቅር ዘላለማዊ እንዲሆን እንመኛለን፤ ዘላለማዊ እንዳልሆነ እያወቅን፤ የፍቅርን ጅማሬ እንጂ መጨረሻውን አናውቅም" ደራሲት ከበደች ተክለአብ 19.12.2024

ደራሲት ከበደች ተክለአብ ሰሞኑን በቀይ ባሕር ፕሬስ ለሕትመት ስላበቋቸው "የት ነው?" እና "ሱታፌ" መፅሐፍት ይዘቶች ይናገራሉ፤ ያስደምጣሉ።

"በልዩነት መሃል የሰውነትን ሰብዓዊነት መገንዘብ ትልቅ ነገር ነው፤ በጥቃቅን ነገሮች መስማማት ከቻልን በትልቁም መስማማት እንችላለን" ደራሲት ከበደች ተክለአብ 19.12.2024

ደራሲት ከበደች ተክለአብ ሰሞኑን በቀይ ባሕር አሳታሚ በኩል ለአንባብያን እነሆኝ ስላሏቸው "የት ነው?" እና "ሱታፌ" መፅሐፍት ጭብጦች ይናገራሉ። ከሥነ ግጥሞቻቸው መካከልም ነቅሰው ያስደምጣሉ።

Summer listening: Into the bush | Let's go bushwalking (Adv) 18.12.2024

Learn how to talk about bushwalking. Plus find out tips on how hikers can stay safe and have fun.

"የት ነው?" ገጣሚት፣ ደራሲትና መምህርት ከበደች ተክለአብ 18.12.2024

በሥነ ግጥም፣ ቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎች ዘርፍ ስመጥር ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆኑት ከበደች ተክለአብ፤ ዳግም ለሕትመት ስላበቁት "የት ነው?" መፅሐፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን አዲስ ስላሳተሙት "ሱታፌ" መፅሐፍ ይዘት ያስረዳሉ፤ ከግጥሞቻቸውም ጥቂቶቹን በአንደበታቸው ያስደምጣሉ።

Are gambling organisations targeting CALD communities? - የቁማር ድርጅቶች ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባትን ዒላማቸው አድርገዋልን? 17.12.2024

Australians lose $32 billion a year to gambling — more per person than any other nation. And it’s affecting diverse communities differently. - አውስትራሊያውያን በዓመት በቁማር 32 ቢሊየን ዶላር ያጣሉ፤ በግለሰብ ደረጃ ከማናቸው አገር በበለጠ። በተለየ ሁኔታም ዝንቅ ማኅበረሰባቱ ላይ ጉዳትን እያስከተለ ነው።

Summer listening: Into the bush | Let's go fishing! (Med) 16.12.2024

Learn how to talk about fishing. Plus, find out a bit of history on why Australians love fishing.

ጉዞ ወደ አውስትራሊያ፤ "ባለ ጋቢው" ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ 16.12.2024

ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ፤ ሜልበርን - አውስትራሊያ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 በሚካሔደው 28ኛው ዓመታዊው የእግር ኳስ ውድድርና የኢትዮጵያ ቀን ክብረ በዓል ላይ ይገኛል። የሕይወት ጉዞውን ከጠዳ እስከ አውስትራሊያ አንስቶ ያወጋል።

"በ13ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ብሔረሰቦች መካከል አርጎባ ነበር" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ 12.12.2024

ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ፤ የ"ኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፍ ደራሲ፤ በኩሽና ኩሻዊነት ዙሪያ ያሉ ብዥታዎችን ያመላክታሉ። የማረቂያ ምክረ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።

በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ ዕውቅናና ውክልና ያላቸው 76 ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ናቸው ተባለ 11.12.2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያውን ደብር ሰየመች

"የጥንቱ የኩሽ ሀገረ መንግሥት ከአሁኑ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር ምንም ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም" ዶ/ር ግርማ ደመቀ 10.12.2024

ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ ሰሞኑን ለሕትመት ስላበቁት "የኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፋቸው ጭብጦች ያስረዳሉ።

"ካለፈው ዓመት ዘንድሮ አንድነታችንን አጠንክረናል፤ ኢትዮጵያውያንን አነቃቅተናል" ወ/ት ገነት ማስረሻና አቶ አሕመድ ዳውድ 09.12.2024

ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና አቶ አሕመድ ዳውድ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ንብረት ኃላፊ ዘንድሮ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 ስለሚካሔደው 28ኛው የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር መሰናዶና ሂደት ይናገራሉ።

ኢሰመኮ በኦሮሚያ አካባቢ የግዳጅ ምልመላ የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ እንደሚገባ አሳሰበ 09.12.2024

አምስቱ የቦብ ማርሌይ ልጆች የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በወርኃ ግንቦት ሊካሔድ ነው

"ትንሽ ፊደል ቀመስን በሚለውም ውስጥ ኩሽና ኩሻዊነትን በተመለከተ ማደናገር አለ" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ 08.12.2024

ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ የሥነ ልሳን ተጠባቢ ናቸው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ታሪክ ዙሪያ የምርምር ግኝቶችን ያካተቱ ደርዘን የተጠጉ መፅሐፍትን ለሕትመት አብቅተዋል። ሰሞኑንም በኩሽ ዙሪያ በውዥንብር የታጨቁ ዕይታዎችን ለማጥራት በሚል ሙያዊ ኃላፊነት ዕሳቤ "ኩሽ እና ኩሻዊ" በሚል ርዕስ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ የፈጀ ጥናታዊ ሥራቸው የተካተተበትና የሁለት ዓመታት የጽሕፈት ጊዜያትን የወሰደባቸውን የአዕምሮ ጭማቂ የመጽሐፍ በረከታቸውን ለአንባብያን እነሆኝ ብለዋል። ከዶ/ር ግርማ ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ በእዚሁ አልተቋጨም። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን የኩሽ ነገድ፣ ሀገረ መንግሥትና የመፅሐፍ ቅዱስን የኩሽ አጠቃቀም አንስተው...

"ኔልሰን ማንዴላን ከአንድ ሳምንት በላይ አስታመናል፤ ከእሥር ነው የወጡት ምንም የላቸውም በሚል 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሰጥቻለሁ" የቀድሞው ፕ/ት መንግሥቱ ኃ/ማርያም 05.12.2024

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የSBS አማርኛ እንግዳ ሆነው ለሁለት ጊዜያት ቀርበዋል። በቀዳሚነት ለደቡብ ሱዳን ነፃነትና ሉዓላዊነት የኢትዮጵያን አስተዋፅፆዎች በማስረዳት፤ ዳግም "ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት ኮከብ ሆና እንደኖረችና ከልጅነት ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲያስቡ፣ ኢትዮጵያን እንደ ተስፋ ሲመለከቱ የኖሩ ሰው መሆናቸውን፤ በሂደትም የተገነዘቡትና ያዩትም ይህንኑ መሆኑን" ከእሥር እንደተፈቱ ያወጓቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ ዲሴምበር 5, 2013 የዛሬ 11 ዓመት ከእዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስመልክተው። የማንዴላን ዝክረ መታሰቢያ አስባብ አድርገን ቃለ ምልልሱን ደግመን አ...

#76 Getting a gift (Med) 04.12.2024

Learn how to talk about getting a gift for someone. Plus, find out what the Secret Santa tradition is all about.

በኢትዮጵያ ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ እንዳለ ተገለጠ 04.12.2024

ለኢትዮጵያ በየዓመቱ 270 ሚሊየን ኮንደም የሚያስፈልግ ቢሆንም ወደ ሀገር ቤት እየገባ ያለው የኮንደም መጠን ከ90 ሚሊየን ያልበለጠ ነው።

የሜልበርን ኢሬቻ በዓል ነፃ አገልግሎት ሰጪ የማኅበረሰብ አባላት የብሩስ በጎ ፈቃደኞች ዕውቅና ሽልማት 2024 ተሸላሚ ሆኑ 03.12.2024

የሜልበርን ኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ፣ ኦቦ ዳኜ ደፈርሻ፣ ኦቦ በንቲ ኦሊቃ እና አዴ ኢፍቱ ሚደቅሳ በተለይ በተከታታይ ለዓመታት ለኢሬቻ በዓል ትውውቅና አከባበር ላበረከቱት የማኅበረሰብ አገልግሎቶች የዘንድሮውን የብሩስ በጎ ፈቃደኞች ዕውቅና ሽልማት ከፌዴራል ኢሚግሬሽንና ዜግነት ረዳት ሚኒስትር ጁሊያን ሂል እጅ ተቀብለዋል።

ከኢትዮጵያ ባንኮች የተሰረቀው የገንዘብ መጠን ከአምናው 1 ቢሊየን ብር ዘንድሮ ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ከፍ አለ 01.12.2024

የገንዘብ ምንዛሪው ገበያ መር መሆን የሀገሪቱ ጥቅል ምርት ዕድገት በቀጣዮቹ ወራት በሶስት በመቶ እንዲቀንስ፤ የዋጋ ግሽበቱ ከ10 በመቶ በላይ እንዲጨምር እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር አመላከተ

ኢትዮጵያን እንታደግ፤ ከውጭ ምንዛሪ ድጎማ ወደ ረድኤት ድርጅት 01.12.2024

ዶ/ር ግርማ ሞላ፤ የኢትዮጵያን እንታደግ ግብረሰናይ ድርጅት ሊቀመንበር፤ ስለ ረድኤት ድርጅቱ ሚና ያስረዳሉ።

#75 Discussing eyesight and vision (Med) 28.11.2024

Learn how to talk about eyesight getting worse. Plus, find out why people with lighter eye colour have a higher risk of UV damage.

"ጤናማ ልጅ ለመውለድ እናቶች አንባቢ መሆን አለባቸው" በየነ መረሳ 27.11.2024

በየነ መረሳ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የነርስነትና አዋላጅነት ትምህርት ቤተ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ፤ በቪክቶሪያ ነዋሪ በሆኑ አፍሪካውያን ሴቶች ላይ በማካሔድ ላይ ስላሉት የቅድመ እርግዝና ክብካቤ ጥናታዊ ምርምር ፕሮጄክት ያስረዳሉ።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.