SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

በ2025 የአፍሪካ 10 ወታደራዊ ኃያል ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 5ኛ ደረጃ ላይ ተመደበች፤ ከዓለም 52ኛ ደረጃን ይዛለች 14.04.2025

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል አጀንዳዎችን ተረከበ

ዝክረ መታሰቢያ፤ "ትምህርት የሰው ልጆች ሁሉ ዕድል ማግኛ መንገድ ነው፤ ትልቅ በር ይከፍታል" ኡርጌ ፈቃዱ ዲነግዴ 11.04.2025

የኡርጌ ፈቃዱ ዲነግዴ ሕልፈተ ሕይወት ውርሰ አሻራ ሕፃናትን በትምህርት አበልፅጎ ለሙሉዕ ሰውነት ማብቃት ነው። ተስፋዋን ብሩህ፣ ሕልሟን ዕውን ለማድረግ ለቅዳሜ ኤፕሪል 12 ዓለም አቀፍ ዝክረ መታሰቢያ ተሰናድቶላታል። አቶ ያደታ ሞሲሳና አቶ ዑመር ኩጂ የዝግጅቱን ሂደትና ፋይዳ አንስተው ያስረዳሉ።

"አውስትራሊያ ውስጥ በምርጫ ወቅት ድምፅ አለመስጠት ሕግ እንደመጣስ ይቆጠራል፤ መራጭነት መሠረታዊ መብትና ኃላፊነት ነው" አቶ አናንያ ኢሳያስ 10.04.2025

አቶ አናንያ ዳንኤል ኢሳያስ፤ የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ቃል አቀባይ፤ ሜይ 3 / ሚያዝያ 25 የሚካሔደውን የአውስትራሊያ የፌዴራል ምርጫ ሂደትና የኮሚሽኑን ሚናዎች አስመልክተው ያስረዳሉ።

"ልጄ ሳላስበው ተለየችኝ፤ አደራ የእናንተው ወገን፣ የእናንተው ደም ናት" እናት አልማዝ አባተ 09.04.2025

የወ/ሮ ትርንጎ አባተ የሕይወት ጉዞ ከሀገረ ኢትዮጵያ ተነስቶ በሕልፈተ ሕይወቷ አውስትራሊያ ላይ አክትሟል። በዘላለማዊ ስንብቷም ተስፋና ሕልሞቿም አክትመዋል። ቅዳሜ ኤፕሪል 12 / ሚያዝያ 17 በደብረ ፅዮን ቤተክርስቲያን ፀሎተ ፍትሐት ክንውን በኋላ የቀብር ሥነ ሥርዓቷ በBulla Cemetery ከቀትር በኋላ 12:30 pm ይፈፀማል።

በመጀመሪያ ዙር የመሪዎች የፌዴራል ምርጫ ክርክር መራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን አሸናፊ አድርገው ሰየሙ 09.04.2025

ሰሜን ኮሪያ ከኑክሊየር ጦር መሣርያዬ አልለይም አለች

በኢትዮጵያ የእሥራኤል አምባሳደር የአፍሪካ ኅብረት የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ ለመዘከር ካዘጋጀው ስብሰባ ተገድደው እንዲወጡ ተደረገ 09.04.2025

በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ሴቶችን ከማኅበራዊ ተሳትፎ እየገደበ ነው ተባለ

በጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚና የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን መካከል ማምሻውን የመጀመሪያ ዙር የምረጡኝ ዘመቻ ክርክር ይካሔዳል 08.04.2025

የግሪንስ ፓርቲ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ በተቻለ ፍጥነት የወለድ መጠን ቅነሳ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ

አውስትራሊያውያን የምርጫ ምዝገባ ቀነ ገደብ ሳያከትም ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ወይም የስምና አድራሻ ለውጦቻቸውን እንዲያስታውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ 07.04.2025

የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ከቤት ውስጥ መሥራትን ለማገድና ከ40ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን ለመቀነስ የነደፈው ፖሊሲ የተሳሳተ መሆኑን አመነ

በኢትዮጵያ ለቤት ሠራተኞች የጡረታ ክፍያ ሊጀመር ነው 07.04.2025

"ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ፤ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው" በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ

"ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ 03.04.2025

አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።

#83 Describing menopause symptoms (Med) - #83 Describing menopause symptoms (Med) 03.04.2025

Learn how to talk about menopause and its symptoms. - Learn how to talk about menopause and its symptoms.

የፌዴራል መንግሥቱ ለሶስት ሚሊየን አውስትራሊያውያን ሠራተኞች ተጨማሪ ደመወዝ ለማስገኘት እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ 02.04.2025

የተቃዋሚ ቡድን መሪው ዶናልድ ትራምፕን በታሪፍ ጭማሪ ላይ ተገዳድረው እንደሚቆሙ ገለጡ

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትን ያለ ክልሎች ፈቃድ ጣልቃ መግባት የሚያስችል የማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ 01.04.2025

በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ሥራዎች ለማጠናቀቅ 18 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለጠ

የፌዴራል መንግሥቱ በጀት ይፋ ከሆነ በኋላ የሌበር ፓርቲ የተቃዋሚ ቡድኑን እየመራ መሆኑን የሕዝብ አስተያየት ስብስብ አመለከተ 31.03.2025

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን እንዳስቆጧቸውና ለሶስተኛ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ለመቀጠል እያሰቡ መሆኑን ገለጡ

በፓስፖርት ድለላ ተሠማርተዋል የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች ተያዙ፤ 25ቱ ሴቶች ናቸው 30.03.2025

በባሕር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ - ኢትዮጵያውያን ሐዋላ የሚያስተላልፉበት አዲስ የክፍያ ሥርዓት ይፋ ሆነ

Why are we debating Welcome to Country? - በወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የምንሟገተው ስለምን ነው? 30.03.2025

The government's Welcome to Country spending has been heavily criticised but some believe the cultural protocol is being used as a "political football". - መንግሥት ለወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የሚያወጣው ወጪ በብርቱ ተትችቷል፤ በተወሰኑቱ ዘንድም ባሕላዊው ፕሮቶኮል ለ"ፖለቲካ እግር ኳስነት" መጠቀሚያ ሆኗል የሚል አመኔታንም አሳድሯል።

" እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ " ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 30.03.2025

በአገር ቤት ምንም እንኳን የሰላም ስጋቱም ሆነ የኑሮ ውድነቱ ህብረተሰቡን ለስጋት ቢጥልም ፤ የእስልምና እምነት ተከታዪች የረመዳን ጾምን በመረዳዳት አሳልፈው ፤ የኢድ አልፈጥር በአልን በደስታ እያከበሩ ነው ፤ ሲሉ በአገር ቤት የሚገኙት እና በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ የሆኑት ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር ተናግረዋል» በአውስትራሊያ ለሚገኙት የእምነቱ ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አድርሰዋል።

"የተማረ የሰው ኃይል በበቂ ቁጥር አለማግኘትን በተግዳሮት፤ ለችግር ፈቺነት መብቃትን በስኬት እንመለከታለን" ዶ/ር አሥራት አፀደወይን 27.03.2025

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አፀደወይን "ምርጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆንና ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት መብቃት የዩኒቨርሲቲያችን ርዕይ ነው" ይላሉ። የዩኒቨርሲቲውን 70ኛ፤ የአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፋይዳና ታሪካዊ ምልከታ አንስተው ያስረዳሉ።

ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ የመንግሥታቸው በጀት አማካይ ገቢ ላላቸው አውስትራሊያውያን 2500 ዶላር ያህል እንደሚያስገኝ ሲገልጡ የተቃዋሚ ቡድኑ የግብር ቅነሳውን አልደግፍም አለ 26.03.2025

ፕሮዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደራቸው ከፍተኛ አመራር አባላት ወታደራዊ ዕቅዶችን በማኅበራዊ ሚዲያ ኧፕ መወያይትን አስመልክቶ ምልከታ እንደሚያደርጉበት አስታወቁ

በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መኪናዎች ኤርትራውያንን ሲያጓጉዙ የተገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእሥራት ተቀጡ 25.03.2025

የኢትዮጵያ የግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያስመጡ ተፈቀደላቸው

"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤታችን ወደ ቀድሞ ስሙ 'ተፈሪ መኮንን' እንዲመለስ አፅድቋል፤ ትልቅ ደስታ ላይ ነው ያለነው" ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ 24.03.2025

ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ፤ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበር ሰብሳቢ፤ የአሁኑ የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ወደ መሠረተ ስያሜው ተፈሪ መኮንን እንዲመለስ የመወሰኑን ታሪካዊ ፋይዳዎችና የትምህርት ቤቱን 100ኛ ዓመት ለማክበር እየተደረጉ ስላሉ መሰናዶዎች ይናገራሉ።

ብርቅዬዎቹ የኢትዮጵያ ቅርስ ዋሊያዎች በሕገወጥ አደን ለምግብነት እየዋሉ መሆኑና ቁጥራቸውም አሽቆልቁሎ 300 መድረሱ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጠ 23.03.2025

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠች

የደብረ ዘይት በአል ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት የሚታዩ ምልክቶችን በተራራው ስብከቱ ያስተማረበትን ለማስታወስ የሚከበር በአል። " 23.03.2025

ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ የተነበያቸው ትንቢቶች በአብዛኛው እየታዩ ናቸው፤ የትንቢቱ መፈጸሚያዎች እንዳንሆን ወደ ንሰሀ መመለስ ይኖርብናል፤ የሚሉን በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ አገልጋይ የሆኑት መጋቢ ሓዲስ ብሩክ ተስፋዬ ናቸው ።

"መሬት ከፖለቲካ ወጥቶ ለኢኮኖሚው መሆን አለበት፤ አለመታደል ሆኖ የብሔር ፖለቲካ ከመሬት ጋር ተጣብቆ ተያይዟል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 22.03.2025

ዶ/ር ዳንኤል ካሣሁን - በኦስተን ኮሌጅ የጂኦ ስፔስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ የመሬት ለአራሹ አዋጅ ግማሽ ክፍለ ዘመን መድፈን አስባብ አድርገው "የመሬት ለአራሹ አዋጅ፤ ዋዜማ፣ መባቻ፣ እና ማግሥት" በሚል ርዕስ ሰሞኑን ለሕትመት ስለአበቁት መጣጥፋቸው አንኳር ጭብጦች ያስረዳሉ።

ማኅበረሰባዊ የስንብት ቃል፤ "የዶ/ር እንግዳ ሕልፈት ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ትልቅ ጉድለት ነው" አቶ ሰለሞን ወንድሙ 21.03.2025

በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩት ዶ/ር እንግዳወርቅ ለማ ዘላለማዊ ዕረፍት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ ጥልቅ ሐዘንን አሳድሯል። የቅርብ ጓደኞቻቸውና ብቸኛ ልጃቸው ጥልቅ የሐዘን ስሜታቸውን ይገልጣሉ። የዶ/ር እንግዳወርቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ መጋቢት 13 / ማርች 22 በ Bulla Cemetery ዕኩለ ቀን ላይ ይከናወናል።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.