DW

የዓለም ዜና

News AM ↓ 100 episodes

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 10, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 20.05.2026

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ «አለአግባብ ከምርጫው ተሳትፎ አግልሎኛል» ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መሠረተ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቅቄ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጀምሬያለሁ ይላል። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከጎርጎሪዮሳዊው 2024 ዓ,ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የቆየው የቪዛ ገደብ መነሳቱን አስታወቀ። የዓለም የጤና ድርጅት በኤቦላ መሞታቸው የተጠረጠረ ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን ዛሬ አስታወቀ። በተሐዋሲው መያዛቸው የተጠረጠረም 600 ደርሰዋል። ሩሲያና ቻይና ለዩክሬን ጦርነት መንስኤ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች እንዲወገዱ ጥሪ አቀረቡ። በኢራን ላይ የሚደርሰውን ጥቃትም ኮነኑ።

የማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 19.05.2026

መቐለ፥ «የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ምሥረታን ሕወሓት አጣጣለ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ-ሕግጋት ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ፤ ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ አኅጉራዊ የጤና ሥጋት መኾኑ ታወጀ፤ ቤርሊን፥ አሜሪካዊ የኮሮና ታማሚ ጀርመን ለልዩ ኅክምና ተወሰደ፤ ሞስኮ፦ ቤላሩስ ከሩስያ ጋር የኑክሊየር ጦር መሣሪያን የሚያካትት ወታደራዊ ልምምድ መጀመሯን ይፋ አደረገች፤ ካይሮ፥ የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ኾነ

የዓለም ዜና፤ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 18.05.2026

አርስተ ዜና፦ በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የተባለ ጭማሪ በመደረጉ አገር አቀፍ የትራንስፖርት አድማ ተቀሰቀሰ። ናይሮቢን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ቀጥሏል። -ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እንዲሰሩ በድጋሚ የተሾሙት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ያለውን ልዩነት በበለጠ ብልሃትና ስልታዊ አካሄድ መፍታት እንደሚገባቸው ተመለከተ።-የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ቴህራን ላይ ጫና በማሳረፍ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ኢራን ትወድማለች" ሲሉ በድጋሚ ዛቱ።-በፈረንጆቹ 2025 ዓመት በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር የሞት ቅጣት መፈፀሙን፤ አምነስቲ አስታወቀ።

DW Amharic- የግንቦት 09 ቀን 2018 የዓለም ዜና 17.05.2026

በዛሬው የዓለም ዜና የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በt,ከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን፣በናይጄሪያ ወታደራዊ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ የአክራሪዎች ጥቃት 17 የፖሊስ ሰልጣኞች መገደላቸውን፣በዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የኒኩሌር ማዕከል ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በማዕከሉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን፣ አሜሪካ ለኢራን የድርድር ሀሳብ በሰጠችው ምላሽ ላይ ምንም አይነት ተጨባጭ የስምምነት ሀሳብ የለውም ሲሉ የኢራን መገናኛ ዘዴዎች መግለፃቸውን እንዲሁም የሰሜን ኮሪያ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ማድረጉን አካቷል።

DW Amharic የግንቦት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና 16.05.2026

ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት የትብብር ሥምምነት ዛሬ ቅዳሜ በአስመራ ተፈራረሙ። ሥምምነቱ የተፈረመው የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተገኙበት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት በኢቦላ ወረርሽኝ ቢያንስ 80 ሰዎች ሞቱ። የቦኮ ሐራም አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከፈጸሙት ጥቃት በኋላ ቢያንስ 42 ልጆች ደብዛቸው መጥፋቱን የአካባቢው ተመራጭ ተናገሩ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ኢዚዲን አል-ሐዳድ ተገደሉ።

የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 15.05.2026

የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -በደቡብ አፍሪካ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ጋብ አያለ ቢመጣም «ሕገ ወጥ ግንባታ» በሚል ምክንያት ሱቆቻቸው እየፈረሱባቸው እንደሚገኙ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያውያን ለዶቼቬለ ተናገሩ ። -በኮንጎዋ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር በተከሰተ አዲስ የኤቦላ ወረርሽኝ 65 ሰዎች መሞታቸውን መታወቁን የአፍሪቃ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል አስታወቀ። -የብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሁለት ቀናት ኒው ዴልሂ ህንድ ውስጥ ያካሄዱትን ጉባኤ የጋራ መግለጫ ሳያወጡ ዛሬ አበቁ።

የዓለም ዜና፤ ግንቦት 6 ቀን 2018 ሐሙስ 14.05.2026

አርስተ ዜና -የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና በፕሬዚዳንት ዢ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸዉ። ትራምፕ አስደናቂ መሪ ሲሉ ዢ ጂንፒንግን አሞካሽተዋቸዋል። የሁለቱ ሀገራት "የተረጋጋ" ግንኙነት ለዓለም ፋይዳ እንደሚሆን የተናገሩት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸዉ፤ የታይዋን ጉዳይ በአግባቡ ካልተያዘ ግን ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።-ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ በዩናይትድ ስቴትስ ከ4 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ መነሳቱ ተገለፀ። ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችዉን ማእቀብ ለማንሳት እያሰበች እንደሆን ያስታወቀችዉ በዚሁ ሰሞን እንደሆን የሚታወስ ነዉ።

የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 13.05.2026

ትናንት ከአሶሳ ወደ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የበርካቶች ሕይወት አለፈ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል። ጋና ከደቡብ አፍሪቃ 300 ዜጎቿን ልታወጣ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከቀትር በኋላ ቻይና ገብተዋል። የትራምፕ ጉዞ በ9 ዓመት በአሜሪካ ፕሬዝደንት ወደ ቻይና የተደረገ የመጀመሪያ ጉብኝት ነው።

የግንቦት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና 12.05.2026

-አርዕስተ ዜና -በጅቡቲ ወይም በሶማሊያ በኩል የአደን ባሕረ-ሠላጤን አቋርጠዉ ወደ አረብ ሐገራት ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቢሞቱም፣ ሌሎች መሰደዳቸዉን አለማቆማቸዉን ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ድርጅት አስታወቀ።-የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶችን ለማስወገድ ኢትዮጵያ «ጠቃሚ» ያሉትን ሚና እየተወጣች ነዉ በማለት አደነቁ።--ፈረንሳይ ከአፍሪቃ ሐገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት በአ,ዲስ መልክ እንደምታጠናክር አስታወቀች።ፈረንሳይ ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶችዋ ከፈረንሳይኛ ተናጋሪ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ጋር ከተቃቃረች ወዲሕ ፊቷን ወደ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ አዙራለች

የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 11.05.2026

የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ፣የክስ ሂደታቸው "በኘላዝማ" እንዲታይ ተወስኖባቸው የነበሩ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር ያሉ የሽብር ተከሳሾች ጉዳያቸውን በአካል እንዲከታተሉ ዛሬ ብይን ሰጠ። ሱዳን ውስጥ በተፈጸሙ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮኖች) ጥቃቶች ከጥር እስከ ሚያዚያ ቢያንስ 880 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የተመድ አስታወቀ። በተመድ የአፍሪቃ ውክልና እንዲጨምር የተሀድሶ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ አሳሰቡ ።

የግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 10.05.2026

• በሰሜናዊ ምስራቋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት ኢቱሪ 69 ሰዎች በሚሊሺያዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች እና የጸጥታ አካላት ተናገሩ። • በማዕከላዊ ማሊ በተመሳሳይ ጂሃዲስቶች አደረሱ በተባለ መጠነ, ሰፊ ጥቃት በ,ርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የጸጥታ ምንጮች ትናንት ቅዳሜ አስታወቁ። • ኢራን አሜሪካ ላቀረበችላት የሰላም ስምምነት መልስ መስጠቷን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ ። • ሩስያ በዩክሬን የምታደርገው ጦርነት በፍጥነት እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች። • በሃንታ ቫይረስ በተመታች የመዝናኛ መርከብ ላይ ያሉ ተጓዦችን የማስወጣት ስራ በይፋ ተጀመረ።

የቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 09.05.2026

በዛሬው የዓለም ዜና በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አከባቢ ባለፈው ሓሙስ «በአንድ የፖሊስ አባል የተገደለ» ወጣት ትናንት ዓርብ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን ፤የናይጄሪያ ጦር በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል 50 ፅንፈኛ ያላቸውን ታጣቂዎች መግደሉን ማስታወቁን፤የዓለም ጤና ድርጅት ሀላፊ የሃንታ ቫይረስ የተከሰተበት መርከብ ከመድረሱ በፊት ስፔን መግባታቸው መገለፁን፤ ሂዝቦላህ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት ማድረጉን መግለፁ፣ሞስኮ በጠንካራ ጥበቃ ስር ዛሬ የድል ቀን በዓልን ማክበሯን፣ኢራን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ማስታወቋን አካቷል።

የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 08.05.2026

መቐለ፥ሕወሓት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ዛሬበይፋ ሥራ መጀመሩን ዐሳወቀ፤ ናይሮቢ፥ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ሦስት የአፍሪቃ አገራትን ሊጎበኙ ነው፤ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ውስጥ ብርቱ የረሐብ አደጋ እልቂት እንዳይፈጥር አስግቷል፤ ሪያድ፥ በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ ዘመቻዋ ዩናይትድ ስቴትስ የዓየር ክልሏን እንዳትጠቀም ሣዑዲ ዓረቢያ አገደች፤ ቴህራን፥ ኢራን መርከቦቼ ላይ ጥቃት አደረሰችብን ያለቻት ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቀች፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራን መርከቦች ላይ ተኩስ ከፈተች

የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 07.05.2026

የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ይበልጥ እንዳሰጋቸው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናገሩ። -የናፍጣ እጥረት ባናረው የጭነት መጓጋዣ ዋጋ ምክንያት፣ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውንና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑንም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶ አደሮች ዐሳወቁ። -ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ የኢራኑን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም እቅድ እየገመገመች መሆኑን ኢራን አሳወቀች።

ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 06.05.2026

• የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን ጥቃት) እጄ የለበትም ስትል አስተባበለች ። • የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በቻድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 23 ወታደሮች ተገደሉ ፤ ሌሎች 26 ቆሰሉ ። • አሜሪካ እና ኢራን የባሕረ ሰላጤውን ጦርነት ለማቆም ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ። • በገዳዩ የሀንታ ተሐዋሲ የተጠረጠሩ ሦስት ተጓዦች ከመንገደኞች መርከብ ተለይተው ወደ ኔዘርላንድስ መወሰዳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 05.05.2026

መቀለ፥ ሕወሓት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን የትግራይ ክልል ፕረዚደንት አድርጎ መረጠ፤ ናይሮቢ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን አንዱ ሌላኛውን በማጥቃት እየተካሰሱ ነው፤ አስመራ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ልታነሳ ነው መባሉ፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ ሠርጥ መርከቦችን ብታስተናብርም የተኩስ አቁሙ ግን እንደተጠበቀ ነው አለች፤ ዬርቬና፥ የአውሮጳ ኅብረት የትራምፕ የቀረጥ ዛቻ ለሚያስከትለው ማንኛውም ነገር ዝግጁ መሆኑን ዐሳወቀ፤ ለንደን፥ ዩክሬንን ለማጥቃት ለሩስያ ተዋጊዎችን የሚመለምሉ ላይ ብሪታንያ ማእቀብ ጣለች፤ ላይፕትሲሽ፥ በተሽከርካሪ ግድያ የፈጸመው ግለሰብ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው

የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 04.05.2026

አርስተ ዜና--የጀርመን መራሄ መንግሥት ፍሬድሪክ መርስ ፤ ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 5,000 የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን ጦር ሰፈር ለማዉጣት ማቀዳቸዉ የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ተናገሩ። ኔቶ በበኩሉ አውሮጳውያን፤ የአሜሪካኑን ፕሬዝዳንት የብስጭት መልእክትን «ሰምተው» ቁርጠኝነታቸዉን እያጠናከሩ ነዉ ሲል መልስ ሰጥቷል።-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ኢሶዴፓ) ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያቀረባቸውን 309 ዕጩዎች ከውድድሩ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ። -በእስር ላይ የሚገኙ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርበት ያላቸው ሰባት ሰዎች መካከል እስካሁን ፍርድ ቤት በቀረቡት ሁለቱ ላይ ፖሊስ የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቋል።

የሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 03.05.2026

• የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በመዲናዪቱ ካርቱም (RSF) ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት አምስት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች አስታወቁ። • በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ሌላ የነዳጅ መርከብ በባሕር ላይ ወንበዴዎች ተጠለፈች • ኢራን በ30 ቀናት ውስጥ ግጭቱ እንዲቆምና የአሜሪካ ማዕቀቦች እንዲነሱ የሚጠይቅ የ14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ አቀረበች። • ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ወንድሙ ዛሬ የተካሄደውን 31ኛው የፕራግ ዓለም አቀፍ ማራቶን አሸነፈ።

የሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 02.05.2026

በኬንያ ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፋና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 10 ሰዎች ሞቱ። ታይዋን ፕሬዝዳንት ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ዲፕሎማሲያዊ አጋር ሀገር ኤስዋቲኒ ገቡ።3,000 የሚጠጉ የየመን ስደተኞች ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳይባረሩ አንድ የፌዴራል ዳኛ ከለከሉ። የነዳጅ ዘይት የጫነ አንድ መርከብ ከየመን የባህር ዳርቻ ተጠለፈ። ዩናይትድ ስቴትስ 5000 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ ነው። የአውሮፓ ህብረት እና የጀርመን ኢንዱስትሪዎች የትራምፕን አዲስ የታሪፍ ዕቅዶች ተቹ።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ክልሉ ሙሉ በሙሉ ለመደበኛ በረራዎች ክፍት እንደሚሆን አስታወቁ።

የሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.05.2026

የአውሮጳ ሕብረት ትግራይ ክልል ውስጥ ሌላ አውዳሚ ጦርነት ከሚያስከትል እርምጃ ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ አሳሰበ። ኢትዮጵያዊን ጨምሮ ዘጠኝ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የአሜሪካ መንግሥት ወደ ካሜሮን ማባረሩን ጠበቃቸው ተናገሩ። የተመድ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር ጁጉ ግዛት በደረሰ ጥቃት ምክንያት ወደ 200 ገደማ ነዋሪዎች ተፈናቅለው መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው አመለከተ። የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያሰማራውን የሰላም አስከባሪ ኃይል ቁጥር ለመቀነስ ወሰነ። የሰላም አስከባሪውን የቆይታ ጊዜም እስከ መጪው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2027 ሚያዝያ 30 ቀን ድረስ አራዝሟል።

የዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 30.04.2026

መስቃን፥ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ናይሮቢ፥ በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊውን ለጥቂት ቀድሞ ክብረወሰን ያስመዘገበው ኬኒያዊው አትሌት የጀግና አቀባበል ተደረገለት፤ ብራስልስ፥ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ ፕሬዚደንቶች መካከል የተደረገው የስልክክ ንግግር አውሮጳን ግራ አጋብቷል፤ ቴሕራን፥ የአሜሪካ የፍኖተ ሆርሙዝ የመርከቦች ፍሰት ክልከላ በአካባቢው አደገኛ አለመረጋጋት ይፈጥራል አለች፤ ቤርሊን፥ የኢራን ጦርነት ዓለምን ቢያስጨንቅም ጀርመን ያልተጠበቀ የኤኮኖሚ እድገት ዐሳይታለች፤ ለንደን፥ ብሪታንያ አይሁዶችን ከጥቃት ለመከላከል ተጨማሪ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ለመመደብ ቃል ገባች

የሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 29.04.2026

ሳውድ አረቢያ ውስጥ ቢያንስ 65 ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተገናኘ ወንጀል የሞት ቅጣት እንደሚያሰጋቸው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች ዐሳወቀ። ለሁለት ሳምንታት የደረሰበት ያልታወቀው የአዲስ ስታንዳርድ አርታኢ ሚሊዮን በየነ ትናንት ወደ ቤቱ መመለሱን አሠሪው ድርጅት ገለጸ። የዩጋንዳ ባለሥልጣናት ከሕገወጥ የሰዎች ሽግግር እና በበይነ መረብ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በርካታ የውጭ ዜጎች ማሰራቸውን አስታወቁ። ሥር ለሰደደ የምግብ እጥረት የተጋለጠችው ሶማሊያ በማያባራው ግጭት እና የገንዘብ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት የተመድ አመለከተ።

የሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና 28.04.2026

በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ62 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ታውቋል። ኢትዮጵያዊያኑ ትናንት የተገደሉት በአንድ ምግቤት ውስጥ በመመገብ ላይ እንዳሉ ነው ፡፡ባሕሬይን አስፈላጊ ተቋሞቿን ፎቶ በማንሳት ለኢራን አስተላልፏል ያለቻቸውን 5 ሰዎች የዕድሜ ይፍታህ እስር ውሳኔ አስተላለፈች። አሜሪካ፤ ኢራን ያቀረበችው የመደራደሪያ ሐሳብ እያጤነችው መሆኗን አስታወቀች።

የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 27.04.2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉና በልዩ ሁኔታ የሚመዘገቡ መራጮች ምዝገባ ማከናወን ዛሬ መጀመሩ አስታወቀ። በደቡብ ሱዳን አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ 14 ተሳፋሪዎችና የበረራ ሰራተኞች በሙሉ አለቁ። የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎች በሶማሊያ የባሕር ክልል ስትጓዝ የነበረችው ስሚንቶ የጫነች መርከብ አገቱ። ሒዝቦላህ፤ ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር የምታካሂደውን ቀጥታዊ ውይይት ውድቅ አደረገ።የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ሐገራቸው የኢራንና በቀጠናው ያሉ ሐገራትን ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚቻላትን ሁሉ ታደርጋለች» አሉ።

የሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 26.04.2026

የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ በጂሃዲስቶች ጥቃት ተገደሉ። በማዕከላዊ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቻድ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ዘጠኝ የተቃዋሚ ንቅናቄ ቡድን ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተገኙበት የእራት ግብዣ ስነ ሥርዓት ላይ ተኩስ መከፈቱ እንዳስደነገጣቸው በመግለጽ በርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች ዛሬ ድርጊቱን ኮንነዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ እሁድ ዩናይትድ ስቴትስን እና ኢራንን ወደ ምታደራድረው ፓኪስታን መዲና ኢስላማባድ ተመለሱ። ኬንያዊው ሴባስቲያን ሳዌ በማራቶን ታሪክ ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ።

Listen to the የዓለም ዜና podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.