SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

" እንኳን ለደመራ እና መስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ። " - መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት 26.09.2025

መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የደመራ እና የመስቀል በአል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ አንድምታ አስረድተዋል ።

"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት መሠረተ ልማትን ለመሥራት ያስገድዳል፤ ወደ ፈጠራ ይመራል። የኤሌክትሪክ ስኩተርና ብስክሌትም አሥፈላጊ ናቸው"ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ 26.09.2025

ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ የኤሌክትሪክ መኪና፣ ስኩተርና ብስክሌት ለኢትዮጵያ ያለውን ጠቀሜታ ከጀርመንና ቻይና ተሞክሮ ጋር አያይዘው ያስረዳሉ።

"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለመንዳት ምቹና ለአካባቢያዊ አየር ብክለት ቅነሳ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም፤ ጉዳትም አላቸው" ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ 26.09.2025

ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ ከነዳጅና ናፍጣ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መኪና ሽግግርን ፋይዳዎች በንፅፅሮሽ አንስተው ያስረዳሉ።

ኢሬቻ መልካ በሜልበርን - አውስትራሊያ እሑድ ዕለት ሊከበር ነው 25.09.2025

የኢሬቻ ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ እና ኦቦ በንቲ ኦሊቃ፤ እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 በ Wilson Botanic Park Berwick ተከብሮ ስለሚውለው የኢሬቻ ክብረ በዓል ሥነ ሥርዓትና ሂደት ይናገራሉ። የአብረን እንታደም የጥሪ ግብዣም ያቀርባሉ።

“ የተቀበልኳቸው ታላላቅ ሽልማቶች እና እውቅናዎች ተጨማሪ ሀላፊነትን መሸከም እና ጠንክሬ መስራት እንዳለብኝ የሚያስታውሱ ናቸው። ” - አርቲስት ሮፍናን 25.09.2025

አባቴ በእኔ ስኬት ውስጥ ታላቅ ስፍራ አለው ፤ ዩኒቨርሳል ሙዚቃ ያቀረበልኝን ውል ስፈርም በእነሱ ቅድመ ሁኔታ ስይሆን በእኔ ምርጫ የተሻለ ውል እንድፈርም የረዳኝ የአባቴን ምክር እና የሕይወት ፍልስፍና መስማቴም መከተሌም ነው ፤ ይለናል ሁለገቡ አርቲስት ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።

"ደሲ ለእግዚአብሔር ቃልና ለፍቅር የተረታች ናት፤ በሕልፈቷ ድንጋጤ ውስጥ ነው ያለሁት፤ ያለ እሷ እንዴት እንደምኖር አላውቅም" የፓስተር ደሲ ባለቤት አቶ ዓይናለም ካሱ 25.09.2025

የመንፈሳዊ ሕይወትና የበጎ አድራጎት አገልጋይዋ ፓስተር ደሲ ባይሳ ከእዚህ ዓለም በሕልፈት ተሰናብተዋል። "አታልቅስ፤ ነገ ይነጋል" ነበር የመጨረሻ ቃሏ ያሉትን ታላቅ ወንድማቸውን ተክሉ ባይሳ አክሎ፤ ቤተስብና ወዳጆች ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ። የፓስተር ደሲ የቀብር ሥነ ሥርዓት እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 ከቀኑ 2:00 pm በ Bulla Cemetery Lane, Bulla ይፈፀማል።

“ራሴን ማድመጤ የተሻለ ሙዚቃን ይዤ እንድመጣ ረድቶኛል ፤ በራሴ መንገድ የመጣሁበት ሙዚቃ ፍሬውን ሳይ እድለኛ ነኝ እንድል ያደርገኛል -አርቲስት ሮፍናን 24.09.2025

የሙዚቀኛ ውጤት የሚታየው በሙዚቀኛው ጥረት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ነው ። አገር ሰላም ሲሆን ማህበረሰብ ሲራጋጋ የኪነ- ጥበብ ባለሙያዎችም ጥሩ ስራን ይዘን መቅረብ እንችላላን፤ የሚለን የሙዚቃ ስራውን በአውስትራሊያ እያሳየ ያለው ሁለገቡ አርቲስት ገጣሚ ፤ አቀናባሪ ፤ ዲጄ እንዲሁም ድምጻዊ ሮፍናን ኒሪ ሙዘይን ነው ።

- አንቶኒ አልበኒዚ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጋር በጥቅምት ወር ሊገናኙ ቀጥሮ ተቆረጠ 24.09.2025

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጋዛ የእስራኤልን ወረራን ተቃወሙ

"የአዲስ ዓመት ዝግጅቱ ሀገር ቤት ያሳለፍናቸውን ጥሩ ጊዜዎች እንድናስታውስ አድርጎናል፤ መበረታትና መጠናከር ያለበት ነው፤ መልካም አዲስ ዓመት!" ዶ/ር አደራጀው ተሾመ 23.09.2025

የኢትዮጵያውያን 2018 አዲስ ዓመት አከባበር በኬንሲንግተን ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሜልበርን አውስትራሊያ።

ዜና -አውስትራሊያዊቷ የከፍታ ዘላይ ኒኮላ ኦላሳርገን የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነች 22.09.2025

እስራኤል የፍርስጤማውያንን ነጻ አገር የመሆን ጥያቄ መቼውንም ቢሆን እውቅናን አልሰጥም አለች፤

አገርኛ ሪፖርት - " ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ 21.09.2025

" ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ

"ነቢይ አይደለሁም፤ ነቢይ እንዳልባል እንጂ ሁለቱም [ኢትዮጵያና ኤርትራ] ተለያይተው የሚኖሩ አይመስልም" ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ 16.09.2025

በሕይወት ዘመናቸው "ኤርትራውያን ጀግናዎች ናቸው፤ ጥሩ ተዋጊዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ስር ወድቀዋል። "አንድነት ኢትዮጵያ" ብለው የሔዱ ናቸው" ያሉን የቀድሞው የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ፣ የብሔራዊ ውትድርና መምሪያ ኃላፊና የ "ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር" መጽሐፍ ደራሲ ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ተለይተዋል። ዝክረ መታሰቢያ ይሆናቸውም ዘንድ ቀደም ሲል በወርኃ ኖቬምበር 2014 ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ ደግመን አቅርበናል።

"ባሕላችን ለትውልድ እንዲቀጥል ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው መጥተው ስለ ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንዲያስረዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ 16.09.2025

ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 በ Kensington Town Hall በማኅበሩ አስተባባሪነት ስለሚከበረው የ2018 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።

አውስትራሊያን አክሎ 42 ሀገራት በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ባለበት መቆሙና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተመድ አስታወቁ 16.09.2025

እስከ አንድ ወር ጊዜ ይወስድ የነበረውን አዲስ የንግድ ምዝገባና ዕድሳት አሠራርን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል በመቀየር በሁለት ቀናት መጨረስ የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ተደረገ

"የእኛ ዕድር ከዘርና ሃይማኖት ነፃ የሆነ ነው፤ ኑ ተደጋግፈን ማኅበራዊ ሕይወታችንን እናጎልበት፤ መልካም አዲስ ዓመት" የኢትዮ-አውስትራሊያ አንድነት መረዳጃ ዕድር 15.09.2025

የኢትዮ - አውስትራሊያ አንድነት ዕድር ሰብሳቢ አቶ መስቀሉ ደሴ፣ ፀሐፊ ብሩክ ይማ እና የበዓል አስተባባሪ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ይልማ፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2018 እና የመስቀል በዓል በጣምራ ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፐርዝ ከተማ Koondoola Community Centre ለማክበር ስላሰናዱት የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ይናገራሉ። የአንድነት ጥሪም ያቀርባሉ።

የጥምር ዜግነት ጉዳይ በአጀንዳነት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀረበ 14.09.2025

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ በኢትዮጵያ ላይ ጥለውት የነበረውን የተለያዩ ዕቀባዎችን የያዘው ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ፤ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ፀንቶ እንዲቆይ ተወሰነ

"ኢትዮጵያ ውስጥ የሁሉንም ክልልሎች ይሁንታ ለማግኘትና ዲሞክራሲም ሥር እንዲሰድ ለማድረግ ፕሬዚደንታዊ ሥርዓት ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም 13.09.2025

ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ ስለምን የሶስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ የምርምር ፅሁፋቸውን ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ አውጥተው "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ስያሜ ለመፅሐፍነት ለማብቃት እንደወደዱ ያነሳሉ፤ ጭብጦቹንም ነቅሰው ይናገራሉ።

"የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚታየው የሀገር ቤት ነፀብራቅ ነው፤ ሀገር ቤት ያለው ሁኔታ እየሰከነ ሲሄድ የዳያስፖራውም እንደዚያ ይሆናል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም 12.09.2025

የ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ መፅሐፋቸው ውስጥ ያሠፈሯቸውን አንኳር ምክረ ሃሳቦች ፋይዳ ነቅሰው ያስገነዝባሉ።

"የኢኮኖሚ ዕድገት ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ያደርጋል፤ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት የሚያስገኘውን ጥቅም እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም 12.09.2025

ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ለሕትመት ስላበቁት መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ይናገራሉ።

2018 - አዲስ ዓመት፣ አውደ ዓመት፣ ዕንቁጣጣሽ 11.09.2025

የ"ክብረ በዓላት፤ ሃይማኖትና ባሕል" መፅሐፍ ደራሲ መላኩ ጌታቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘመን ቅመራና ባሕላዊ አከባበር ያስረዳል።

"አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 10.09.2025

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

" አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋበት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ" - ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ 10.09.2025

ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋብት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

" አዲሱ አመት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን "- ሼህ አብዱራህማን 10.09.2025

ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ አዲሱ የ2018 አመተ ምህረት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

"ዕንቁጣጣሽ ወዳጅነትና ክብር በተመላበት መልኩ ሁሉንም የማሰባሰቢያ ጊዜ ነው፤የእናንተ ስኬት የአውስትራሊያ ስኬት ነው፤መልካም አዲስ ዓመት!" የተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ 10.09.2025

የአውስትራሊያ ፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ፤ ለኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት።

"ኢትዮጵያዊነት ልዩ ኩራታችን ነው፤ ይህን አዲስ ዓመት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለልጆቿ የሰላም፣ የጤናና የሕዳሴ ያድርግልን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ 09.09.2025

"አንድ ስንሆን፤ ሳንለያይ ብዙ መስራት እንደምንችል ይህ [ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ] ትልቅ ምሳሌ ነው። እግዚአብሔርም የግርማዊ ጃንሆይን ሕልም ተሠርቶ ስላሳየን ስሙ ምስጉን ይሁን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.