DW

የዓለም ዜና

News AM ↓ 100 episodes

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 10, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 25.04.2026

• በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመሬት ናዳ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ ። • የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ጠለፉ። • በማሊ መዲናዪቱ ባማኮን ጨምሮ ታጣቂዎች በቅንጅት ጥቃት መፈጸማቸውን ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናገሩ። • በጋዛ እና የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ፍልስጤም ግዛቶች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ የአከባቢ አስተዳደር ምርጫ እየተካሄደ ነው። • አሜሪካ እና ኢራን ለተኩስ አቁም ድርድር ባለስልጣናቶቻቸውን ወደ ፓኪስታን መላካቸውን አስታወቁ ።

የሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 24.04.2026

የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። በሶማሊያ በተከሰተው ድርቅ በ 5 ወረዳዎች ብቻ ወደ 62,000 የሚጠጉ ሶማሊያውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት አስታወቀ። እስራኤልና ሊባኖስ ከዚህ ቀደም የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ለሦስት ሳምንታት ማራዘማቸውን የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ማምሻውን ወደ ኢዝላማባድ እንደሚገቡ ኢራን አረጋገጠች።

የሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና 23.04.2026

የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ደቡብ ኮርዶፋን ላይ የአየር ጥቃት መጀመሩ ተነገረ። የኢራን ጦርነት መዘዝ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደድህነት ሊመልስ እንደሚችል የተመድ አመለከተ። የአሜሪካ ጦር በዛሬው ዕለት የኢራንን ነዳጅ ዘይት በሕገወጥ መንገድ ጭኗል ያለውን ሌላ መርከብ መያዙን አስታወቀ። በኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል መካከል በመካከለኛው ምሥራቅ የቀጠለው ውዝግብ እንዲያበቃ ፓኪስታን የጀመረችውን ጥረት ቀጥላለች። የዋና ከተማ ኢዝላማባድ መንገዶች መዘጋጋት ሀገሬውን አማርሯል። የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ችሎት ዳኞች የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዝደንት በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ክስ እንደሚቀርብባቸው አስታወቁ።

የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 22.04.2026

በአማራ ክልል የዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ጦርነት የአካባቢው አስተዳደር ሰራተኞች መታገታቸው እና ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) አባል የአቶ ታዬ ደንደዓ አዲሱ ክስ ተቋረጠ።የኒጀር መንግሥት  2900 የሀገር ውስጥ እና የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንቅስቃሴን አገደ።ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መርከቦች ላይ መተኮሷን ቀጥላለች።ሉፍታንዛ 20,000 የአጭር ርቀት በረራዎችን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።

የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 21.04.2026

የዛሬው የዓለም ዜና የህወሐት ውሳኔ የፕሪቶሪያ ውልን ውድቅ ያደርጋል»ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለፁ፤ተቃዋሚው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግሬስ ወደ ትጥቅ ትግል መሸጋገሩን ማስታወቁን፤ናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን አከሸፍኩ ማለቷን፤ በሁለተኛው ዙር የአሜሪካ-ኢራን ውይይት ቫንስ እና ቃሊባፍ እንደሚገኙ መገለጹን በ2025 8000 የሚጠጉ ሰደተኞች ጎዞ ላይ ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ሲል የተመድ መግለፁን ፤ ኢራን ፤ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከ3,600 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች መባሉን እንዲሁምየአውሮፓ ህብረት የኃይል እጥረትን ለመፍታት የኑክሌር ማብላያዎች እንዳይዘጉ ሊያስጠነቅቅ ነው መባሉን አካቷል።

DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና 20.04.2026

ህወሓት ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት በተካሔደ ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ወደ ሥራ እንዲመለስ” ወሰነ። ፓኪስታን ለሱዳን የጦር መሣሪያዎች እና ተዋጊ ጀቶች ለማቅረብ የገባችውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በይደር ማቆየቷን የሀገሪቱ የደሕንነት የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች በአቡጃ እና በኒጀር ግዛቶች እስላማዊ ታጣቂዎች በመንግሥት መሠረተ-ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዐቅደዋል በሚል ሥጋት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናቸው ተባለ። አሜሪካ የኢራንን መርከብ ከሖርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ መያዟ ዓለም አቀፍ ሕግ እና ሁለቱ ሀገሮች የተስማሙበትን የተኩስ አቁም እንደሚጥስ ኢራን አሳወቀች።

የሚያዚያ11 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 19.04.2026

የዛሬው የዓለም ዜና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለመነጋገር የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ነገ ሰኞ ፓኪስታን እንደሚገቡ መግለፃቸው፤የኢራን አጋር የሆኑት የየመን ሁቲ ሚሊሻዎች ቁልፉን የንግድ መስመር ባብ ኤል ማንዳብን እንደሚዘጉ በድጋሚ ማስጠንቀቁ፤ሶሪያ በሂዝቦላህ እና በቀድሞው መሪ አሳድ ቅሪቶች ሊፈፀም ነበር ያለችውን ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ማክሸፏን መግለጿ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና ሃንጋሪ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለመልቀቅ የሚያስችል 'ቴክኒካዊ' ውይይት ማድረጋቸው መግለፃቸውን አካቷል።

የሚያዝያ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና 18.04.2026

ስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሠላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የምትቀጥል ከሆነ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን መልሳ እንደምትዘጋ ዛሬ አስጠነቀቀች። እስራኤል የደህንነት ስጋትን ተጨማሪ ቦታ ለማስፋፋት እየተጠቀመችበት ነው ሲሉ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሰሱ።

የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 17.04.2026

ኮሬ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፍተው ነዋሪዎችን ገደሉ፤ ኪንሻሳ፥ ከዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ የተሰናበቱ 15 ደቡብ አሜሪካውያን ኮንጎ ደረሱ፤ ቤሩት፥ እሥራኤል እና የሊባኖሱ ሒዝቦላህ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ፤ ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍኖተ-ሆርሙዝ ከእንግዲህ «መቼም» አይዘጋም አሉ፤ ቴሕራን፥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ተኩስ አቁሙ ተጥሶ ጥቃት ቢደርስበት እንደሚበቀል አስጠነቀቀ፤ ናይፒይዳው፥ ምያንማር በዓመታዊ ልማዷ 4,000 እስረኞችን ነጻ ለቀቀች

የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 16.04.2026

ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ እና ሲቪል የለበሱ በተባሉ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ እስካሁን ያለበት ቦታ እንዳልታወቀ ተገለፀ። -ትራምፕ «እስራኤል እና ሊባኖስ ለ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል»-የኬንያ ፍርድ ቤት አንድ ቻይናዊ ህገ-ወጥ የጉንዳን አዘዋዋሪ ላይ የአንድ ዓመት እስራት ፈረደ።-የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በካሜሩን የሚገኙ ባለስልጣናት ሕሊናቸውን እንዲመረምሩ እና "የሙስና ሰንሰለትን" እንዲሰብሩ ጥሪ አቀረቡ።

የሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 15.04.2026

አራተኛ ዓመቱን በያዘው የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በረሐብ እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን ለመርዳት ጀርመን 20 ሚልዩን ዩሮ እንደምትለግስ አስታወቀች። አሜሪካ ከኢራን ወደቦች የሚወጡና የሚገቡ መርከቦችን ማገዷን ከቀጠለች በቀይባሕር፣ የፐርሺያ ባሕረሰላጤና በኦማን የባሕር ሰርጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ እንደምታግድ ኢራን አስጠነቀቀች። እስራኤል በአለፉት 24 ሰዓታት በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ከ200 በላይ «የሒዝቦላሕ ወታደራዊ ይዞታዎች» ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።

የሚያዚያ 6 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና 14.04.2026

የዛሬው የዓለም ዜና ፤የናይጄሪያ ፖሊስ በምዕመናን እገታ የተሳተፉ 33 አባላት ያሉት የወሮበሎች ቡድንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለፁ፤የቤኔን የምርጫ ኮሚሽን የዘንድሮውን ሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ይፋ ማድረጉን፤ሊባኖስ እና እስራኤል ቀጥተኛ የዲፕሎማሲ ውይይት ዛሬ በዋሽንግተን ማካሄዳቸውን፣በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የዓለም አቀፍ የእድገት ትንበያ መቀነሱን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለፁን፤ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ንግግራቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ ፈረንሣይ ጥሪ ማቅረቧን እንዲሁም የጀርመን መራሄ መንግስት አውሮጳ በማንኛውም የዩክሬን የሰላም ስምምነት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባት ማለታቸውን ያስቃኛል።

የሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 13.04.2026

በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሱዳናውያን ሕይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ቅጠላ ቅጠልና የእንስሳት መኖ ጭምር ለመመገብ መገደዳቸውን 5 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታወቁ። በናይጄርያ ሰሜን ምስራቅ በምትገኝ አንዲት መንደር የሐገሪቱ አየር ሃይል በገበያ ቦታ ፈጸመው በተባለው የአየር ድብደባ ቢያንስ 200 ሰላማዊ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ወደቦች በሙሉ እንዲዘጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ኢራን ፈጣን የዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።

የሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና 12.04.2026

የዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትንሳኤ በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በመላው ዓለም መከበሩን ፣በቤኒኒናውያን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ መዋላቸውን፣አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን፣ኩዌት በሐገር ደሕንነት ላይ ያነጣጠረ የሽብር ሴራን አከሸፍኩ ማለቷን እና ሳውዲ አረቢያ በድሮንና በሚሳይል ጥቃቶች ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የሓይል መሰረተ ልማቶችን ጠግና ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጓን ያስቃኛል።

የሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 11.04.2026

ኢትዮጵያ ውስጥ የከርቤ ዛፍ በድርቅ ምክንያት እየተመናመነ እንደሆነ አሶሺየትድ ፕረስ ዘገበ። የጅቡቲው ፕሬዝደንት ጉሌሕ 97.81% የመራጭ ድምፅ በማግኘት አሸነፉ። የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት ሊባኖስ ውስጥ ከ200 በላይ የሂዝቦላ ኢላማዎች መደብደቡን አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚደረግ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት እንዲቆም ጠይቁ። የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ የፊት ለፊት ድርድር ዛሬ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ጀምሯል። ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ አቅራቢያ የነበሩት የጠፈር ተመራማሪዎች በሰላም ወደ ምድር ተመለሱ።

DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና 10.04.2026

በዎላይታ ዞን ከባድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 7 ሰዎች ሲሞቱ 6 ተጎዱ። ኢሕአፓ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅትን ወክለው ለድሬደዋ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ አባሉን እስር አወገዘ። የጅቡቲ ዜጎች ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ያሸንፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ጄድ ቫንስ በኢዝላማባድ ድርድር ኢራን ዩናይትድ ስቴትስን "ለማታለል" እንዳትሞክር አስጠነቀቁ። የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት በሊባኖስ የተኩስ አቁም መደረግ እንዳለበት ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል።

የሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 09.04.2026

በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ባገረሸው የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ተሰማ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በመጪዉ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ10 የኢትዮጵያ ከተሞች የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያከናውን አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተረዥ ኢራን በሊባኖስ ስቪል ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በጥብቅ አወገዙ።

የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 08.04.2026

በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቀዬያቸው ተፈናቀሉ። የጅቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ዓርብ የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያሸንፉ እየተጠበቀ ነው። እስራኤል በኢራን የሚደገፈውን የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ለማጥቃት በሚል ሊባኖስን ደብድባለች። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ዛሬ በዋይት ሀውስ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢራን እና በአዘርባጃን የባህር ዳርቻዎች ዛሬ በሬክተር ስኬል መለኪያ 5.6 የነበረ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና 07.04.2026

-ከ80 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንደሚለለዉ 120 ስደተኞች አሳፍራ ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ ትቀዝፍ የነበረች አነስተኛ ጀልባ ባለፈዉ ዕሁድ ሰጥማለች።32ቱ በሕይወት ተርፈዋል።-----የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላዉን ተቋማትና ይዞታዎች በደብደባቸዉን ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።የቃላት ጦርነቱም እንደናረ ነዉ።---ጦርነቱ የእርዳታ ምግብ፣መድሐኒትና ቁሳቁስ እንዳይንቀሳቀስ ወይም እንዲዘገይ ማድረጉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች አስታወቁ።

የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 06.04.2026

የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና እሥራኤልና አሜሪካ ዛሬ በኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ25 ሰዎች በላይ ተገደሉ። ከመካከላቸው የኢራን ፈጥኖ ደራሽ አብዮታዊ ዘብ የስለላ ክፍል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ማጃድ ክሀዴሚ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ዛሬ በእሥራኤል ላይ ዛሬ ከኢራን ከሂዝቦላ እና ከየመን በተመሳሳይ ጊዜ ጥቃቶች ተፈጽመውባታል ኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ ለ45 ቀናት የተኩስ አቁም እንዲያደርጉና የሆርሙዝ ሰርጥም እንዲከፈት የቀረበውን ረቂቅ ምክረ ሃሳብ ኢራን እንደማትቀበለው አስታወቀች የናይጀሪያ ጦር ት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተፈፀሙ ሦስት ጥቃቶች ቢያንስ 26 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቁ ።

የመጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 05.04.2026

ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም። ሰሜንናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ትናንት ቅዳሜ በፈጸሙት ጥቃት አራት የፖሊስ መኮንኖች ተገደሉ ። ኢራን በዛሬው ዕለት በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟን የየሐገራቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የመጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 04.04.2026

በዛሬው የዓለም ዜና፤ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከአንድ ሺ ለሚበልጡ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ፤ሴኔጋል ከኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የነዳጅ ወጭ ለመቀነስ የባለስልጣናትን የውጭ ጉዞ መገደቧን፣ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች ኢራን ውስጥ ዛሬም በርካታ ቦታዎችን ኢላማ ማድረጋቸውን፣ የተባበሩት መንግስታት የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለማስከፈትን በተመለከተ ለዛሬ ታቅዶ የነበረው ድምጽ አሰጣጥ ለሌላ ጊዜ መገፋቱን ፤አሜሪካ በኢራን ተመቶ ከወደቀ አውሮፕላን አንድ አብራሪዋን መታደጓን ባለስልጣናት መግለፃቸውን እና ኔዘርላንድ በሚገኝ አንድ የእስራኤል ደጋፊ ማዕከል ላይ ፍንዳታ በመከሰቱን ያስቃኛል።

የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና 03.04.2026

በዛሬው የዓለም ዜና፤ በሀዋሳ ከተማ በመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን፤የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማዕቀብ «ለሩዋንዳ ስድብ» ሲሉ መግለፃቸውን፤በኢራን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ማስታወቁን፤ኢራን እና እሥራኤል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት መቀጠሉን፤ ኢራን ዉስጥ አንድ የአሜሪካተዋጊ ጄት ተመትቶ ወደቀ መባሉን እንዲሁም ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት በጋራ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ያስቃኛል።

የመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 02.04.2026

የጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የ19 ተሰዳጆችን አስከሬን ማግኘታቸው ተገለጸ። ሌሎች 58 ተሰዳጆችን በሕይወት አትርፈዋል። ከአሜሪካን የተባረሩ 12 ወደየትውልድ ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ስደተኞች ዩጋንዳ መግባታቸውን የዩጋንዳ የሕግ ማኅበረሰብ ዛሬ አስታወቀ። ኢራን በዛሬው ዕለትም በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው የአረብ ሃገራት ላይ የሚሳኤል ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች። ፕሬዝደንት ትራምፕ ኢራን ከእንግዲህ የሚያሰጋ ኃይል የላትም እያሉ ነው። ፈረንሳይ የሆርሙዝን መተላለፊያ ለማስከፈት ኃይል መጠቀሙ አዋጪ እንዳልሆነ አሳስባለች። ሩሲያ ቡሼር ከተሰኘው ከኢራኑ የኒኩሊየር የኃይል ተቋም ዜጎቿን ማስወጣት ጀምራለች።

የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.04.2026

የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ" የለም በሚል አጀንዳ የማሰባሰብና የጉባኤ ተሳታፊ ልየታ ሥራ ዛሬ አዲስ አበባ ከሚኖሩና ከክልሉ መጡ ከተባሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር ማካሄድ በጀመረበት በዛሬው መድረክ ሥራው በክልሉ ውስጥ እንዲደረግ ተጠየቀ ። ሁለተኛው ወሩን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት አሜሪካና እሥራኤል የኢራን የብረታ ብረት ማምረቻዎችን ደበደቡ። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚካሄድ ምንም ዓይነት ድርድር የለም ሲሉ አስታወቁ።

Listen to the የዓለም ዜና podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.