SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 1001 episodes

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.sbs.com.au

Author

SBS

Category

News

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Oct 1, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android almost 10M downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመግታት የድርጊት እርምጃ ጥሪ ቀረበ 24.04.2024

ሕወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ነው የሚለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው አለ

በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተገለጠ 23.04.2024

ከየመን የባሕር ዳርቻ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ በነበረች አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ተሳፋሪ ከነበሩት 77 ኢትዮጵያውያን ውስጥ 5 ሕፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ የ16 ዜጎች ሕይወት አለፈ

Tackling misinformation: How to identify and combat false news - ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል 23.04.2024

In an era where information travels at the speed of light, it has become increasingly difficult to distinguish between true and false. Whether deemed false news, misinformation, or disinformation, the consequences are the same - a distortion of reality that can affect people's opinions, beliefs, and even important decisions. - መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች...

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትጥቅ ታጋዮች በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ፤ ጥበቃም እንደሚደረግላቸው ገለጠ 23.04.2024

የራያና አላማጣ ተፈናቃዮች ቁጥር እንደሚጨምር ተመለከተ

በጅሮንድ ቻልመርስ የአውስትራሊያ የወደፊት የምጣኔ ሃብት ዕድገት ትንበያን አለዝበው ገለጡ 22.04.2024

በሲድኒ ቦንዳይ ጃንክሽን የገበያ ማዕከል በስለት ተወግታ የነበረችው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን አገግማ ከሆስፒታል ወጣች

"የጋምቤላ ችግር መታየት ያለበት የኑዌሮችና አኟኮች ተደርጎ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ሊያዋጋ የሚችል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ነው" ዶ/ር ኦፒዎ ቻም 22.04.2024

ዶ/ር ኦፒው ኦሙት ቻም፤ የቀድሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ተከስተው ስላሉት ዋነኛ ችግሮች፣ መንስዔዎችና ምክረ ሃሳቦችን አንስተው ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በአገራዊ ምክክር ሂደቱና በኮሚሽኑ ዕቅዶች ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ገለጠ 21.04.2024

ኢትዮጵያ የጠየቀችውን አዲስ ብድር አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር ያላት ልዩነት አልተፈታም

"በሐረሪ ሕብረተሰብ ውስጥ 40 ያህል የአለላ ስፌት ዓይነቶች መኖራቸውን ጥናቶች ያመለከታሉ" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም 20.04.2024

ወ/ሮ ዉዳድ ሳሊም፤ የጤና ባለሙያና አንቂ፤ ስለ ሐረሪ ማኅበረሰብ የአለላ ስፌት ባሕላዊ ቅርስነትና የማንነት መገለጫነት አስመልክተው ይናገራሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በረሃብና ተላላፊ በሽታ እየተፈነች እንደሆነና ከፍ ያለ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻት አሳሰበ 18.04.2024

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት 'ሕወሓት ወረራ ፈፅሞብኛል' ሲል ለፀጥታ አካላት፣ ለነዋሪዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አስታወቀ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ግጭት ውስጥ አይደለሁም አለ

የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ 18.04.2024

በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።

በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ 16.04.2024

ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች? 16.04.2024

የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።

"የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የማነአብ 16.04.2024

"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።

" 'የመኢሶን ሰማዕታት' መጽሐፍ ፋይዳ አንድ ተጨባጭ የሆነ የታሪክ ሰነድ ማቆየት ነው" ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ 16.04.2024

"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የድርጅታቸው የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት የመዘከሪያ መጽሐፍን መሰናዶና ትሩፋቶቹን አስመልክተው ያስረዳሉ።

የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ የገበያ ማዕከል በስለት የተገደሉ ስድስት ሰዎችን በክብርና በሐዘን ለመዘከር በግማሽ ዝቅ ብሏል 15.04.2024

አውስትራሊያ ኢራን በእሥራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አወገዘች

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተካተተች 14.04.2024

ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች ከሥራና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች እንዲገለሉ የሚያደርግ ምዝገባ ልትጀምር ነው

ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ባቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ ገለልተኛና ሙሉዕ ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ 11.04.2024

ዩናይትድ ስቴትስ የዊኪሊክስ መሥራቹን ጁሊያን አሳንጅ ክስ ልታነሳ እንደምትችል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አመላከቱ

#59 Talking about cooking (Med) 11.04.2024

Learn how to talk about cooking and sharing recipes.

ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ይጓዙ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ 10.04.2024

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ አውስትራሊያ ለፍልስጤም አገራዊ ዕውቅና ለመስጠት ዕሳቤ እንዳላት አመላከቱ

"ኢድ አልፈጥር! አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን፤ ደም ማፍሰሱን አላህ በኃይሉ ያስተካክልልን" ሼክ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር 10.04.2024

ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የዘንድሮውን ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የፆምና ፀሎት መንፈሳዊ ፋይዳዎችንና የሰላም ምኞታቸውን አሰናስለው ይገልጣሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ ከ2035 አንስቶ በነዳጅና በናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዳይውሉ ጥሪ ቀረበ 09.04.2024

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት አዲስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሾመ

ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድርድር ሊቀጥል ነው 09.04.2024

በነዳጅ የሚሠሩና ሙሉ በሙሉ በውጭ አገር ተገጣጥመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ ተጣለ

በአዲሱ የምግብና ግሮሰሪ ሥነ ምግባር ደንብ ሱፐርማርኬቶች እስከ 10 ሚሊየን ዶላርስ የሚደርስ መቀጮ ሊያገኛቸው ነው 08.04.2024

የቀድሞው የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አዛዥ በእሥራኤል የአየር ጥቃት ለተገደለችው አውስትራሊያዊት የእርዳታ ሠራተኛ ምርመራ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሰየሙ

"ኤልያስ ካለ ጎል አለ፤ አብዛኛዎቹ የመብራት ኃይል ቡድን ዋንጫዎች የኤልያስ ጁሐር ዋንጫዎች ናቸው" የፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 08.04.2024

"የኤልያስ ዋንጫ" አዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ በዘጋቢ ፊልም ቀርፀው ለሕዝብ ዕይታ ለማቅረብ ስለምን እንደወደዱና የፊልሙን ጭብጥ አሰናስለው ይናገራሉ። "የኤልያስ ዋንጫ" በሳምንቱ መጨረሻ በሜልበርን - አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ በነፃ ይቀርባል።

" የደብረ ዘይት በዓልን ስናከብር የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እያሰብን ነው ። ” መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ 07.04.2024

መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ በአውስትራሊያ የልደታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በትናንትናው እለት የተከበረውን የደብረ ዘይት በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ አደራ ብለዋል ።

Listen to the SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.