SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
"ሰንደቁን እንደ አንድ ዋርካ ነው የምናየው፤ ሰውን በዘሩ፣ በሃይማኖቱ የማያርቅ ሰው ነው ያጣነው" አቶ መስቀሉ ደሴ 14.01.2025 11:45
አቶ ሰንደቁ ተሰማ፤ በምዕራብ አውስትራሊያ - ፐርዝ ከተማ በታክሲ አገልግሎት ሥራ ላይ ተሠማርተው ሳለ፤ በፖሊስ ገለጣ መሠረት ሆን ብሎ መንገድ አሳብሮ በመጣ መኪና በደረሰባቸው የግጭት አደጋ ከጫኗቸው ሁለት ተሳፋሪዎቻቸው ጋር በ58 ዓመታቸው ከባለቤታቸውና ሶስት ልጆቻቸው ተነጥለው ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
"በዓለ ጥምቀት በሃይማኖትም፣ በማኅበራዊም፣ እንዲሁም፤ ባሕልን አስጠብቆ ለትውልድ ለማውረስ ትልቅ ፋይዳ አለው" ቀሲስ አንተነህ ወርቁ 14.01.2025 11:53
ቀሲስ አንተነህ ወርቁ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ዲያቆን ዳዊት ይርጉ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ፤ ስለ ዘንድሮው የሲድኒ በዓለ ጥምቀትና በዓለ ጊዮርጊስ አከባበር መርሃ ግብሮችና ትሩፋቶች ይገልጣሉ።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ አዲስ አበባና ሞቃዲሾ ላይ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ውክልና ለማድረግ ተስማሙ 12.01.2025 11:43
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደገና እንዲዋቀር ተጠየቀ
"ኤርምያስ ወንድሙ ከመሀል ሜዳ መትቶ ያስቆጠራት ግብ ዛሬ ድረስ ባልንጀሮች ሆነን እንድንቀር መንሰአኤ ናት ።" - ሻምበል በላይነህ 09.01.2025 16:20
ድምጻዊ ሻምበል በላይነህ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ኤርሚያስ ወንድሙ ሩብ ምእተ አመት ያስቆጠረው የጓደኝነታቸውን ትሩፋት አጫውተውናል ።
ሶስና ወጋየሁ፤ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሀገረ አውስትራሊያ 09.01.2025 18:30
ሶስና ወጋየሁ፤ ስርከስ ኢትዮጵያ ካፈራቸው ምርጥ ኮከቦች አንዷ ናቸው። ከሜክሲኮ አደባባይ ውልደትና ዕድገታቸው እስከ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃ ሕይወታቸው ያወጋሉ።
"የእኔ ሕልም ኢትዮጵያውያን ተስማምተው፤ በአንድነት ሀገራቸውን አሳድገው እኩልና ባለፀጋ እንዲሆኑ ነው፤ በሕይወት ዘመኔ ይኼ ሆኖ አያለሁ ብዬ አላስብም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ 09.01.2025 10:11
ያለ ዝንፈት ሁሌም ውድ ሀገሬ ብለው በጠሯት የኢትዮጵያ ዕቅፍ ውስጥ ዳግም ላይመለሱ ለዘላለሙ ያረፉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ሀገራቸውን በምጣኔ ሃብት ባለሙያነት በምክትል የፋይናንስ ሚኒስትርነት፣ በዓለም አቀፍ መድረክ በዓለም ባንክና በተባበሩት መንግሥታት፣ በፖለቲካው መስክ ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማ የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል። በሕይወት ሳሉ ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ በዝክረ መታሰቢያነት ደግመን አቅርበናል።
በዓለ ልደት በኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን ዘንድ 07.01.2025 8:35
ወ/ሮ ወጋሐተ መለስ (ከሜልበርን)፣ አቶ ጥላዬ ታረቀኝ (ከብሪስበን)፣ እና ወ/ሮ ሱዛ አበበ (ከፐርዝ)፤ እንደምን በዓለ ልደት 2017ን እንዳከበሩ ይገልጣሉ፤ የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውንም ያስተላልፋሉ።
"ይህን ታላቅ በዓል በአውስትራሊያና የተለያዩ ቦታዎች ለምታከብሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን፤ ምኞቴም ፀሎቴም የሕይወት ለውጥ እንዲሆንላችሁ ነው" ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 06.01.2025 6:37
ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ በዓለ ልደትን አስመልክተው መንፈሳዊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።
"በዓሉ የእምነት፣ የትህትና፣ የደስታና የሰላም እንደመሆኑ እግዚአብሔር የደስታ በዓል ያድርግልን፤ በመከራ ውስጥ ያሉ ወገኖችን በምሕረት እጁ ይጎብኝልን" ቀሲስ መልአከ ፀሐይ 06.01.2025 7:57
መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የገና በዓልን አስመልክተው መንፈሳዊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያና ሶማሊያ አልሻባብን ለመፋለም ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቀ 05.01.2025 12:25
ሴት እንጀራ ልጁን ለ10 ዓመታት አስገድዶ ሲደፍር ቆይቶ የገደላት ግለሰብ የሞት ፍርድ ተበየነበት
"በእርግዝና ወቅት ማጤስ ለከማኅፀን ውጪ እርግዝና ያጋልጣል፤ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው እናቶች ልጆች በሁለት እጥፍ ለኦቲዝም የተጋለጡ ይሆናሉ"ዶ/ር በረከት ዱኮ 05.01.2025 20:18
ዶ/ር በረከት ዱኮ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ተመራማሪ ናቸው። በቅርቡ ከአንድ አጥኚ ቡድ ጋር በመሆን በቅድመ እርግዝናና በእርግዝና ወቅት ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች ላይ የሚከሰቱ የጤና ጠንቆችን፤ እንዲሁም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ሴቶች የሚወልዷቸው ልጆች ለኦቲዝም ተጋላጭነታቸው እጥፍ መሆኑን ስለሚያመላክተው የጥናት ግኝቶቻቸው ያስረዳሉ።
የኢትዮጵያውያን-አውስራሊያውያን የ2025 አዲስ ዓመት ተስፋና ምኞቶች 05.01.2025 7:39
ኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዮናስ ሐጎስ (ከብሪስበን)፣ ቲቲ ጥሩነህ (ከሜልበርን) እና አዱኛ ኢቲቻ (ከፐርዝ)፤ የ2024 ስንብትንና የ2025 አዲስ ዓመት ቅበላን አስመልክተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለገናና ጥምቀት በዓላት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ በረራዎችን መመደቡንና የዋጋ ጭማሪም ማድረጉን አስታወቀ 01.01.2025 8:45
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሕወሓት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ከዋጋ ግሽበት ቅነሳ እስከ የግዴታ መጠባበቂያ ተቀማጭ ሂሳብ ላይ ማስወሰኑን አስታወቀ 01.01.2025 7:56
የ2025 አዲስ ዓመት ቅበላ በዓለም ዙሪያ ተካሔደ
"በሜልበርን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ፍቅር፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ ሰላማዊነትና አንድነት እረክቻለሁ" የሀገረ ጀርመን ነዋሪ አቶ ደረጀ ኃይሉ 31.12.2024 7:37
ከ28ኛው የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር ጋር ተያይዞ ዲሴምበር 28 / ታሕሳስ 19 በድምቀት ተከብሮ የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ ቀን በማስመልከት ጎብኚና ነዋሪ የማኅበረሰቡ አባላት አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።
"የስፖርት ውድድሩና የኢትዮጵያ ቀን ካሰብነው በላይ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቅቋል፤ ዓመቱን ሙሉ በልጆቻችን የሚናፈቅ እናድርገው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 30.12.2024 14:35
28ኛው የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር መጠናቀቅን አስመልክቶ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፣ የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ ስቲት ሁመራ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ወጣት ዮሃንስ እና ቢንያም ከበደ፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የ renewaustraliaforall.org አስተባባሪና ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።
ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ መካተት እስካሁን አልተረጋገጠም 29.12.2024 13:09
መንግሥት በአምስት የሲቪል ማኅበረሰብ ላይ የጣለውን ዕገዳ እንዲያነሳ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
"28ኛውን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር ጀምረናል፤ 'የኢትዮጵያ ቀን' ን በጉጉት እየተጠባበቅን ነው" አስተባባሪዎችና ታዳሚዎች 26.12.2024 5:43
የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያዎችና ውጤቶች
"ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች!"ተወዳጅ ሚዲያና የአንጋፋ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዕውቅናና ምስጋና 26.12.2024 22:48
ዕዝራ እጅጉ፤ የተወዳጅ ሚዲያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የ"ታላላቆቻንን እናክብር" የዕውቅናና ምስጋና ሽልማት ተሽላሚ ስለሆኑት 13 አንጋፋ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጉልህ ሥራዎችን በማጣቀስ የውርሰ አሻራዎቻቸውን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ፋይዳዎች ያስገነዝባል።
" እንኳን ለፈረንጆቹ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ " - ዶ/ር ግርማ ሞላ 25.12.2024 2:02
ዶ/ር ግርማ ሞላ የኢትዮጵያን እናድን ሰብሳቢ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውን የፈርንጆቹን የገና በዓል እንዲሁም የመጪውን አዲስ ዓመት እና የኢትዮጵያን ገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡
ቪክቶርያ ከ2019 በኋላ ከፍተኛ በተባለ የእሳት አደጋ ስጋት ላይ ወድቃለች ተባለ 25.12.2024 7:41
ከአውስትራሊያ ውጭ አገራቸውን በማገልገል ላይ ያሉ የጦር ኃይል አባላት የገና በዓልን አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላለፉ
ከመተሀራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ 25.12.2024 7:25
ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የአፍሪካ የቀረጥ ነፃ አገራት ዝርዝር ዳግም መመለስ አልቻለችም
"ለP2P 25ኛ ዓመት የደረስነው ትኩረታችንን ጎሣ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ላይ ሳይሆን ሳይማር ያስተማረን ሕዝባችን ላይ በማድረግ ነው" ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ 24.12.2024 19:44
ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ፤ የPeople To People Inc (P2P) የቦርድ ሊቀመንበርና ዶ/ር እናውጋው መሃሪ፤ የPeople To People Inc (P2P) መሥራችና ፕሬዚደንት፤ የP2Pን የ25 ዓመታት የሕክምና መስክ ዋነኛ አስተዋፅዖዎችና የወደፊት ውጥኖች አንስተው ይናገራሉ።
"የ P2P አነሳስ 'የሰዎች ችግር፤ በሰዎች ይፈታል' በሚል ዕሳቤ ነው" ዶ/ር እናውጋው መሃሪ 23.12.2024 14:37
ዶ/ር እናውጋው መሃሪ፤ የPeople To People Inc (P2P) መሥራችና ፕሬዚደንት፤ ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ፤ የPeople To People Inc (P2P) የቦርድ ሊቀመንበር፤ የሩብ ክፍለ ዘመን የአገልግሎት ዓመታትን ስላስቆጠረው P2P ጅማሮና አስተዋፅዖዎች ያስረዳሉ።
አዲስ አበባ ለመኖር ውድ ከሆኑ ከተሞች መካከል ተካተተች 23.12.2024 10:57
'ሕወሓት ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው' ሲሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመላከቱ
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.