DW

የወጣቶች ዓለም | Deutsche Welle

News AM ↓ 50 episodes

የወጣቶች ክፍለ ጊዜ ነው።

Author

DW

Category

News

Latest episode

Jul 10, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

ለ100ኛ ጊዜ ደም ለጋሹ ልባም በጎ ፈቃደኛ ቃዲ አደም 06.03.2026

በእናቶች እና የጨቅላ ሕጻናት ጤና ፣ በግጭቶች እና አደጋዎች የሚከሰቱ የአካል ጉዳት እና የደም መፍሰስ እንዲሁም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የደም ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል። ይህም በኢትዮጵያ በህክምናው ዘርፍ የሚፈለገው የደም ፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠኑን ተከትሎ አንደኛው የጤና ዘርፍ ተግዳሮት መሆኑ ይጠቀሳል።

የአፍሪቃ ወጣቶች በአፍሪቃ ኅብረት ተዘንግተናል ይላሉ 20.02.2026
በኅብረቱ አዛውንቶች የተዘነጉ ወጣቶች ምሬት 20.02.2026

1.4 ቢሊዮን ግድም ነዋሪዎች ባሏት አፍሪቃ ሲሦው ወጣት ነው ። የአፍሪቃ ወጣቶች የአፍሪቃ ኅብረት የአብዛኞቻችንን ፍላጎት አላሟላም ሲሉ በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ኅብረቱ ወጣቶቹ ላይ የተከሰተውን ቀውስ መፍታት ተስኖታል ሲሉ ይተቹታል ባለሞያዎች ። ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው መከታተል ይችላል ።

የጎዳና ላይ ውይይት በዩጋንዳ: ጥቃት መፈፀም ወንጀል ከሆነ ለምን እንደ ቀላል ነገር ይታለፋል? 13.02.2026

የዶይቸ ቬለ የወጣቶች ዝግጅት በቅርቡ ዩጋንዳ ውስጥ አንድ የጎዳና ላይ ውይይት አካሂዶ ነበር። ውይይቱም በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት ላይ አተኩሯል። በውይይቱ ተጎጂዎች፤ ጥቃት ፈፃሚ፤ ጋዜጠኛ እና የፖሊስ ባልደረባ ተሳትፈዋል።

በየል ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነው ቢኒያም ሎሊሶ 06.02.2026

“በ15 ዓመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነፃ የትምህርት ቱቶሪያል የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀምሬ ነበር። “ ይላል ቢኒያም ሎሊሶ። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኘው የል ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነው። በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ አዲስኮደር (AddisCoder) በተባለው ተቋም በበጎ ፍቃደኝነት ስልጠናም ይሰጣል።

„ውጤታቸው ከ90 በላይ የሆኑ ለዚህ ፕሮግራም ቢያመለክቱ የመመረጥ እድላቸው ሰፊ ነው“ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ቢኒያም ሎሊሶ 06.02.2026

“በ15 ዓመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነፃ የትምህርት ቱቶሪያል የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀምሬ ነበር። “ ይላል ቢኒያም ሎሊሶ። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኘው የል ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነው። በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ አዲስኮደር (AddisCoder) በተባለው ተቋም በበጎ ፍቃደኝነት ስልጠናም ይሰጣል።

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሜክአፕ ጥቅም እና ጉዳቱ 23.01.2026

ቃል ኪዳን ማንከልክሎት እና ሲፈን አንተነህ በሀዋሳ ከተማ የሜክፕ አርት ሥልጠና እየወሰዱ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል ናቸው ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሆኑት አቤጊያ ያሬድ እና ማይገነት ጠለለ በአንጻሩ ሜክአፕ አሥፈላጊ አይደለም የሚል አምነት እንዳላቸው ይናገራሉ ፡፡ ወጣቶች ሥለሜክአፕ አርት ምን ይላሉ?

ስኮላርሺፕ በጀርመን፥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዶይቸ ቬለ አካዳሚ 16.01.2026

ዶይቸ ቬለ አካዳሚ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉ ኢትዮጵያውን ወጣቶች መካከል አንዱን ለዛሬ የወጣቶች ዓለም እንግዳችን አድርገናል ። እስካሁን በአካዳሚው ስላገኘው ትምህርት፣ ወደፊት ምን እንዳቀደ እና ስኮላርሺፑን እንዴት እንዳገኘ ያዋየናል ። ሙሉ ዘገባውን ታች ባለው ማገናኛ በድምፅ ያድምጡ ።

"አይነ ስውርነት ተጨምሮበት አይደለም በራሱ ኢትዮጵያ ላይ መኖር ይከብዳል" መምህር አብረኃም ወሰን 09.01.2026

አብረኃም ወሰን በሙያው መምህር ነው። አይነ ስውር መሆኑና ገና በልጅነቱ እናቱን ከዚህ ዓለም በሞት ማጣቱ የወጣትነት ህይወቱን ፈታኝ አድርገውበት ነበር። በአሁን ሰዓት ደሴ ላይ ለኢትዮጵያ አይዶል ጉዞ ጥበብን ፍለጋ በሚል የተደረገውን ካስቲንግ ወይም ውድድር አልፎ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር በተስፋ ላይ ይገኛል።

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: በሳምንታት መጨረሻ የሚሰጡ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ጥቅማቸው ወይስ ጉዳታቸው ያመዝናል? 02.01.2026

ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ማሽቆልቆሉን ተከትሎ መንግሥት የተለያዩ የትምህርቱ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ነው። የዚህ ትምህርት ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ታዳጊዎች የወላጆች ምክርን እንዴት ይመለከቱታል? 26.12.2025

ወላጆች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክሮችን ሊለግሱ ይችላሉ፡፡ ይሁንእንጂ ታዳጊዎች ወላጆች በሚሰጧቸው ምክሮች እና ተግፃፆች ላይ የተለያየ አረዳድ አላቸው ፡፡ አንዳንዶች ፤ ቤተሰብ ሁልጊዜ ልክ ነው ታዳጊዎች ቤተሰቦቻቸውን መስማት አለባቸው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ልጆች የማያምኑበት ነገር ሲኖር ሀሳባቸው መግለጽና ማስረዳት አለባቸው ይላሉ ፡፡

ሀገራዊ ፖሊሲዎች ሲወጡ ወጣቶች ያላቸው ድርሻ 19.12.2025
ሱሰኝነት ልጅነቱን ቢወስድበትም እጅ አልሰጠም፤ ታሪክ ቀያሪው ናቲ ባርበር 12.12.2025

እድሜው በሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ሆኖ እሱ ግንየቀረውን የሱስ አይነት እና ከኢትዮጵያ እስከ ሱዳን ከዚያምየግብፅና ሊቢያ በርሃን ስቃይ አስመልክቶታል፡፡ ዛሬ ላይበኢትዮጵያ በወንዶች የፀጉር ውበት ቤት ሥራ ላይ ቀዳሚለመሆን የበቃው ወጣት ናትናኤል ተስፋዬ ናቲ ባርበር ሾፕየትናንት ህይወቱን እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡

"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ 05.12.2025

አሰፋ ዳኜ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ፣ አቀናባሪ እና መምህር ነው። የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከልጅነቱ አንስቶ መጫወት የሚችል ሲሆን ከኢትዮጵያ ታዋቂ አርቲስቶች ጋርም ሰርቷል። ስራዎቹን ውጭ ሀገር ድረስ የማሳየት እድልም ነበረው።

"እዚህ የአበሻ ቀጠሮ የለም" ኢትዮጵያ ውስጥ ያደገችው ኖርዌያዊት ሀኔ 29.11.2025

ምናልባት ማህበራዊ ሚዲያ የሚከታተሉ ወጣቶች ሀኔን በምትሰራቸው ቪዲዮዎች ያውቋት ይሆናል። የሮርዌይ ዜጋ ስትሆን አማርኛ ትናገራለች። ከእጇ ላይም የቡና ስኒ አይጠፋም።

ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ? 21.11.2025

ሰሞኑን ኢትዮጵያው ውስጥ ሥራውን በይፋ አስፋፍቶ የጀመረው "የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ" ፕሮጀክት በ10 ዓመታት ውስጥ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እና ምስራቅ አፍሪቃውያን ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሥራ ብቁ ማድረግ ይሻል ። ይኽ ፕሮጀክት ወጣቶችን የማብቃት፣ የማሰልጠን እና የማማከር የመሳሰሉ ድጋፎችን የሚሰጥ ይሆናል።

በወላጅ እናቱ መሪነት መክሊቱን ያገኘው ወጣት ሙዚቀኛ 16.11.2025

ትውልድ እና ዕድገቱ ጅማ ከተማ ነው ። በቅርቡ ኤን ቢ ሲ በተሰኘ የቴሌቬዥን ጣቢያ በሚያሰናዳው የሙዚቃ የተሰጥዖ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይ አሸናፊ መሆን ችሏል። የቤት መኪናም ተሸልሟል። ሱራፌል አስቴር ። «እናቴ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆና ስላሳደገችኝ በርሷ መጠራትን መረጥኩ» አሸናፊ መሆንም ልዩ ልዩ ስሜት አለው ይላል።

የአሸናፊዎች አሸናፊው ድምጻዊ ሱራፌል አስቴር ከየት ተነስቶ እዚህ ደረሰ? 31.10.2025
በተማሪዎች የሚከበሩ "ቀናቶች" ጠቃሚ ወይንስ ጎጂ? 17.10.2025

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ወጣቶች የተለያዩ ቀናቶችን ሲያከብሩ ይስተዋላል ፡፡ ለዚህም ገንዘብ ያሰባስባሉ። በተማሪዎች ዘንድ ስለሚከበሩት እነዚሁ ቀናት ጠቀሜታ እና ጉዳቶች ላይ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ትንቢት ሰውነት ከሁለት ሴት ታዳጊዎች ጋር ተወያይታለች።

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: በተማሪዎች የሚከበሩ "ቀናቶች" ጠቃሚ ወይንስ ጎጂ? 17.10.2025

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ወጣቶች የተለያዩ ቀናቶችን ሲያከብሩ ይስተዋላል ፡፡ ለዚህም ገንዘብ ያሰባስባሉ። በተማሪዎች ዘንድ ስለሚከበሩት እነዚሁ ቀናት ጠቀሜታ እና ጉዳቶች ላይ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ትንቢት ሰውነት ከሁለት ሴት ታዳጊዎች ጋር ተወያይታለች።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ለተማሪዎች ጠቃሚ ወይስ ጎጂ? 10.10.2025

በቅርቡ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተው የሚጠቀሙ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያው በመሳብ የትምህርታቸው ትኩረት ያጣሉ በሚል ተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ (አካውንት) እንዳይኖራቸው የሚል ሃሳብ አቅርባል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ከሁለት ታዳጊዎችን አከራክራለች።

Listen to the የወጣቶች ዓለም | Deutsche Welle podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.