DW
ማሕደረ ዜና
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ለኢትዮጵያ ቀውስ መፍትሔ ሳይበጅ፣ ግጭት ሳይቆም የሽግግር ፍትሕ ተጎጂዎችን ይፈውስ ይሆን? 22.12.2024 13:00
በኢትዮጵያ የቀውስ አዙሪት ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር እና መፈናቀልን ጨምሮ የተለያዩ ግፎች የተፈጸሙባቸው ዜጎች ፍትሕ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ጭምር ለሽግግር ፍትሕ እየተዘጋጀች ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ግጭት ሳይቆም፤ ሀገሪቱን ቀውስ ውስጥ ለከተቱ ፖለቲካዊ ልዩነቶችም መፍትሔ ሳይበጅ ተግባራዊ የሚደረግ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት በእርግጥ ተጎጂዎችን ለመፈወሱ በርካቶች ጥያቄ አላቸው።
ተዳፍኖ የቆየው የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እያገረሸ ይሆን? 02.12.2024 11:37
የሶርያ አማጽያን በፕሬዝደንት በሺር አል አሳድ መንግሥት ላይ የከፈቱት ጥቃት ተዳፍኖ የቆየውን የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየቆሰቆሰው ይገኛል። አማጽያኑ አሌፖን ተቆጣጥረው ሐማ ወደ ተባለች ከተማ ሲገሰግሱ ሶርያ እና ሩሲያ በአየር ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸሙ ነው። የአሳድ አጋር ሒዝቦላሕ አሁን ተዋጊዎች ወደ ሶርያ የመላክ ዕቅድ እንደሌለው አስታውቋል። የሶርያን ጉዳይ የቀጠናው ሀገራት እና ልዕለ ኃያላን በእግር ጥፍራቸው ቆመው እየተከታተሉ ነው።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የ50 ዓመት ትግል፣ ዉጤትና ክሽፈት 15.11.2024 16:57
«የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ ይሠራል።አሁንም እየሠራ ነዉ።----በሚቀጥለዉ ምርጫ ይወዳደራል--------የአማራ ሕዝብን አይጠላም-----የመገንጠል ዓላማ የለዉም---» ያላሉ ዶክተር ሽጉጥ ገለታ።»
የማሕደረ ዜና ማስተዋወቂያ 08.11.2024 0:59
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሀገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
ቃለ መጠይቅ፤ የፕሪቶሪያ የሰላም ዉልና የሰላም ዉል ማግሥት ጦርነት 05.11.2024 24:08
ሥለጦርነቱ መነሻ እስካሁን ድረስ በግልፅ የወጡት መረጃዎች የሚቃረኑ ናቸዉ።ተፋላሚ ኃይላት በየፊናቸዉ የሚሰጧቸዉ ምክንያቶች አሉ።እስካሁን ሥለጦርነቱ መነሻ በገለልተኛ ወገን የተደረገ ጥናት ወይም ይፋ የሆነ መረጃ የለም።በዚሕም ምክንያት ለጦርነቱ መጫርና ላደረሰዉ ጥፋት ተጠያቂ የሚባል ወገንን ለመለየት በጣም አስቸጋሪ ነዉ።
ቃለ መጠይቅ፣ የሶማሊያና የግብፅ ወታደራዊ ዝግጅት ያስከተለዉ ሥጋት 04.09.2024 18:05
ግብፅ ከዚሕ በተጨማሪ በመጪዉ ታሕሳስ ባዲስ መልክ ይዋቀራል ለተባለዉ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት 5000፣ ለሶማሊያ መንግሥት በቀጥታ ድጋፍ የሚሰጥ ሌላ 5000 ጦር ኃይል ሶማሊያ ዉስጥ ለማስፈር ማቀዷም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የሶማሊያና የግብፅ ጦር ኃይላት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸዉም ተነግሯል
የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትን ከምክትል ሊቀመንበርነት አሰናብቶ ተጠቀቀ-ከዚያስ? 19.08.2024 13:28
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮቹን ለውዝግብ የዳረገውን ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀ-መንበርነታቸው ቀጥለዋል። አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው አቶ ጌታቸው ረዳን ተክተዋል። ለህወሓት አዲስ የሥራ አስፈፃሚ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ቁጥጥር ኮሚሽን የተመረጠበት ጉባኤም ይሁን ውጤቱ ግን በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። በህወሓት መሪዎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት የፖለቲካ መሪዎች እና ነዋሪዎችን አስግቷቸዋል።
ማሕደረ ዜና፦ የጎፋ ሕዝብ ለቅሶ የኢትዮጵያ ሐዘን 29.07.2024 12:32
በጎፋ ዞን በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት 231 የአካባቢው ነዋሪዎች 260 ሰዎች እንደሞቱ ይገልጻሉ። በርካቶች የሟቾች ትክክለኛ ቁጥር ተድበስብሷል የሚል ሥጋት አላቸው። አደጋው “ማምረት የሚችሉትን” ሕይወት ነጥቆ ሕጻናት እና አቅመ ደካሞችን ያለ ረዳት ያስቀረ ነው። አስከሬን ፈልጎ ማንነቱን መለየት ለቤተሰብ ማስረከብ በአካባቢው ነዋሪዎች ጫንቃ ወድቋል።
ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ሲሰናበቱ ዶናልድ ትራም ተፎካካሪያቸውን እየጠበቁ ነው 22.07.2024 12:05
ጆ ባይደን ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ሲያገልሉ ይሁንታቸውን ለካማላ ሐሪስ ሰጥተዋል። የ59 ዓመቷ ካማላ ሐሪስ የሥመ-ጥር ዴሞክራቶችን ድጋፍ ቢያገኙም የዴሞክራቲክ ፓርቲው እጩ መሆናቸው በይፋ የሚወሰነው በነሐሴ ወር ነው። ካማላ ሐሪስ የዴሞክራቶች እጩ ሆነው ዶናልድ ትራምፕን ቢያሸንፉ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። “ግብጽ የህዳሴ ግድብን ታፈርሳለች” ብለው ኢትዮጵያን ያስቆጡት፤ አፍሪካን በአጸያፊ ቋንቋ የጠሩት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተቀናቃኛቸውን ማንነት ለመየት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.