SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ Odcinki: 1031

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Koniecznie odwiedź stronę podcastu i wesprzyj twórcę: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Kategoria

News

Strona podcastu

www.sbs.com.au

Ostatni odcinek

29 paź 2026

Gdzie słuchać?

Podcasty w aplikacji Replaio Radio Już wkrótce

Podcasty trafią do aplikacji już wkrótce. Zainstaluj teraz i jako pierwszy zobacz nowe podejście do podcastów

Pobierz z Google Play Zainstaluj za darmo Android prawie 10 mln pobrań · ocena 4,8 iOS niedługo

Odcinki

የአንድ አውስትራሊያዊ አባትና ሁለት ሕፃናት ልጆች ሕይወት ባሊ - ኢንዶኔዥያ ውስጥ አለፈ 14.09.2026

የዋን ኔሽን ፓርቲ የፍልሰተኞች ቁጥር ቅነሳ ፖሊሲ ከየአቅጣጫው ብርቱ ትችት ገጠመው #sbsaudiopodcast

"አዲሱ ዓመት የጤና፣ የመተሰሳብና የፍቅር እንዲሆንልን፤ ሰላምንም ይዞ እንዲመጣልን ጥልቅ ምኞታችንን እንገልጣለን" በፐርዝ የኢትዮ- አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር 14.09.2026

አቶ ብሩክ የማ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የመረዳጃ ዕድር ፀሐፊ፤ ስለ ዕድሩ አመሠራረትና ተልዕኮ ያስተዋውቃሉ። የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውንም በዕድሩ ስም ያስተላልፋሉ። #sbsaudiopodcast

"አዲሱ አመት የታሰሩት የሚፈቱበት የተፈናቀሉት ወደቤታቸው የሚመለሱበት የወደቁት የሚነሱበት ፍቅር እና አንድነት የሚሰፍንበት የበረከት አመት ይሁንልን ።" መላክ ጸሃይ ቀሰስ መንግስቱ ሀይሌ 10.09.2026

እንኳን 2019 የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት አደረሰን መላክ ጸሃይ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ #sbsaudiopodcast

የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ 10.09.2026

የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ በዘጸአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር #sbsaudiopodcast

" አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን "- ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 10.09.2026

አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን ሲሉ ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ መለክታቸውን አስተላልፈዋል :: #sbsaudiopodcast

"መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት - ዕንቁጣጣሽ!" የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቀዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር 10.09.2026

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር ለኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያንና ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ያቀርባሉ። #sbsaudiopodcast

አዲስ ኮከብ - ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ 10.09.2026

በአዲስ አንፀባራቂ ኮከብነት ስሙ እየተነሳ ያለው ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ፤ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከጋይንት ንፋስ መውጫ እስከ ፋና ላምሮት አይዶል አሸናፊነት እንደምን እንደበቃ ያወጋል። በ2019 አዳዲስ ዘፈኖቹን በአልበም አካትቶ ለኢትዮጵያውያን እነሆኝ ለማለት መሰናዳቱንም ያበሥራል። #sbsaudiopodcast

"2019 ተስፋን ይዞ፣ የደከምንበት የሚያፈራበት፣ ሐዘናችን በደስታ የሚቀየርበት፣ መከፋታችን በፈገግታ የሚተካበት ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ 09.09.2026

ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - የኩዊንስላንድ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት። #sbsaudiopodcast

የሃይማኖት አባቶች የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መልዕክት በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ 09.09.2026

የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ የሃይማኖት መሪዎች መልዕክትና መንፈሳዊ ዝማሬዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ። #sbsaudiopodcast

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ ዲጂታል ደህንነት ጥበቃ ረቂቅ ሕግ በሳንሱር ተፈርጆ ትችት ተሰነዘረበት 09.09.2026

አውስትራሊያ ውስጥ የወሲባዊ ጥቃት ደረጃ መናሩ ተመለከተ #sbsaudiopodcast

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) 'ሠራተኞች ማኅበራትን ማደራጀታቸውና መብታቸውን መጠየቃቸውን እንደ ተቃውሞና ችግር ፈጣሪነት መታየት የለበትም' ሲል አሳሰበ 07.09.2026

ኢትዮጵያ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ልታቋቁም ነው

"የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም አቀርባለሁ" አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ 07.09.2026

አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

"የዘመን መቁጠሪያችን የሚያኮራ ልዩ ሀብታችን፤ የኢትዮጵያዊነት ልዩ ሥርዓታችንም ነው" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ 07.09.2026

ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።

"መጪው ዓመት የሀገራችን አንድነት የሚፀናበት፤ የሰዎች ማንነት የኩራታቸው ምንጭ ብቻ የሚሆንበት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 07.09.2026

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

"አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላምና መረጋጋትን፤ ለወገኖቻችንም ከስጋት ነፃ የሆነ ዓመት እንዲሆን በፅኑ እመኛለሁ" ዶ/ር ለገሰ ጋረደው 07.09.2026

ዶ/ር ለገሰ ጋረደው - የደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

የ2019 አዲስ ዓመት ቅበላ በሜልበርን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አንደበት 07.09.2026

የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን-ፉትስክሬይ ፓርክ በድምቀት ተከብሯል። ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የበዓሉን መሰናዶ፣ የአዲስ ዓመት ምኞትና ተስፋዎቻቸውን አሰናስለው አጋርተዋል።

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በ "አዲስ አበባ" አዘጋጅነት በዕለተ ዕንቁጣጣሽ ሜልበርን ከተማ ላይ ደምቆ ሊከበር ነው 04.09.2026

ወ/ሮ ነፃነት ኃይሌ እና አቶ ቶም ኑናን፤ የ New Flower Sound 2019 የኢዮሃ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት አስተባባሪዎች፤ ዓርብ መስከረም 1 ቀን / September 11 በ 342 High St, Northcote ከ 6:00 pm እስከ 11:00 pm ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ታዳሚዎች ስላዘጋጁት ልዩ ኩነት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ አባላት የአዲስ ዓመት ታዳሚ እንዲሆኑ ያጋብዛሉ።

"2019 የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ምኞቱ ዕቅዶቹ የሚሳኩበት የሰላም ዓመት ይሁንልን!" ደራሲ ታክሎ ተሾመ 03.09.2026

የሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አስመልክተው ለመላ ኢትዮጵያውያን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

#118 Losing a job (Med) - #118 Losing a job (Med) 03.09.2026

Learn English for talking about losing your job. Practise ways to explain workplace changes and sympathetic responses to someone who has had bad news. - ከሥራ መሰናበትን አስመልክተው ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩ። የሥራ ቦታ ለውጦችን እንዴት ማብራራት እንደሚቻል እና መጥፎ ዜና ለገጠመው ሰው ርኅራኄ የተመላበት ምላሽ አሰጣጥን ይለማመዱ። Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - ከእዚህ ክፍለ ዝግጅት ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ፤ የቀሰ...

በሳዑዲ አረቢያ በፍልሰተኞች መካከል በቅርቡ ከተከሰተ የቡድን ግጭትና ግድያ ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ተያዙ 02.09.2026

ከስምንት ዓመት በፊት ለተፈረመው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፍልሰት ሰነድ ኢትዮጵያ የትግበራ ዕቅድ ረቂቅ አዘጋጀች

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አለመታወቅ በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታወቀ 02.09.2026

የሲድኒና የሜልበርን ቤቶች ዋጋ ማሽቆልቆል የፖለቲካ ትኩሳት ፈጥሯል

ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አልታወቀም የተባሉ አውስትራሊያውያን ቁጥር ጨመረ 31.08.2026

የዋን ኔሽን ፓርቲ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ከፋፋይና አደገኛ ሲሉ የሰነዘሩበትን የከረረ ትችት አሌ አለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል ገለልተኛና ሕጋዊ አካል እንዲቋቋም ጠየቀ 31.08.2026

የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 15 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ

"ኢትዮጵያዊነታችንን ካላስቀደምንና በጎሳ አካሔድ የሚኬድ ከሆነ፤ አሁን እንኳ የተረፈችዋን ኢትዮጵያ ላናገኛት እንችላለን" የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ 28.08.2026

በሕይወት ዘመናቸው ስለ "እኛና አብዮቱ" መፅሓፋቸው ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ ይቆጨኛል፣ ያናድደኛል፣ ያሳዝነኛል። ወደብ አልባ ሀገር ነፃ ሀገር አይደለም። መጪዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥታት የሚያስቡበት ጉዳይ ይመስለኛል" ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ ዘርፈ ብዙ አተያዮች። (ምልሰታዊ ምልከታ

"የአዲስ አበባን ሀብትና የፖለቲካ ስልጣን መቆጣጠር ኢትዮጵያን መቆጣጠር ተደርጎ በተቀናቃኝ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቡድኖች ዘንድ በግልፅ ይታያል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 26.08.2026

ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ፤ በካሳሁን ሰቦቃ በSBS የተደረጉ ቃለ መጠይቆችና መጣጥፎች" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመዲናዎች ዝውውር ጂኦግራፊያዊ ጠባያት" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።

Słuchaj podcastu SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ w Replaio

Radio i podcasty w jednej aplikacji - za darmo, bez zakładania konta. Zainstaluj już dziś i nie przegap premiery

Pobierz z Google Play

Replaio nie jest wydawcą podcastów; nazwy audycji, okładki i audio należą do ich autorów i są rozpowszechniane przez publiczne kanały RSS