DW
የዓለም ዜና
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 21.07.2026 10:46
አርስተ ዜና፤ ኢሕአፓ በትግራይ አዲስ የጦርነት ሥጋት ማንዣበቡን በመግለፅ ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው መንግሥት በሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙኃን የሚካሄድ ያለው "የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የሕዝብን ሥነ-ልቦና ለጦርነት የማዘጋጀት ሙከራ" ከአራት ዓመታት በፊት በትግራይ ጦርነት ዋዜማ ከታየው ሂደት ጋር አንድ አይነት ነው"ብሏል።- የአራት ቀናት አፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን ከሞሪታንያ የጀመሩት የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃን ቫዴፉል የሞሪታንያ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ናይጀርያ ገብተዋል። ሚኒስትሩ አገራቸዉ እና ሞሪታኒያ በንግድ፣ በኃይል ቀርቦትና በደኅንነት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠነክሩ ገልፀዋል።
የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 20.07.2026 11:12
የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ከሱዳኑ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋር በምታካሂደው ጦርነት ኬሚካዊ የጦር መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውላለች ባለቻት በሱዳን ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።ለክሱ ያቀረበችው ማስረጃ ግን የለም ተብሏል። ዛሬ የተመረጡት አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሀም መንግሥት እንዲመሰርቱ በንጉሥ ቻርልስ ሣልሳዊ ተጠየቁ። የቀድሞ የግሬተር ማንቼስተር ከንቲባ የ56 ዓመቱ በርንሀም ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት የሌበር ፓርቲ መሪነት ከተመረጡ ከ3 ቀናት በኋላ ነው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ የስፔን ቡድን ዛሬ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና አቀባበል ተደርገለት።
DW Amharic የሐምሌ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና 19.07.2026 7:55
በሶማሌ ክልል ቀብሪ በያሕ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ለ2019 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 704 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ምዕራባዊ ክፍሎች፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በጋምቤላ ክልል በተወሰኑ አካባቢዎች በሚጥል ከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስጠነቀቀ። የታንዛኒያ ሰንደቅ የሚያውለበልብ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከየመን የባሕር ዳርቻ በሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ታገተ። አሜሪካ ሁለት ወታደሮቿ በዮርዳኖስ ከተገደሉ በኋላ ኢራንን “ለመቅጣት” አዲስ ዙር የለሊት የአየር ላይ ድብደባ ፈጸመች።
የሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ-ም የዓለም ዜና 18.07.2026 10:48
የዛሬው የዓለም ዜና ፤በአዲስ አበባ ከተማ ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱን፤ኢራን 'የአሜሪካ ጥቃቶች ከቀጠሉ ምንም አይነት የፖለቲካ ድንበር ደህንነቱ የተጠበቀ አይሆንም' ስትል ማስጠንቀቋን፣የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለማግኘት ወደ ዋሽንግተን ማቅናታቸውን፤በጀርመን ከፍተኛ የሽብር ስጋት መኖሩን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መግለፁን፣ዩክሬይን በሁለት የሩስያ ግዛቶች ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ ፈጸመችው በተባለ የድሮን ጥቃቶች 9 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሩስያ ባለስላጣናት ማስታወቃቸውን እንዲሁም ህንድ የመጀመሪያውን የግል ሮኬት ወደ ህዋ ማምጠቋን አካቷል።
የሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 17.07.2026 11:22
በዛሬው የዓለም ዜና፤ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታኅ አል ቡርኻን በአስመራ መገናኘታቸውን፣ሶማሊያ በየኮቪድ-19 ሰበብ የ250 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር የተከሰሰ ቁልፍ ተጠርጣሪን ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠቷን፣የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዮርዳኖስ የአሜሪካን አውሮፕላኖችን በሚሳኤልና በድሮን መምታቱን፣ አንዲ ቡርንኻም በብሪታኒያ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ሊበር ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸውን እና ቻይና አሜሪካ በጋዜጠኞች የቆይታ ጊዜ ላይ በጣለችው ገደብ ላይ 'የአፀፋ እርምጃዎችን' እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን አካቷል።
የሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 16.07.2026 9:11
አ.አ፥ ስለተጀመረው አገራዊ ምክክር የፓርቲዎች ትችት እና ድጋፍ፤ ሙዋንጋ ፥ ዛምቤዚ ባህር ሰጥመዋል የተባሉ ኢትዮጵያዉያን በሕይወት ተገኙ፤ ዋሽንግቶን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በኢቦላ ከተጠቃችው ኮንጎ የሚመጡ ዜጎቿን ወደ አገር መግባት ከለከለች፤ ኪዬቭ፥ አዲስ ጠቅላይ ሚንሥትት ተሾሙ፥ መከላከያ ሚንሥትሩ ተሻሩ፤ቴሕራን፥ ኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ስትደበድባት የባህረ ሠላጤው አገራት ላይ ጥቃቷን አጠናከረች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን የሣዑዲ ዓረቢያን እንደሚደበድቡ ዛቱ
የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 15.07.2026 10:13
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ « ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ምክክሩ ፍሬያማ ይሆናል በማለት ለጉባኤተኞቹ ጥሪ አቅርበዋል። ወደቦትስዋና ለመሻገር የሞከሩ 10 ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ታንኳ ተገልብጣ ሳይሰጥሙ እንዳልቀረ የዛምብያ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። በታንኳዋ ተሳፍረው ከነበሩት 15 ኢትዮጵያውያን አስሩ ሰጥመዋል ተብሎ እንደሚታመን የተናገረው ፖሊስ ሦስት ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል። ከመካከላቸው በህይወት የተረፉትን ሁለቱን ፖሊስ አስሯቸዋል። የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ጥቃትና የአጸፋ ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል።
የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 7 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ 14.07.2026 12:14
አርስተ ዜና-የአሜሪካ ጦር ለሦስተኛ ተከታታይ ምሽት በኢራን ኢላማዎች ላይ ጥቃቶችን ማካሄዱን አስታወቀ። የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ ፤ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ሁለት ከፍተኛ ነዳጅ መርከቦችን መምታቱን እና ከጉዞ ማሰናከሉን አስታውቋል።-ከስድስት ዓመት በላይ ከኦሮሚያ ክልልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን በመጠለያ ጣቢያና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ሥጋት መጋለጣቸውን ተናገሩ።-አውሮጳ ህብረት በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ የሚዉለዉን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ በሱዳን የወርቅ ንግድ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ።
የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 13.07.2026 12:37
የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ በማስቆም ሕገ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። የየመን ሑቲ ታጣቂዎች ሳውዲ ዓረብያ በሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ«ፈጸመችው» ላሉት ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠነቀቁ። አሜሪካ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ «እየፈጸመው ነው» ላለችው ማስተጓጎል ያስታገሰ ያለችውን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች። ኢራን በበኩሏ በዮርዳኖስ፣ ባሕረይና ኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ደብድባለች።
የሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 12.07.2026 8:32
• የሱዳን ፍርድ ቤት መሐመድ ሐምዳን ዳግሎን ጨምሮ 16 የፈጥኖ ደራሹ ኃይል RSF አመራር በሌሉበት የሞት ቅጣት ፈረደ። • ደቡብ አፍሪካ ሶስት የቤተሰቡን አባላት በመግደል ሸሽቶ ወደ ሐገሯ ገብቶ የነበረውን ብሪታንያዊ አሳልፋ ልትሰጥ ነው። • የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ሰርጥ መዝጋቱን አስታወቀ። • የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ሰርጥ ባደረሳቸው ጥቃቶች አንዲት የ9 ዓመት ሴት ልጅን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታወቁ። • የቀድሞው የቃጣር መሪ ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ። 74 ዓመታቸው ነበር ።
DW Amharic የሐምሌ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና 11.07.2026 10:38
አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመች። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አሜሪካ ያዘጋጀችውን ምክረ-ሐሳብ የሚቀበለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ለቅቆ ሲወጣ እንደሆነ ቅድመ-ሁኔታ አስቀመጠ። የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ገደለ ተባለ። የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞሽታባ ኻሜኒ አገራቸው የአባታቸውን ገዳዮች መበቀሏ “አይቀሬ” እንደሆነ ዛቱ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት በኢራን ላይ ያነጣጠሩ 1,000 ሚሳይሎች መጠመዳቸውን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 29 ቆሰሉ።
የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 10.07.2026 10:32
የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢኩዋቶርያል ጊኒ የተጠረዙ ከኢትጵዮያ፣ከአንጎላ እና ከሞሪቴንያ መሆናቸው የተገለፀ 17 ስደተኞች በተያዙበት ሆቴል ውስጥ በኤቦላ እንደተያዘ የሚጠረጠር ቢያንስ አንድ ሰው ተገልሎ እንደሚገኝ የተጠራዦቹ ጠበቆች ተናገሩ። ማላዊ 38 ሺህ ዜጎቿን በአንድ ወር ውስጥ ከደቡብ አፍሪቃ ወደ ሀገራቸው መመለሷን ዛሬ አስታውቃለች። ስድስት የማላዊ ዜጎች መንገድ ላይ ታመው ሞተዋል። የጀርመን የእግር ኳስ ፌደሬሽን በምህጻሩ DFB ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አስልጣኝነት ከታጩት ከዩርገን ክሎፕ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ ኒውዮርክ ተጓዙ።
የሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 09.07.2026 9:57
ናሜይ፥ ሩስያ እና የሣኅል ቀጠና አገራት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው ፤ አንካራ፥ የኔቶ ጉባኤ በተሳታፊዎች ስምምነት ተጠናቀቀ፤ቤርሊን፥ ራኄ መንግሥት ፍሪደሪሽ ሜርስ ትናንት የተጠናቀቀው ኔቶ ጉባኤ ከጠበቁት በላይ መኾኑን ተናገሩ፤ ቴሕራን፥ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጥቃት እየተሰናዘሩ ነው፤ ማሽሐድ፥የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ፤ ሞሮኮ እና ፈረንሣይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ፍልሚያ
የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓም ረቡዕ 08.07.2026 10:54
አርስተ ዜና፤ የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስና ወታደራዊ ኃይል በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረጉት ከፍተኛ ዘመቻ ከ200 በላይ ሰዎችን አሰሩ። በደቡብ አፍሪቃ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ህጋዊ ወረቅት የሌላቸዉ ስለመያዝ አለመያዛቸዉ እስካሁን የወጣ ግልፅ መረጃ የለም።-የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔቶ ስብሰባ አንካራ ተገኝተዋል። ትራምፕ ድርጅቱ ባሳየዉን ወታደራዊ ኤግዚቢሽን የተደሰቱ አይመስልም። የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ኔቶን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትና የኢራን ጦርነት ለመቀላቀል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ትራምፕ በተደጋጋሚ ተችተዋል።
የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 07.07.2026 11:22
አ.አ፥ ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሕገ መንግሥቱ ተናገሩ
DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና 06.07.2026 12:14
የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የ15 ዓመት አዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያፈኑ በግዳጅ ለውትድርና በመመልመል ላይ እንደሚገኙ ሒውማን ራይት ዎች ወነጀለ። በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው ጦርነት በስድስት ወራት ብቻ 330 ሕጻናት መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ሐማስ የጋዛን መንግሥታዊ መዋቅር መፍረሱን አስታወቀ። የዩክሬን ጦር ኦምስክ በተባለ ግዙፉ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ፈጸመ። ለጀርመን ለሚቀጥለው ዓመት የ555.4 ቢሊዮን ዩሮ ረቂቅ በጀት ጸደቀ። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር ከሥምምነት ላይ ካልደረሰች አገራቸው የጀመረችውን ጦርነት "እንጨርሰዋለን" ሲሉ ዛቱ
DW Amharic-የሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና 05.07.2026 7:44
በዛሬው የዓለም ዜና በቀይ ባሕር ትቀዝፍ የነበረች አንዲት ዕቃ ጫኝ መርከብ በየመን ሁዴይዳ የባሕር ክልል አካባቢ ጥቃት ተፈፀመባት መባሉን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሂዝቦላህ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለጿን፣በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት የጋዛ ሆስፒታል ዳይሬክተር ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል መባሉን፣ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአያቶላህ አሊ ካማኔይ የሀዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ልጆቻቸው እና ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት መገኘታቸውን እንዲሁም ትራምፕ በአሜሪካ 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ባደረጉት ንግግር የሀገር ፍቅርን ከፓርቲ ፖለቲካ ጋር ቀላቅለዋል በሚል መተቸታቸውን አካቷል።
የሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና 04.07.2026 10:17
በዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትግራይ ክልል አሁን ያለበት ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለፁን፣የአውሮፓ እና የአሜሪካ መሪዎች ስደተኞችን ለመጠበቅ እና ለማዋሃድ የበለጠ እንዲሰሩ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳሥ ማሳሰባቸውን፣ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊካሜኒ ብሄራዊ የሽኝት ሥነ ስርዓት ዛሬ በይፋ መጀመሯን፣ጀርመን፤ ቤጂንግ የሩሲያ ወታደሮችን ማሰልጠኗን የሚያሳዩ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ቻይናን ማስጠንቀቋን፣አማራጭ ለጀርመን የተባለው መጤ ጠል ፓርቲ ዛሬ መሪዎቹን መምረጡን እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ ለ11 ተከሳሾች ይቅርታ ማድረጋቸውን የሚያስቃኙ ዜናዎች ተካተዋል።
የሰኔ 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና 03.07.2026 11:52
-በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዘይሴ ወረዳ የመንግሥት ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸዉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።---የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አ,ያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ አስከሬን የሽኝት ሥርዓት ዛሬ ቴሕራን ዉስጥ ተጀመረ።ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ የተገደሉት ኻምኔይ ኢራንን ለ37 ዓመት መርተዋል።86 ዓመታቸዉ ነበር።--ሐሙስ ይቀበራሉ።-የጀርመን የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዩሊያን ናግልስ ማን በከፍተኛ ግፊት ሥልጣኑን ለቀቀ።
የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 02.07.2026 11:41
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሬ ዞን ተማሪዎች እስካሁን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና እንዳልተፈተኑ ወላጆች ገለጹ። መምህራኑ «መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመደጎም ያደረገው ውዝፍ የደመወዝ ጭማሪ በተሟላ ሁኔታ አልተከፈለንም» በሚል ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል። በሰሜናዊ ናይጀሪያ ማለቂያ ባጣው ግጭት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ ረሀብ መከሰቱን ዛሬ የተመድ አስታወቀ። የኬንያ ፍርድ ቤት በስምንት ተማሪዎች ላይ የግድያ ክስ መሰረተ። ዛሬ ማለዳ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አመለከቱ። 86 ሰዎችም ተጎድተዋል።
የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.07.2026 9:49
የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አርእስተ ዜና አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ RSFን በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎችና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ ። ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ ሶሻል ዴሞክራት ሜላት ኪሮስ ትናንት ማክሰኞ በአሜሪካ በዴንቨር አካባቢ የተካሄደውን ምርጫ አሸነፉ። ሜላት ኪሮስ ለ15 ጊዜ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ዲያና ደጌትን ነew ያሸነፉት ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በቀጠር ዋና ከተማ ዶሀ ዛሬ ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል ።
የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 30.06.2026 11:27
የተመድ የኢቦላ ወረርሽኝ አፍሪቃን እስከ 3,6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ያስወጣታል አለ። የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት እገታን በመቃወም አደባባይ የወጡ ናቸው በተባሉ ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንድ ሰው መግለደሉን እማኞች አመለከቱ። ሁለት ሰዎችም በጥይት ተጎድተዋል። የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን አል ኦቢድ ጉዳይ አስቸኳይ ክርክር ሊያካሂድ መሆኑ ተገለጸ። በተጠቀሰችው ከተማ ዙሪያ የፈጥኖ ደራሹና ደጋፊዎቹ ኃይሎች መከማቸታቸው ስጋት አስከትሏል። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመጪዎቹ ቀናት የመገናኘት እቅድ የለኝም አለች። ሁለት የአሜሪካ ልዑካን በኢራን ጉዳይ ለመነጋገር ዛሬ ቀጠር መግባታቸው ተዘግቧል።
DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና 29.06.2026 9:40
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ማሕሙድ ተገናኙ። ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ቅንጡ የእጅ ሰዓቶችና ማዳመጫዎች ወደ መፈተኛ ክፍል ይዘው መግባት ተከለከሉ። ኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶችን ከሚወክል ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ለማድረግ በመርኅ ደረጃ ከሥምምነት መደረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኬንያ መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ሊፈራረም ነው የተባለው የውድ ማዕድናት ፍለጋ “ግልጽነት ይጎድለዋል” የሚል ክስ በፍርድ ቤት ቀረበበት። በጀርመን ኒደር ዛክሰን ግዛት ሽታደ ከተማ በተከፈተ ተኩስ 5 ሰዎች ተገደሉ
የዕሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ. ም ፤ የዓለም ዜና 28.06.2026 8:40
የዛሬው የዓለም ዜና በሳውዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ በደረሰ የሄሊኮፕተር እና የአውሮፕላን አደጋ 25 ሰዎች መሞታቸውን፣ በአውሮጳ በተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ1,300 በላይ ሞት መመዝገቡን፣ ቢያንስ 191 ሚሊዮን ሰዎች ለ35 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ይጋለጣሉ መባሉን፣ ኢራን የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ በባህሬን እና ኩዌት ላይ ጥቃት ማድረሷን እንዲሁም የዩክሬንን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያው መሪ የሀገራቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ቃል መግባታቸውን አካቷል።
የሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 27.06.2026 11:30
• በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮጳ ኅብረት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እያካሔደ ነው የተባለው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ የፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ስምምነት በግልጽ የጣሰ ነው ሲል ነቀፈ። • በሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚካሄደው ውጊያ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ። • የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በጎረቤት ሩዋንዳ ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት (ICJ) ክስ መሰረተች። • ኢራን አሜሪካን "ጦርነቱን ለማቆም የተደረገውን ስምምነት ጥሳለች" ስትል ከሰሰች።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.