DW

ማሕደረ ዜና

News AM ↓ 100 episodes

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ

Author

DW

Category

News

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 6, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ማሕደረ ዜና፣ የቀይ ባሕር አካባቢ መንግሥታት ዉስብስብ ግጭትና ዉጥረት 14.07.2025

ነሐሴ ላይ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዱረሕማን መሐመድ ኢሮ አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉብኝቱ «በጠወለገዉ» የመግባቢያ ስምምነት ላይ ነብስ ከዘረባት እስካሁን ገሚስ የህወሓት መሪዎችን የክበቡ አካል ለማድረግ የሚዉተረተረዉ የሞቃዲሾ፣ ካይሮ፣ አሥመራ ገዢዎች አክሲስ ወይም ሥብስብ ምናልባት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ገሚስ መሪዎችን ሊያቅፍ፣ አጓጉል መዘዙ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን ሊደርስ ይችላል።

ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታ 07.07.2025

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዋሽግተን ዉስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ሁለቱ መሪዎች የዓመት ከዘጠኝ ወራቱን ወታደራዊ ዘመቻ ለ60 ቀናት ለማቆም ያላቸዉን ዕቅድ ያስታዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዩናይትድ ስቴትስና ቀጠር አቀረቡት የተባለዉን ሐሳብ እስራኤልም-ሐማስም ተቀብለዉታል ተብሏል።ሐሳቡ መፅደቅ-መዉደቁ የሚወሰነዉ ግን በትራምፕና በኔትንያሁ ትዕዛዝ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል፣ የአሜሪካና የኢራን የጦርነት ማግሥት የጦርነት ዝግጅት 30.06.2025

በርግጥ ጀግናዉ ማነዉ? 12 ቀናት የቆየዉን፣ከ600 በላይ ኢራናዉያንን፣ 28 እስራኤላዉያንን የገደለዉን፣ የሁለቱን ሐገራት ምጣኔ ሐብት ያሽመደ።መደዉን ዉጊያ ቀድማ የከፈተችዉ እስራኤል ናት።ዩናይትድ ድብደባዉን ፈቅዳለች፣ ኋላ ራሷ ቀጠላበታለች።አሁን የሚሞጋገሱት የሁለቱ ጥብቅ ወዳጅ መንግሥታት መሪዎች ኢራንን ለመደብደባቸዉ የሰጡት ምክንያት የቴሕራንን የኑክሌር ተቋማት ለማዉደም ነዉ።ወሕኒ ቤት የኑክሌር ተቋም ይሆን?

ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ፣ መዘዙና ሕግ አልባዋ ዓለም 23.06.2025

የቀድሞዉ የዶናልድ ትራምፕ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ባንድ ወቅት «የዓለም ማሕበረሰብ የሚባል ነገር የለም።ያለችዉ አንድ ልዕለ ኃያል ሐገር ናት-ዩናይትድ ስቴትስ።» ብለዉ ነበር።አላበሉም።ዓለም የጋራ ማሕበር፣ ፍርድ ቤት፣ ሕግ፣ ደንብ፣ ሥምምነት የሚኖራት ለአሜሪካና ለእስራኤል እስከጠቀመ ብቻ ነዉ።ባይሆን ኖሮ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯ ከተወገዘ፣ በማዕቀብ ካስቀጣ፣እስራኤልና አሜሪካ ሊባኖስን፣የመንን፣ ሶሪያን፣ኢራንን መደብደባቸዉ፣ታጣቂዎችን ከሕሙማን ሳይለዩ መግደላቸው የማያስወገዝ፣ የማያስጠይቅ፣ የማያስቀጣበት ምክንያት የለም።

የእስራኤል ኢራን ጦርነት ዓለማቀፍ ስጋት ደቅኗል 17.06.2025
ማሕደረ ዜና፤ ሊቢያ፣ ኃያላን ያወደሟት፣ታጣቂዎች የሚተራመሱ፣ ዘራፊዎች የሚሻሙባት ሐገር 02.06.2025

የአሜሪካዉ ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ በ2022 እንደዘገበዉ በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔ የዘመተዉ የኔቶ ጦር ከመርከብ የተኮሰዉ ሳይቆጠር በጦር ጄት ብቻ ሊቢያን 10ሺሕ ጊዜ ደብድቧል።በድብደባዉ የተገደለዉን ሰዉ ቁጥር እስከ 500,000 የሚያደርሱት አሉ።መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥርን ሲያንስ 70 ሲበዛ 403 ያደርሱታል።የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ምብቶች ምክር ቤት የኔቶ ጦር 60 ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን አረጋግጧል።ሟች ቁስለኛዉ 60፣70፣400 ይሁን 500 መቶ ሺሕ ተጠያቂዎች ለፍርድ ቀርበዉ ይሆን? ሐገር ማፍረስስ ያስወነጅል ይሆን? አናዉቅም።ሊቢያ ግን በርግጥ ፈርሳለች።

የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትችትና ነቀፋ የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን? 26.05.2025

ፐሬዝደንት ኢሳያስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወይም ባካባቢዉ የታወጀ ጦርነት አንድ አይደለም። «ብዙ ጦርነቶችን ለማስቀጠል ዘመናይ ቴክኖሎጂና ጦር መሳሪያ እየተሰበሰበ ነዉ» ብለዋል።የብልፅግና ፓርቲ ለቴክኖሎጂና ለጦር መሳሪያ የሚያወጣዉ ዶላርም ልክ የለዉም ብለዋል።ኢሳያስ «ርካሽ» ያሉት ፉከራና ቀረርቶ በእሳቸወ አገላለፅ ተመዝግቧል።«የኤርትራን ሕዝብና መንግሥትን ወደ ግጭት ለማስገባት የሚሸረበዉ ግልፅና ሥዉር ሴራን ያላወቀዉ የለም» ይላሉ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት።የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?

ማሕደረ ዜና፣ የምርጫ 97 ሒደት፣ዉጤትና አሳዛኝ ፍፃሜዉ 20 ዓመት ደፈነ 19.05.2025

ከ25 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ ሰጥቶበታል።ሕዝባዊ፣ ታሪካዊ፣ አብነታዊም ነበር።የአሸናፊ-ተሸናፊዉ ዉዝግብ፣ የገዢዉ ፓርቲ ጨካኝ ርምጃና እስከዛሬ የተረፈዉ መዘዝ ሲጤን ግን ራቅ ሲል በ1953 በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ከሞከረዉ መፈንቅለ መንግስት፣ ቀረብ ሲል በ1969 በኮሌኔል መንሥቱ ላይ ከተሞከረዉ የግድያ ጥቃት ዉጤት ጋር የሚያመሳስሉት አሉ።

ማሕደረ ዜና፣ ሕንድና ፓኪስታን የዝንተ ዓለም ጠላቶች 12.05.2025

የሒንዱ፣የሲክና የቡዳሐ አማኞች በብዛት የሚኖሩበት ግዛት ሕንድ ሲባል፣ ሙስሊሞች የሚበዙበት የዛሬዎቹ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ግዛቶች ደግሞ ፓኪስታን ሆኑ።ክፍፍሉ ሲደረግ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩበት የጃሙ ካሽሚር ካሽሚር ግዛት ግን የሒንዱ እምነት የሚከተሉት የግዛቱ አገረ-ገዢ እንደጠየቁት ነፃ መንግስትም ሳይሆን፣ ከፓኪስታንና ሕንድም ሳይጠቃለል ለወደፊቱ ግጭት እንዲመች ተንጠልጥሎ ቀረ።

ማሕደረ ዜና፣ የፕሬዝደንት ትራምፕ ሠላም የማስፈን ቃልና ተቃራኒ ርምጃ 05.05.2025

በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ የእስራኤል ጦር ገና በቅጡ ያልጠናዉን የሶሪያ መንግስት ይዞታዎችን በተዋጊ ጄቶች ደብድቧል።እስራኤል ጋዛን፣ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻን ፣የመንን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን መናደፏ አልበቃ ብሏት በተለያዩ የሶሪያ ጎሳ ወይም የሐይማኖት ሐራጥቃ ተከታዮች መካከል በተነሳ ጠብ ጣልቃ ገብታ በ14 ዓመት ጦርነት የወደመችዉን ሶሪያን ደጋግማ መደብደቧ ለብዙ ታዛቢ ግራ አጋቢ ነዉ።ሶሪያዊ አዛዉንት እንደሚሉት ግን የእስራኤል ጥቃት በአረብ መሪዎች ዝምታ፤ በዶንልድ ትራምፕ ይሁንታ የታገዘ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቃል፣ መርሕና እርምጃ ቁንፅል ትዉስታ 28.04.2025

ሕይወቱን ለኃይማኖት ከሰጠ በኋላ ግን እንደ ድሆች ሁሉ ለስደተኞችም ሲሟገት አድጎ፣ጦርነትን ሲቃወም በስሎ አርጅተዋል። ፍራንሲስ። በ 12 ዓመታት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣናቸዉ ዘመን 68 ሐገራትንና በመቶ የሚቆጠሩ ግዛቶችን ጎብኝተዋል።ከሮም ዉጪ መጀመሪያ የጎበኙት ግን በአብዛኛዉ የአፍሪቃ ስደተኞችን የሜድትራንያንን ባሕር ለማቆረጥ ሲቀዝፉ በብዛት የሚልቁበትን ባሕር፣ ከዳኑ የሚያርፉበትን ደሴት ነበር።ላፔዱዛን ሐምሌ 8፣ 2013

ማሕደረ ዜና፣የሱዳን ዉድመትና የመከፋፈሏ ሥጋት 21.04.2025

የለንደኑ ጉባኤ የተደረገዉ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ያደረጁት «የሱዳን የሰላምና የአንድነት» ወይም የሱዳን ትዩዩ መንግሥት መመሥረቱ ናይሮቢ ላይ በታወጀ ማግሥት፣አል ቡርሐን የሚመሩት መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤት ላይ በከሰሰ ሳልስት ነበር።ሚዚያ 16።ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመሯቸዉ ቡድናት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የገንዘብ ድጋፍ፣በኬንያዉ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ አስተናጋጅነት የትይዩ መንግስት መመሥረታቸዉን ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ አዉግዘዉታል

ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን? 14.04.2025

የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003።ዋሽግተን።ሲሞን ሔርሽና ኮኒ ብሩክ የተባሉት መርማሪ ጋዜጠኞች እንደፀፋት የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ መሪዎች የቴሕራኖችን ሚስጥር እንዲያጋልጡ የገፋፏችዉ መረጃዉንም የሰጧቸዉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ናቸዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታ 07.04.2025

የቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ 31.03.2025

የብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?

ማሕደረ ዜና፣ ሱዳኖች አንድም ሁለትም ሆነዉ ከግጭት-ጦርነት ያልተዩ ሐገራት 24.03.2025

የማቻር ደጋፊ የሚባሉት የኑዌር ጉሳ ሚሊሻዎች ኢትዮጵያን በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢ ከሠፈረዉ ከፕሬዝደንት ሳልቫኪር መንግስት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩ ሳምንት አልፈዋል።የጁባዎች ጠብ የናረዉ ጁባዎች ከጋራንግ ሞት በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ ከአል በሽር መወገድ በኋላ ዋና እና ምክትል ሆነዉ የካርቱም ሪፐብሊካን ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት የሱዳን ጄኔራሎች የገጠሙት ጠብ በጦር ሜዳዉም በፖለቲካዉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት መሆኑ ነዉ።የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከደቡብ ሱዳን ቡድናት ካንደኛዉ ጋር ያለዉን ትብብር ከማጠናከርም አልፎ የትይይዩ መንግስት--- ዳርፉር ግዛት ሊመሰርት ይችላል የሚለዉ ግምትም እያየለ ነዉ

“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር 17.03.2025

የህወሓት አመራሮች ልዩነት ሲበረታ በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ያለፈው የትግራይ ክልል ነዋሪ “ነገስ ምን ይፈጠራል?” በሚል “እየተሳቀቀ እንዲኖር” ተገዷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ሥጋት “ሰዉ በጣም ተረባብሿል”፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ “መከፋፈል” ተፈጥሯል። ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው “የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ” ነው።

ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየተንሸራተተች ይሆን? 10.03.2025

ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ናስር ከተማ በደቡብ ሱዳን ጦር ሠፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጁባን ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ከቷታል። በናስር በሚገኝ የደቡብ ሱዳን የጦር ሠፈር ላይ ባለፈው ሣምንት ጥቃት የፈጸመው ዋይት አርሚ ተብሎ የሚጠራ የኑዌር ጎሳ ታጣቂ ቡድን ነው። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸው ሪየክ ማቻርን ሳያማክሩ የወሰዷቸው ርምጃዎችም ቅሬታ ፈጥረዋል። ሁለቱ የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ፈርሶ ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ ሥጋት አለ።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ሶማሊያ ወዳጅነት ካንጀት ወይስ ካንገት? 03.03.2025

የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች የጠባቸዉን መሰረታዊ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ማስወገዳቸዉን በይፋ ሳይናገሩ በወር ዕድሜ ለመወዳደስ፣ መተቃቀፍ መነፋፈቅ መድረሳቸዉ በርግጥ ጉድ አጃኢብ ማሰኘቱ አልቀረም።ማስታወቂያ ሚንስትር ዳዉድ አዌስ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምነት ተሰርዟል።አዲሱ የትብብር ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ወደብ ሥለ ማስገኘት አለማስገኘቱ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የምክር ቤት አባልናየፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር አብዲ ቡባል እንደሚሉት ደግሞ መተማመንን ለመገንባት ከአዲስ አበባ-ሞቃዲሾ-አንካራ የሚባክኑት ባለሥልጣናት ወደብን በተመለከተ አሁንም አይተማመኑም

ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ትዩዩ መንግስት፣ ጦርነቱና የዉጪ ጣልቃ ገብነት 24.02.2025

ጉባኤተኞቹ እንዳሉት ዓላማቸዉ የሱዳንን አንድነት፣ የሕዝቧን ሠላምና ደሕንነት በጋራ ማስከበር ነዉ።የጉባኤተኞቹን ዉሳኔ በንባብ ያሰሙት የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ ሳንዳል ሐጋር እንዳሉት ደግሞ ጦርነቶችን በሙሉ ለማቆም ቆርጠዋልምተባባሪዎቹ በአማላይ ቃላት የከሸኑትን ሥምምነትና ትብብር ገቢር ማድረግ አለማድረጋቸዉ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከቀድሞ ቀንደኛ ጠላቶቹ በተለይም ከSPLM-N ጋር መወዳጀቱ ግን የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከምዕራባዊ ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ጥግ፣ ከሊቢያ ጠረፍ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር በሚደርሱ አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ይጠቅመዋል።

ማሕደረ ዜና፣ የሁለት ጉባኤዎች አጭር ወግ 17.02.2025

የሐገራት መሪዎች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የማሕበራት ሊቃነ መናብርት፣ ባለሙያዎች፣ የሠላምን ጥቅም፣ የዴሞክራሲን ፋይዳ፣ ተባብሮ የመሥራትን አስፈላነትን፣ ግጭት፣ጦርነት፣ አለመግባባት ያደረሱና የሚያደርሱትን ጉዳት የሚገልፁ፣ዉብ፣አማላይ፣ ማራኪ ቃላትን በየአዳራሹ አዘነቡት።በነዚያዉ ቃላት ተጠዛጠዙባቸዉም።የአፍሪቃ መሪዎች ዉሳኔ፣ መግለጫ ከአዲስ አበባ ሲናኝ የሙኒክ ጉባኤተኞች የፕሬዝደንት ሼሴኬዲን ማብራሪያ ያዳምጡ ነበር።እዚያዉ ምሥራቃዊ ኮንጎ ግን በሩዋንዳ የሚደገፈዉ M23 አርብ የቡካቩ አዉሮፕላን ማረፊያን ቅዳሜ ከተማይቱን ተቆጣጠረ

ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ መርሕ፣ርምጃና ዉሳኔ ልማት ወይስ ጥፋት 11.02.2025

የትራምፕን እርምጃ ከማንም ቀድመዉ የአሜሪካ ታማኝ፣ የቅርብ ወዳጆች ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይን ጨምሮ 79 መንግስታት አዉግዘዉታልፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ 21 ቀናት ዉስጥ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች፣ ያሰለፏቸዉ ዉሳኔዎችና ያፀደቋቸዉ ትዕዛዛት ነባሩን የዓለም ፖለቲካዊ ሥርዓት ግራ ቀኝ ያላጉ፣ የአሜሪካንን ተቀባይነት የሸረሸሩ፣ እርዳታ ተቀባዮችን፣ ሰጪዎችንም የሚጎዳ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም በያለበት «አንድ እግር በርበሬ----»ን በተናጥል ከማላዘን ባለፍ እስካሁን ሰብሰብ ብሉ ጠንካራ አፀፋ ለመስጠት አልቃጣም ወይም አልቻለም።ትራምፕም ቀጥለዋል።መጨረሻቸዉ ነዉ-ናፋቂዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ጦርነት ድል-ሽንፈት 03.02.2025
ከጋዛ እስከ ዩክሬን ጦርነት ያልተለየዉ ዓለም ከአዉሽቪትስ ምን ተማረ? 27.01.2025
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን የካበተ ልምድ ጠቀመ ወይስ ጎዳ? 20.01.2025

Listen to the ማሕደረ ዜና podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.