SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የአባቶች ቀን አከባበር በሀገረ አውስትራሊያ 08.09.2025 10:54
አቶ ጉግሳ አሊጋዝ "ለኢትዮጵያውያን ሁሌም የአባቶች ቀን ነው። እኛ ጥሩ አባቶች ነን። ልጆቼን እጅግ በጣም ነው የምወዳቸው፤ በእዚህ ምድር ላይ በጣም ያስደሰተኝ ነገር ቢኖር ከልጆቼ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ነው " ሲሉ፤ አቶ ኃይለማርያም ኃይለየሱስ በበኩላቸው "እግዚአብሔር በልጆች ባርኮኛል፤ ልጆቼን በፍቅር ነው ያሳደግኳቸው። የወላጅ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ ብዬ አስባለሁ። ልጆቼም ለእኔ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት አላቸው፤ የአባቶችን ቀን በጣም ደስ ብሎኝ ነው ያከበርኩት" ይላሉ።
"አዲሱን ዓመት ስናከብር በአንድነቷ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ጠንክራችሁ የምትቀጥሉበት ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" አምባሳደር አንዋር ሙክታር 08.09.2025 4:40
አኑዋር ሙክታር፤ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ አምባሳደር፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 233 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አስታወቀ 08.09.2025 8:19
በሰሜን ጎንደር ዞን ድርቅ ስጋት ማስከተሉ ተመለከተ
የቀን መቁጠሪያችን የማንነታችንን መገለጫ እሴቶቻችን አንዱ ነው ፤ ይህንንም ቤ/ክ ብቻ ሳትሆን መላው ኢትዮጵያውያን የማስጠብቅ ሀላፊነት አለብን 07.09.2025 11:41
ከኢትዮጵያውያን ማንንት መገለጫ አንዱ ልዩ የሆነ የቀን መቁጠሪያችን ነው ። ምንጩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ቢሆንም አገልግሎቱ ግን ለመላው ኢትዮጵያውያን ነው በዚህም ልንኮራ ይገባናል፤ የሚሉን መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት የሜልበርን ምእራፈ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያ አስተዳዳሪ እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ቀሲስ ቴዎድሮስ በሜልበርን ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው።
የጳጉሚት ወር በአትዮጵያውያን የቀን መቁጠሪያ የአመቱን ትርፍ ቀናት ሸክፋ የያዘች ልዩ ወር ናት ። 06.09.2025 18:33
መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት የሜልበርን ምእራፈ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያ አስተዳዳሪ ፤ እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ቀሲስ ቴዎድሮስ በሜልበርን ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የጳጉሜ ወር ትርጓሜን ፤ ሀይማኖታዊ እና አገራዊ ጠቀሜታን አስረድተውናል
#94 Talking about autism (Med) - #94 Talking about autism (Med) 05.09.2025 18:21
Learn how to talk about Autism Spectrum Disorder respectfully. Understand common autism symptoms and use simple language to describe autism in everyday conversations. - Learn how to talk about Autism Spectrum Disorder respectfully. Understand common autism symptoms and use simple language to describe autism in everyday conversations.
"ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መጪው ዘመን ከትናንት የተሻለ፣ ሀገራችን ገናናነቷ ጎልቶ የሚወጣበትና አብረን የምንቆምበት እንዲሆን እመኛለሁ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 04.09.2025 7:23
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
"ለመላ ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመት! አብረን እናሳልፍ፤ አንድ ጎረቤት አንድ ጓደኛ ይዛችሁ ኑ፤ በባሕላችሁ ተደሰቱ!" የአዲስ ዓመት ቅበላ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት 03.09.2025 23:20
አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የመድረክ መሪ፤ በሜልበር ፉትስክሬይ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6 / ጳጉሜን 1 በሚካሔደው የአዲስ ዓመት ቅበላ ልዩ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲገኙ ይጋብዛሉ።
"የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ፉትስክሬይ ላይ ማድረጋችን፤ የሕዝባችን ሱቆችና ንግዶች ብዛቱና የመገናኛ ቦታው ፉትስክሬይ ስለሆነ ነው" ዳይሬክተር ካሪም ደጋል 03.09.2025 14:42
አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የመድረክ መሪ፤ በሜልበር ፉትስክሬይ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6 / ጳጉሜን 1 ስለሚካሔደው የአዲስ ዓመት ቅበላ ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ 46 በመቶ የሚሆነውንና የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጠ 02.09.2025 10:28
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራ ማኅበረሰብ 50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አዘጋጅቻለሁ አለ
የፀረ ፍልስተኞች የተቃውሞ ሰልፍ ውግዘት ደረሰበት 01.09.2025 11:20
የትራምፕ አስተዳደር ፍልስጥኤማውያንን የቤት ኪራይ ገንዘብ ሰጥቶ ከጋዛ ለማስወጣት መወጠኑ ተጠቆመ
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 4 ቀን ይመረቃል ተባለ 01.09.2025 10:58
የቦይንግ ኩባንያ አዲሱ የአውሮፕላኑ ሞዴል በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ፍተሻ ይደረግለታል አለ
ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር 30.08.2025 22:38
ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።
"ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር 30.08.2025 13:18
"የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን ከእሥር እንዳስለቀቀው ነቅሶ ያወጋል።
ዓለም አቀፍ በረራዎች ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመቀሌ፣ ባሕርዳርና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሊጀመር ነው 27.08.2025 9:33
የግዕዝ ቋንቋ ከመጪው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በአማራ ክልል ከሶስተኛ ክፍል በመጀመር እንደሚሰጥ ተገለጠ
"የአሸንዳ በዓል ሃይማኖታዊም ባሕላዊም ነው፤ ክብርና ልጅነታችንን ያስታውሳል፤ የሴቶች በዓል በመሆኑ የነፃነታችን በዓል ነው" ነርስ ሰላማዊት ደሞዝ 27.08.2025 17:38
በተለይ የሴቶች ልዩ በዓል የሆነው ሀገር በቀሉ የአሸንዳ ክብረ በዓል በሜልበርን አውስትራሊያ ቅዳሜ ነሐሴ 17 / ኦገስት 23 በትግራይ ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ በሐሴት ተመልቶ፤ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በቪክቶሪያ የትግራይ ሴቶች ማኅበር አመራር አባላትና የበዓሉ ተሳታፊዎች የአሸንዳ በዓል ስሜቶቻቸውን ገልጠዋል፤ ለመላ ኢትዮጵያውያንም የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ኢ-ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ነው፤ 32 በመቶ የሚሆነው የማኅበረሰብ ክፍልም ሱስ ውስጥ ይገኛል 25.08.2025 11:51
የውጭ ዜጎች በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ለሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት በእጥፍ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ
"ትዝታ ትናንትን በምልስት በማውሳት ዛሬ ላይ ሕይወት ዘርተን የምናቆየው ነው፤ ለፊልሜ መጠሪያ ያደረግኩትም ቃለ መልዕክቱ ለልብና ለነፍስ ስለሆነ ነው"አራማዝት ካላይጂያን 22.08.2025 20:08
የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ። አርመናውያን በአጼዎቹ ዮሐንስ አራተኛ፣ ዳግማዊ ምኒልክና ቀዳማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥታት ውስጥ ከአድዋ ጦርነት ጣሊያንን መመከቻ መሣሪያ አበርካችነት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግንባታዎችና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ መስኮች ያበረከቷቸውን ሁነኛ አስተዋፅዖዎች ያነሳሉ። ትዝታ ነሐሴ 25 /ኦገስት 31 በሜልበርን Lido Cinemas ለሕዝብ ይቀርባል።
#93 Bragging about your car (Med) - #93 Bragging about your car (Med) 20.08.2025 15:11
Learn how to talk about cars and understand common Aussie car slang. - Learn how to talk about cars and understand common Aussie car slang.
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ 20.08.2025 9:08
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የመግቢያ ቲኬት ዋጋ ጭማሪ አደረገ
1934 - 2017፤ የተዋናይ ደበበ እሸቱ ዕረፍት 18.08.2025 7:12
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ሰው ሠራሽ አስተውሎት በነገው ዕለት ለሚጀመረው የምርታማነት ጉባኤ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አመላከቱ
ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ 49 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ብቻ የባንክ ሂሳብ እንዳላቸው ተገለጠ 17.08.2025 10:12
በአፋር ክልል 2.6 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ የሰው ቅሪተ አካል ተገኘ
"በስደት ሕይወት እንኳንስ ለሌሎች ለመትረፍ ለራስ ቆሞ ለመሔድም የሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ መውደቅ አለ፤ የሁሉም ሕይወት ባይሆን" ደራሲ ማትያስ ከተማ 14.08.2025 11:08
ደራሲ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ) በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው የቀለም ጠብታዎቹ በረከት "ጉርሻና ቅምሻ፤ የዳመና ግላጭ ወጎች" መፅሐፉ ይዘት ያወጋል።
"ጥላሁን ገሠሠ ለሁለት በሰጠን አንድ ብር ብስኩት በልተን፣ ጫማ አስጠርገን፣ አውቶብስ ተሳፍረን፤ የተረፈንን 20 ሳንቲም ለሌላ ሰው ሰጥተናል" ማትያስ ከተማ 14.08.2025 14:59
ደራሲ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ) በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው የቀለም ጠብታዎቹ በረከት "ጉርሻና ቅምሻ፤ የዳመና ግላጭ ወጎች" መፅሐፉ ይዘት ያወጋል።
"የብዕር ስሜን 'ወለላዬ' ማለቴ እናቴንና ሀገሬን አንድ ላይ ጠቅልሎ ይይዝልኛል ብዬ ነው። እናትም ወለላ ናት፤ ሀገርም ወላላ ናት" ደራሲ ማቲያስ ከተማ 14.08.2025 14:58
ደራሲ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ) በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው የቀለም ጠብታዎቹ በረከት "ጉርሻና ቅምሻ፤ የዳመና ግላጭ ወጎች" መፅሐፉ ይዘት ያወጋል።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.