DW
ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle
አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።
Author
DW
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 4, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ሩስያና አሜሪካ፥ አፍሪቃን ለመቆጣጠር ሩጫ 07.02.2026 7:36
ሩሲያ ቀድማ እግሯን ባደላደለችባቸው የሣኅል አገራት ጎዳና ላይ ዩናይትድ ስቴትስም መገስገስ ትሻለች ። ከማሊ፣ ከኒጀር እና ከቡርኪናፋሶ ላይ ያላትን አቀራረብም ከወታደራዊ ኹንታው ጋር ቢሆንም እንደገና እያስተካከለች ነው ።
በአማጺው M23 ስር ያለችው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዋ ከተማ ጎማ ከአንድ ዓመት በኋላ 31.01.2026 10:17
ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ጎማ ለጦርነት ክፍት የሆነች ከተማ አይደለችም። የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል። ገበያዎች እንደገና ተከፍተዋል፣ትምህርት ቤቶችም ተከፍተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሁኔታው አሁንም አስቸጋሪ ነው። ከተማዋ አሁንም በአማፂያን ቁጥጥር ስር ነች። ከሁሉም በላይ፣ ስነልቦናዊ መዘዞች በስፋት አሉ። ጭንቀት የብዙዎች የዕለት ተዕለት እውነታ ነው።
የዩጋንዳ ምርጫ ወዴት? 17.01.2026 6:46
ከ40 ዓመታት በላይ ሐገሪቱን ያስተዳደሩት የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረጓል። ዩጋንዳ ውስጥ ሐሙስ በተከናወነው አገር አቀፍ ምርጫ ከ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ሰባት እጩዎች ተፎካክረው ነበር ።
የሱዳን ስደተኞች ብርቱ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል፦ ተመድ 17.01.2026 2:13
በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ባፋጣኝ ካልቀረበ ክምችቱ የፊታችን መጋቢት ወር ማገባደጃ ላይ ሊሟጠጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል የተመድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፎልከር ቱይርክ ሱዳን ውስጥ ከ50 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አወያይተዋል ።
የጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ትኩረት በአፍሪካ 10.01.2026 12:18
ቻይና ለአፍሪካ ሐገራት ያለፖሊሲ ጫናና በቀላል የቢሮክራሲ ውጣውረድ በገፍ የምታቀርበውን ብድር የሐገራቱን መጻኢ ዕድል በቻይና ስር እንዲወድቅ ያደርጋል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ተንታኞችም ይደመጣሉ።
የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ እና የጊኒ ምርጫ 03.01.2026 9:58
ባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው ውዝግብ ቀስቅሷል
ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት 20.12.2025 6:16
በሱዳን የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በሳተላይት የሚከታተለው የየል ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ ጉዳዮች ጥናት ላቦራቶሪ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሚሊሻያዎች የፈጸሟቸውን የጅምላ ግድያዎች ማስረጃዎች እያወደሙና እየደበቁ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስጠንቀቂያ የካተተ ዘገባ አቅርቧል።ሂዩመን ራይትስ ዋች በሱዳን ጦር እስር ቤቶች ሰዎች እየሞቱ ነው የሚሉ ዘገባዎች ደርሰውታል።
ትኩረት በአፍሪቃ 201225 ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት ፤ በአፍሪቃ የተካሄዱት መፈንቅለ መንግሥታት 20.12.2025 6:13
ትኩረት በአፍሪቃ በሱዳኑ ውጊያ ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ቢሆንም ለነዚህ በዓለማችን እጅግ አስከፊ ለሚባሉ የሰብዓዊነትና እና የመፈናቀል ቀውሶች የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ትኩረት አሁንም አነስተኛ ነው። በቅርብ ጊዜያት በሁለት የአፍሪቃ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥታት ፣በአንድ ሌላ ሀገር ደግሞ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጓል። ተከታታዮቹ መፈንቅለ መንግስታትና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ምን ያመለክታሉ? የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ኂሩትመለሰ አጠናቅራዋለች።
የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍ 15.11.2025 6:25
በጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።
ትኩረት በአፍሪካ፦ የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍ፤ በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ 15.11.2025 13:49
በጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።
በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ 15.11.2025 7:24
«ይህ የኦጎኒ ዘይት በእጁ ብዙ ደም አለው። እርስዎ እኔን ተረድተውኝ ከሆነ አላውቅም ። ይህ የኦጎኒ ዘይት ብዙ ደም አለው። ሕዝባችን ሞቷል፣ ብዙ ሰዎች፣ የኦጎኒዎች ሕይወት ብቻ አይደለም የጠፋው። በተቃውሞው ወቅት ከ4,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ታውቃላችሁ፣ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የፌዴራል መንግሥት በመጀመሪያ የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት። »
በሱዳን፡ ጦርነቱን ያቀጣጠሉት የውጭ ኃይሎች ጦርነቱን ማስቆም ይችሉ ይሆን? 08.11.2025 7:36
የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ድጋፍ በውጭ ሀገራት ላይ የተመሰረተ ነው።በጄኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ሀይል የሚደግፈው በግብፅ፣ ቱርክ፣ ሩሲያ እና ኢራን መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ደግሞ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይደገፋል። ለመሆኑ ሀገራቱ ከሱዳን ምን ይፈልጋሉ? ጦርነቱን ማስቆም ይችሉ ይሆን?
ናይጄሪያ፤ “የክርስቲያን ዘር ማጥፋት” ወይስ የትርርክት ቀውስ? 08.11.2025 8:32
በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ላይ «የዘር ማጥፋት» ዘመቻ እየተካሄደ ነው መባሉ ሞቅ ያለ ክርክር አስነስቷል፣ ተንታኞች እንዲህ ያሉት ትርክቶች የሀገሪቱን የሰላም ግንባታ ጥረቶችን ሊያዳክሙ እና መለያየትንና አለመተማመንን ሊያባብስ ይችላሉ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ትራምፕ ግን አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ትወስዳለች ብለው እያስፈራሩ ነው።
ከ18 ዓመት በታች ስደተኞች የሊቢያና የባሕር ላይ መከራ 25.10.2025 7:20
ስደተኞችን ከመስጠም አደጋ የሚታደጉ የባሕር ላይ ነፍስ አድን ድርጅቶች የማንቂያ ደውሉን እያሰሙ ነው ። በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች በዓለም ላይ ካሉ አደገኛ የስደት መስመሮች አንዱ የሆነውን የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው እየፈለሱ ነው ። በባሕር ከመስጠም ከተረፉት መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።
የኮትዲቫር ምርጫ እና የዴሞክራሲ ጥያቄ 25.10.2025 6:36
30 ሚሊዮን ነዋሪ ያላት ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ኮትዲቫር ቅዳሜ፤ ጥቅምት 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አካሂዳለች ። ለአራተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራ ያሸንፋሉ የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቷል ። የ83 ዓመቱ አዛውንት የአገሪቱ ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራን ጨምሮ አምስት ተፎካካሪዎች ለፕሬዚደንትነት ተፎካክረዋል
ትኩረት በአፍሪካ የጥቅምት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና 18.10.2025 14:44
አምስት ጊዜ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረው ባይሳካላቸውም ራይላ ኦዲንጋ የኬንያን ዴሞክራሲ እና ምርጫ የይስሙላ እንዳሆን ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል። በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦዲንጋ በተቃዋሚነታቸው ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ ተሰደዋል። ግን እስከ መጨረሻው አላፈገፈጉም። በማዳጋስካር ጦር ሠራዊት ውስጥ ካፕሳት ተብሎ የሚጠራው ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ሚካኤል ራንጄሬሪና ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። የ51 ዓመቱ የጦር መኮንን ሥልጣን የጨበጡት ለሦስት ሣምንታት ከተካሔደ የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጄሊና ከሥልጣን ተባረው ነው።
የካሜሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ43 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩትን የፓል ቢያን ሥልጣን ያራዝም ይሆን ? 11.10.2025 11:22
ፎኩም «በምርጫው ቀን ለመምረጥ መውጣት መቻላችንን መጠየቅ ጀምሬያለሁ፣ሁሉ ነገር ከተዘጋጋ ድምጽ ለመስጠት ወደምርጫ ጣቢያ እንዴት እንሄዳለን» ይላሉ።«የመራጮች ቁጥር በፀጥታ እጦት ካነሰ ምርጫው የተሀድሶ መንገድ ሳይሆን “የይስሙላ” ነው የሚለውን ግንዛቤ ያጠናክራል ፤መራጮች እንቅፋቶችን ከተቃወሙ ግን ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።»
ትኩረት በአፍሪካ፤ የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ፤ ኡጋንዳ 40 ዓመታት በዩዌሪ ሙሰቬኒ ሥር 27.09.2025 13:02
የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ ተጨምሮበት ደቡብ ሱዳንን እንደገና ወደ ግጭት ሊመልሳት ይችላል እየተባለ ነው። ለዛም ነው የሪክ ማቻር የፍርድ ሂደት የእሳቸውና እና የተባባሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የደቡብ ሱዳን የወደፊት እጣ ፈንታን የሚወስን ነው የሚባለው።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.