DW
ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle
አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።
Autor
DW
Kategorie
Podcast-Website
Neueste Folge
4. Jul 2026
Wo hören?
Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbarPodcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts
Folgen
ትኩረት በአፍሪቃ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 04.07.2026 15:16
የደቡብ አፍሪቃ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ አብዛኞቹን የአፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት አስቆጥቷል። ናይጀሪያ እና ኬንያን ጨምሮ በርካቶቹ ዜጎቻቸውን ለማውጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ደክመው ያፈሩት ሀብት ለተዘረፈ ለወደመባቸውም ካሣ እንደሚጠይቁ እየገለጹ ነው። በዚህ መሀል እዚያ ያሉ ወገኖች ሰቀቀን ከፍቷል።
ትኩረት በአፍሪቃ፣ ሱዳን-አል ዑቤይድ ላይ ያጠላዉ ሥጋት፤ የጊኒ ቢሳዉ ቀዉስ 20.06.2026 12:11
ከዚሕ ዉስጥ ከ14 ሚሊዮን የሚበልጠዉ አንድም ተፈናቃይ ሁለትም ሥደተኛ ነዉ።የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) እና የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ባለሥልጣናት ባገባደድነዉ ሳምንት አጋማሽ እንዳሉት በዓለም በርካታ ሕዝብ ለረሐብ ከተጋለጠባቸዉ 13 ሐገራት ወይም ግዛቶች ግንባር ቀደሟ ሱዳን ናት።
የደቡብ አፍሪቃ የፍልሰተኞች ቀውስ፥ የፕሬዚደንቱ ዕቅድ ያጠራጥራል 13.06.2026 7:59
የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት «ሕገ ወጥ» ያላቸው ስደተኞች ላይ ቁጥጥሩን እንደሚያጠብቅ ዝቷል ። ስደተኞቹ እንዲወጡ የሚያስተባብሩ የደቡብ አፍሪቃ ሰልፈኞች ግን የአገሪቱን መንግሥት ዕቅድ የመስማት ፍላጎቱም ያላቸው አይመስሉም ።
ሶማሊያ ቱርክ የነዳጅ ክምችቷን እንድትጠቀም ለምን ፈቀደች? 18.04.2026 6:17
ቱርክ በሶማሊያ የባህር ዳርቻ ነዳጅ ለማውጣት ዝግጅት ላይ ነች፡። ለነዳጅ ፍለጋው ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ትልቅ መርከብ ካግሪ ቤይ፤ ከሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ደርሳለች። በጎርጎሪያኑ በ2024 ሁለቱ ሀገራት የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብሩ አሁን ወደ ነዳጅ ፍለጋ አድጓል።
በአፍሪቃ የኑክሌር ተቋምን ለመገንባት ሩጫ 28.03.2026 8:26
የግል የኒኩሌር ተቋም፦ ደቡብ አፍሪቃ የራሷ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አላት፣ ግብፅ በግንባታ ላይ ነች፣ ኬንያ፣ ጋና እና አንዳንድ ሌሎች አገራት እናም ቢኖረን ሲሉ ያልማሉ ። ስኬቱ ለየቅል ቢሆንም፤ የሕዝቡ ስጋት ግን ተመሳሳይ ነው ። ሙሉ ዘገባውን በድምጽ እና በጽሑፍ ከገናኛው ማግኘት ይቻላል።
ናይጄሪያ ወደቦቿ ከብሪታንያ ብዙ ያተርፋሉ ስትል አቅዳለች 28.03.2026 3:01
ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ናይጄሪያ፦ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት የብሪታንያ ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ የተገነባው የአገሪቱ ዋነኛ የንግድ ማሳለጪያ አፓፓን ጨምሮ የቲንካን ደሴት ወደቦችን ለማሻሻልም ከፍተኛ ተስፋ ሰንቃለች ። ሙሉ ዘገባውን በድምጽ እና በጽሑፍ ከገናኛው ማግኘት ይቻላል።
የአፍሪቃ የነዳጅ ምርት ቢጨመር የዓለም የነዳጅ ገበያን ያረጋጋ ይሆን? የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪቃ 21.03.2026 11:10
ናይጀሪያዊው ተንታኝ አዮዴሌ ኦኒ ከአፍሪቃ ነዳጅ ዘይት አምራቾች ናይጀሪያ ብዙ ነዳጅ ዘይት የማምረት አቅም እንዳላት ገልጸዋል። ይሁንና በርሳቸው አስተያየት በአሠራር ችግርና በነዳጅ ክምችት ማነስ ምክንያት ለአሁኑ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ቀውስ ግን መድረስ አትችልም
ትኩረት በአፍሪቃ፣ የባሕረ ሰላጤዉ ጦርነት መዘዝ በሶማሊላንድ፣ ደቡብ አፍሪቃ-ወርሮበላን ለመምታት ጦር ሠራዊት 14.03.2026 12:11
ታዛቢዎች እንደሚገምቱት የእስራኤል ጦር ገና ካሁኑ ሶማሊላንድ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጦር ሠፈር ዉስጥ ሳይሰፍር አልቀረም።ጦሩ ሶማሊላንድ የሰፈረዉ የሁቲ አማፂያንን ከቅርብ ርቀት ለማጥቃት ነዉ
ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? 07.03.2026 6:18
የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፍ ንግድን እያስተጓጎለ ነው። የንግድ መርከቦች ከሱዌዝ ቦይ ይልቅ አፍሪካ ወደሚገኘው ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ለመሄድ ይገደዳሉ። ይህም ወጪን ይጨምራል፤በነዳጅ እና በሌሎች ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ ያስከትላል። ጦርነቱ በውጭ አገር ተቀጥረው ለሚሠሩ አፍሪቃውያንም የኢኮኖሚ መዘዝ አለው።
ትኩረት በአፍሪቃ፤ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን ስጋት ገባት? 07.03.2026 5:49
ከ400,000 በላይ ኬንያውያን እንደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር ባሉ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ይሰራሉ። ብዙዎቹ በቤት ውስጥ ሥራ፣ በግንባታ፣ በእንግዳ ተቀባይነት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ተቀጥረው ይሰራሉ።የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እነዚህን ኬንያውያን ስጋት ውስጥ ከቷል።
በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚና 28.02.2026 5:34
በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ ጎረቤት ቻድም እየተቃረበ ነው። ያለፈው ሳምንት መጨረሻ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በድንበር ላይ ከሚገኙት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ የRSF ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል። የቻድ መንግስትም ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዘግቷል።
ፕሬዝዳንት ኪር ደቡብ ሱዳንን ማረጋጋት ይችሉ ይሆን? 28.02.2026 5:33
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሰሞኑን ባለስልጣኖቻቸውን ከስልጣን ማባረር ይዘዋል። ተንታኞች እንደሚሉት የሰሞኑ የፕሬዚዳንቱ እርምጃ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት የሚያባባስ ነው። በሙስና፣ በጎሰኝነት እና በብልሹ አስተዳደር የሚተቸው የሳልቫኪር መንግስት ምክትላቸውን ሪክ ማቻርን ካሰሯቸው ወዲህ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ተባብሷል።
አሜሪካ እጇን ያስገባችበት የኮንጎ የሰላም ስምምነት ይጸና ይኾን? 21.02.2026 5:35
በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓመታት የዘለቀው ደም መፋሰስ እንዲቆም አዲስ የተስፋ ጭላንጭል አሳይቷል። ባለፈው ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው የተኩስ አቁም ስምምነት፤ «ለመጨረሻ ጊዜ የተገኘ የሰላም ዕድል ይሆን?» የሚለው ጥያቄ የአለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ትኩረት ስቧል።
ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ከአሜሪካ ወደ ቻይና አዙራ ይኾን ? 21.02.2026 6:17
በሁለቱ የዓለማችን ልዕለ ኃያላን የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ መሃል የገባችው ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ወደ ምሥራቅ ታዞር ይኾን? የሚለው ጥያቄ አሁን የበርካቶችን ትኩረት የሳበ መስሏል። ላለፉት 20 ዓመታት ደቡብ አፍሪካ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚገርም ብልሃት ሚዛኑን ጠብቃ ማቆየቷ ነው የሚነገርላት።
የሱዳን ጦርነት ከኤል ፋሸር እስከ በኒ ሻንጉል፤ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤና የአሕጉሪቱ ሠላም 14.02.2026 12:13
የብሪታንያዉ ዜና አገ,ልግሎት ሮይተርስ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ተዋጊዎች የሚሰለጥኑበት ጦር ሠፈር ኢትዮጵያ ዉስጥ መግንባቱን ከዘገበ ወዲሕ ጉዳዩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ።
Ähnliche Podcasts
Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet