SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
"የኤርትራ ሁለት ትናንሽ ከተሞች ግርዛትን ትተዋል የሚለው ሪፖርት ደስ የሚል ነው፤ ግርዛት የጠፋ ጎጂ ባሕል አይደለም" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም 06.02.2025 9:14
ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፤ ፌብሪዋሪ 6 / ጥር 29 የልጃገረዶችና ሴቶች ግርዛት የሚያስከትላቸውን አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት በመላው ዓለም በግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንነት የማሰቡን ፋይዳዎች አስመልክተው ይናገራሉ።
ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጥኤማውያንን ከጋዛ ወደ አጎራባች አገራት በቋሚነት የማስፈር አተያያቸውን ደግመው አነሱ 05.02.2025 7:13
ዩክሬይን በሩስያ እጅ ያለውን አውስትራሊያዊ የጦር እሥረኛ ለማስለቀቅ እንደምትደራደር ቃል ገባች
በሞት የተለዩ ተጠርጣሪዎችን ንብረት እንዲወረስ የሚያደርገው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ግብር ላይ ሊውል ነው 04.02.2025 8:18
የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል አካባቢ በሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በተለምዶ ሸኔ) ላይ ዒላማ ያደረገ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት ሥራውን በይፋ ጀመረ 04.02.2025 3:21
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳና ሜክሲኮ ላይ የጣሉትን የ25 ፐርሰንት ታሪፍ ለ30 ቀናት ግብር ላይ ከመዋል ተገትቶ እንዲቆም ወሰኑ
"በየዓመቱ የመሰባሰባችን ዓላማ በሜልበርን የሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት እንዲተዋወቁ፣ እንዳይረሳሱና ወደ አንድነት እንዲመጡ ለማስቻል ነው" ኦቦ ተስፋዬ ደፋ 04.02.2025 6:17
አቶ አብዱሰላም ሁሴን፤ በሜልበርን የኦሮሞ አረጋውያን በጎ አድራጎት ፕሬዚደንትና አቶ ተስፋዬ ደፋ፤ በሜልበርን የኦሮሞ አረጋውያን በጎ አድራጎት ፀሐፊ፤ ቅዳሜ ጥር 24 ከኦሮሞ ሲቪክ ድርጅቶች ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ስላዘጋጁት የእራት ግብዣ ተልዕኮ ያስረዳሉ።
"የእግር ጉዞው ዓላማ ራቅ ባለው ዓለም የሚኖሩ ወገኖቻችንን በመንፈሳዊ፣ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ሀገራዊ ጉዳይም እንዲቀራረብ ማድረግ ነው"መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ 03.02.2025 17:50
መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሰሜን አፍሪካ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ - በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሶስተኛ ጊዘ ስላዘጋጀችው "ታላቁ የእግር ጉዞና የቤተሰብ ቀን" ዓላማና መርሃ ግብር ያስረዳሉ።
'አንድ ሀገራዊ ቋንቋን በግልፅ አላሠፈረም፣ ሕገ መንግሥቱን ይቃረናል፣ የሕዝብ መግባባትን ይቀንሳል' የሚል የሰላ ትችት የደረሰበት አጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ፀደቀ 02.02.2025 10:51
ብልፅግና ፓርቲ ነባር አመራሮቹን በድጋሚ መረጠ
በአማራ ክልል የዘፈቀደ ጅምላ ታሣሪዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሊያም ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ባለው የወንጀል ሕግ ክስ ይመሥረትባቸው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ 30.01.2025 3:52
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ተቀማጭ 2 ነጥብ 74 ትሪሊየን ብር መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
የአውስትራሊያ የዋጋ ግሽበት ዝቅ አለ 29.01.2025 7:44
የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ዕገዳ የጣሱ ርዕሰ መምህራን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጠ
"የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁ 29.01.2025 21:53
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ገታ 28.01.2025 7:15
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየጨመረ የመጣውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለማስቀረት በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሊያጣራ ነው።
በአፋር፣ ኦሮሚያና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው ርዕደ መሬት ከ99 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ለጉዳት መዳረጉ ተመለከተ 26.01.2025 13:13
የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች 'የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፍረስ ወስነናል' መባሉን እናወግዛለን አሉ
በአማራ ክልል ያለውን የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል ለመቋቋም መምህራን የጉልበት ሥራ ለመሥራት ግድ መሰኘታቸው ተመለከተ 22.01.2025 9:24
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት በይፋ የተመዘገበው የፍቺ መጠን በ34 በመቶ ሲጨምር የጋብቻ መጠን በሰባት በመቶ ቀንሷል።
Celebrating, reflecting, mourning: Indigenous and migrant perspectives on January 26 - አከባበር፣ ምልሰታዊ ምልከታ፣ ሐዘን፤ የነባር ዜጎችና ፍልስተኞች የጃኑዋሪ 26 አተያይ 21.01.2025 7:56
Some celebrate Australia Day with patriotic pride, others mourn and protest. What’s the right way to mark January 26, and can you have pride in your country while also standing against injustice? - የተወሰኑቱ የአውስትራሊያ ቀንን በአርበኛነት ስሜት ያከብሩታል፤ ሌሎች በፊናቸው በሐዘንና ተቃውሞ ያስቡታል። ጃኑዋሪ 26ን ተገቢ በሆነ መልኩ የማክበሪያ መንገዱ እንደምን ነው? ኢ-ፍትሐዊነትን ተፃርረው ቆመው ሳለ በሀገርዎ ላይ ኩራት ይሰማዎታልን?
"አባቶቻችን አንድ የሚያደርግ፤ የሚያሰባስብ ጥምቀትን ፈጥረውልናል፤ ልንጠብቀው የሚገባ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ዕሴት ነው" አቶ ሰለሞን በላይ 21.01.2025 6:43
በዓለ ጥምቀት በሀገረ አውስትራሊያ ሜልበርን በድምቀት ተከብሮ አልፏል። የሜልበርን ነዋሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት የመጡ ኢትዮጵያውያን የበዓሉን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ።
ሶስና ወጋየሁ፤ ከአውስትራሊያ ጥገኝነት ጥየቃ ለክብር ሽልማት መብቃት 21.01.2025 14:15
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ እንደምን በሀገረ አውስትራሊያ ከጥገኝነት ጥየቃ ለከፍተኛ የክብር ሽልማት እንደበቁ ያወጋሉ።
#77 Setting up a tent (Med) 21.01.2025 15:43
Learn how to talk about setting up a tent.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማካሔድ ተቋሙ የሚመራበትን አዋጅ ለማሻሻል መዘጋጀቱን አስታወቀ 20.01.2025 11:11
በጦርነት ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረውን የአዋሽ - ወልዲያ ሃራ ገበያ ባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ
በሜልበርን የጥምቀት በአል እንዴት አለፈ ? በካህናት ዕይታ 19.01.2025 16:01
መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤እንዲሁም መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ አባተ፤ በምሥራቅ አውስትራሊያ አኅጉረ ስብከት የሜልበርን ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በካህናቱ እና ምእመናኑ የጋር ሥራ የተዋጣለት በዓል እንደነበረ ተናግረዋል ።
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ ኢትዮጵያን ከራሷ ልጆች ማን ያድናታል? 19.01.2025 17:59
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።
"እንኳን ለበአለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ።"- ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ 17.01.2025 8:51
መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ ጥምቀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሀንስ እጅ መጠመቁን የምታዘክረበት በአል ነው ብለዋል ።
የጥምቀት ዋዜማ፤ የሙዚቃ ድግስ በሜልበርን 17.01.2025 8:33
አንጋፋውን ድምፃዊ ሻምበል በላይነህን ማዕከል ያደረገ፤ በሜልበርን ምርጥ ድምፃውያንና ሙዚቀኞች የታጀበ የሙዚቃ ድግስ ምሽት ስለመሰናዳቱ አስተባባሪው አቶ አበራ አያሌውና የጥበብ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።
"ሕዝቤ የማያውቀውንና ከሕይወቱ ጋር ግንኙነት በሌለው የባዕዳን ሀገር ዕውቀትና ሀብት ራሴን ትልቅ አድርጌ ለማቅረብ የምሞክር ዘመናዊ ደንቆሮ አይደለሁም" ዶ/ር ይርጋ ገላው 16.01.2025 12:38
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።
"የተራቡትን ይመግብልን፣ የተበተኑትን ይሰብስብልን፣ በዓላችን የታይታ ሳይሆን የክብር በዓል ይሁንልን" መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ 15.01.2025 28:11
መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ ተስፍዬ፣ የደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ዜናዊ ቸኮል፣ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ መል አከ ሕይወት ቀሲስ ሰናይ ዜና፣ የመካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ በዓለ ጥምቀት የሚከበርበትን ዋነኛ ምክንያትና ፋይዳዎች አንስተው ይናገራሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥትና ታጣቂ ኃይሎች መካከል በየትኛውም ሥፍራ ንግግር እንዲደረግ ለመደገፍ ዝግጁነቷን ገለጠች 15.01.2025 8:34
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለስልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሾመለት
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.