SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የውይይት መድረክ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ከየት ተነስቶ የት ደርሷል? 18.07.2025

ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር፣ ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣ አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፣ አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በቀዳሚ የመወያያ አጀንዳነት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የ38 ዓመታት ጉዞ በከፊል ነቅሰው ግለ አተያያያቸውን ያጋራሉ።

ዜና - በሙአለ ህጻናት በሚጠበቁ ህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጾታ ጥቃት ለመከልከል መረጃ አያያዝ ላይ ማሻሻያዎች ያስፈልጋል ተባለ 16.07.2025

አውስትራሊያ እና ቻይና የፍራፍሬ ንግድ ስምምነትን ተፈራረሙ

" እድር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ዋስትናችን ነው " ፟ ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን የኢትዮጵያውያን የእድር መረዳጃ ማህበር በቪክቶርያ ጸሀፊ 16.07.2025

የኢትዮጵያውያን የእድር መረዳጃ ማህበር በቪክቶርያ ባሳለፍነ ሰሞን አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል ፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ማህሌት ማስረሻ ፤ ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን ጸሀፊ እንዲሁም አቶ ዮናስ ደገፋ ገንዘብ ያዥ ፤ እድሩ ከነበረበት ተነስቶ በአሁን ሰአት ምን ደርጃ ላይ እንዳለ እና እና የወደፊት እቅዶቻቸውን በተመለከተ ሀሳባቸውን አጋርተውናል ፡፡

አገርኛ ሪፖርት - በአዲስ አበባ እና አጎርባች ከተሞች ለመጪው አስር ቀናት ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ናብ ሊኖር ይችላል ተባለ 15.07.2025

ከኢትዮጵያ ከሀምሳ አምስት እስከ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ገንዘብ በህገ ወጥ ንግድ ሳቢያ ከአገር ወስጥ እንደሚወጣ የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ፡፡

"ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የዘንድሮውን ዕንቁጣጣሽ አብረን ሲድኒ ላይ በትልቁ ለማክበር በናፍቆት እየጠበቅን በዝግጅት ላይ ነን" ወ/ሮ መሠረት አሰፋ 14.07.2025

ወ/ሮ መሠረት አሰፋ፤ የ Habesha Spices and Events መሥራች፤ መጪውን የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት 2018 ቅበላና የኤርትራውያንን ቅዱስ ዮሐንስ በዓላት እንደምን በጋራ ድምቀትን በተላበሰ ሁኔታ ለማክበር መሰናዶ ላይ እንደሚገኙ ይገልጣሉ።

"በቦርድ መኖር ጥቅም እንጂ ጉዳት አላየንም፤ ቦርዱ የግድ መኖር አለበት የሚል ፅኑዕ እምነት አለን" አቶ ጋሻው አንለይ እና አቶ ታጠቅ መንጂ 14.07.2025

በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ አፈፃፀም፣ በቦርድ አስፈላጊነት እና አላስፈላጊነት ላይ ያሉ አተያዮችን አስመልክተው አቋማቸውን ያንፀባርቃሉ።

"በእኛ በኩል በሽምግልናም ይሁን በጠቅላላ ጉባኤ ተገናኝተን የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኞች ነን" አቶ ጋሻው አንለይ እና አቶ ታጠቅ መንጂ 13.07.2025

በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ ከማኅበር እስከ ቦርድ ምሥረታ የነበሩ ሂደቶችንና በቦርድና የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ተከስተው ያሉ የሥራ ግንኙነቶች መሻከርን አንስተው ይናገራሉ። የመፍትሔ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።

First Nations representation in media: What’s changing, why it matters - በሚዲያ የነባር ዜጎች ውክልና፤ ምን ዓይነት ለውጥ እየተካሔደ ነው፤ ፋይዳውስ ምንድን ነው? 12.07.2025

The representation of Indigenous Australians in media has historically been shaped by stereotypes and exclusion, but this is gradually changing. Indigenous platforms like National Indigenous Television (NITV) and social media are breaking barriers, empowering First Nations voices, and fostering a more inclusive understanding of Australia’s diverse cultural identity. Learning about these changes of...

#90 Talking about role models | First Nations Elders (Med) - #90 Talking about role models | First Nations Elders (Med) 10.07.2025

Learn how to describe people who inspire you. - Learn how to describe people who inspire you.

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች ሥራ በለቀቁ በአምስት ዓመታት ውስጥ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም አመራር እንዳይሆኑ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ 09.07.2025

ቻይና የኢትዮጵያ አኩሪ አተር ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቃድ ሰጠች

አዲስ አበባ እንጦጦ ላይ የሚገኙትን የባሕር ዛፎች በሶስት ዓመታት ውስጥ በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ዕቅድ መያዟን አስታወቀች 06.07.2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስጋትን፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬንና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈፅመዋል ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ አዲስ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ

ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌና ሬስቶራንት ከሜልበርን - አውስትራሊያ 15 ምርጥ ካፌዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ 04.07.2025

አቶ ዳንኤል አለማር፤ የጎጆ ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት የቡናና ምግብ አቅርቦታቸው ለሽልማት የመጨረሻ ማጣሪያ ከቀረቡት 15 የሜልበር ምርጥ ካፌዎች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ "የሬስቶራንቴ ስም 'ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌ እና ሬስቶራንት'፤ ሀገርን ተሸክሞ ያለ ትልቅ ስም ያለው ነው። ሀገሬን በማስጠራቴ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል" ሲሉ፤ እህታቸውና ሥራ አስኪያጅ መሠረት አለማር ፤ ሕልማቸው በዕጩነት ከ15 ምርጥ የሜልበርን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ አንዱ ለመሆን በመብቃት እንደማይገታ ይናገራሉ።

"ጠቅላላ ጉባኤ የጠራነው የፋይናንስ ሪፖርት ለማቅረብ፤ ለአሁኑና ወደፊትም ለሚመጣው ማኅበረሰብ የሚጠቅም የመተዳደሪያ ደንብ ክለሳ ላይ ለመነጋገር ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 04.07.2025

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለሰኔ 29 / ጁላይ 6 በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለመላ የማኅበረስብ አባላት ስለቀረበው የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪና የመነጋገሪያ ዋነኛ አጀንዳዎች ያስረዳሉ።

ሃማስ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ "የመጨረሻ" የተኩስ አቁም ውል ብለው ያቀረቡትን ዕሳቤ እንደሚያጤነው አስታወቀ 03.07.2025

የኢራን ፕሬዚደንት ኢራን ለዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጄንሲ ትብብሯን እንድትነፍግ የሚፈቅድ ሕግ አፀደቁ

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እሥራኤል ለ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ይሁንታዋን መቸሯን ገለጡ 02.07.2025

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ የአራትዮሹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ፍሬያማ ነበር አሉ

የሕገ መንግሥት ጥሰት ጥያቄ አስነስቶ የነበረው የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት ረቂቅ አዋጅ በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ተቀይሮ ፀደቀ 02.07.2025

የሕወሓትን ክፍፍል ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመሩ ነው የሚል ስጋት ተፈጥሯል ተባለ

"ፕሮፌሰሮቹ - መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ፕሮፌሰሮች ያለፉበትን ሕይወት፣ ለሀገሪቱ ያላቸው ከፍተኛ ሚናና የኢትዮጵያን የታሪክ ገፅታ ለማሳየት የተፃፈ ነው" ተሾመ ብርሃኑ 01.07.2025

ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ አዲስ ለሕትመት ባበቁት "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ስለምን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ሙያዊ አስተዋፅዖዎች ላይ ለማተኮር እንደወደዱ ይናገራሉ።

"መጽሐፉን መፃፉ እንደመስታወት በለሰለሰ አለት ላይ የመውጣት ያህል ነው" ደራሲ ብርሃኑ ተሾመ ከማል 01.07.2025

በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው 32 መፃሕፍትንና ከ2000 በላይ መጣጥፎችን ለአንባቢያን ያበረከቱት አንጋፋ ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ ሰሞነኛ ስለሆነው "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ተልዕኮና ይዘት ያስረዳሉ።

"ያስመረቅነው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ለአማኞች አምልኮ ብቻ ሳይሆን ለማኅበረሰቡም ጭምር ነው" ፓስተር ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ 30.06.2025

"በቤተ ክርስቲያንም ተከፋፍለን፣ በማኅበረሰብም ተከፋፍለን፣ በዘርም ተከፋፍለን ያሳለፍናቸው ምንም አልጠቀሙንም። አንድ ከሆንን፤ ከተባበርን፤ ከእዚህ በላይ መሥራት እንችላለን። ኅብረት የውስጥም የውጭም ጩኸቴ ነው!" አቶ ዳንኤል አለማር፤ በሜልበርን የዘፀዓት ኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ኅብረት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ

የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ለውጭ ባንኮችና ሙዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች በይፋ መከፈቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ 29.06.2025

ኢትዮጵያን ጨምሮ 39 ሀገራት በግጭቶችና አለመረጋጋቶች ምክንያት የከፋ ረሃብና ድህነት ማዕከል እየሆኑ ስለመሆናቸው የዓለም ባንክ ባወጣው ይፋ ሪፖርት አመላከተ

ዶናልድ ትራምፕ የኢራንና እሥራኤል ጦርነት ከእነአካቴው ማክተሙን ዳግም ሲያስታውቁ፤ የኢራን ፓርላማ የሀገሪቱ ኑክሊየር ፕሮግራም ተፋጥኖ እንዲቀጥል በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳለፈ 26.06.2025

ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በሚቀጥለው ሳምንት የቀጥታ ሁለትዮሽ ውይይት ሊጀምሩ ነው

ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ከሕግና መመሪያ ውጪ የተጠቀሙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እስካሁን የገንዘቡን 86 በመቶ አለመመለሳቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ 25.06.2025

አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ሆስፒታል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ተገልጋዮች የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ገለጠ

የዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት ያሰራውን ህንጻ ቤ/ክ በመጪው ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው 24.06.2025

አቶ ዳንኤል አለማር ከዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት የህንጻ አሰሪ ሰብሳቢ ፤ በሜልበርን ከተማ በመጪው ቅድሚ የሚመረቀው የቤተክርስቲያን ህንጻ ፤ ህብረተሰቡ ከሌለው አቅሙ ቀንሦ ለትውልዱ እና ለመጪው ትውልድ ያሳነጸው ሲሆን ፡ በህንጻ አሰሪው ኮሚቴው ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ ብለዋል ። አያይዘውም በምርቃቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

ፕሬዚደንት ትራምፕ ኢራንና እሥራኤል ለተኩስ አቁም ተስማምተዋል ማለታቸውን ኢራን አስተባበለች፤ ከእሥራኤል በኩል ይፋዊ ምላሽ እየተጠበቀ ነው 24.06.2025

የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን "ኢራን ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ማድረግ ካስፈለገ በኢራን ሕዝብ እንጂ በቦምብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን የሥርዓት ለውጥ ዕሳቤ ተቹ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍን ከሰኔ 24 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ልታደርግ ነው 23.06.2025

በሳዑዲ ዓረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.