SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

"እስልምናን አያይዞ የተወሰኑ የትግራይ አባቶች አቋም 'አክሱምን ቅድስት ከተማ፤ እንደ ቫቲካን ራሷን የቻለች እናደርጋታለን' ከሚል የመነጨ ነው" ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል 11.06.2026

አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪና የታሪክ አጥኚ አቶ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ በቅርቡ "የአክሱም ተማሪዎች የሂጃብ ጥያቄ የፖለቲካ ሕመሙ ምልክት ወይስ እራሱ ሕመሙ ነው?" በሚል መጠይቅ ለሕትመት ያበቁትን ተከታይ መጣጥፋቸውን ጭብጦች ነቅሰው ያስረዳሉ። ተጨማሪ ያድምጡ

በ442 ወታደራዊ ካምፖችና በ82 መጠለያ ጣቢያዎች ለመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ 11.06.2026

ኮትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዲወረሱ የሚደነግገው አዋጅ ፀደቀ

"ስልጣን ላይ መውጣቱም መውደቁም መከራ ነው፤ የመውጣትን ያህል መውደቁ ግን ይብሳል።" - ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 10.06.2026

ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መምህር፤ ስለ አዲሱ የግጥም መድብል መጽሐፋቸው "ትዝብትና ተስፋ" ጭብጦች ይናገራሉ።

"ትዝብቴ ሰብዓዊ ሆነን ተፈጥረን፤ ኢ-ሰብዓዊ ሆነን የመውደቅ ትዝብት ነው።" - ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 10.06.2026

ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መምህር፤ ስለ አዲሱ የግጥም መድብል መጽሐፋቸው "ትዝብትና ተስፋ" ጭብጦች ይናገራሉ።

Are electric vehicles worth it in Australia?| Fuel in Focus - Are electric vehicles worth it in Australia?| Fuel in Focus 09.06.2026

Electric vehicles are becoming more common on Australian roads as fuel prices remain unstable and more drivers look for cheaper ways to travel. Here's what you need to know if you are thinking about making the switch. - የነዳጅ ዋጋ አለመረጋጋት ቀጥሎ አለ። የኤሌክትሪክ መኪናዎች በአውስትራሊያ ጎዳናዎች ላይ መታየትም እየተለመደ መጥቷል። ፊትዎን ወደ የኤሌክትሪክ መኪና ማዞር ከፈለጉ ሊያውቁ የሚገባዎትን እነሆን።

እሥራኤል ቤይሩት ላይ ጥቃት ሰነዘረች 08.06.2026

የአውስትራሊያ መንግሥት የሕዝብን የለውጥ ጥያቄ እያደመጥን ነው አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 47 መደበኛ ቅሬታዎች እንደቀረቡለትና 825 የምርጫ ጣቢያዎች ውጤቶቻቸውን ይፋ እንዳደረጉ አስታወቀ 08.06.2026

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ በፈለገችው መንገድ መጠቀም እንደምትችል ሶማሌላንድ አመላከተች

እንጀራ (ግጥም) - በኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ብዕርና አንደበት 04.06.2026

ከኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ማሞ አዲስ መድብለ ግጥም መጽሐፍ "ትዝብትና ተስፋ" ተመርጦ በደራሲው አንደበት የተነበበ።

የብሪስበን 2032 ኦሎምፒክ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በይፋ ይጀመራል 01.06.2026

የደቡብ አፍሪካ ቡድን በቪዛ ችግር ሳቢያ የሜክሲኮ ጉዞው ተስተጓጉሏል

"በአሜሪካን ሀገር 'ወደ ነጮቹ ነው የንሳበው ወይስ ወደ ጥቁሮቹ?' የሚል ትልቅ ጥያቄ አለ። ስንቶቹ አስበውበታል? ስንቶቹ ችላ ብለውታል?" ዶ/ር ስዩም ገብረእግዚአብሔር 31.05.2026

ዝክረ መታሰቢያ - ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር፤ የ Symphony of My Life መጽሐፍ ደራሲ፤ ከጎንደር ከተማ ከንቲባነት እስከ ስደት ሕይወት ትረካ (በሕይወት ሳሉ)።

"ሳልጠየቅ፣ ሳልፈቅድ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆነህ ተሹመሃል ተባልኩ። 'እንዴት ይሆናል?' ብዬ ጃንሆይ ዘንድ ቀረብኩ" ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር 31.05.2026

ዝክረ መታሰቢያ - ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር፤ የ Symphony of My Life መጽሐፍ ደራሲ፤ ግለ ታሪካቸውን ባሰፈሩበት መጽሐፋቸው በሀገረ አሜሪክ "ኢትዮጵያ PhD ለምን ያስፈልጋታል?" ተብለው 'ሀገሬ እንዴት እንዲህ ትባላለች?' ብለው ትምህርታቸውን እንደምን እንደጨረሱና 'ያለ ፈቃዴ እንደምን ነው የጎንደር ከታማ ከንቲባ ሆኜ የምሾመው?' በሚል ቁጣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት እንደቀረቡ ካወጉት (በሕይወት ሳሉ)።

#111 Water problems at home? |Talking to a plumber (Med) - #111 Water problems at home? |Talking to a plumber (Med) 28.05.2026

Learn English useful for describing plumbing problems at home. Practise everyday phrases for explaining issues, asking about cost, and arranging repairs. - የመፀዳጃ፣ መታጠቢያና ቧምቧ የመሳሰሉ ቁሳ ቁሶች ችግር ቤት ውስጥ ሲገጥም ዘርዝሮ ለማስረዳት ያስችል ዘንድ እንግሊዝኛን መማር ጠቀሜታ ይኖረዋል። እክሎችን ለማብራራት፣ ዋጋን ለመጠየቅና ጥገናን ለማመቻቸት እያንዳንዱን አባባል በየዕለቱ ይለማመዱ።

"በኢትዮጵያዊነቴ ሁሌ እኮራለሁ፤ ተሸማቅቄ አላውቅም። በአፍሪካ ቀን ስሸለም በወገኖቻችን ከፍ ያለ ድጋፍ በጣም ነው የኮራሁት። የጋራ ክብር ነው።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 27.05.2026

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የአፍሪካ ቀን የማኅበረሰብ ስኬት ሽልማት ተሸላሚ፤ የሽልማቱን ፋይዳና የማኅበሩን ማኅበረሰባዊ አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል ካሉ ስምንት የምርጫ ጣቢያዎች በስተቀር በተያዘለት የምርጫ መርሃ ግብር መሠረት እንደሚካሔድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ 27.05.2026

ኢትዮ- ቴሌኮም በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዋዕለ ንዋይ ላይ በይፋ ተመዘገበ

"ወደ አረንጓዴ ምጣኔ ሀብት መሸጋገሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም እንዲያስችላቸው ሊያግዝ ይችላል የሚል እምነት ነው ያለኝ" ዶ/ር ዮናታን ድንቁ 27.05.2026

ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ ከ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት ጋር የተሰናሰሉ ምክረ ሃሳቦችን ያጋራሉ።

" ሀጅ መሄድ እና በአረፋ ቦታ መቆም ከእስልምና እምነት ምሶሶዎች አንዱ ነው :: " ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 26.05.2026

ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር ፤ በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ እንዳሉት ፤ አረፋ አደም እና ሀዋ የተገናኙበት ቦታ ሲሆን ፤ ለሀጂ የሚጓዙ ሰዎች አረፋ የተባለው ቦታ ከጠዋት ጀምረው እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰአት ባለው ጊዜ ከዚያ በመሄድ ያሳልፋሉ ። አረፋ ሰፊ ስፍራ ሲሆን በተራራም የታጀበ ነው ። ቦታው የአእምሮ ሰላምን የሚሰጥ የሚያረጋጋ ስፍራ ነው ።

አውስትራሊያ ውስጥ የግል ተመራጭ የምክር ቤት አባላትን ያሰባሰበ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ታስቧል 25.05.2026

የኢቦላ ወረርሽኝ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ስር እየሰደደ ነው

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀጥታ አካላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈፀሙ የአፈሳና የጅምላ እሥር ድርጊቶች አሁንም አሳሳቢ ሆነው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ አመለከተ 25.05.2026

ኢትዮጵያ በዜጎቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የሚከታተል የልዑካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደምትልክ አስታወቀች

"ትልቁ የቤት ችግር አቅርቦት ነው እንጂ የፍልሰተኞች ቁጥር አይደለም፤አንደኛና ሁለተኛ ዜጎችን የመፍጠር አዝማሚያ ማኅበራዊ ትስስሮሽ ላይ ችግር ይፈጥራል" ዶ/ር ደሴ ታርቆ 22.05.2026

ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ የ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖችን አንስተው ያስረዳሉ።

"አባታችን መቼም እንደማይተካ እናውቃለን። በጣም አዝነናል። ለማኅበረሰቡ ምስጋናችን ትልቅ ነው።" ሚካኤል ብርሃኑ 21.05.2026

ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ለመጨረሻ ጊዜ ለተለዩት የማኅበረሰብ መሪ፣ ቅን አገልጋይ፣ የሶስት ልጆች አባትና መልካም ወዳጅ ዶ/ር ብርሃኑ ወልደኪዳንን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክቶ ልጃቸው ሚካኤል ብርሃኑና የቅርብ ወዳጆቻቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጣሉ። ለዶ/ር ብርሃኑ ቤተሰቦችና የማኅበረሰብ አባላት በሙሉ መፅናናትን ይመኛሉ።

የ2026 የአውስትራሊያ ፌዴራል በጀት ተጠቃሚና ተጎጂዎች እነማን ናቸው? 21.05.2026

ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ የ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት ትሩፋቶችንና እንከኖችን ነቅሰው ያመላክታሉ።

የትግራይ ክልልን ለማስተዳደር ዓላማ ያደረገ ነው የተባለለት ጊዜያዊ ምክር ቤት መመሥረቱ ተገለጠ 20.05.2026

ዳን ጎቴ ለማዳበሪያ ፋብሪካ የመደበውን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረጉን አስታወቀ

"አማርኛ እየተናገረ ትምህርት ቤት የሚገባውም፣ በትግርኛ የሚማረውም፤ በቋንቋህ ፃፍ ስትለው አይችልም። ኦሮምኛውም እንደዚሁ ነው።" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026

ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህርና "የአማርኛ ሰዋሰው" መጽሐፍ ደራሲ፤ በመጽሐፋቸው ውስጥ ስላነሷቸው የአማርኛ ሰዋሰው አወዳደቅ ሂደትና ደረጃ፣ የሆህያት አጠቃቀምና ጥቅል የቋንቋ ሥርዓተ ትምህርትን አስመልክተው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።

"ቋንቋ የሃሳብ መግለጫ፣ የሃሳብ መመሥረቻ፤ ዐልፎም ሃሳቡን የሚገልፀውን ሰው ማንነት ማሳወቂያ ነው" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026

ኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህር፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ባሉት "የአማርኛ ሰዋሰው" መጽሐፋቸው አማርኛ ግዕዝንና አገውኛን ተክቶ እንደምን ለቤተ መንግሥት ቋንቋነት እንደበቃ፤ የቋንቋን ውልደትና ሞት ጊዜ ፈጂነት ከሌሎች አንኳር ሃሳቦቻቸው ጋር አያይዘው ይናገራሉ።

"እኔ እንደምገምተው፤ የማናውቀው ጉዳይ ቢኖር የቋንቋን ረቂቅነት ነው" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026

በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህር፤ ኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም፤ በቅርቡ ለሕተመት ስላበቁት "የአማርኛ ሰዋሰው" መፅሐፋቸውን ትሩፋቶች ነቅሰው ያስረዳሉ።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.